No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 24 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የአቶ አሰፊ አባዱዮ ባለቤት እና ወራሾች - አልቀረቡም ወራሾች፡- 1. ወ/ሮ ፅጌ ሽኔ 2. አቶ ዋሚ አሰፊ 3. አቶ እስጢፊኖስ አሰፊ 4. ወ/ሮ ሚሚ አሰፊ አልቀረቡም 5. ወ/ሮ ፊሲካ አሰፊ 6. አቶ ሱራፋል አሰፊ 7. ወ/ሮ ጫልቱ አሰፊ ተጠሪ፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ አቶ ጌታቸው ምንተስኖት መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው ከአዋጅ ውጭ የተወሰደ ንብረት ነው በሚል ንብረት ያስመለሰ ወገን፤
የንብረቱ አመላለስ አግባብነት የላለው ሆኖ መገኘቱ ከተረጋገጠና ንብረቱ ወደ ባለቤቱ ወደ መንግስት እንዱመለስ ከተደረገ ንብረቱ ያለአግባብ በዕጁ በቆየበት ጊዜ ንብረቱ ያስገኝ የነበረውን ገቢ ወይም የታጣ ገቢ ጭምር የመክፈል ግዳታ አለበት ወይስ የለበትም? የሚለውን ነጥብ ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ ተመልክቶ ተገቢውን ትርጉም ለመስጠት በሚል ነው።
የአሁን አመልካቾች መጋዘን ከአዋጅ ውጭ ተወርሶብናል በማለት በ1992 ዓ.ም አቤቱታ በማቅረባቸው ይህንኑ ንብረት ሰኔ 29 ቀን 1997 ዓ.ም ተረክበዋል። ነገር ግን ይህ ንብረት ያለአግባብ ወደ አሁን አመልካቾች እጅ ሉገባ የቻለ መሆኑ ተጣርቶ እንደገና ወደ መንግስት እንዱመለስ ተደርጓል።
የአሁን ተጠሪ ይህንኑ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ይህ መጋዘን ተገቢ ባልሆነ መንገድ በማስወሰናቸው የተነሳ ንብረቱ ሉያስገኝ ይችል የነበረውን ጥቅም በማስላት በጠቅላላው ብር 687,742.00 /ስድስት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ሁለት/ ብር ይክፈለ በማለት በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ክስ መስርቷል።
የአሁን አመልካቾችም በተከሳሽነት ንብረቱን ስልጣን ባለው አካል አስወስነን የተረከብነው በመሆኑ የታጣ ጥቅም የመክፈል ኃላፉነት የለብንም፤ይመለስ በመባለ ለታጣ ጉዲት ኃላፉ ልንሆን አይገባም፤ ለጉዲዩ አግባብነት ባለው አዋጅ አዋጅ ቁጥር 572/2000 መሰረት እንደ ከሳሽ አቀራረብ ከሆነ የታጣ ጥቅም ለመጠየቅ መብት አይሰጠውም በማለት ተከራክረዋል።
ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የአሁን አመልካቾች አውራሽ ባቀረቡት ጥያቄ መነሻ ንብረቱ ተመልሶላቸዋል፣ በ1997 ዓ.ም ተረክበዋል። በተጭበረበረ ማስረጃ መሰረት የተወሰደ ቤቶች በድጋሚ ወደ መንግስት እንዱመለሱ ለማድረግ በወጣው ህግ አዋጅ ቁጥር 572/2000 መሰረት ጉዲዩ ታይቶ ይኸው ንብረት እንደገና ወደ መንግስት እንዱመለስ ተደርጓል። በወንጀል ጉዲይ ተከሰን አልተቀጣንም ቢለም ቦርደ ለታጣ ጥቅም ሉጠየቁ የሚችለ መሆኑን ገልፆ ወስኗል። በወንጀል ጉዲይም አለመጠየቅ የፍ/ብሓር ኃላፉነትን አያስቀርም የሚለውን ትንተና መሰረት አድርጎ ንብረቱን ያለአግባብ እንዱመለስ በማድረጋቸው ሳቢያ መንግስት ያጣውን ጥቅም የመተካት፤ የመካስ ኃላፉነት አለባቸው በማለት ከወሰነ በኋላ የታጣውን ጥቅም በሚመለከት ብር 92,786 መሆኑን ለይቶ ወስኗል።
አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው የይግባኝ አቤቱታ በማቅረባቸው ይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አፅድቆታል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበውም በዚህ አኳኋን የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለትና ምክንያቱን በመጥቀስ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ሲሆን፤ በወንጀለ ጉዲይ ተከሰው ጥፊተኛ መሆናቸው ሳይረጋገጥ ለታጣ ጥቅም ኃላፉ መባላቸው አግባብ ነው አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ለመለየት ሲባል ተጠሪ ቀርቦ በዚህ ነጥብ ላይ ክርክሩን በፅሐፍ አቅርቧል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ ሁለቱም ወገኖች ያቀረቡት የፅሁፍ ክርክር በይዘቱ በሥር ፍ/ቤት ካቀረቡት የተለየ ሆኖ አልተገኘም።
የጉዲዩ አመጣጥና ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ጉዲይ ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን፤ ይህንኑ ክርክር ከስር ፍ/ቤቶች ዲኝነትና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ንብረት ከአዋጅ ውጭ እንደተወረሰ በማስመሰል ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ጉዲዩ ታይቶ ንብረቱ ወደ አመልካቾች መመለሱንና በኋላ ግን በዚህ አኳኋን ያለአግባብ የተመለሱ የመንግስት ንብረቶችን እንደገና ለማስመለስ ሲባል በወጣው አዋጅ ቁጥር 572/2000 መሰረት የአመልካቾች ጉዲይ እንደገና ተመርምሮ ንብረቱን ወደ መንግስት እጅ እንዱመልሱ መደረጉን በስር ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ረገድ በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
አከራካሪ ሆኖ የተገኘውና በሰበር ችልት ጉዲዩ ቀርቦ እንዱተረጎም የተደረገበት ዋናው ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 572/2000 አንቀጽ 6 እንደተመለከተው ያለአግባብ ንብረት ያስመለሱ ሰዎች ላይ የወንጀል ክስ ሉመሰረትባቸው እንደሚችል እና ጥፊተኛ ሆኖ ሲገኙም ከወንጀለ ቅጣት በተጨማሪ መንግስት ያገኝ የነበረውን ጥቅም በማጣቱ የጉዲት ካሳ እንዱከፍል ይደረጋል በሚል መደንገጉ ለጉዲት ካሣ ጥያቄ በወንጀለ ጉዲይ ጥፊተኛ ሆኖ መገኘትና መቀጣት ቅድመ ሁኔታ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
ይህንኑ አከራካሪ ነጥብ ለይቶ ለመወሰን በቅድሚያ ለጉዲይ በተለይ አግባብነት ባለው አዋጅ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች እርስ በእርሳቸው በማቆራኘት፤ ዐውደ ንባቡን መሰረት በማድረግ ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
አለአግባብ የተመለሱ የመንግስት ንብረቶችን ለማስመለስ የሚቻለው ቀደም ሲል ንብረቱ በቂ ባልሆኑ ወይም ሐሰተኛ በሆኑ ማስረጃዎች ለአመልካቾች እንዱመለሱ ተደርጎ የተገኘ እንደሆነ ስለመሆኑ በአዋጁ መግቢያ ሁለተኛ አንቀጽ እና ንብረቶችን ለማስመለስ ኃላፉነት የወሰደውን አካል አዲዱስ ሥልጣንና ተግባር በሚዘረዝረው አንቀጽ 4 ንዐስ ቁጥር 6 ተመልክቷል።
ስለሆነም የማስመለሻ ምክንያቶች አንድም በቂ ባልሆነ ምክንያት ወይም ደግሞ በሐሰተኛ ማስረጃ የተነሳ ተረክበውት የተገኙ እስከሆነ ድረስ ያለአግባብ ንብረት ያስመለሱ ሰዎች ሁለ የወንጀል ክስ ይቀርብባቸዋል ማለት አይቻልም።
ይሁን እንጂ የመንግስት ንብረት ወደ ግለሰቦች እጅ ሉገባ የቻለው በቂ ባልሆነ ምክንያትም ሆነ ወይም በሐሰተኛ ማስረጃ መሰረት ያለአግባብ እንዱመለስ የተደረገ የንግድ ድርጅት የተዘጋ ወይም ሉነጣጠል በማይችል ሁኔታ ከላላ ንብረት ጋር የተቀላቀለ ከሆነ በርክክቡ ወቅት የነበረውን ንብረት ግምት ከእነ ወለደ ለመንግስት እንዱከፈል ይደረጋል በሚል፤ የሚከፈለውም ወለድ የሚታሰበው ድርጅቱ ያለአግባብ ከተመለሰበት ቀን ጀምሮና በባንክ የማበደሪያ ወለድ ተመን መሰረት ይሆናል በማለት በአንቀጽ 5(2)(ለ) እና 5(3) ከተደነገገው መረዲት የሚቻለው በወንጀል