No summary available.
ታህሣስ 05 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የአቶ ናስር አባጃቢር አባጅፊር ሚስትና ወራሾች
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጉዲት ካሣ ይከፈለኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች አውራሽ ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ሰኔ 01 ቀን 1992 ዓ.ም እና ህዲር 22 ቀን 1993 ዓ.ም በተደረገው የብድር ውል በዋስትና ያስያዙት ንብረት በሐራጅ በተሸጠበት ወቅት ተጠሪ ሆነ ብል በእዲ ከያዘው ንብረቶች ውስጥ በሐራጅ መካተት የሚገባቸውን ንብረቶችን ባለማካተቱና ንብረቱ በተገቢው መንገድ ባለመሸጡ ከሣሽ ብር 1,280 ,556.70 /አንድ ሚሉዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ አምስት መቶ ሃምሣ ስድስት ብር ከሰባ ሣንቲም/ ያጡ መሆኑን ገልጸው ተጠሪ ይህንኑ ገንዘብ ከእነ ወለደ እንዱከፍላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸዉን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርቧል። በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበው ክርክርም ሐራጁ ከተከናወነ ከሶስት ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ክሱ መቅረቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 447/1/ ድንጋጌ መሰረት የማይፈቀድ በመሆኑ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። የስር ፍ/ቤትም የከሣሽ ጥያቄ ንብረቱ በሐራጅ በመሸጡ ላይ የቀረበ ተቃውሞ ሳይሆን በሐራጅ ጊዜ መካተት የሚገባቸው ንብረቶች ሣይካተቱ ቀርተው ጉዲት ደርሶብኛል የሚል ነው የሚል ምክንያት በመያዝ ይኸው ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 447/1/ መሰረት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ላቀርብ ይገባ ነበር በማለት ክሱን ውድቅ አድርጏታል። በዚህ ብይን የስር ከሣሽ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በተጠሪ ላይ የቀረበው ክስ ለክርክሩ ምክንያት በሆኑት ንብረቶች ላይ የተካሄደው የሐራጅ ሽያጭ ይፍረስልኝ ወይም ይሰረዝልኝ ሳይሆን ንብረቶችን ያለዋጋ ስለአስተላለፊቸው ግምታቸውን ተጠሪ ሉከፍል ይገባል የሚል ሁኖ እያለ የበታች ፍ/ቤቶች ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 447/1/ በመጥቀስ ክሱ በሁለት ወር ይርጋ የታገደ ነው በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢነት የላለው ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለጉዲዩ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 447/1/ ተጠቅሶ ክሱ በሁለት ወር ይርጋ ቀሪ ነው ተብል መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርበ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጏለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን ውሣኔ ከህጉ ጋር አገናዝቦ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካቾች አውራሽና በተጠሪ መካከል የብድር ውል ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ብድሩ የተወሰደውም በተለያዩ ጊዜአት ሁኖ ተበዲሪው ገንዘቡን ሉመልሱ ባለመቻላቸው ተጠሪ በብድር ውለ በመያዣነት የያዘውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሰረት በሐራጅ መሸጡን ተበዲሪው ግንቦት 05 ቀን 2002 ዓ.ም ለመሰረቱት ክስ መሰረት ያደረጉት ምክንያትም ተጠሪ በዋስትና የያዘውን ንብረት ታህሣስ 20 ቀን 1999 ዓ.ም ሲሸጥ በሐራጁ መካተት የሚገባቸውን ንብረቶች ሳያካትት ቀርቶ ያለዋጋ ማስተላለፊን የሚገልጽ ሁኖ የጠየቁት ዲኝነት የእነዚህ ንብረቶች ግምት እንዱከፈላቸው መሆኑን ነው። የስር ከሣሽ ከሐራጅ መሰረዝ ወይም መፍረስ ጋር አያይዘው ያነሱት የዲኝነት ጥያቄ የላለ መሆኑንም ተገንዝበናል።
በመሰረቱ የአንድ መብትና ግዳታ ምንጭ ህግ ወይም ውል ነው በህግ ወይም በውል ጥበቃ ያገኘ መብት ወይም ግዳታ ጉዲት ሲደርስበት ወይም ተገቢው ካሣ የሚያስከፍል ከሆነ በህጉ ተለይቶ በተመለከተው የጊዜ ገደብና አካል ተገቢው ዲኝነት እንዱሰጥ ክስ ላቀርብበት የሚገባው ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የስር ከሣሽ ለክሳቸው መሰረት ያደረጉት ተጠሪ ባንክ ለብድሩ በዋስትና የተሰጡትን ንብረቶች በሐራጅ ሲሸጥ በሐራጅ መካተት የሚገባቸውን ንብረቶችን ሳያካትት በመቅረቱ ያለዋጋ ንብረቶችን በማስተላለፍ ጉዲት በማድረሱ የንብረቶችን ግምት ሉከፍል ይገባል በማለት ነው። ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች በሐራጅ መሸጥ እንዱችል በአዋጅ ቁጥር 97/90 አዋጅ ቁጥር 98/90 እና አዋጅ ቁጥር 216/92 መሰረት የህግ ሥርዓት ተዘርግቷል። ባንኩ መያዣውን ሲሸጥ ሉከተለው የሚገባው ሥርዓትም በ1958ቱ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህጋችን ከቁጥር 394 እስከ 449 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ስለመሆኑም አዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 6 ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 7 ድንጋጌ ሲታይም የሐራጅ ሽያጩ ሂደት በህጉ አግባብ ካልተፈጸመ እና ይህ በተገቢው መንገድ ከተረጋገጠ ህጉ ባንኩን ለተፈጸመው ስህተትና ውጤቱ ተጠያቂ እንደሚያረገው ያስገነዝባል። አመልካች በተጠሪ ደርጊት ከላይ በተገለጸው አግባብ የተፈጸመባቸው እና የጉዲት ኪሣራ የጠየቁም አይደለም። ለክሳቸው መሰረት ያደረጉት በአዋጁ መሰረት አመልካች ሐራጁን ሲያወጣ መካተት የሚገባቸው ንብረቶች ሳይካተት ቀርቷል የሚል ነው። እንዱህ ከሆነ የአመልካቾች አውራሽ የዲነኝት ጥያቄ መሰረት ያደረገው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2027 እና 2028 መሰረት የጉዲት ካሣ የሚጠየቅበትን አግባብ ነው። ምክንያቱም አንድ ንብረት በሐራጅ ሲሸጥ በሐራጁ መካተት የሚገባቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 423/2/ ስር ተዘርዝረዋል። ይህ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 አንቀጽ 6 መሰረት ባንኩ የሐራጁን ስራ በሚያከናውንበት ጊዜ ሉከተላቸው ይገባቸዋል ተብለው ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ስር የሚገኝ ነው። ይህን ደንጋጌ ባለመከተል የሚደርሰው ጉዲት /DAMAGE/ ደግሞ የሚጠየቀው በአዋጅ ቁጥር 97/1990 አንቀጽ 7 መሰረት ነው። አንድ ሰዉ ህግን በመጣስ በልላ ሰው ላይ ለሚያደርሰው ጉዲት ከውል ውጪ ኋላፉነት ያለበት ስለመሆኑ ደግሞ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2027፣ 2028 ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2035 ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም የውል ግንኙነትን መሰረት በማድረግ በሚካሄድ እንቅስቃሴና በአዋጅ ቁጥር 97/90 የተሰጠውን ስልጣን ለመጠቀም መነሻ ያደረገ እርምጃን ለመውሰድ በህጉ የተመለከተውን ስርዓት ያለመከተል እንደጥፊት በመቁጠር ባንኩ ካሣ እንዱከፍል አዋጅ ቁጥር 97/1990 አንቀጽ 7 ስለሚደነግግ እና ይህ ድንጋጌ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2037 ድንጋጌ ጋር ተዛምድ ሲታይ ከላይ በተመለከተው መንገድ የሚጠየቀው የጉዲት ካሣ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143/1/ ድንጋጌ መሰረት እስከ ሁለት ዓመት ክስ ሲቀርብ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 447/1/ ስር የተመለከተው የሁለት ወር የጊዜ ገደብ የሐራጅ ይፍረስልኝ ወይም ይሰረዝልኝ ጥያቄን የሚገዛ እንጂ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ፣ 98/1990 እና 216/1992 በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ሐራጁ በሚከናወንበት ጊዜ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 394 እስከ 449 ድረስ ያለትን ድንጋጌዎችን ባለመከተል የሚደርሰውን ጉዲት ካሣ ለመጠየቅ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አይደለም። ምክንያቱም በፍርክልዠር ሕግ መሰረት የሚከናወን ሐራጅ በፍ/ቤት የሚሰርዝበትአግባብ የላለ ሲሆን ሐራጁ በሕግ አግባብ ያለመከናወን በባንኩ ላይ የጉዲት ካሣ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ተቀምጧልና።
በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች የአመልካች አውራሽ ጥያቄ የጉዲት ካሣ ጥያቄ ሆኖ እያለ ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 447/1/ ድንጋጌን መሰረት በማድረግ ውድቅ ማድረጋቸው በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው። ይሁን እንጂ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2143/1/ ድንጋጌ ስር የተመለከተው የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ ማለፍ ያለማለፊ ሲታይ የአመልካቾች አውራሽ ክስ የመሰረቱት ግንቦት 05 ቀን 2002 ሲሆን ንብረቶቹ በሐራጁ ላይ ሳይካተቱ ተሸጡ የተባለት ጊዜ ደግሞ ታህሣስ 20 ቀን 1999 ነው። ይህም ጊዜ ሲሰላ የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ ከአለፈ በሁዋላ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች ክሱን ውድቅ ማድርጋቸው በውጤት ደረጃ የምንቀበለው ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.