No summary available.
ሚያዚያ 24 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ድፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሶሬሳ ጋሪ ከጠበቃ አቶ መልካም አለማየሁ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አብርሃም ፍቃደ - ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው አመልካች ለተጠሪ የሰጠሁትን ገንዘብ ብር 280,000.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) ይመልስልኝ በማለት ያቀረበው የክስ አቤቱታ እና የጠየቀው ዲኝነት የገንዘብ አደራን መነሻ ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመለየትና ጉዲዩን ከማስረጃ አቀባበል ስርዓት አንፃር ተመልክቶ ተገቢውን የህግ ትርጉም ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩም አመጣጥ ባጭሩ የአሁኑን አመልካች መኪና ለመግዛት ወስኜ እያለ በመካከለ ወደ ቻይና ሀገር ለመሄድ በማቀዳ የመኪናውን ዋጋ ተጠሪ እንዱከፍለልኝ ብር 280,000.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) በአደራ ሰጥቻቸዋለሁ። ይሁን እንጂ ብሩን እንዱከፍለኝ ብጠይቅ ዛሬ ነገ እያለ ፍቃደኛ ስላልሆኑ ይመልሱልኝ በማለት በአሁን ተጠሪ ላይ ክስ አቅርቧል።
ተጠሪም በሰጡት መልስ የሥጋ ዝምድና፣ የሥራ ሽርክና ወይም የውክልና ግንኙነት ሳይኖረን ይህንን ብር ሰጠሁ የሚለት ሐሰት ነው። አልሰጡኝም። በማለት ክድ ተከራክሯል። ክሱ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ከዋናው የክርክር ደረጃ ከመድረሱ በፉት ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው የግራ ቀኙ የፅሐፍ ክርክር ላይ በመመርኮዝ ከሳሽ የአሁን አመልካች ገንዘቡን በአደራ ሰጠሁ የሚለው ገንዘብ ተቀባዩ እንዱገለገልበት ፈቅድ ከሆነ የግራ ቀኙ ክርክር በፍ/ብ/ህ/ቁ 2782(1) እንደተደነገገው የብድር ውልን በሚመለከቱት ደንቦች መሰረት ሉገዛ ወይም ሉወስን የሚገባው ነው። ስለዚህ ከሳሽ የአሁኑ አመልካች ገንዘቡን ለተከሳሽ ለአሁን ተጠሪ የሰጠሁት የመኪና ግዥ ዋጋ እንዱከፍለልኝ ነው በሚል ምክንያት ሰጠሁ ካለ ገንዘቡ ሳይታሸግና ሳይዘጋበት መሰጠቱን ያሳያል ገንዘብ ሳይታሸግና ሳይዘጋበት ተሰጥቶ ከሆነ ደግሞ ገንዘብ ተቀባዩ እንዱገለገልበት ተፈልጎ እንደተሰጠ ስለሚቆጠር ይህ የግራ ቀኙ ጉዲይ ስለ ገንዘብ ብድር በሚመለከቱት ደንቦች መሰረት ሉጣራ የሚገባው ነው። ከእነዚህም ደንቦች መካከል በፍ/ብ/ህ/ቁ 2472 እንደተመለከተው ከብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በላይ የተሰጠን የብድር ገንዘብ ለማስረዲት መቅረብ የሚገባው የማስረጃ አይነት የጽሐፍ እንጂ የሰው ምስክርነት ቃል አይደለም። ከሳሽ ክሱን ለማስረዲት የቆጠረው የሰው ማስረጃ ስለሆነ ማስረጃው ተቀባይነት የለውም ስለዚህ ክሱ ወድቅ ነው በማለት ወስኗል።
የአሁን አመልካች ያቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.
