No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ሐጂ መሐመድ አመዳ ጠበቃቸው አቶ ብሥራት መኮንን ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መኮንን መስፍን ጠበቃቸው አቶ ረዲኢ ባራኪ ቀረቡ መዝገቡ መርምረን የሚከተለው ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው በፋ/ከ/ፍርድ ቤት የፍርድ ባለመብት በሆኑት የአሁኑ ሰበር ተጠሪና 2ኛ የፍርድ ባለ ዕዲ በሆኑት የሰበር አመልካች መካከል በነበረው የአፈፃፀም ክስ የፍርድ ባለእዲው የሆነው ቤት ለእዲው እንዱሸጥ የሰጠው ትእዛዝ ነው። የፍርድ ባለዕዲው በዋናነት የሚከራከሩት በፍርድ ባለ መብት ንብረት ላይ ለደረሰው ጉዲት በአራት ተከሣሾች ላይ ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ /አንድ ሚሉዮን /እንዱንከፍል የተወሰነብን በመሆኑ ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ መክፈል የሚገባኝ ብር 25ዐ,ዐዐዐ እና የዚሁ ወለድ ነው በሚል ነው።
የፍርድ ባለመብቱ በበኩላቸው ለፍርድ ባለዕዲው ክርክር በሰጡት መልስ እዲው የመጣው በወንጀል ሀላፉነት በመሆኑ ሀላፉነቱ የሚከፊፈል ባለመሆኑ የፍርድ ባለእዲው ድርሻቸውን ብቻ ለመክፈል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በዋናው ፍርድ የፍርድ ባለዕዲዎቹ ለካሣው ክፍያ ሀላፉነት አለባቸው ስለተባለ የፍርድ ባለእዲው ባልተነጣጠለ ኃላፉነት የማይጠየቁበት ምክንያት የለም ብሎል።
የፋ/ጠ/ፍርድ ቤትም የፍርድ ባለዕዲው ያቀረቡትን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት በመዝጋት ይግባኝ ባዩን አሰናብቷል።
የሰበር አመልካችም በሰበር ቅሬታቸው በዋናነት የጠቀሱት የፍርድ ባለዕዲዎቹ ሀላፉነት ያልተነጣጠለ ነው ከተባለ በዋናው ጉዲይ የተሰጠውን ፍርድ መሰረት ያላደረገ ነው የሚል ነው። ተጠሪው በበኩላቸው በሰጡት መልስ አመልካች ገንዘቡን ከፍለው ከላልች የፍርድ ባለዕዲዎች ከሚጠይቁ በስተቀር በድርሻቸው ብቻ ለመክፈል ያቀረቡት ክርክር የህግ መሰረት የለውም ብለዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካች ያልተነጣጠለ ሀላፉነት ስላለባቸው በአፈጻጸም ክስ የቀረበውን ገንዘብ መክፈል አለባቸው በሚል የተወሰነው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ለዚህ አፈፃፀም ክስ መነሻ የሆነውን ፍርድ በመ/ የሰጠው የፋ/ከ/ፍርድ ቤት ሲሆን የቀበረውም ክስ የአሁኑን የሰበር አመልካች ጨምሮ በመዝገቡ ተከሣሾች የሆኑት በከሣሽ ንብረት ላይ ላደረሱት ጉዲት ብር 1,457,934.50 ባልተነጣጠለ ሀላፉነት እንዱከፍለ ይወሰንባቸው የሚል ሲሆን ፍርድ ቤቱም የአሁኑን የሰበር አመልካች ጨምሮ 4 ተከሣሾች ለደረሰው ጉዲት ሀላፉነት አለባቸው በሚል ብር 1,ዐዐዐ,ዐዐዐ/አንድ ሚሉዮን ብር/ ክሱ ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለከሣሽ ይክፈለ ብል መወሰኑን መዝገቡ ያመለክታል። በዚህ መዝገብ የተሰጠው ፍርድ አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይ አመልካች እና በመዝገቡ ሀላፉነት አለባቸው የተባለ ተከሣሾች ገንዘቡን እንዱከፍለ ከመወሰኑ በስተቀር አከፊፈለን በተመለከተ ሀላፉነት አለባቸው የተባለውን የገንዘብ መጠን እያንዲንዲቸው ድርሻቸውን እንዱከፍለ በሚል በግልጽ ተለይቶ አልተወሰነም። የአመልካች የክስ አቀራረብም ቢሆን የጉዲቱን መጠን በገንዘብ ተምኖ በማቅረብ ተከሣሾቹ ባልተነጣጠለ ሀላፉነት እንዱከፍለ የሚል እንጂ የሚፈለግባቸውን ገንዘብ በድርሻቸው ከፊፍለው አልጠየቁም። በፍ/ህ/ቁ 2155/1/ ብዙ ሰዎች አንድ በሆነ ጉዲይ ለደረሰው ጉዲት ካሣን እንዱከፍለ የተገደደ እንደሆነ በአንድነት እያንዲንዲቸው ሀላፉ እንደሚሆኑ በግልጽ የተደነገገ ሲሆን የካሣው አከፊፈለም ቢሆን ለበደለ ተግባር አነሳሽ በሆነው ፣ በዋናው ወንጀል አድራጊና በበደለ ተግባር ተባባሪ በሆኑ ሰዎች መካከል ልዩነት የማይደረግ መሆኑን በዚሁ በተጠቀሰው ደንጋጌ በንዐስ ቁጥር 2 ተመልክቷል።
በመሆኑም የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ባልተነጣጠለ ሀላፉነት በአፈጻጸም የማይገደደበት ምክንያት የለም በሚል ዕዲውን በድርሻቸው መጠን ለመክፈል ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ ማድረጉ ዋናውን ፍርድ መሰረት ያደረገ ከመሆኑም በላይ በፍ/ህ/ቁ 2155 ስለአንድነት ሀላፉነት የተደነገገውን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝም ሆነ የፋ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህንኑ በማጽናት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ባለማግኘታችን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
የፋ/ከ/ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 3ዐ/6/2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድ እና የፋ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በቀን ዐ3/09/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት አጽንተናል።
አመልካች ያልተነጣጠለ ሀላፉነት ያለባቸው ስለሆነ የአፈፃፀም ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ሉከፍለ ይገደዲለ በሚል የፋ/ከ/ፍርድ ቤትና የፋ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የወሰኑት በአግባቡ ነው ብለናል። አመልካች ባልተነጣጠለ ሀላፉነት የተወሰነባቸውን ገንዘብ ከከፈለ በኋላ ከድርሻቸው በላይ የከፈለትን ገንዘብ ከመጠየቅ ይህ ውሣኔ የሚያግዲቸው አይደለም ብለናል።
የዚህ ፍርድ ቤትን ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።