No summary available.
መስከረም 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን - ዐቃቤ ህግ አቶ ሽመልስ አበበ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ንጉሴ ገብረፃዱቅ - ጠበቃ አቶ አበበ ታዬ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ተሻሽል እንዱወሰንልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 64/4 እንደተሻሻለ በመተላለፍ የጋራ ንብረቱ በሆነውና የሰላዲ ቁጥሩ 3- 02587/አ.አ/ የሆነውን መኪና በሹፋርነት እያሽከረከረ እያለ ወደ አገር ውስጥ እንዲይገባ በህግ የተከለከለ ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ከቡታጅራ ወደ አዱሰ አበባ ለማስገባት ሲሞክር ነሐሴ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. ከላሉቱ ዘጠኝ ሰዓት ሰበታ ከተማ ስለተያዘ የጉምሩክን ህግ የመጣስ ወንጀል ፈፅሟል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ የወንጀለን ድርጊት አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል። አመልካች ተጠሪ ሲያሽከረክረው በነበረው መኪና ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ተጭኖ የተገኘ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አቅርቧል። እንዱሁም ወንጀለ የተፈፀመበት የሰላዲ ቁጥሩ 3-02587/አ.አ/ የሆነው መኪና የተጠሪው የአቶ ንጉሴ ገ/ፃዱቅ እና የአቶ ጌታቸው ገዛኸኝ የጋራ ሀብት መሆኑን የሚያስረዲ የመኪናውን የባለሀብትነት ማረጋገጫ ደብተርና ከአዱስ አበባ ትራንስፕርት ቢሮ የተፃፈ የሰነድ ማስረጃ አቅርቧል። ተጠሪ በወቅቱ እሱ ወባ ተነስቶበት ታሞ የነበረ መሆኑን ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ከእኔ እውቅና ውጭ የተጫነ መሆኑን ያስረደልኛል በማለት ሁለት የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃ ከመረመረና ከመዘነ በኋላ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ የጠቀሰውን አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀፅ 64/4/ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 113/2/ መሰረት ወደ አዋጅ ቁጥር 6ዐ/89 አንቀፅ 74 በመለወጥ ተጠሪ ከላይ የአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀፅ 74 እንደተሻሻለው በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት የጥፊተኝነት ውሣኔ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን የቅጣት አስተያየት ከሰማ በኋላ ተጠሪ በሶስት ዓመት እስራት እንዱቀጣና የተያዘው ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ለመንግስት ገቢ እንዱሆን ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪን ጥፊተኛ ያለበት የህግ ድንጋጌና የሰጠውን የቅጣት ውሣኔ በመቃወም ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ሚያዝያ 7 ቀን 2002 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ አዋጅ ቁጥር 60/89 እና የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4/ የተደነገገውን በመተላለፍ በሀላፉነት ይዞ በሚያሽከረክረውና የጋራ ንብረቱ በሆነው መኪና ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ይዞ መገኘቱ በማስረጃ ተረጋግጧል። የመጓጓዥያ ሀላፉ የሚለው ሀሳብ በአዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀጽ 2/14/ ግልፅ ትርጉም ተሰጥቶታል። በዚህ ድንጋጌ በተሰጠው ትርጓሜ መሰረት ማንኛውም መጓጓዥያ በጉዞ ላይ እንዲለ እንዱይዝ፣ እንዱቆጣጠር ወይም ሥራውን እንዱመራ ሥልጣን የተሰጠው ሰው ወይም ወኪለን የሚያጠቃልል መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል። የተጠሪ አድራጎት በአዋጅ ቁጥር 60/89 በአዋጅ ቁጥር 368/95 በአንቀፅ 64/4/ እንደተሻሻለው የሚሸፍን ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የህጉን ድንጋጌ ግልፅ ይዘት በመተላለፍ ተጠሪ የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 74 የተመለከተውን በተመላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የሥር ፍርድ ቤት ተይዞ የነበረው መኪና ለተጠሪ እንዱመለስለት የሰጠው ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀፅ 79፣ አንቀፅ 80/1/ አንቀፅ 81 የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱሻሽልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ታህሣሥ 20 ቀን 2003 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ መልስ በመኪናው ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ጭኖ ተገኝቷል በተባለበት ዕለት በመኪናው ውስጥ የነበርኩ ቢሆንም እኔ ወባ ታምሜ ስለነበረ ህጋዊ መንጃ ፈቃድ ያለው የመኪና ረዲት ሹፋር አቶ ሀይለ ቢሰጠኝ መኪናውን ያሽከረክር እንደነበርና ልባሽ ቦንዲ ጨርቁ በመኪናው ላይ መጫኑን የማላውቅ መሆኔን በመከላከያ ማስረጃ አስረድቻለሁ። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ባቀረበው የወንጀል ክስ የጠቀሰውን የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4 ድንጋጌ በመለወጥ በአዋጁ አንቀፅ 74 በተደነገገው መሰረት ጥፊተኛ ብለው የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔና ትዕዛዝ አግባብነት ያላቸውን የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረበው ማስረጃ ተጠሪ የጋራ ንብረቱ በሆነውና በወቅቱም በሀላፉነት ይዞት በነበረው መኪና ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ ጭኖ መገኘቱን የሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዲይ ደረጃ አረጋግጧል። ይህ የተጠሪ አድርጎት በየትኛው የህግ ድንጋጌ ያስጠይቃል የሚለውን ስንመለከት “በማጓጓዣው የውጭም ሆነ የውስጥ አካል የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመበት ክልከላ፣ ገደብ ወይም ቁጥጥር የተደረገበትን ወይም የኮንትሮባንድ ዕቃን ሲያጓጉዝ ከተገኘ ይህንን የወንጀል አድራጎት ለመከላከል ተገቢነት ያላቸውን ጥንቃቄዎች ሁለ መውሰደን ካላሥረዲ ዕቃው ወይም ማጓጓዥያው መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ዕቃው ላይ ሉከፈል ከሚገባው ቀረጥ የማያንስ የገንዘብ መቀጮ እና ከአሥራ አምስት እስከ ሀያ ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል በማለት በደነገገው በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4 ድንጋጌ የሚሸፈን ነው።
ከዚህ አንፃር ስንመለከተው የሥር ፍርድ ቤት የማጓጓዥያ ሀላፉነትን የሚደነግገውን የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4 በመጥቀስ አመልካች ያቀረበውን ክስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 113/2/ በመቀየር ተጠሪ ህገ ወጥ ዕቃዎችን ይዞ ስለመገኘት በሚደነግገው የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀፅ 74 ጥፊተኛ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ የተጠሪን ግዙፍ ተግባር ሞራላዊ ሁኔታ አግባብነት ካለው የህጉ ድንጋጌ ጋር ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195/2//ለ-2/ መሰረት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊኝነት ውሣኔ በማሻሻል ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀፅ 64/4 የተደነገገውን በመተላለፍ ወደ አገር ውስጥ እንዲይገባ የተከለከለ ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ የጋራ ባለሀብት በሆነበት መኪና ሲያስገባ የተያዘ ጥፊተኛ ነው በማለት የጥፊተኛነት ውሣኔ ሰጥተናል።
የቅጣቱን መጠን በተመለከተ፣ ተጠሪ በሶስት ዓመት እስራት እንዱቀጣና የተያዘው ዘጠኝ ቦንዲ ልባሽ ጨርቅ እንዱወረስ የበታች ፍርድ ቤቶች ወስነዋል። የበታች ፍርድ ቤቶች ከሰጡት ከዚህ የቅጣት ውሣኔ በተጨማሪ ተጠሪ ጥፊተኛ ሆኖ በተገኘበት የአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 64/4/ ድንጋጌ መሰረት ተጠሪ አቶ ጌታቸው ገዛኸኝ ጋር የጋራ ባለንብረት የሆነበት የሰልዲ ቁጥሩ 3- 02587/አ.አ/ የሆነው መኪና ላይ ተጠሪ ያላቸው ድርሻ ሉወረስ እንደሚገባው ከህጉ ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የቅጣት ውሣኔ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጠሪ የሰላዲ ቁጥሩ 3-02587/አ.አ/ ላይ ያለው የባለሀብትነት ድርሻ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ላሆን ይገባል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 2/መ/ መሰረት በማሻሻል ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪ ከአቶ ጌታቸው ገዛኸኝ ጋር የጋራ ባለሀብት የሆነበት የሰላዲ ቁጥሩ 3-02587/አ.አ/ በመሆነው መኪና ላይ ያለው ድርሻ ለመንግስት ገቢ ላሆን ይገባል በማለት በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀፅ 64/4 መሰረት ወስነናል።
ይኸ ውሣኔ አቶ ጌታቸው ገዛኸኝ የሰላዲ ቁጥሩ 3-02587/አ.አ/ በሆነው መኪና ላይ ያላቸውን ግማሽ የጋራ ባለሀብትነት የሚነካ አይደለም ብለናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.