ሉያስጠይቅ በማይችል በቂ ባልሆነ ምክንያት ንብረቱ የተመለሰ መሆኑ ቢታወቅም እንኳ ንብረቱን ከመመለስ ጋር ወለድ ሉከፈል የሚገባ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ወለድ ደግሞ የታጣ ጥቅም ወይም የጉዲት ካሣ ለማስከፈል ሲባል እንደማካካሻ በህጉ የተቀመጠ አንደ መንገድ ስለመሆኑ ስለ ውልና ከውል ውጪ ስለሚደርስ ኃላፉነት በህግ ተመልክቷል። ከዚህ አንፃር በአዋጁ አንቀጽ 6 በወንጀለ ጥፊተኛ ሆነው ከተጣለባቸው ቅጣት በተጨማሪ መንግስት ያገኝ የነበረውን ጥቅም በማጣቱ የጉዲት ካሳ እንዱከፍል ይደረጋል በሚል የተደነገገው በፍ/ብሓሩ ጉዲይ የታጣ ጥቅምን ለመጠየቅ በወንጀለ ጉዲይ አስቀድሞ ጥፊተኛ ሆኖ መገኘትና መቀጣት ቋሚ ማሟያ መስፈርት ነው ከሚል መደምደሚያ ሉያደርስ አይችልም።
ይልቁንም በዚሁ አንቀጽ 6 በወንጀለ ጉዲይ ጥፊተኛ ሆኖ ከመገኘትና ከመቀጣት ባሻገር የጉዲት ካሣ እንዱከፍለ የሚደረጉት ንብረቱን ተረክበው በእጃቸው አድርገው የተገለገለበት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ በንብረቱ ሳይገለገለ፤ ነገር ግን ንብረቱ ያለአግባብ እንዱመለስ በማስደረጉ ረገድ ተባባሪ ሆኖ የተገኘን ማናቸውም ሰው ሁለ የሚያካትት በመሆኑ በድንጋጌው ስር በወንጀለ ጉዲይ ጥፊተኛ ሆኖ መገኘትና የቅጣት መጣል ያለአግባብ በሐሰተኛ ማስረጃ ንብረት የማስመለስ ተግባር ሉያስከትል የሚችለውን የጎላ ኃላፉነት ለማመልከት እንጂ ምንጊዜም እና በማናቸውም ምክንያት የጉዲት ካሳ ክስ ለማቅረብ በወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ መገኘትና ቅጣት እንደ ቅድመ ሁኔታ ሉወሰድ የሚገባ መሆኑን ሉያሳይ የሚችል ነው ከሚል መደምደሚያ ሉያደርስ የሚችል ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ ሁለ ምክንያት በአዋጁ አንቀጽ 6 የወንጀል ኃላፉነትን በሚመለከት የተጠቀሰው አንድን ንብረት አንድ ሰው ያለአግባብ ወስድ በተገኘ ጊዜ ንብረቱ በእጁ በነበረበት ጊዜ ያለአግባብ በበለፀገበት መጠን ከመካስ ጋር ንብረቱን የመመለስ ግዳታ አለበት በሚል በአጠቃላይ በፍ/ብሓር ህጉ የተመለከተውን ኃላፉነት የተካ ልዩ የሆነ አዋጅ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም አመልካቾች በአዋጅ ቁጥር 572/2000 አንቀጽ 6 የተመለከተውን የወንጀል ኃላፉነት ለፍትሐብሓሩ ኃላፉነት ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ አድርገው በመተርጎም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የህግ መሰረት ያለው አይደለም። በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብሉክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 80(3) (ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 25/80 አንቀጽ 10 መሰረት ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አንድን የመጨረሻ ፍርድ ሉያርም የሚችለው በፍርደ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ከተገኘ ብቻ መሆኑን መሰረት በማድረግ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 60439 የካቲት 15 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት አፅንተናል።
አመልካች በሰበር ደረጃ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ያለው አይደለም ብለናል።
በዚህ የሰበር ክርክር ሳቢያ ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሳራ በየግላቸው ይቻለ።
No topics extracted.