337 መሰረት ተቀባይነት የለውም በሚል በመዘጋቱ ምክንያት ይህ የሰበር መዝገብ ላቀርብ ችሎል።
በሰበር ቅሬታው ላይ የአሁን አመልካች ያቀረቡት እና በሰበር ፍ/ቤቶች ዲኝነት ያላረፈበት አንደ የክርክር ነጥብ ለዚሁ የፍታብሓር ብይን መነሻ በሆነው ገንዘብ ምክንያት በተጠሪ ላይ የወንጀል ክስ ቀርቦ ጉዲዩ ሲታይ ከቆየ በኋላ ጥፊተኛ ተብል ቅጣት ተጥልበታል። ይህንን ማስረጃ በክሱ ሂደት ለስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በማስረጃነት ባቀርበውም ፍ/ቤት አልተመለከተልኝም የሚለው ነው። ተጠሪ በበኩለ በሥር ፍ/ቤት ያልተሰማና ያልታየን ማስረጃ እንደ አዱስ በሰበር ደረጃ ባለ ክርክር ለማቅርብ ስነ ስርዓት ህጉ ሰለማይፈቅድ ተቀባይነት ያለው አይደለም በማለት ተከራክሯል። ከዚህ በቀር ሁለቱም ወገኖች በዚህ ሰበር ደረጃ ያቀረቡት ላልች የመከራከሪያ ነጥቦች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡትን ክርክር የሚያጠናክር በመሆኑ በድጋሜ ማስፈሩ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም። እንዱሁም የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበው የክስ አቤቱታ ከተገለፁት የፍሬ ነገር ዝርዝር ጉዲዮች ገንዘቡን በአደራ ሰጥቻቸዋለሁ የሚል ሀረግ እንደታከለበት ይመልከት እንጂ ዝርዝር የክስ ምክንያቱን ማየት እንደሚቻለው ገንዘቡን ለተጠሪ ሰጠሁ የሚለበት ምክንያት እራሳቸው አመልካች ለፈፀሙት ውልና ግዥ ለክፍያ እንዱውል ክፍያውን እንደ አመልካች ሆነው እንዱፈፅሙላቸው እንጂ ገንዘቡ የተሰጠው ተጠሪ በእጃቸው አድርገው በአደራ እንዱያቆዩላቸው የሚገልጽ አይደለም። አደራ የሚለው ቃል መካተቱ የክሱን ጉዲይ በፍ/ብሓር ህጉ የተመለከተውን የአደራ የህግ ጽንስ ሀሳብ ሉያመለክት የሚችል አይደለም። ስለሆነም የአሁን አመልካች እንደ አባባላቸው ገንዘቡን ለተጠሪ ሰጥተዋል ወይስ አልሰጡም? የሚለውን ክርክር ለማስረዲት የአሁን አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 መሰረት ዘርዝሮ ያቀረባቸው የሰው ማስረጃዎች ተቀባይነት ያላቸው በመሆኑ ክሱ ከጅምሩ በህግ በተፈቀደ ማስረጃ ተደግፍ እንዲልቀረበ ተቆጥሮ ወድቅ ነው መባለ የክሱን አርእስተ ጉዲይ እና ጉዲዩን ለማስረዲት የቀረበውን ማስረጃና የማስረጃ አቀባበል ስርዓትን ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በውሳኔው ላይ እንደገለጸው ጉዲዩን የሚያስረዲልኝ በወንጀል ችልት የተሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔና ቅጣት የስር ፍ/ቤት ሉመለከትልኝ አልቻለም በማለት የአሁኑ አመልካች ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 222 እና 223 በሚያዘው መሰረት የቀረበ አለመሆኑን ተረድተናል። ይልቁንም ክሱ ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀረበ በኋላ የአሁኑ ተጠሪ ሐምል 23 ቀን 2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት በወንጀል ችልት ጥፊተኛ መባለ ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ሆኖም ይህ ማስረጃ እንደ ሥርዓቱ የቀረበ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ግራ ቀኙ በየፉናቸው ለሰበር ሰሚ ችልት ለማስረዲት ካቀረቡት የጽሐፍ ክርክር መገንዘብ እንደተቻለው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለዚህ ሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን የፍ/ብሓር ክስ ተከሳሹ በላለበት እንዱታይ ብይን ሰጥቶ የነበረ መሆኑንና ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ይህንኑ እርሱ በላለበት እንዱታይ የሚያደርገውን ብይን ለማስነሳት ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ በወንጀል እስር ምክንያት ማረሚያ ቤት የነበረ መሆኑን በማስረዲት አቅርቦት በዚህም ሳቢያ ጉዲዩ እርሱ ባለበት ታይቶ ሉወሰን መቻለን አስመልክቶ የአሁን አመልካች ያቀረበውን ክርክር የአሁን ተጠሪ አላስተባበለም። በዚህ አኳኋን በእራሱ ተከሳሽ በነበረው ወገን የቀረበን ማስረጃ እኔ ሳላውቀው እንደ አዱስ የቀረበ ማስረጃ ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 239 የተመለከተውን ሥርዓት የሚያሟላ አይደለም በሚል የአሁን ተጠሪ ያቀረበው ክርክር የማስረጃ ማቅረቢያ ጊዜንና ደረጃ አስመልክቶ የተመለከተውን ሥርዓት እና የህጉን መነሻ ዓላማ መሰረት ያደረገ አይደለም።
