No summary available.
ግንቦት 6 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዪጵ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - ነ/ፈጅ ተስፊዬ ኬርጋ ቀረበ ተጠሪ፡- አቶ ወልደ ሚካኤል ሻንቆ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የካሳ ክፍያ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረዉ በደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝቦች ብሓ/ክልላዊ መንግስት በሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ከሳሽነት ነዉ። የካሳ ክፍያ ክሱን የተመለከተዉ ይሄዉ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ በመስማት አመልካች በዘረጋዉ የኤላክትሪክ መስመር ላይ እሳት በመፈጠሩ ምክንያት በተከሰተ አደጋ በተጠሪ የተለያዩ የሰዉነት ክፍልች ላይ ጉዲት የደረሰ ስለመሆኑ፣በዚህም ጉዲት ምክንያት የቀኝ እጁ ያለመንቀሳቀስ ችግር፣የቀኝ ቀለበት ጣት እና ትንሽ ጣት መቆረጥ፣የቀኝ መካከለኛ ጣት፣አመልካች ጣት እና የትልቁ ጣት መድረቅ እና ከአገልግልት ዉጪ መሆን፣የቀኝ እግር 5ኛ ጣት መቆረጥ እና ስቃይ ደርሷል፤ በተጠሪ ላይ 63% ከፉል አቋም የአካል ጉዲት በመድረሱ እንደድሮዉ የማስተማር ስራዉን ማከናወን ባለመቻለ፣ ስራዉን በአግባቡ በሚያከናዉንበት ወቅት የወር ጥቅል ደመወዙ ብር 1,692.00 /አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት/ ሁኖ ከዚህ ዉስጥ በእጅ የሚደርሰዉ 1,403.42 ብር /አንድ ሺህ አራት መቶ ሶስት ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም/ በመሆኑ እስከ ጡረታ መዉጫ ዕድሜ ታስቦ፣ የተለያዩ ወጪና ኪሳራ እንደዚሁም የሞራል ካሳን ጨምሮ ባጠቃላይ 139,228.26 /አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ከሃያ ስድስት ሳንቲም/ አመልካች ድርጅት እንዱከፍለዉ በማለት ዉሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ቅሬታ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.337 መሰረት ሰርዞታል።
አሁን የቀረበዉ ቅሬታ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በቀን 07-4-2003 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል ያላቸዉን ነጥቦች ያነሳ ሲሆን ፍሬ-ሃሳቡ፡- አመልካች ኃላፉ ላሆን በማይችልበት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ከ2124 እስከ 2136 ድረስ በተዘረዘሩት በልላ ሰዉ ጥፊት የጉዲት ካሳ እንዱከፍል መደረግ የላለበት በመሆኑ፣አደጋዉ ሉፈጠር የቻለዉ የከሳሽ ጎረቤት አቶ ማቴዎስ የቴላቪዥን አንቴና የሰቀለበት የባህር ዛፍ እንጨት ከላሉቱ በግምት 9፡15 ላይ በነፊስ ኃይል ተገፍትሮ በአከባቢዉ ከሚገኘዉ የኤላክትርክ መስመር ላይ ሲወድቅበት ቴላቪዥኑ ከፍተኛ ድምጽ ሉያሰማ መቻለ፣ይሄዉ ጎረቤታቸዉ ቤታቸዉ ውስጥ በከፍተኛ ብርሃን ሲሞላ አይተዉ የድረሱልኝ ድምጽ ማሰማቱ፣ተጠሪም በዚህን ወቅት ደርሰዉ መስመሩን ለማላቀቅ ሲሞክሩ የደረሰባቸዉ በመሆኑ ብቻ አመልካች በፍትሐብሕር ህግ ቁ.2069 መሰረት ኃላፉነት አለበት ልባል የማይገባ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጡት ዉሳኔ አግባብነት የላለዉና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ። ላላዉ የክልለ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ክስ ሲያቀርብ በየወሩ ያገኝ የነበረዉ ደመወዝ በቀለብ መልክ እንዲይቋረጥበት ዕድሜዉ 70 ዓመት እስኪሞላቸዉ እንዱከፈል ሆኖ እያለ በደረሰዉ ጉዲት መጠን ካሳ እንዱከፍል ውሳኔ መስጠቱ እና ይሰሩበት የነበረዉ መስሪያ ቤት የጡረታ መብታቸዉን እንዱጠብቅ ዉሳኔ መስጠቱ አግባብነት የላለዉ በመሆኑ እንዱታረምልኝ የሚል ነዉ።
የቀረበዉ ቅሬታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች በፍትሐብሕር ህግ ቁ.2069 መሰረት በተጠሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት በበታች ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር በሚል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ተብል ጭብጥ ተይዞ ተጠሪ በጉዲዩ ላይ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ ቀርቦ መልሱን አቅርቧል። ተጠሪ የሰጠዉ የመልስ ፍሬ-ሃሳብ፡የቀረበዉ ቅሬታ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ የሚያመላክት አይደለም፣ አመልካች ላላ ሰዉ ባጠፊዉ ጥፊት ኃላፉ ላሆን አይገባዉም ለሚለዉ ቅሬታ አመልካች በበታች ፍርድ ቤት ጥፊተኛ የተባለዉ አመልካች በዘረጋዉ የኤላክትሪክ መስመር ምክንያት ጉዲት በመድረሱ በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ደግሞ ምንም ዓይነት ጥፊት ባይኖርም በሰራዉ አደገኛ ስራ ምክንያት በፍትሐብሕር ህግ ቁ.2069 መሰረት ኃላፉነት ስላለበት በመሆኑ፣ የካሳ መጠኑን በተመለከተም የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ምክንያት የቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም የሚል ነዉ። አመልካች ባቀረበዉ የመልስ መልስ ቅሬታዉን በማጠናከር ተከራክሯል።
በግራቀኙ መካከል የተደረገዉ የክርክር ሂደት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም በቅድሚያ እልባት ማግኘት ያለበት ነጥብ የበታች ፍ/ቤቶች በቀረበው ክስ ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የኃላፉነት እና የካሳ መጠን ውሳኔ የሰጡበት ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑ መመልከት ተገቢ ይሆናል።
No topics extracted.
