No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 25 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- 1- አቶ ፍቃደ ተስፊዬ ቀረቡ 2- አቶ በጡሬ ሲማ 3- ወ/ሮ ዘብደሩ ወኑ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አንድ የፍርድ አፈፃፀም ጥያቄ በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ የባለእዲው ንብረት እዲውን ሉሸፍን ባለመቻለ በከፉል ተፈፅሞ ከቆየ በኋላ የፍርድ ባለመብት የባለእዲውን ንብረት አፈላልጎ በማግኘት አፈፃፀሙን ለመቀጠል ሲፈልግ ይርጋው ሉቆጠር የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነው። የአፈፃፀም ክሱ /ክርክሩ/ የጀመረው በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ነው። በአፈፃፀም ክሱ እንደተመለከተው ለአቶ ፈቃደ ተስፊዬ የሰጠው ብድር በወለ መሰረት ባለመከፈለ በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ የአፈፃፀም ተከሣሾች /የአሁኑ ተጠሪዎች/ በአንድነት እና በነጠላ ያለባቸውን ቀሪ እዲ ብር 147,922.00 /አንድ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት ብር /እንዱከፍለ ሕዲር 2 ቀን 199ዐ ዓ.ም በዋለው ችልት መወሰኑን ፣ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሰረት በአገኘው መብት አፈፃፀሙን በራሱ ቀጥል ግንቦት 21 ቀን 1999 ዓ.ም. በዝዋይ ከተማ ዐ2 ቀበላ ውስጥ በአቶ ፍቃደ ተስፊዬ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውንና ቁጥር 21/164/80 የሆነውን ቤት በብር 5ዐ,4ዐዐ.ዐዐ በመሸጥ ይህንኑ የሽያጭ ገንዘብ ከእዲው የቀነሰ ሲሆን በወቅቱ የባለእዲዎች ንብረት ባለመኖሩ አፈፃፀሙን መቀጠል ያለመቻለን ፣ ከዚህ በኋላ የዋናው ተበዲሪ ዋስ በሆኑት በአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበ ንብረት ማግኘቱን ገልጾ ቀድሞ በፍርድ ቤት በአገኘው ውሣኔ መሰረት አፈፃፀሙን በዚሁ በዋሱ ንብርት እንዱቀጥልለት ጥቅምት 23 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርቧል። የስር ፍርድ ቤትም የአፈፃፀም መዝገቡ የቀረበው በፍርድ ቤቱ ውሣኔ ከተሰጠ ከአስራ አራት አመታት በኋላ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ቀሪ እዲ መኖሩን አውቋል ልባል የሚችለው የአቶ ፈቃደ ተስፊዬ ንብረት ሽጦ ቀሪ እዲው መኖሩን ከአወቀበት ጊዜ ጀምሮ ሁኖ እያለ ይርጋው ከሕዲር ዐ2 ቀን 199ዐ ዓ.ም ጀምሮ ነው መቆጠር ያለበት ተብል የአፈፃፀም መዝገቡ መዝጋቱ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የአመልካች የአፈፃፀም መዝገብ በይርጋ ቀሪ ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪዎች ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች የብድሩን ገንዘብ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባለመክፈላቸው አመልካች በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦባቸው ፍርድ ቤቱ ሕዲር ዐ2 ቀን 1990 ዓ.ም በዋለው ችልት በዋናው ጉዲይ ላይ ውሣኔ መስጠቱን ይህንኑ ውሣኔ መሰረት በማድረግ አመልካች አፈፃፀሙን በፍርድ ሳይቀጥል ቆይቶ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሰረት በአገኘው መብት አፈፃፀሙን በራሱ ቀጥል ግምቱ ብር 5ዐ,4ዐዐ.ዐዐ /ሃምሳ ሺህ አራት መቶ ብር/ የሆነውን የዋናውን ተበዲሪ ንብረት ግንቦት 21 ቀን 1999 ዓ.ም በመሸጥ በፍርድ ቤቱ ከተወሰነበት ከብር 147,922.ዐዐ ገንዘብ ውስጥ ተቀናሽ ማድረጉንና ከዚህ በኋላ በመያዣነት ያልተያዘ የዋሱ ንብረት ተገኝቷል በሚል ምክንያት አፈፃፀሙን በፍርድ ቤት በኩል ለመቀጠል ጥቅምት 23 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም መንቀሳቀሱን ነው። ከዚህ በቀላለ መገንዘብ የሚቻለው አመልካች የዋናውን ተበዲሪ ቤት ለእዲው መክፈያ ግንቦት 21 ቀን 1999 ዓ.ም ቢያውልም የቤቱ ግምት እዲውን ሙለ በሙለ ሳይሸፈን መቅረቱን ነው። የዋናውን ባለዕዲ ቤት ሽጦ ከእዲው ተቀናሽ ቢያደርግም በዚህ ረገድ ተከፈለ ልባል የሚችለው ዕዲ በተጠሪዎች ላይ የሚፈለገውን አጠቃላይ ዕዲ የሚሸፍንለት ሆኖ ባለማግኘቱ ቀሪው ዕዲ እንዱከፈለው በመጠየቁ የአፈፃፀም ክስ መስርቶአል። አመልካች የዋሱን ቤት ሽጦ የሸያጩን ገንዘብ ከእዲ ተቀናሽ የአደረገበት ጊዜ ቀሪ እዲ የሚፈልግ መሆኑን ያረጋገጠበት ጊዜ ነው የሚባል ከመሆኑም በላይ ባለእዲዎች በዚህ ጊዜ እዲውን ለመሸፈን የሚያስችል ንብረት የነበራቸው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም።
No topics extracted.
