No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 16 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዲ 06 አስተዲደር ነገረ ፈጅ አቶ አማረ ከፍያለው - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለምፀሐይ ወልዳ ጠበቃ አቶ ፀጋዬ ተስፊዬ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በሁከት ይወገድልኝ የቀረበን ክርክር የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበችው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ነው። ተጠሪ በቂርቆስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 10 ቁጥሩ 059 ከመንግስት ተከራይተው ብቻቸውን በመኖር ላይ እያለ አመልካች ነሐሴ 27 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ደብደቤ በባለቤትሽ ስም የመኖሪያ ቤት ያለሽ በመሆኑ የያዝሽውን የቀበላ ቤት እንድትለቂ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛአል። ስለዚህ ባል ያለኝ ወይም የላለኝ መሆኑን በአግባቡ ሣያረጋግጥ ቤቱን እንድለቅ ማስጠንቀቂያ በመፃፍ የፈጠረብኝ ሁከት ይወገድልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርቦ ከከሳሽ ጋር ያለን ከቤት ኪራይ ውል የመነጨ ግንኙነት ነው። ከሣሽ በንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበላ 02 ሁለት ልጆች በትዲር ከወለደላቸውና አብረዋቸው በሚኖሩት ባለቤታቸው አቶ ክፍለ ኢሣያስ ስም ቤት እንዲላቸው ስለተረጋገጠ ከቀበላ የተከራዩትን ቤት እንዱለቁ ማስጠንቀቂያ መስጠታችን ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ (ከሳሽ) በባለቤታቸው ስም መኖሪያ ቤት ያላቸው በመሆኑ አመልካች (ተከሣሽ) የቀበላውን ቤት እንዱለቁ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተገቢ ነው በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጓል። ተጠሪ ይግባኝ ለአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካችን ይግባኝ በፍታብሓር ሥነ- ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰረዞታል። ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለከተማው የሰበር ችልት አቅርበዋል የከተማው የሰበር ችልት ተጠሪ ከአቶ ክፍለ ኢሳያስ ጋር ጋብቻ ያላቸው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሣኔ ሽሯል።
አመልካች ሚያዚያ 11 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በባለቤታቸው ስም የግል የመኖሪያ ቤት እንዲላቸው ተረጋግጦ እያለ ከአመልካች የተከራዩትን ቤት እንዲይለቁ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው ሰኔ 20 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ከአቶ ክፍለ ኢሣያስ ጋር ጋብቻ ወይም የጋብቻ ሁኔታ የላለን መሆኑ ስለተረጋገጠ የከተማው ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክረዋል። አመልካች ሐምል 18 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አመልካች በተጠሪ ላይ ሁከት ፈጥሯል በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪ የሚኖሩበት የቤት ቁጥር 059 ባለሀብት መሆኑ አላከራከረም። ተጠሪ በዚሀ ቤት ውስጥ የሚኖሩበት ከአመልካች ጋር ባደረጉት የኪራይ ውል መሰረት መሆኑን ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ እና በየደረጃው ባቀረቡት ክርክር አረጋገጠዋል። አመልካች ተጠሪ በኪራይ ውል የያዙትን ቤት እንዱለቁ እና የኪራዩን ውል ለማቋረጥ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? አመልካች በኪራይ ውለ ይገደዲል ወይስ አይገደድም? የሚለት ጭብጦች በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የኪራይ ውልና አግባብነት ያላቸውን የህግ ማእቀፍች መሰረት በማድረግ የሚታይ ነው።
አንድ ሰው በልላው ሰው ላይ ሁከት ፈጠረ ተብል ውሣኔ የሚሰጠው የላላ ሰውን ይዞታ የወሰደበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት የፈጠረበት መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ በፍታብሓር ሕግ ቀጥር 1149 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ የቤቱ ባለሀብት የሆነው አመልካች ቤቱን በኪራይ የያዙት ተጠሪ እንዱለቁለት ማስጠንቀቂያ መፃፈና የኪራይ ውልን የማቋረጥ ሀሣብ ያለው መሆኑን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 2966 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ማሳወቁ ከአከራይ ተከራይ ውልና ግንኙነት አንፃር የሚያታይ እንጂ እንደ ሁከት ተግባር የሚቆጠር አይደለም።
No topics extracted.
ስለሆነም ተጠሪ ለአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በግልፅ ያቀረበችው የዲኝነት ጥያቄ አከራዩ አመልካች ከህግ ውጭ የኪራይ ውልን ለማቋረጥ ማድረጉ ተገቢ ስላልሆነ በኪራይ ውለ እንዱገደድ ውሣኔ ይሰጥልኝ የሚል ሣይሆን አመልካች ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሁከት እየፈጠረብኝ ስለሆነ ሁከቱ ይወገድልኝ የሚል ነው። የሥር ፍርድ ቤት ሁከት አለ ወይስ የለም?
የሚለውን ጭብጥ መወሰን ሲገባው አመልካች የኪራይ ውለን ያቋረጠው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመመርመር ውሣኔ መስጠቱ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 182 ንዐስ አንቀጽ 2 የሚጥስ ሲሆን የከተማው የሰበር ችልትም አመልካች በተጠሪ ላይ የፈጠረው ሁከት አለ ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ ብቻ በመወሰን ውሣኔ መስጠት ሲገባው አመልካች የኪራይ ውልን ለማቋረጥ ማስጠንቀቂያ የሰጠው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተጠሪ አመልካች ሁከት ፈጥሮብኛል ሁከቱ ይወገድልኝ በማለት ያቀረበችው ክስ የህግ መሰረት የላለው ሆኖ እያለ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ከጠየቀችው ዲኝነት በመውጣት አመልካች የኪራይ ውለን ለማቋረጥ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ላይ ውሣኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪ ላይ የፈፀመው የሁከት ተግባር የለም በማለት ወስነናል።
ይኸ ውሣኔ ተጠሪ የኪራይ ውለን መሰረት በማድረግ ሥልጣን ላለው አካል መብቱን ከመጠየቅ የሚገድባት አይደለም። ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።