በእርግጥ በፍትሐብሕር ህግ ቁ. 2027 ስር ከውል ውጭ ኃላፉነት የሚመጡበትን አግባቦች የሚያመለክት ሲሆን በተለይ የዚህ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር ሁለት ስር አንድ ሰው በህጉ ላይ እንደተመለከተው በልላ ሰው ላይ ጉዲት ሉያደርስ የሚችል ስራ ከሰራ ወይም በእጁ የያዘው ነገር በልላው ሰው ላይ ጉዲት ካደረሰ ኃላፉ እንደሚሆን ያመላክታል። በልላ በኩል አንድ ሰው ኃላፉነት ሉመጣበት የሚችለው ጥፊትን መሰረት አድርጏ ስለመሆኑ ከፍትሐብሕር ህግ ቁ.
2028 እና ተከታዮቹ እንደዚሁም ጥፊት ሳይኖርበት ኃላፉነት ሉመጣበት እንደሚችል ከፍትሐብሕር ህግ ቁ.2066 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻል ከመሆኑም በላይ እንደየ ኃላፉነቱ ዓይነት መሟላት ያለባቸውን ነጥቦች በዝርዝር ያስቀምጣል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው የኤላክትሪክ መስመሩ በራሱ ጉዲት አድርሶ ሳይሆን የጎረቤት የቴላቪዥን አንቴና በተዘረጋው የኤላክትሪክ መስመር ላይ በመውደቁ እና ከፍተኛ ድምጽ በዚህ ምክንያት በመፈጠሩ ጎረቤቶቹ የድረሱልኝ ድምጽ በማሰማታቸው አመልካች ለእነዚሁ ጎረቤቶች እርዲታ ለማድረግ ሲሄድ ለክሱ ምክንያት የሆነው ጉዲት የደረሰበት ስለመሆኑ ነው። የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች ኃላፉነት አለበት ወደሚለው መደምደሚያ የደረሱት በደፈናው በፍትሐብሕር ህግ ቁ. 2069 መሰረት አመልካች አውቆ የሰራው ጥፊት ባይኖርም አጥፉ ሳይሆን ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ በመጥቀስ ነው።
ሆኖም አመልካች ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም?፣ ኃላፉነት አለበት ከተባለስ በየትኛው የህግ አግባብ እንደሆነ ድምዲሜ ከመደረሱ በፉት ሉጣሩ የሚገባቸው በርካታ ነጥቦች እንዲለ መገንዘብ ይቻላል። መጣራት ካለባቸው ነጥቦች መካከል በተጠሪ ላይ ጉዲት ሉደርስ የቻለው አመልካች እንደሚለው የተጠሪ ጎረቤት የቴላቪዥን አንቴና በኤላክትሪክ መስመሩ ላይ በመውደቁ ምክንያት ነው ወይስ በልላ ምክንያት?፣ ጉዲቱ ሉደርስ የቻለው በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሆነ፣ አመልካችን ጥፊት ሳይኖር ኃላፉ ሉያደርጉ የሚችለ አደገኛ ሁኔታዎችን ስለመፍጠሩ የሚያመላክት ነጥብ ስለመኖር ወይም አለመኖር፣ ወይም ጥፊትን መሰረት ያደረገ ኃላፉነት ሉያመጣ የሚችል እና አመልካች በስራው ሉያደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ ሳያደርግ የቀረ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ በግራቀኙ ማስረጃ በበታች ፍርድ ቤቶች መንጠር የነበረባቸው ፍሬ ነገሮች ናቸው። እነዚህ ፍሬ ነገሮች ሳይነጥሩ በዚህ ጉዲይ የበታች ፍ/ቤቶች ወደ ድምዲሜ መድረሳቸው በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.
246፣247 እና ተከታዮቹ እንደዚሁም በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ፣ 259 እና ተከታዮቹ ስር የተመለከቱትን አግባብነት ያላቸውን ጭብጥ ስለመያዝ፣ ክስ ስለመስማት እና ማስረጃን ስለመመርመር በተመለከተ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ዓላማ፣ ይዘት እና መንፈስ ያላገናዘበ መሆኑን መመልከት ይቻላል። በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት የጉዲት ካሳ እንዱከፍል ውሳኔ የሰጡት ተገቢው ማጣራት ባልተደረገበት ሁኔታ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አካሄድ ሆኖ አልተገኘም።
ባጠቃላይ የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት የኃላፉነት እና የካሳ ክፍያ ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢው መጣራት ሳይደረግበት በመሆኑ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የደቡብ ብሓ/ብሓ/ህዝ/ብሓ/ክል/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.50846 በቀን 24-03- 2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት እና የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.06278 በቀን 19-2- 2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት ወደሚለው መደምደሚያ የደረሱት ተገቢውን ማጣራት ሳያደርጉ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አካሄድ አይደለም ብለናል።
የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍርድ ሀተታው በተመለከተው አግባብ የቀረበውን ክስ በግራ ቀኙ ማስረጃ በማጣራት ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት ጉዲዩን በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.
343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።