No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ትዕዛዝ ኮሬ አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ነገረ ፈጅ አቶ ገብረ መድህን ባህታ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በንብረት ላይ ለደረሰ ጉዲት በኃላፉነት ስለመጠየቅና የካሣ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከካሽ በመሆን ተከራክረዋል።
አመልካች ተከራይቶ የንግድ ሥራ የሚያከናወንበት የቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 03/05 ቁጥር 382 በሆነ ቤት የሚያከናውነው ‘’ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዲራሽ‘’ የሚል የንግድ ስም የሚጠራ ድርጅት ሚያዝያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ተከሳሹ /ተጠሪ/ ሉቆጣጠረው በሚገባው የኤላትሪክ መስመር ላይ የተፈጠረው ብልሽት ባስከተለው ቃጠል በንብረቱ ላይ ውድመት ደርሶብኛል። ስለዚህ ለጉዲቱ ተከሳሽ ኃላፉ በመሆኑ ብር 1,024,563.02 /አንድ ሚሉዮን ሃያ አራት ሺህ አምስት መቶ ስልሣ ሶስት ብር ከዜሮ ሁለት ሣንቲም/ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ የእሳት አደጋው ደርሶ ንብረቱ ከመውደሙ በፉት የተበጠሰ ኤላትሪክ የለም። የቃጠልው ምክንያት ኤላትሪክ ስለመሆኑ የቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት ያለው አይደለም። መስመሩ ሲዘረጋ የንግድ ድርጅቱ አልነበረም ስለዚህ በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባኝም የሚል የፅሐፍ ክርክር አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትን ጭብጥ ለመመሥረት እንዱመቸው የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት የግራ ቀኙን የቃል ክርክር አመልካች ተጠሪ ላደረሰው ጉዲት በጥፊት ላይ የተመሰረተ ኃላፉነት አለበት።
የኤላክትሪክ መስመሩ ተበጥሶ በከሳሽ ድርጅት ላይ በማረፈ ምክንያት የእሳት ቃጠል የተነሳ በመሆኑ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተከሳሽ /ተጠሪ/ በበኩለ እሳቱ የተነሳው የኤላትሪክ መስመሩ በመበጠሱ ምክንያት አይደለም። የኤላትሪክ መስመሩ ያልተበጠሰ በመሆኑ ለጉዲቱ ኃላፉነት የለብንም የሚለው የመከራከሪያ ነጥባቸው መሆኑን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 29 ቀን 2001 ዓ.ም ባቀረቡት የቃል ክርክር አስመዝግበዋል።
አመልካች /ተከሳሽ/ የእሳት ቃጠልው የተነሳው ተጠሪ /ተከሳሽ/ ከዘረጋው የኤላትሪክ መስመር መሆኑን ያስረደልኛል የሚላቸውን የፅሐፍና የሰው ምስክሮች አቅርቧል። ተጠሪም የሰውና የፅሐፍ ማስረጃ አቅርቧል። ከዚህ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ /ተጠሪ/ ለጉዲቱ ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም? ኃላፉነት አለበት ከተባለ ተከካሸ ለከሳሽ ምን ያህል ካሣ ሉከፍል ይገባል? የሚለትን ጭብጦች በመመሥረት፣ ከሳሽ የተከሳሹ ኃላፉነት በጥፊት ላይ የተመሰረተ ነው ብሎል። የከሳሽ የሰነድ ማስረጃዎች ድርጅቱ የተቃጠለው ከሣሽ በዘረጋው የኤላትሪክ መስመር መሆኑን ያሣያለ። የከሳሽ የሰው ምስክሮችም ቃጠልም የደረሰው የኤላትሪክ መስመሩ ተበጥሶ በቤቱ ቆርቆሮ ላይ ከወደቀ በኋላ በተፈጠረው እሳት መሆኑን አስረድተዋል። ሆኖም ከሳሽ ቃጠልው የደረሰው ተከሳሽ ሆን ብል ወይም በቸልኝነት በፈፀመው ተግባር መሆኑን "የማያስረደ" በመሆኑ ተከሳሽ ለጉዲቱ በኃላፉነት አይጠየቅም። ከሳሽ ተከሳሽ ጥፊት የፈፀመ መሆኑን ስላላስረዲ የተከሳሹን ማስረጃ ታዓሚነትና ክብደት መመርመር አስፈላጊ አይደለም በማለት የከሳሽን ክስ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች የካቲት 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት የእሳት ቃጠልው የተነሳው አመልካች በባለቤትነት የሚያስተዲድረው የኤላትሪክ መስመር ተበጥሶ በቤቱ ጣሪያ ላይ በማረፈ ምክንያት መሆኑን አመልካች በማስረጃ እንዲረጋገጠ በውሣኔው ውስጥ በግልፅ አስፍሯል። ተጠሪ በባለቤትነት የያዛቸው የሚያዝባቸውና የሚቆጣጠራቸው የኤላትሪክ መስመሮች በተለያዩ ምክንያቶች ተበላሽተው ወይም ተበጥሰው በልላው ሰው ህይወትና ንብረት ላይ አደጋ እንዲያደርሱ ተገቢውን ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን የተጠሪ የኤላትሪክ መስመር አደጋው ከመድረሱ በፉት ደርሶበት አመልካች ሪፕርት አድርጎ ከተጠገነ በኋላ ተጠሪ ያደረገው ጥገና አስተማማኝ ባለመሆኑ ምክንያት አደጋው የደረሰ መሆኑን አስረድቻለሁ። ይህም የተጠሪን ቸልተኝነት የሚያረጋግጥ ሆኖ እያለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠሪን ማስረጃ ሣይመዝን ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ሚያዝያ 24 ቀን 2003 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከፕሉስ ያቀረቡትን ማስረጃ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው። ተጠሪ የኤላትሪክ መስመሩ ባለቤት ስለሆነ ብቻ ለደረሰው ጉዲት በኃላፉነት ሉጠየቅ አይገባም። የእሳት ቃጠልው የተነሳው ከተጠሪ የኤላትሪክ መስመር ሳይሆን በአመልካች ወጥ ቤት በተነሣ የእሳት ቃጠል ምክንያት ስለመሆኑ ተጠሪ ሙያዊ ማስረጃ አቅርቧል። ስለዚህ የአመልካች የሰበር አቤቱታ የሕግ ድጋፍ የላለው በመሆኑ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ግንቦት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ለደረሰው ጉዲት ተጠሪ ኃላፉነት የለበትም በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርመረናል። ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰንና የሥር ፍርድ ቤት አግባብነት ያላቸውን የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ተገቢውንና ትክክለኛውን ጭብጥ የመሰረተና የግራ ቀኙን ማስረጃ መዝኖ ውሣኔ የሰጠ መሆኑን ለመረዲት እንድንችል የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ በትዕዛዝ በማስቀረብ ተመልክተናል።
ከላይ የተገለፀውን መሰረታዊ ጭብጥ ተጠሪ የኤላትሪክ የማመንጨት፣ የማስተላለፍ፣ የማከፊፈልና የኤላትሪክ ኃይል የመሸጥ ተግባር ሲያከናወን በምን ዓይነት የጥራት ደረጃ /quality standard/ ማከናወን አለበት የሚለውን ነጥብ ማየቱ ተገቢ ነው። ማንኛውም ኤላትሪክ የማመንጨት፣ የማስተላለፍ የማከፊፈልና የመሸጥ ሥራዎችን እንዱሰራ የተፈቀደለት ድርጅት አዋጅ ቁጥር 86/1989 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም የወጡ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እንዱሁም የአካባቢ ጥበቃ በሚመለከት የወጡ ሕጏችንና በኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኤጀንሲ የተወሰኑትን የጥራት ደረጃዎች በማክበር ሥራውን ማከናወን እንዲለበት አዋጅ ቁጥር 86/1989 አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደነግጋል። የኤላትሪክ አቅርቦትን የመስመሮች እና የመሣሪያዎች ደህንነት በሚመለከት አቅርቦት፣ መስመሮችና መሣሪያዎች በተዘረጉበት የአካባቢ ሁኔታዎች የሚጠበቅባቸውን አገልግልት መስጠት እንዱችለ በቂ ኃይል የመሸከምና የኢንሱላሽን ብቃት እንደዚሁም በብልሽት ወቅት ሉከሰት የሚችለውን የኤላትሪክ መጠን የመቋቋም ችልታና በቂ የመካኒካል ጥንካሬ ደረጃ ሉኖራቸውና በሰው፣ በእንስሳት በንብረት ላይ አደጋ በማያስከትል ሁኔታ ሉገነቡ፣ ሉገጣጠሙ፣ ሉጠበቁና ሉጠገኑ እንደሚገባ አዋጅ ቁጥር 86/1989ን ለማስፈፀም የሚኒስሮች ምክር ቤት ያወጣው ደንብ ቁጥር 49/1991 አንቀፅ 35 የሚደነገግ ሲሆን ማንኛውም ኤላትሪክ ለመሥራት