No summary available.
የካቲት 27 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወጋገን ባንክ አ.ማ ነ/ፈጅ ገቢሣ ተሬሣ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ አበዲሪ ባንክ ለሰጠው ብድር ሁለትና ከዚያ በላይ መያዣ ይዞ ቆይቶ ብድሩ ባለመመለሱ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት መያዣውን ለመሸጥ ሲንቀሳቀስ ከመያዣዎቹ መካከል ቀድሞ መሸጥ ያለበት ንብረት የትኛው እንደሆነ በፍርድ ቤት ሉወሰን የሚችል መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች ከሣሽ፣አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ። ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የመሰረቱት ክስ ባጭሩ፡- አመልካች ለሚለማ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብር አምስት ሚሉዮን የኦቨር ድራፍት ብድር በዋስትና መያዥነት ተበዲሪው በቡራዩ ከተማ ካለው መጋዘን ቤት በተጨማሪ በውርስ የተገኘውን የተጠሪዎችን መኖሪያ ቤት በተጨማሪ መያዥነት አስይዞ እንደነበር፣ተበዲሪው የተበደሩትን ብድር ያልመለሱ መሆኑን፣አመልካች ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን የተበዲሪውን መጋዘን ሸጦ ለብድሩ ማስመለሻ ማድረግ ሲገባው የባለዲውን መጋዘን ትቶ የተጠሪዎችን የውርስ ቤት በሐራጅ ሉሸጥ እንደማይገባ ዘርዝረው በተጠሪዎች ቤት ላይ የጀመረውን የሐራጅ ሽያጭ አቁሞ በመጀመሪያ የተበዲሪውን ንብረት የዕዲው ማስመለሻ አድርጏ እንዱቀጥል፣የተጠሪዎችን የቤት ካርታ እንዱመልስ ይወሰንልን በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስ በአዋጅ ቁ 97/90 እና 216/92 መሰረት ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የላለው መሆኑን፣ እዲው አለመከፈለና ቤቱ መያዣ መሆኑ ባለመካደ ተጠሪዎች ክስ ለማቅረብ መብት የላላቸው መሆኑን፣ተበዲሪ ካልከፈለ በቅድሚያ በአንደኛ ደረጃ የተያዘው የተበዲሪው ንብረት ይሸጣል የሚል ስምምነት ባለመኖሩ በዚህ በኩል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የላለው መሆኑን፣የፍ/ሕጉን ድንጋጌዎች በመጥቀስ የቀረቡ ክርክሮች ከአዋጅ ቁ 97/90 ድንጋጌ ውጪ መሆናቸውን፣አመልካች ከአዋጅ ቁ 97/99 አንፃር ያመነበትን ንብረት መሸጥ የሚችል መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ከሣሽና ተከሣሽ በቅድሚያ የባለዕዲው ንብረት ሉሸጥ ይገባል በማለት በመያዣ በተሰጠ ንብረት ላይ የተጀመረ ሐራጅን ለማስቆም ይችላል? ወይንስ አይችልም? የሚል ጭብጥ መስርቶ መዝገቡን በመመርመር ባንክ የሰጠው ብድር ሣይመለስ ሲቀር መያዣውን በመሸጥ የባለቤትነት መብት እንዱዛወር ለማድረግ ካባለዕዲው ጋር መስማማትና በዚሁ ስምምነት ተፈጻሚ ማድረግ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት መደንገጉን፣ክስ በቀረበበት ጉዲይም ከሣሽ በመያዣ የሰጡት ቤት ዕዲ ካልተከፈለ ባንኩ እንዱሸጥ መስማማቱን የመያዣ ውለ የሚያሳይ መሆኑን፣ይህ ሥርዓት በአዋጅ ለባንኩ የተፈቀደው ባንኩ የሰጠውን ብድር በፍጥነት መሰብሰብ የማስቻል ዓላማ የያዘ መሆኑ ግልጽ መሆኑን፣አመልካች በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን ተፈፃሚ ለማድረግ ሲንቀሣቀስ ተጠሪዎች የፍትሒ ብሓር ሕጉ ስለተራ ዋስትና የደነገገውን መነሻ በማድረግ በቅድሚያ የባለዕዲው ንብረት ሣይሸጥ ባንኩ በተጠሪዎች