አመልካችም ቢሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሰረት ለማረጋገጥ የቀረበን ማስረጃ በአንድ በኩል ከቁጥር 78 አንፃር የበኩለን ክርክር ማቅረብ ወይም ማስረጃነቱን የሚቀበለው ከሆነም ሲያየው ጉዲዩ ያለውን አግባብነት በማሳየት እንደ ሥርዓቱ በማስረጃ እንዱታይለት መጠየቅ እንጂ በቁጥር 78 መሰረት ተከሳሹ ባለበት ክርክሩ ይታያል ወይስ አይታይም የሚለው ጭብጥ ለመለየት በተደረገው የክርክር ደረጃ ማስረጃው እኔንም አንደሚጠቅመኝ ገልፀው ተከራክሪያለሁ ሆኖም ፍ/ቤቱ አለተመለከተልኝም የሚለው መከራከሪያ ነጥብ የእራሱን የክርክር አቀራረብ ጉድለት ከሚያሳይ በቀር ፍ/ቤቱ የፈፀመውን የጉዲይ አካሄድ ጉድለት አይመለከትም።
ይሁን እንጂ ማስረጃው ከፍ/ብሓር ክርክሩ ዘግይቶ መገኘቱን ክርክሩ ለደረሰበት ደረጃ እና ማስረጃው ለክርክሩ ካለው አግባብነት አንፃር በማየት ጉዲዩን ሲመለከተው የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ይህንኑ ማስረጃ በማቅረብ ረገድ የፈፀመውን የአቀራረቡ ሥርዓት እንዱታረምና እንዱስተካከል በማድረግ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ሲባል መቀበል ይችል የነበረ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 137፣256 እና 91 ደንጋጌዎች አመልካች ናቸው።
በዚህ ሁለ ምክንያት ይህ ጉዲይ በይዘቱ ገንዘብ አደራ ክርክር እንደሆነ በመቁጠር ይህንንም ክርክር ለማስረዲት የቀረቡት የሰው ማስረጃዎች ተቀባይነት ያላቸው አይደለም በማለት የተሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የሥነ ሥርዓት ህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ፤ እንዱሁም የአሁን ተጠሪ በዚሁ ጉዲይ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ የተባለበትና የቅጣት ውሣኔ የተሰጠበት የወንጀል ፍርድ ለፍትሐብሓሩ ክርክር በማስረጃነት ቀርቦ ላታይ የሚችልበት ሥርዓትና አግባብ እያለ ሳይታይ በዝምታ መታለፈም ከማስረጃ አቀባበል ሥርዓት አንፃር የታለፈ ጉድለት በመሆኑ እነዚህ በጉዲዩ አመራር ሂደት የተከሰቱት ሥነ ሥርዓታዊ ጉድለቶች የታረሙ ሆኖ በማግኘታችን በኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስ አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት የሚከለተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ፍርድ እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ በመ/ቁ.
107513 ግንቦት 2 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በፍርድ ሐተታው እንደተገለፀው የግራ ቀኙ ገንዘብ ነክ ክርክር የአደራ ገንዘብ የሚመለከት ሳይሆን የአሁን ተጠሪ የመኪና ግዥ ዋጋ እንደ አመልካች እንደ ሥር ተከሳሽ ሆኖ ለመክፈል ብር 280,000.00 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) ተቀብሎል ወይስ አልተቀበለም የሚለውን አከራካሪ ነጥብ የሚመለከት በመሆኑና ይህንንም በሰው ማስረጃ ለማስረዲት ህግ ስለማይከለክል እንዱሁም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ጉዲዩን ለማስረዲት የቀረበውን የወንጀል ጥፊተኝነት ውሳኔ በማስረጃነቱ ተይዞ በተሟላ የክርክር አካሄድ ግራ ቀኙን በማሰማት በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ዲኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መዝገቡን ወደ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይመለስ ብለናል።
ይህ የሰበር ክርክር ስለተገኘው ወጪና ኪሣራ ሁለቱም ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ፤
No topics extracted.