ለማሰራጨትና ለመሸጥ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ሥራውን ሲያከናውን የሰውን ሕይወት፣ ንብረትና የአካባቢ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን የመውሰድ ግዳታ እንዲለበት በደንብ ቁጥር 49/91 አንቀፅ 23 ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች አደጋው ከመከሰቱ በፉት በመስመሩ ላይ ብልሽት ተከስቶ የነበረና ይህንንም ለተጠሪ አመልካችና ላልች በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች አሳውቀው ተጠሪ መስመሩን የጠገነ መሆኑን፣ ተጠሪ የጥገና ሥራውን ካከናወነ በኋላ የኤላትሪክ መስመሩ ተበጥሶ ከአመልካች ድርጅት ቆርቆሮ ላይ በማረፈ የእሳት አደጋ በማስነሳቱ አመልካች መስመሩን በንብረት ላይ ጉዲት በሚያስከትል ሁኔታ የመጠገንና የመጠበቅ ግዳታውን ባለመወጣቱ ንብረቱ ወድሞብኛል፣ ተጠሪ ኃላፉነት አለበት በማለት በቃልና በፅሐፍ ያቀረበ ቢሆንም በቃል ክርክር ወቅት ዋናው የመከራከሪያ ጭብጡ በአመልካች ድርጅት ላይ ውድመት ያስከተለው የእሳት አደጋ በኤላትሪክ መስመሩ ብልሸት ወይም መበጠስ ምክንያት የደረሰ አይደለም የሚለው ነጥብ እንደሆነ ጥር 29 ቀን 2001 ዓ.ም በትራንስክራይበር ማሽን የተቀዲውና በፅሐፍ ተገልብጦ ከሥር ፍርድ ቤት ጋር ከተያያዘው የተጠሪን ክርክር ለመገንዘብ ችለናል።
አንድ ፍርድ ቤት የክርክሩን ጭብጥ የሚመሰርተው ከሳሽ ያቀረበውን የክስ ማመልከቻና ክሱን ለማስረዲት ያቀረባቸውን የፅሐፍ ማስረጃዎች ተከሳሽ ያቀረበውን የመከላከያ መልስና የመከላከያ ማስረጃዎች እንደዚሁም ፍርድ ቤቱ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት የቃል ምርመራ ሲያደርግ ተከራካሪዎች ያቀረቡትን ክርክር መሰረት በማድረግ መሆን እንደሚገባው የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ድንጋጌዎች በግልፅ ይደነግጋለ። አመልካችና ተጠሪ ሚያዝያ 9 ቀን 2000 ዓ.ም ለተነሳው የእሳት አደጋ ዋናው መንስኤ አመልካች በአግባቡ ሉጠብቀውና ሉጠግነው ከሚገባው የኤላትሪክ መስመር የኤላትሪክ ሽቦ ተበጥሶ በአመልካች ድርጅት የጣሪያ ሽፊን /ቆርቆሮ/ ላይ በማረፈ ነው ወይስ አይደለም?
በሚለው ነጥብ ላይ ሰፉ ልዩነት ያላቸው መሆኑን በሥር ፍርድ ቤት በቃልና በፅሐፍ ካደረጉት ክርክር ተረድተናል።
ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤት ሉመሰርተው የሚገባው ጭብጥ የእሳት አደጋው የተከሰተው በኤላትሪክ መስመሩ ብልሽትና የኤላትሪክ ሽቦው ተበጥሶ በአመልካች ድርጅት የጣሪያ ክዲን /ቆርቆሮ/ ላይ በማረፈ ነው? ወይስ በአመልካች ኩሽና በተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ የሚለው ጭብጥ መሆን ነበረበት። የሥር ፍርድ ቤት አመልካችን ብቻ ሣይሆን ተጠሪ ይህንን ጭብጥ ለማስረዲት ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች መመርመርና ተጠሪ ታህሳስ 24 ቀን 2001 ዓ.ም ባቀረበው የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር ማስረጃ ውስጥ ስማቸውን የጠቀሳቸውንና የሰማቸውን ሁለት ምስክሮች ቃል መመርመርና መወሰን ይገባዋል። ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤቱ የእሳት አደጋው የተከሰተው ተጠሪ በሚያስተዲድረው የኤላክትሪክ መስመር ላይ በተከሰተ ብልሽትና የኤላትሪክ ማስተላለፉያ ሽቦው ተበጥሶ ከአመልካች ድርጅት የጣሪያ ክዲን /ቆርቆሮ/ ላይ በማረፈ ምክንያት ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ከደረሰ፣ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 86/1989፣ በደንብ ቁጥር 49/91 እና የኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኤጀንሲ ያወጣቸውን የጥራት ደረጃዎች ሙለ በሙለ አሟልቶ መስመሩን የመጠገንና የመጠበቅ ግዳታውን የተወጣ መሆኑን የማስረዲት ሸክሙን ተዓማኒነትና ክብደት