ንብረት ላይ ሐራጅ መቀጠል አይችልም በማለት መከራከራቸው አግባብነት የላለውና አዋጁን የሚቃረን መሆኑን በመዘርዘርና በምክንያትነት በመያዝ የተጠሪዎችን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጥቶታል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪዎች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማሻሻል በመያዣነት የቀረበው የተጠሪዎችን ንብረት ማረጋገጫ ሰነድ በአመልካች ዘንድ እንደሆነ አመልካች በቅድሚያ ለዚሁ ብድር በመያዣ የያዘውንና በቡራዩ ከተማ የሚገኘውን የተበዲሪውን ንብረት በጨረታ ሸጦ የሰጠውን ብድር ያስመልስ፣አመልካች የሚሸጠው የተበዲሪው መጋዘን ብድሩን በሙለ ካላስመለሰለት የተጠሪዎችን የመያዣ ንብረት ሸጦ ቀሪውን ብድር ያስመልስ በማለት ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለውጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የአዋጅ ቁ 97/90 ዋና ዓላማ በፍ/ቤት የሚፈጀውን ጊዜ በማሣጠር ለልማት እንቅስቃሴው የሚሰጡ ብድሮችን ወቅቱን ጠብቆ እንዱሰበሰብ ማስቻል መሆኑን፣የደረሰ ጉዲትን ከሚመለከት ጉዲይ በስተቀር ጉዲዮች ወደ ፍ/ቤት ለመምጣት የማይችለ መሆኑን፣ ወደ ፍ/ቤት መምጣት ይችላለ ከተባለ ወደ ነበርንበት መመለስና ባንኯችም ብድራቸውን በጊዜው እንዲይሰበስቡ የሚያደርጋቸው መሆኑን፣በተጠሪዎች የተጠቀሱት የፍትሒ ብሓር ሕግ ድንጋጌዎች ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የላላቸው መሆኑን፣በሕጉ አግባብ በተደረገው ውል መሰረት አከራካሪው ንብረት መያዣ መሆኑ ያለመካደን፣እንዱህ ከሆነ ደግሞ ግራ ቀኙ የሚገዙት በውለ መሆኑን፣በውለ ደግሞ መጀመሪያ የተበዲሪውን ንብረት ሸጠህ ነው ወደ እኔ የምትመጣው የሚል ስምምነት የላለ መሆኑን፣ውለ የሚለው ዕዲው ካልተከፈለ ንብረቱ ይሸጣል ስለመሆኑ፣ የተበዲሪው መጋዘን ብር 12 ሚሉዮን ያወጣል የተባለውም በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ ያልተረጋገጠ መሆኑን፣ ተበዲሪው በርካታ እዲ እንዲለባቸው እና ተጠሪዎችም የተበዲሪው ድርጅት እዲ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸው መሆኑን፣ የመያዣውን ንብረት የመሸጥ መብት መያዣ ያዡ ባንክ እንጂ ተበዲሪው ከመያዣዎቹ ውስጥ መያዣ ያዡን ባንክ ይህን ሽጥ ይህን ደግሞ አትሽጥ የማለት መብት የላላው መሆኑንና መብቱ የአመልካች ባንክ መሆኑን፣ፍ/ቤቶች በአዋጅ ቁ 97/90 አፈጻጸም ላይ ጣልቃ የሚገባቡት መንገድ የተለየ መሆኑን በመዘርዘር የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ተሸሮ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዱፀና ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርመሮም አመልካች በቅድሚያ የተበዲሪውን ንብረት ሽጦ ለእዲ መመለሻ ያውል የመባለን እና ላልች ነጥቦችን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በጽሐፍ የሰጡት መልስ ባጭሩ፡- የአዋጅ ቁጥር 97/90 ዓላማ ባንኮች በመያዣ የሚያዟቸውን ንብረቶች ለፍ/ቤት ማመልከት ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው መሸጥ እንዱችለ ሆኖ በመሆኑ የይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል ያለውን በውል ላይ የተመሰረተ እኩልነትን ያረጋገጠ መሆኑን፣አመልካች የሰጠውን ብድር እጥፍ የሚሸፍን ንብረት በእጁ እያለ የተጠሪዎችን መኖሪያ ቤት ለመሸጥ መንቀሣቀሱ ቅን ልቦና የላለው አካሄድ መሆኑን፣ተበዲሪው ከአመልካች ዘንድ በመያዣ የተያዘውን በቡራዩ ከተማ የሚገኘውን መጋዘን ሸጬ የብድሩ መመለሻ እንዲደርግ ይፈቀድልኝ ብል ጥያቄ አቅርቦ በአመልካች ትብብር መከልከለ ያላግባብ መሆኑን፣ተጠሪዎች የተበዲሪው ንብረት በቅድሚያ እንዱሸጥ ጠቁመው በአመልካች ጥያቄአችን ውድቅ ተደርጎ የተጠሪዎች ንብረት ለመሸጥ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ትክክል አይደለም ተብል በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት መወሰኑ የተጠሪዎችን በሕግ ፉት እኩልነትና ፍትሕ የማግኘት መብትን ያረጋገጠና በሕግ፣ በሞራልና ከአመክንዮ ጋር የተጣጣመ መሆኑን፣የብድሩን መጠን በተመለከተ አመልካች በሰበር አቤቱታው ላይ የጠቀሰውም በማስረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን በመዘርዘር የይግባኝ ሰሚው ችልት ውሣኔ ምንም የሕግ ስህተት የለውም ተብል ሉጸና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የተጠሪዎች ጥያቄ በፍርድ ቤት ላታይ የሚችልበት ሕጋዊ አግባብ አለ? ወይስ የለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት አመልካች በመያዣ ከያዛቸው ንብረቶች መካከል አንደ የሆነውን የተጠሪዎችን ንብረት ከመሸጡ በፉት ላላ መያዣ የሆነ የተበዲሪ ድርጅት መጋዝን ስለአለ ይህንኑ መጋዝን ቀድሞ ሉሸጥ ሲገባ የተጠሪዎችን መኖሪያ ቤት ለመሸጥ መንቀሳቀሱ ተገቢ አይደለም በሚል ምክንያት መሆኑን፣የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔውን ሉያሳልፍ የቻለው አከራካሪው ንብረት በመያዣ መሰጠቱን አረጋግጦ ከዚሁ ንብረት ጋር በመያዣነት የተሰጠ የተበዲሪ ንብረት ስላለ ይኸው ቀድሞ ሳይሸጥ የተጠሪዎች ንብረት መያዣ በመሆኑ ብቻ የሚሸጥበት አግባብ የለም በሚል ምክንያት መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች በሐራጅ መሸጥ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 98/90 እና 216/92 የሕግ ሥርዓት ተዘርግቷል። ይህንን በሚያደርግበት ጊዜ ባንኩ ሉከተለው የሚገባው ሥርዓትም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ከቁጥር 394- 449 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች ስር በተመለከተው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 97/90 በአንቀጽ 6 በግልጽ አስፍሯል። በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀፅ 3 እና 4 መሰረት እንደዚሁም በአዋጅ ቁጥር 216/19992 በተደረገው ማሻሻያ ባንኮች ለሰጡት ብድር አከፊፈል በመያዣነት በዋስትና የተቀበለትን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት የብድር እዲው እንዱከፈለው በተወሰነው ጊዜ ሳይከፈል ከቀረ ከሰላሳ ቀናት ያላነሰ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የመያዣ ንብረቱን በሐራጅ ለመሸጥና ባለቤትነቱንም ለገዢው ለማዛወር ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። ከአዋጁ ድንጋጌዎችም መረዲት የሚቻለው አበዲሪው ባንክ በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች የብድር ገንዘቡን ካልተመለሰለት ያለማንም ጣልቃ ገብነት አግባብነት ያላቸውን የሕጉን ድንጋጌዎችን በመከተል በሐራጅ ሽጦ ለእዲው ክፍያ ማዋል እንደሚችልና በአሻሻጡ ሂደት ባንኩ ሕጉን ባለመከተል የፈጸመው ስህተት ቢኖርና በዚህም በባለእዲው ላይ ጉዲት ቢደርስ ለዚህ ጉዲት ባንኩ ለባለእዲው ካሳ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ነው። የአዋጆቹ ዝርዝር ድንጋጌዎች ይዘት ሲታይም የሕጎቹ ዓይነተኛ አላማ ባንኮች የሚሰጧቸውን ብድሮች በተቀላጠፈ አኳኋን ለመሰብሰብ እንዱችለ ስለመሆኑ የሚያስገነዝብ ሲሆን ይህ ስለመሆኑም አዋጅ ቁጥር 97/1990 መግቢያው ላይ በግልፅ አስቀምጧል።
