No summary available.
ሐምል 04 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የማህደር ኤጄንሲ ባለቤት ወ/ሮ አለምነሽ ኤርሞ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሪት አለም መስፍን ተወካይ ገበየ ደጉ ቀረቡ።
መዝገቡ ያደረው ለውሣኔ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የጉዲት ካሣ ክስ የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፋ/የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ከሣሽነት ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ ተከሣሽ ከሣሽን ወደ ቤይሩት ለስራ ብር 8000 በማስከፈል የተከች ሲሆን አሰሪዬ ከ3ኛ ፍቅ ወርውራኝ በግራ እግሬ ላይ 30% ዘላቂ ጉዲት ደርሶብኛል፣ በተጨማሪም አሰሪዬ የስድስት ወር ደመወዝ በወር 100 ድላር ወይም ብር 1300 ያልከፈለኝ ሲሆን ለህክምና እና ትራንስፕርት እንዱሁም ለምግብ ወጪ አውጥቼያለው። በመሆኑም ተከሣሽ ለደረሰብኝ ጉዲት ኃላፉ ስለሆነ ወደፉት በወር ብር 130 የቀረብኝ ሆኖ ለ33 ዓመት በጉዲት ምክንያት ያጣሁትን እና ላልች ወጪዎችን ጨምሮ /ሁለት መቶ ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ብር/ ተከሣሽ እንዱከፍል እንዱወስንልኝ የሚል ነው። በቀረበው ክስ ላይ ተከሣሽ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ በሰጠው መልስ ተከሣሽ ብር 8000 /ስምንት ሺህ ብር/ አልተቀበለም፣ ተቀብል ቢሆንም ይመልስልኝ ማለት አይችለም፣ በአሰሪያቸው ያልተከፈላቸው ደመወዝም የለም፣ የስድስት ወራት ደመወዝ በዌስተርን ዩኒየን ለአቶ አያልነህ ገና ተልኳል። የከሣሽ ደህንነት እንዱጠበቅ ተገቢውን አድርገናል፣ አሰሪዋ ከፍቅ የወረወረቻት ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የለም፣ ተከሣሽም በሰብአዊነት አሣክሜያታለሁ እንደዚሁም ጉዲቱ የደረሰው ከካንሰር በሽታ ጋር በተያያዘ እንጂ በመውደቋ ባለመሆኑ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዱሆን በማለት ተከራክራለች።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ በመቀበል ጉዲቱ የደረሰው በመውደቋ ምክንያት ስለመሆኑ የቀረቡት ማስረጃዎች አያስረደም በማለት የተጠየቀውን የጉዲት ካሣ ክስ ውድቅ ሲያደርግ ተከሣሽን ወደ ውጭ አገር ለመላኪያ በሚል ብር 8000 /ስምንት ሺህ ብር/ በአዋጅ ቁ. 632/2001 መሰረት መቀበል የላለባቸውን የተቀበለ በመሆኑ ለከሣሽ እንዱመልሱ እና የከሣሽን ደመወዝ በተመለከተ የስድስት ወራት ደመወዝ ስለመላኩ ማስረጃ ስለቀረበ ሁኖም ግን ከሣሽ የሰራችው ለ11 ወራት በመሆኑ የቀሪዎቹን የ5/አምስት ወራት/ ደመወዝ ተከሣሽ እንዱከፍሎት በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የአሁን ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ተጠሪ በተላከችበት አገር አሰሪዋ ከ3ኛ ፍቅ ላይ ተወርውራ በእግሯ ላይ ጉዲት የደሰረ ስለመሆኑ እና በዚህም ምክንያት በዊልቸር እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ከማረጋገጡ በላይ የቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ደግሞ አመልካች ከቤይሩት አገር አስመጡ የተባለው እና ተጠሪ ከጥቁር አንበሣ ሆስፑታል ያቀረቡት የህክምና ማስረጃዎች ሲሆን 30% ቋሚ የአካል ጉዲት የደሰረባት ስለመሆኑ ስለሚያመላክቱ አመልካች ከሰጠችው የምስክርነት ቃል ጋር አንድ ላይ ስንመለከት በአሰሪዋ ከፍቅ ላይ በመወርወሯ ምክንያት ከላይ የተመለከተው ጉዲይ የደረሰባት ስለመሆኑ ያረጋግጣል / አንድ መቶ ሃምሣ ሰባት ሺህ አራት መቶ አርባ ብር/ አመልካች ለተጠሪ እንድትከፍል በማለት ክፍያው የሚፈጽምበትን አግባብ በማመላከት እና የሞራል ካሣ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በተጨማሪ እንዱከፈላት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ቅሬታ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል። አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙ ክርክር በጽሐፍ ተሰምቷል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ አመልካች ደረሰ ለተባለው ጉዲት ኃላፉት አለባቸው በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር በሚል በመሆኑ የተያዘው ጉዲይ በዚህ መልኩ ቀደም