No summary available.
ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉምሩክ ወንጀልን ተከትል ሉጣል ስለሚገባው ቅጣትና ፍርድ ቤቱ በቅጣት አጣጣል ሉከተለው ስለሚገባው ስርዓት የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾችና በላልች አምስት ሰዎች የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 93(1(መ) እና (2) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በአመልካቾች አማካኝነት ወደ አገር ውስጥ እንዱገባ የተደረገ የባትሪ ድንጋይ ባልተሟላ ሰነድ ቀረጥና ታክስ ሳይከፍለ ፣ ፍተሻ ሳይደረግ ፣ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሳይጠናቀቅ በማን እንደተዘጋጀ ባልታወቀ የእቃ መልቀቂያ እንዱለቀቅ በማድረግ የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀል ፈፅመዋል፣ እንዱሁም በተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 97 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከላይ የተገለፀውን እቃ ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልበት እንዱቆይ በማድረጋቸው የጉምሩክ ስነ ሥርዓትን የማሰናከል ወንጀል ፈጸመዋል በሚል በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካቾች ክሱን ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አስምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች የወንጀል ድርጊቶቹን ስለመፈፀማቸው አቃቤ ሕግ በማስረጃዎቹ ማስረዲቱን ፍርድ ቤቱ በማመን አመልካቾች እንዱከላከለ ሲል ብይን ሰጥቶ አመልካቾች አለን ያሎቸውን ማስረጃዎችን አቅርበው አሰምተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ አመልካቾች የተከሰሱባቸውን ወንጀልች ያለመፈጸማቸውን በመካላከያ ማስረጃዎቻቸው አስረድተዋል ፣ በዚህም ምክንያት የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አስተባብለዋል በሚል ምክንያት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 149(2) መሰረት ከክሱ በነፃ አሰናብቷቸዋል።
ኢግዚብትን በተመለከተ ግን 1ኛ አመልካች በማጭበርበር ስራ ባይሳተፈም እንደባለንብረት ተከታትለው ጉዲዩን ከማስፈጸም አንፃር ያደረጉት ጥረት ስለመኖሩ አላስረደም በማለት ንብረቱ ሉመለስላቸው የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም ሲል በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 106 መሰረት ለመንግስት እንዱወረስ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የሥር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሰረት ያደረገው ድንጋጌ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን በመጥቀስና ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104(3(ሀ)) ስር የተመለከተው መሆኑን በመለየት በስር ፍርድ ቤት ንብረቱ ለመንግስት ውርስ ይሁን ተብል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ሕጋዊ መሆኑን በመቀበል ውሳኔን በውጤት ደረጃ አንፅቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካቾች ከወንጀል ተግባሩ ነፃ ተብለው ከተወሰነ በሁዋላ በኢግዚቢትነት የተያዘው እቃ በመንግስት እንዱወረስ ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ከአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104(3(ለ)) ድንጋጌ አኳያ ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት እንዱታረምላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች ከተከሰሱበት ወንጀል ነጻ የተሰናበቱ ቢሆንም በተጠሪ መስሪያ ቤት የነበረው ንብረት በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104(3(ሀ)) መሰረት ሉወረስ ይገባል የመባለን አግባብነት ከተጠቃሹ አዋጅ አንቀጽ 104(3(ለ)) ድንጋጌ አኳያ ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች ከላልች ሰዎች ጋር በስር ፍርድ ቤት ክስ የቀረበባቸው 1ኛ አመልካች ወደ ሀገር ውስጥ ባትሪ ድንጋይ ለማስገባት በዱክላራሲዮን ቁጥር C- 22074 በስር ተከሳሽ በነበሩት የጉምሩክ አስተላላፉ ድርጅትና ሰራተኞች አማካኝት ዱክላራሲዮን ሲቀርብ ለጉምሩክ ባለስልጣን የአዱስ አበባ ንግድ እቃዎች ማስተናገጃ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለሚቀርበው ዱክላራሲዮን ጋር አባሪ ሆኖ የቀረበው የእቃ ማስጫኛ ሰነድ( packing list/ ብዛቱ 60,480 ደርዘን ኦሴል ባትሪ ድንጋይ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ የሚገልፅ ሰነድ ለውጭ ምንዛሪ ማስፈቀጃ ለአቢሲኒያ ባንክ በሚቀርበው 100,800 ደርዘን ኦሴል ባትሪ ድንጋይ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ አድርጎ በማቅረብ የጉምሩክ ሥነ ሥርአት ያልተፈፀመበትና የቀረጥና ታክስ መጠኑ ብር 278,247.09 (ሁለት መቶ ሰባ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ብር ከዜሮ ዘጠኝ ሳንቲም) ሳይከፈልበት በ2ኛ አመልካች መጋዘን በተደረገ ብርበራ ብዛቱ 4200 ካርቶን የሆነ ኦሴል