ባንክ ከላይ በተጠቀሱት አዋጆች መሰረት በመያዣ የያዘውን ንብረት አስገምቶ ሐራጅ ቢያወጣና ቢሸጥ ወይም በሕጉ መሰረት ቢረከብ ግምቱን ወይም በመያዣ የተሰጡትን ንብረቶች አሻሻጥ ቅደም ተከተል ምክንያት በማድረግ ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደገና እንዱያይ፣እንዱያስገምት ወይም ከመያዣዎቹ አንደ ቀድሞ መሸጥ አለበት ብል ለመወሰን የሚያስችል ከሕግ የመነጨ ሥልጣን የለውም። በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 7 ስር የተደነገገውን ድንጋጌ መግቢያ በማድረግ መያዣው በብድሩ ወቅት በተገመተበት ግምት እንዱያዝ መጠየቅም ሆነ በሐራጅ ወቅት የወጣው መነሻ ግምት አነስተኛ ነው ብል ለፍ/ቤት ጥያቄ ማቅረብ ከፍ/ቤቱ ስልጣን ውጪ ከመሆኑም በላይ አዋጁ የወጣበትን ዓላማም ከግብ እንዲይደርስ የሚያደርግ ጭምር ስለመሆኑ የሚታመን ነው። ይህ የሕጉ አጠቃላይ ቅርፅ የሚያስገነዝበን ላላው ቁም ነገር በመያዣ ውለ የተቀመጡት ንብረቶች ተለይተው የታወቁ እስከሆነ ድረስና የተያዙበት አግባብም አንደ መያዣ ከላላው በቅደም ተከተል የሚሸጥ አለመሆኑን የሚያሳይ ከሆነ ከመያዣዎች ውስጥ ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረት ሳይሸጥ አነስተኛ ግምት ያለው ቀድሞ ሉሸጥ አይገባም በሚል የሚቀርበው የዲኝነት ጥያቄ የመያዣ ውለንና ከላይ ከተጠቀሱት አዋጆች አላማ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ፍርድ ቤት የሐራጁን ስርዓት በማስቆም የሚያስተናግድበት አግባብ ሉኖር አይችልም።
ከላይ እንደተጠቀሰው ባንክ የሐራጅ ሽያጩን የሚያከናውነው ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 394-449 ስር በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ነው። የሐራጁ ሽያጭ ሂደት በሕጉ አግባብ ካለተፈፀመ እና ይህ ከተረጋገጠ ሕጉ ባንኩን ለተፈፀመው ስህተትና ውጤቱ ተጠያቂ ያደርገዋል። ይህም በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 7 ስር ከተመለከተው ድንጋጌ የምንገነዘበው ሐቅ ነው። ይህ ድንጋጌ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌዎች ተላልፍ በመያዣው ላይ ሽያጭ ከተፈፀመ ሃላፉነቱ የባንኩ እንደሆነም በግልጽ ያሣያል። ከላይ የተመለከቱት የፍትሒ ብሓር ስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተጥሰዋል የሚለው ክርክር በባንኩ ላይ በፍርድ ቤት ላቀርብ የሚችለው ባንኩ ሐራጁን እንዲያከናውን በማድረግ ሳይሆን የሐራጅ ስርአቱ ከተከናወነ በሁዋላ ስለመሆኑም የሚታመን ነው። ጥያቄው ከሐራጁ በፉት በፍርድ ቤት ላታይና ሐራጁ እንዱቆም ላደረግ ይችላል ከተባለ ከላይ እንደተገለጸው በፍርክልዠር ሕጎች የታሰበው የብድሮች በተቀላጠፈ ሁኔታ የመሰብሰብ እድል የተገደበ እንዱሆን የሚያደርግ መሆኑ ግልጽ ነው። የተጠሪዎች ጥያቄ ይዘቱ ሲታይ አመልካች በመያዣ ከያዛቸው ንብረቶች መካከል የመኖሪያ ቤቱ ከመሸጡ በፉት ለእዲው ተመጣጣኝ የሆነ መጋዘን ስላለ ይህንኑ ንብረት መሸጥ አለበት የሚልና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 394(2) ስር የተመለከተውን የስነ ስርዓት ሕግ አጠቃላይ መንፈስ መሰረት ያደረገ ነው።