ሲል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚህ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ አገልግልት ሥራ የተሰማራ እንደመሆኑ መጠን የአዋጅ ቁ. 632/2001 አጠቃላይ ንባብ መገንዘብ እንሚቻለው በተለይ ወደ ውጭ አገር ለስራ የሚሄደ ኢትዮጵያዊያን መብታቸው፣ ድህንነታቸውና ክብራቸው ተጠብቆላቸው ወደ ስራ የሚሰማሩበትን አግባብ ለማመቻቸት በመሆኑ እና ይሄንንም ኃላፉነት መወጣት ያለባቸው በዚሁ ስራ የተሰማሩት እንደአመልካች ዓይነት ድርጅቶች ስለመሆናቸው ያስገነዝባል። አመልካችም ቢሆን በበታች ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የተጠሪ ድህንነት እንዱጠበቅ ተገቢውን ሁለ አድርጌአለሁ በሚል እንጂ ኀላፉነት የለብኝም በሚል የቀረበ ክርክር የለም። በመሆኑም በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ አሰሪዋ ላደረሰችው ጉዲት ኃላፉነት የለብኝም በሚል የቀረበው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት ያለው ሁኖ አልተገኘም።
ላላው የደረሰው ቋሚ የአካል ጉዲት ከምን የተነሣ እንደሆነ አመልካች ተጠሪ ባለባት የካንሰር በሽታ እንጂ በመውደቅ የደረሰ አይደለም በሚል ተከራክራለች። ተጠሪ በበኩሎ ጉዲት የደረሰብኝ አሰሪዬ ከ3ኛ ፍቅ ላይ ስለጣለችኝ የደረሰብኝ ነው በማለት ተከራክራለች። ይሄን ክርክር በተመለከተ በተለይ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ተጠሪ በመውደቋ ምክንያት ቋሚ 30% የአካል ጉዲት የደረሰባት ስለመሆኑ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል ወደ ሚለው ድምዲሜ ደርሷል። ይሄው የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ በፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ፀንቷል። በተጠሪ አካል ላይ የደሰረው ቋሚ የአካል ጉዲት የደረሰው በመወድቅ ምክንያት ነው ወይስ በልላ ምክንያት የሚለውን ክርክር ደግሞ የፍሬ ነገር እንጂ የመሰረታዊ የህግ ስህተት ክርክር ባለመሆኑ በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ ሉነሣ የሚችል ሁኖ አልተገኘም።
በዚህ የክርክር ነጥብ ላይ ደግሞ የበታች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ጉዲቱ የደረሰው በደረሰባት የመውደቅ አደጋ ምክንያት እንደሆነ በፍሬ ነገር ረገድ ድምዲሜ ላይ ደርሰዋል። ማስረጃን መመዘን እና ፍሬ ጉዲይን ማጣራት ደግሞ የበታች ፍርድ ቤቶች ስልጣን በመሆኑ እና የዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን መሰታዊ የህግ ስህተት ሲኖር ማቃናት ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ. ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 10 ስር የተመለከተ በመሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ በበታች ፍርድ ቤቶች የተደረሰበትን ድምዲሜ እንዲለ የምንቀበለው ይሆናል ማለት ነው። በመሆኑም አመልካች በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዲት በመውደቋ ሣይሆን በልላ በሽታ ምክንያት ነው በማለት የምታነሣው ክርክር በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ የሚስተናገድ ባለመሆኑ አልፈነዋል። አመልካችም ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለባት ተብል ለተጠሪ ካሣ እንድትከፍል መወሰኑ በአግባቡ ነው ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍበትን ምክንያት አላገኘንም።
ባጠቃላይ የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ለደረሰው ቋሚ የአካል ጉዲት አመልካች ኃላፉነት አለባት በማለት ካሣ እንድትከፍል መወሰኑ እና የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይሄንን ውሣኔ ማጽናቱ በአግባቡና የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝ. ቁ. 72389 ጥቅምት 22 ቀን 2004 ዓ.ም እና የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 103953 ሐምል 06 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ቋሚ የአካል ጉዲት ኃላፉነት አለባት በማለት በፋ/የከፍተኛ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ታህሣስ 2 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.