No summary available.
ሚያዝያ 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ በላቸው እሸቴ - ጠበቃ አቶ ወርቅዬ አባይነህ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነገረ ፈጅ ማህላት ዓለሙ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። አመልካችና ተጠሪ ለደረሰው አደጋ ተጠሪ ካሣ የመክፈል ከውል የመነጨ ኃላፉነት አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ነጥብ ሲከራከሩ ቆይተው ተጠሪ አደጋውን ያደረሰው ጉዲት በመድን ውለ መሰረት ካሣ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ ውሣኔ ተሰጥቷል።
የዚህ ክርክር መሰረታዊ ጉዲይ አመልካች ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በእሳት የተቃጠለችው ቁጥር ኮድ 3-02549 ለሆነችው መኪና በመድን በውለ የተሰጠው ሽፊን ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በመሆኑ በዚህ መሰረት ሉከፈል ይገባል በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ መኪናው አደጋ በደረሰበት ጊዜ የነበረው ዋጋ ብር 95,099.92 እንደሆነ በገለልተኛ ባለሙያ ተገምቷል። ልከፍል የሚገባው ይህንን ገንዘብ ነው በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት መኪናዋ አደጋ ሲደርስ የነበራትን ዋጋ አመልካች እንዲልተቃወመ በውሣኔው ገልፆ፣ ተጠሪ ብር 95,099.92 /ዘጠና አምስት ሺህ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሁለት ሣንቲም/ ለአመልካች እንዱከፍል የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ሰጥቷል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ሰኔ 6 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ሑሳብ ፔሪሚየም ሲሰበሰብ ቆይቷል። የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ የንግድ ሕግ ቁጥር 654/1/ እና የንግድ ሕግ ቁጥር 665/1/ መሰረታዊ ድንጋጌዎች የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ኀዲር 18 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር መልስ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የንግድ ሕግ ቁጥር 678 በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ በሰበር ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት በአመልካች ሉከፈለው የሚገባው መድን የተገባለት መኪና በአደጋው ጊዜ የነበረትን ዋጋ ያህል ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በንግድ ሕጉ እውቅናና ጥበቃ ስለተሰጣቸው የኢንሹራንስ /የመድን ሽፊን/ አይነቶችንና ባህሪያት መመርመር አስፈላጊ ነው። በንግድ ሕጉ እውቅና የተሰጠው የመጀመሪያው የኢንሹራንስ ውል የደረሰን ጉዲት ለመካስ ወይም ለመተካት /Indemnity Insurance/ የሚደረግ ውል እንደሆነ በንግድ ሕጉ አንቀፅ 654 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገገ ሲሆን፣ የደረሰን ጉዲት ለመካስ ወይም ለመተካት /Indemnity Insurance/ የሚደረግ የኢንሹራንስ ውልች በንብረት ላይ ለሚደረስ ጉዲትና በፍታብሓር የሚመጣ ኃላፉነት /Indemnity Insurance/ የሚያካትት እንደሆነ በግልፅ ተደንግጓል። ሁለተኛው ዓይነት የኢንሹራንስ ውል የደረሰን ጉዲት ለመካስ ወይም ለመተካት ሳይሆን አደጋው ሲደርስ በውለ የተገለፀውን