በእርግጥ ይኸው ድንጋጌ ባንኩ እንዱከተለው በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ግዳታ የተጣለበት ነው።
ይሁን እንጂ ይኸው ድንጋጌ ተጥሷል የሚለው ወገን በፍርድ ቤት ዲኝነት የሚያቀርበው የሐራጅ ስርዓቱ እንዱቆም በማድረግ ሳይሆን ይኸው ድንጋጌ በሐራጅ ጊዜ በባንኩ ባለመጠበቁ የደረሰ ጉዲት ካላ ይህንኑ በማረጋገጥ ነው። በአጠቃላይ ተጠሪዎች አመልካች በመያዣ ከያዛቸው ንብረቶች መካከል ከፍተኛ ግምት ያለውን የተበዲሪውን መያዣ ሉሸጥ ይገባል እንጂ በመያዣ የተሰጠውንና አነስተኛ ግምት ያለውን መኖሪያ ቤት አመልካች ሉሸጥ አይገባም በማለት ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ በፍርድ ቤት የሚስተናገድ አይደለም። ስለሆነም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 ዓይነተኛ አላማን ከተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ እንዱሁም አከራካሪው ንብረት በሕግ አግባብ በተቋቋመ የመያዣ ውል መሰረት የተያዘ ከመሆኑ አንፃር በመመርመር ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማስተናገድ ስልጣን ያለው መሆን ያለመሆኑን ማገናዘብ ሲገባው አመልካች ከያዛቸው ንብረቶች መካከል የተበዲሪ ድርጅት መጋዘን ከፍተኛ ግምት ስላለው የተጠሪዎች መኖሪያ ቤት ከመሸጡ በፉት ቀድሞ መሸጥ አለበት ሲል የሰጠው ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 ስር የተመለከቱትን ግልፅ ድንጋጌዎችን የሚቃረን ሁኖ አግኝተናል። ግልጽ ሕግ ደግሞ ውጤት እንዲይኖር የሚደረግበት የዲኝነት አሰጣጥ ስርዓትም ሆነ የሕግ አተረጎጎም ደንብ የለም። በመሆነም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች የስር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ስላገኘን የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 12 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በሕግ አግባብ በተቋቋመ የመያዣ ውል ከተያዙት ንብረቶች መካከል የትኛው ንብረትና የማን ንብረት መሸጥ አለበት የሚለው ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እንደተሻሻለው የዋስትና መያዣዎችን ባንኮች ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሸጠው ለዕዲ ክፍያ ማዋል የሚችለ ስለመሆኑ ከተደነገገው ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ በፍርድ ቤት ላታይ የሚችል አይደለም ብለናል።
በመሆኑም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በተሰጠው ስልጣን መሰረት በተጠሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ የጀመረው የሀራጅ እንቅስቃሴ የተበዲሪው ንብረት የሆነውና የብድሩ መያዣ መጋዝን ከተሸጠ በሁዋላ ሉከናወን ይገባል ብል ፍርድ ቤት ሉወሰን የሚችልበት ከሕግ የመነጨ ስልጣን የለውም ብለናል።
የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 99689 የካቲት 07 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ የክርክር ደረጃ ያለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.