No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ ነገረ ፈጅ አቶ ነጌሣ አሉ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1- መሐመድ አባ አሉ 2- ዘሀራ አባኑር አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው የበታች ፍርድ ቤቶች ለተጠሪዎች ለእያንዲንዲቸው ብር 1ዐዐዐ /አንድ ሺህ ብር/ በድምሩ ብር 2ዐዐዐ /ሁለት ሺህ ብር/ አመልካች እንዱከፍል የሰጡትን ውሣኔ ህጋዊነት አጣርቶ ለመወሰን ነው። አመልካች ለሞራል ካሣ በድምሩ ከአንድ ሺህ ብር በላይ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያመለከተ ሲሆን ተጠሪዎች ባለመቅረባቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
እኛም ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ የተያዘውን ጭብጥ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን መርምረናል።
አመልካች የተጠሪዎች ልጅ በመሞቱ ምክንያት እንዱከፍል የተወሰነበትን የካሣ ገንዘብ በተመለከተ ለሰበር ችልት ጭብጥ ሆኖ ያልቀረበ በመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ የፀናና ተፈፃሚነት ያለው ነው።
የሞራል ጉዲት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚከፈለው የካሣ መጠን በማናቸውም ሁኔታ ከብር አንድ ሺህ ብር /ብር 1000/ መብለጥ የላለበት መሆኑን “የጉዲት ካሣውም በማናቸውም ምክንያት ከብር 1ዐዐዐ /አንድ ሺህ ብር/ የበለጠ ላሆን አይችልም” በማለት የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2116 ንዐስ አንቀፅ 3 ይደነግጋል። ይህም በአደጋው ጉዲት የደረሰባቸው ሰዎች ብዙ ቢሆንም ለእነርሱ የሚከፈለው የሞራል ካሣ ተደምሮ ከብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ ሉበልጥ የማይገባው መሆኑን ያሣያል። ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ልጃቸው በአደጋው በመሞቱ ምክንያት ለደረሰባቸው የሞራል ጉዲት ለእያንዲንዲቸው ብር 1ዐዐዐ/ አንድ ሺህ ብር/ በድምሩ ብር 2ዐዐዐ /ሁለት ሺህ ብር/ አመልካች የሞራል ካሣ እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2116 ንዐስ አንቀፅ 3 አስገዲጅ ድንጋጌን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ብር 52,2ዐዐ /ሃምሣ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ብር/ ካሣ እንዱከፍል የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካች ለተጠሪዎች ለእያንዲንዲቸው ብር 5ዐዐ /አምስት መቶ ብር/ በድምሩ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ብቻ የሞራል ካሣ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስነናል።
No topics extracted.