ገንዘብ ለተጠቃሚው ወይም የመድን ውል ለገባው ሰው ለመስጠት የኢንሹራንስ ውል (non Indemnity Insurance or capital insurance) እንደሆነና ይህም ለህይወት ወይም በአካል ጉዲት ወይም በሕመም ለሚደርስ አደጋ የሚሰጥ የመድን ሽፊን እንደሆነ በንግድ ሕጉ አንቀፅ 654 ንዐስ አንቀፅ 3 ተደንግጓል። የንግድ ሕጉ በተለያየ መንገድ ፈርጆ ያስቀመጣቸው እነዚህ ሁለት አይነት የመድን ውልች በይዘታቸው፣ በባህሪያቸውና በሚኖራቸው ውጤት የሚመሳሰለበትና የሚለያዩበት ሁኔታ መኖሩን ሕግ አውጭው በምዕራፍ ሁለት ማለትም ከንግድ ሕጉ አንቀፅ 657 እስከ አንቀፅ 674 ጠቅላላ የመድን ሕግ ድንጋጌዎችን፣ በምዕራፍ ሶስት ማለትም በንግድ ሕጉ ከአንቀፅ 675 እስከ አንቀፅ 688 ስለጉዲት ኪሣራ ኢንሹራንስ ላይ ልዩ ተፈፃሚነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን፣ በምዕራፍ ሶስት ማለትም ከአንቀጽ 689 እስከ አንቀፅ 712 የሰዎች ኢንሹራንስ ላይ ተፈፃሚነት ያላቸውን ልዩ ድንጋጌዎች በመደንገግ በግልጽ አሳይቶናል።
የንግድ ሕግ አንቀጽ 665 በአጠቃላይ ጉዲት ለመካስ ወይም ለመተካት እና ለሰዎች ኢንሹራንስ ላይ ተፈፃሚነት ያለው ጠቅላላ ድንጋጌ ሲሆን፣ በይዘቱ የመድን ሽፊን የሚሰጠው የኢንሹራንስ ኩባንያ ለመድን ገቢው ወይም ለተጠቃሚው ሉከፍለው የሚችለው ወይም ሉከፍለው የሚገባው የኢንሹራንስ ገንዘብ በመድን ውለ ከተገለፀው ሉበልጥ የማይችል መሆኑን የሚያሣይ ነው።
ንግድ ሕግ አንቀፅ 678 ስለንብረት የተደረገ ኢንሹራንስ ውል የሚኖረውን ውጤት በልዩ ሁኔታ የሚደነግግ የሕግ ድንጋጌ ነው። በመርሕ ደረጃ ለንብረት የሚሰጥ የኢንሹራንስ ሽፊን አደጋው በደረሰበት ጊዜ ንብረቱ የነበረውን ዋጋ የሚያካክስ መሆን እንዲለበት የሚደነግግ ነው። በንብረት የሚደረግ ኢንሹራንስ መሰረታዊ ዓላማው ንብረቱ በመጎዲቱ ወይም ንብረቱ በመውደሙ በባለንብረቱ ላይ የደረሰውን ኪሣራ ለመተካት ነው። ይህም በመሆኑ የንብረቱ ዋጋ ከተሰጠው የኢንሹራንስ ሽፊን በልጦ ሲገኝ መድን ገቢው በመድን ውለ ሽፊን ከተሰጠው ዋጋ በላይ ላለው ገንዘብ ራሱ የመድን ሽፊን እንደሰጠ ተቆጥሮ፣ መድን ሰጭው በውለ የተገለፀውን ዋጋ ብቻ የሚከፍል ስለመሆኑ፣ የዕቃው ዋጋ ከተሰጠው የመድን ሽፊን አንሶ ሲገኝና መድን ገቢው የማታለል፣ የማጭበርበር ተግባር ያልፈፀመ በሆነ ጊዜ የዕቃው እውነተኛ ዋጋ የሚከፈለው መሆኑን በንግድ ሕጉ አንቀፅ 680 ንዐስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል። እንደዚሁም አንድ ሰው አንድን ንብረት ለተመሣሣይ አደጋ ለተለያዩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የመድን ሽፊን እንዱኖረው ቢያደርግ የመድን ሽፊን የሰጡት ኩባንያዎች በውላቸው ፔሮፕርሽናል በሆነ መንገድ አዋጥተው የዕቃውን ዋጋ ብቻ የሚክሱት ስለመሆኑና አንድ ሰው ከዕቃው ዋጋ በላይ የሆነ ገንዘብ አንድን ዕቃ በተለያየ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሽፊን እንደሰጡት በማድረግ ሉያገኝ እንደማይችል በንግድ ሕጉ አንቀጽ 681 በግልፅ ተደንግጓል።
ከላይ ከገለፅነው መሰረታዊ ድንጋጌዎች አንፃር ስንመለከተው የአመልካች መኪና ጉዲት በደረሰበት ጊዜ የነበራት ዋጋ በመድን ውለ ከተገለፀው ያነሰ እንደሆነ ተረጋግጧል። ስለሆነም ተጠሪ የሚከፍለው በውለ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን ሳይሆን ንብረቱ በአደጋው ውድመት ሲደርስበት የነበረውን ዋጋ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሣኔ የንግድ ሕግ አንቀፅ 678 እና የንግድ ሕግ አንቀፅ 680 ንዐስ አንቀጽ 2 እና ስለንብረት ጉዲት የተደረገ የመድን ውል የሚኖረውን ውጤት የሚደነግጉ ላልች ልዩ ድንጋጌዎችን ይዘት፣ ባህሪያትና ውጤት ያገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.