ያለው ማስረጃ በማቅረብ አስረድቷል ወይስ አላስረዲም? የሚለውን ጭብጥ በመመዘን፣ አመልካች በተጠሪ ጥፊት በሆነ ቸልተኝነት ምክንያት ለተከሰተው የእሳት አደጋና በንብረት ላይ ለደረሰው ውድመት ተጠሪ በኃላፉነት ሉጠየቅ ይገባል በማለት ያቀረበውን ክስ መቀበል ወይም ውድቅ ማድረግ ሲገባው፣ የሥር ፍርድ ቤት ትክክለኛውን ጭብጥ ሣይመሰረት፣ ተጠሪ በማስረጃ ዝርዝር መግለጫው ስማቸውን የገለፃቸው ምስክሮች ቃል ሣይሰማና የፍታብሓር የማስረጃ ምዘና መርህን መሰረት በማድረግ ከአመልካችና ከተጠሪ የተሻለና ሚዛን የሚደፊ ማስረጃ ያቀረበው የትኛው ነው? የሚለውን ነጥብ ይዞ የአመልካችና የተጠሪን ማስረጃ ተዓሚነትና ክብደት ሣይመዝን የአመልካችን ማስረጃ ብቻ በመመርመርና በመተርጎም የሰጠው ውሣኔ ስለ ጭብጥ አመሰራረት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 246፣ 247 እና 248 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች መሰረት ያላደረገ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የሥር ፍርድ ቤት በፍታብሓር ጉዲይ የተሻለና ሚዛን የሚደፈ ማስረጃ ያቀረበው ጉዲዩን እንዲስረዲ ይቆጠራል የሚለውን የፍታብሓር የማስረጃ አመዛዘን መርህ ያልተከተለና የተጠሪን የመከላከያ ምስክሮች ቃልና የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት ተዓሚነትና ክብደት አልመረመረም፣ አልመዘነም። እንደዚሁም የሥር ፍርድ ቤት በወቅቱ በአካባቢው ተጠሪ የኤላትሪክ ኃይል የማከፊፈል፣ የማሰራጨትና የመሸጥ ሥራ ሲያከናውን ሉያደርጋቸው የሚገቡ ቴክኒካል፣ ሜካኒካልና ላልች የጥንቃቄ መስፈርቶችን ያሟላ መሆን አለመሆኑን አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁጥር 86/1989፣ ደንብ ቁጥር 49/1991 እና የኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኤጀንሲ ያወጣቸውን የጥራት ደረጃዎች መሰረት በማድረግ መመርመርና መመዘን ሲገባው ይህንን ያላደረገ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የፈፀማቸውንና ከላይ የዘረዘናቸውን ስህተቶች ሣያርም ውሣኔውን አፅንቶታል።
በመሆኑም ከላይ በዝርዝር በገለፅናቸው ምክንያቶች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተጠሪ በጉዲቱ በኃላፉነት አይጠየቅም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች ድርጅት ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ /ምክንያት/ ተጠሪ የሚያስተዲድረው የኤላትሪክ መስመር ሽቦ ተበጥሶ ከአመልካች ድርጅት ጣሪያ /ቆርቆሮ/ ላይ በማረፈ ነው ወይስ አይደለም? አደጋው የደረሰው የኤላትሪክ መስመሩ ተቆርጦ በተጠሪ ጣሪያ /ቆርቆሮ/ ላይ በማረፈ ምክንያት ነው ከሚል መደምደሚያ ላይ ከደረሰ፣ ተጠሪ በአካባቢው የኤላትሪክ ኃይል ሲያሰራጭ፣ መስመሩን ሲዘረጋና እድሳት ሲያደርግ በአዋጅ ቁጥር 86/1989፣ በደንብ ቁጥር 49/1991 እና በኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኤጀንሲ የወጡትን የጥራት ደረጃዎች በማሟላት አገልግልቱን የሰጠ መሆኑንና ተጠሪ ማድረግ የሚገባውን ማናቸውንም ጥንቃቄ ያደረገ መሆኑን የቀረበው ማስረጃ ያስረዲል ወይስ አያስረዲም? ተጠሪ በሕግ የተጣለበትን ግዳታ በአግባቡ የተወጣ መሆኑን ካላስረዲ ለደረሰው ጉዲት ጥፊት በሆነ ቸልተኝነት በኃላፉነት ይጠይቃል ወይስ አይጠየቅም? ተጠሪ በኃላፉነት ይጠየቃል ቢባል ሉከፍል የሚገባው የካሣ መጠን ስንት ነው? የሚለትን ጭብጦች በመያዝና የአመልካችንና የተጠሪን የፅሐፍ ማስረጃና የምስክሮች ቃል በመመርመርና በመመዘን አስፈላጊም ከሆነ የኢትዮጵያ ኤላትሪክ ኤጀንሲ ሙያዊ ማብራሪያ እንዱያቀርብ በማድረግ በመመርመር ውሣኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
በትውስት የመጣው የከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ይመለስ።
No topics extracted.