ለአፈፃፀም የሚውል የባለእዲ ንብረት ከላለ አፈፃፀሙ መቀጠል የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 329/2/ ድንጋጌ ያሳያል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት የፍርድ ባለእዲውን እንደፍርደ ለመፈፀም የማይቻል መሆኑን ከአረጋገጠ ፍርደ እንዱፈፀም ትዕዛዝ እንደማይሰጥ ሆኖም ለመፈጸም ችልታ በሚያገኝበት በማናቸውም ጊዜ እንዱፈፀም ትእዛዝ ከመስጠት እንደማይታገድ ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 384 ድንጋጌ ልዩ ሁኔታ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 384 ስር የተመለከተው የአስር አመት የጊዜ ገደብ የፍርድ ባለመብት ምንም እንቅስቃሴ ሳያደርግ ቆይቶ ፍርደን ለማስፈፀም ሲንቀሳቀስ ተፈፃሚ የሚሆን ድንጋጌ ነው። በልላ በኩል በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ቡድሩን ለማስመለስ ስልጣን የተሰጠው ባንክ አፈፃፀሙን ራሱ የሚመራው ቢሆንም የባለእዲው መያዣ የሆነ ንብረት ያለመኖሩንና መያዣ በሆነ ንብረት እዲውን መሸፈን ካልቻለ አፈፃጸሙን መቀጠል ያለበት ይህንኑ ከአረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ላሆን ይገባል። አመልካች በባለእዲው ንብረት ላይ ሕዲር 23 ቀን 1990 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ ለአፈፀፀም ላቀርብ የሚገባው በአስር አመት በመሆኑ አመልካች ግንቦት 21 ቀን 1999 ዓ.ም በዋናው ባለእዲ ንብረት ላይ አፈፃፀም መቀጠለ የይርጋ ጊዜውን የሚያቋርጥ ሕጋዊ ምክንያት ነው። በመሆኑም አዱሱ ይርጋ መቆጠር የሚጀምረው ከሕዲር 23 ቀን 199ዐ ዓ.ም ጀምሮ ሳይሆን ከግንቦት 21 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ በመሆኑ እና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እንደገና እንደአዱስ የይርጋ ዘመን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1852 መሰረት ሲቆጠር አመልካች የአፈጻጸሙን ክስ ያቀረበው ጥቅምት 23 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በመሆኑ በሕጉ የተመለከተው የአስር አመት የይርጋ ጊዜ አላለፈም። ስለሆነም ከግንቦት 21 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዲር 21 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዜ ሲታሰብ አስር ዓመት አልሞላም። የስር ፍርድ ቤቶች የይርጋውን ጊዜ ያሰለት ከህዲር 23 ቀን 199ዐ ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ የአስር ዓመትን የይርጋ ጊዜ መሰረት በማድረግ ክስ የማቅረቢያ ጊዜው አልፍአል የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሳቸው በህጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ሕዲር 19 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ. ህዲር 22 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ አልሆነም ብለናል። በመሆኑም የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን በተጀመረው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ በአፈፃፀም ክሱ ስረ ነገር ላይ ግራ ቀኝ ወገኖች የሚያቀርቡለትን ክርክር እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341/1/ መሰረት መልሰንለታል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።