ባትሪ ድንጋይ ተከማችቶ በመገኘቱ የጉምሩክ ማጭበርበር ወንጀልና የጉምሩክ ስነሥርዓትን የማሰናከል ወንጀል ተከሰው የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው አስተባብለዋል በማለት በነፃ የተሰናበቱ መሆኑን ፣ ለወንጀል ድርጊቶች መሰረት የሆነውን የባትሪ ድንጋይ ግን ለመንግስት እንዱወረስ በማለት የቅጣት ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አዋጅ ቁጥር 622/2001 በክፍል አራት በጉምሩክ ሥራ ላይ ስለሚፈፀሙ ወንጀልች የሚደነግጉ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን ይኸው የአዋጁ ክፍል በምዕራፍ አንድ በባለስልጣኑ ሰራተኞች ስለሚፈፀሙ ወንጀልችና ቅጣታቸው ሲደነግግ በምዕራፍ ሁለት ስር በተለይም ከአንቀፅ 92 እስከ 108 ድረስ በተደነገጉት ድንጋጌዎች በላልች ሰዎች ስለሚፈፀሙ የጉምሩክ ወንጀልችና የቅጣት አይነትና መጠን እንዱሁም ስለፍርደ ቤቱ ስልጣን የሚደነግግ መሆኑ ግልጽ ነው። አሁን በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት የበታች ፍርድ ቤቶች የቅጣት ውሳኔ የአዋጁን አንቀጽ 104(3(ሀ)) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት ማድረጉ ያላግባብ ነው ፣ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ የአዋጁ አንቀጽ 104(3(ለ)) ስር የተመለከተው ነው በማለት ነው። በእርግጥ ሁለቱ ንዐስ ድንጋጌዎች ጥፊተኛ ወይም ነጻ የማድረግ ውሳኔ በውርስ ላይ ስለሚኖረው ውጤት በሚደነግገው አንቀጽ ስር ያለ ሲሆን ተፈጻሚ የሚሆኑበት አግባብ የተለያየ መሆኑን የድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያሳያል። የአዋጁ አንቀጽ 104(3(ሀ)) ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው የአዋጁን ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የተከሰሰ ሰው በነፃ የተሰናበተ ከሆነ ፍርድ ቤቱ እቃው ወይም ማጓጓዣው የጉምሩክ ሕግን የመተላለፍ ድርጊት የተፈፀመበት ስለመሆኑ የቀረበለት ማስረጃ አጥጋቢ ሆኖ ካገኘው የውርስ ትዕዛዝ የሚሰጥበትን አግባብ የሚደነግግ ሲሆን በፉደል "ለ" ስር የተመለከተው ድንጋጌ ደግሞ እቃው ወይም ማጓጓዣው የጉምሩክ ሕግን የመተላለፍ ድርጊት የተፈፀመበት ስለመሆኑ የቀረበለት ማስረጃ አጥጋቢ ሆኖ ካላገኘው ተገቢው ቀረጥና ታክስ እንዱከፈል ወይም ላላ አግባብነት ያለውን ትዕዛዝ በመስጠት እቃው ወይም ማጓጓዣው ለባለቤቱ ወይም ለተያዘበት ሰው እንዱመለስ የሚደረግበትን አግባብ የሚደነግግ ነው። ሁለቱ ድንጋጌዎች ይዘታቸው ሲታይ የሚፈጸሙበት አግባብ እጅጉን የተለያየ ነው። በጉምሩክ ወንጀል የተከሰሰ ሰው በነፃ የተለቀቀ ቢሆንም ወንጀለ የተፈጸመበት እቃ ወይም ማጓጓዣ የሚወረሰው የጉምሩክ ሕግን የመተላለፍ ድርጊት ስለመፈፀሙ ፍርድ ቤቱን የሚያጠግብ ማስረጃ ሲቀርብ ሲሆን ማስረጃው አጥጋቢ ካልሆነ ብቻ ፍርድ ቤት እቃውን ወይም ማጓጓዣውን እንዲይወረስ በማድረግ ተገቢው ቀረጥና ታክስ እንዱከፈል ሉያዝ የሚገባው መሆኑን ድንጋጌዎቹ እንደየቅደምተከተላቸው ያሳያለ። ለጉዲዩ የቀረበው ማስረጃ አጥጋቢ መሆን ያለመሆኑ ደግሞ ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የሚታይ ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ለወንጀለ ክስ መሰረት የሆነው የባትሪ ድንጋይ በአዋጁ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 2(1) ስር ስለእቃ የተሰጠውን ትርጉም የሚያሟላ ሲሆን ከአመልካቾች ጋር በስር ፍርድ ቤት ተከሰው በነበሩት የተወሰኑት ሰዎች የጉምሩክ ሕግን የመተላለፍ ድርጊት የተፈፀመበት መሆኑ ተረጋግጧል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ በስር ፍርድ ቤት የተያዘው ንብረት የጉምሩክ ሕግን የመተላለፍ ድርጊት የተፈጸመበት ስለመሆኑ ባቀረበው ማስረጃ በአጥጋቢ ሁኔታ ማስረዲቱን በውሳኔው ላይ በግልፅ አስፍሯል። ይህ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ በዚህ ችልት ተቀባይነት የማያገኝበት አግባብ የላለ መሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ))እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ምክንያቱም የማስረጃው አጥጋቢ መሆን ያለመሆኑ የማስረጃ ምዘና ጉዲይ እንጂ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ አይደለም። በመሆኑም አመልካቾች የአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104(3(ለ)) ድንጋጌ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ሉኖረው ይገባል በማለት ያቀረቡት ክርክር ለወንጀል ድርጊቱ መሰረት የሆነው እቃ የጉምሩክ ሕግን የመተላለፍ ድርጊት የተፈጸመበት መሆኑን አቃቤ ሕግ በአጥጋቢ ማስረጃ አስረድቶ በመገኘቱ ፍርድ ቤቶቹ እንዱወረስ ያዘዙ መሆኑን ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ሲሆን የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአዋጅን አንቀጽ 104(3)(ሀ)) ድንጋጌ ለምክንያቱ መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ምንም አይነት የሕግ ስህተት የላለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 12 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 104(3(ሀ)) ድንጋጌ በመሆኑ የአመልካቾች አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
No topics extracted.