No summary available.
መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካች፡- የወ/ሮ ጣይቱ ከበደ ወራሾች
ጉዲዩ የባለሀብትነት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካቾች ከሳሽነት ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ የወላጅ እናታችን የወ/ሮ ጣይቱ ከበደ በአራዲ ክ/ከተማ ቀበላ 03/09 ክልል ውስጥ የቤት ቁጥር 615 የሆነ ከወላጅ አያቴ ከአቶ ወንድተገኝ በላይነህ በውርስ የተላለፈላትን የተፈቀደ ቤት ከሳሾች የእናታችን የወ/ሮ ጣይቱ ከበደ ወራሾች መሆናችንን በፍርድ ቤት አረጋግጠናል፤ ቀደም ሲል የከሳሾች ወላጅ እናት በፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ቤቱን እንዱለቁ የተወሰነባቸው ሲሆን ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ቅሬታ አቅርበው በመዝ.ቁ.11399 በቀን 04-6-96 ዓ.ም. በዋለው ችልት የስር ከሳሽ ደብተር ወይም ካርታ አውጥተው ቤቱን ለማስለቀቅ ይችላለ በማለት ውሳኔ ሰጥቶበታል። አውራሻችን ወ/ሮ ጣይቱ ከበደ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ በካርታ ቁ. አ03/09/0673 መስከረም 12 ቀን 1998 ዓ/ም የተሰጣቸው ሲሆን የቤትና ቦታ ግብር ከፍለዋል። ነገር ግን የከሳሾች አውራሽ በቤቱ ላይ ግብር እየከፈለች መሆኑን እያወቁ 3ኛ ተከሳሽ በህገ-ወጥ አሰራር ቤቱን በማከራየት የሚጠቀም ሲሆን 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የቤቱ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ከተሰጠበት መስከረም 12 ቀን 1998 ዓ/ም ጀምሮ ቤቱን እንዱለቁ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ቤቱን እንዱያስረክቡ እንደዚሁም የቤቱን ኪራይ እንዱከፍለ የሚል ነው። ተከሳሾች በቀረበው ክስ ላይ መልስ እንዱሰጡበት ታዞ መልስ የሰጡ ሲሆን 3ኛ ተከሳሽ የሰጠው መልስ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የከተማ ቦታ እና ትርፍ ቤትን የመንግስት ባደረገው አዋጅ ቁ. 47/67 የተወረሰ ቤት በመሆኑ ከሳሾች በዚህ ቤት ላይ መብት የላቸውም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ከሳሾች ለክሳቸው መሰረት ያደረጉት በዚህ ቤት ላይ በ1998 ዓ.ም. የተሰጣቸውን የባለሀብትነት ማረጋገጫ ሲሆን ቀድሞ በዚሁ መልክ ተሰጥቶ የነበረው ካርታ መጋቢት 16 ቀን 2002 ዓ.ም.
የተሰረዘ በመሆኑ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ የቀረበውን ቅሬታ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.337 መሰረት ሰርዞታል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩም ያስቀርባል በመባለ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር በጽሁፍ ሰምቷል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል አከራካሪ በሆነው ቤት ላይ የቀረበው የአመልካች የባለሃብትነት ጥያቄ ተሰጥቶ የነበረው የባለሃብትነት ማረጋገጫ ተሰርዟል በማለት ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል በመሆኑ ከዚሁ ቀደም ሲል ተይዞ ከነበረው ጭብጥ አኳያ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የበታች ፍ/ቤቶች አመልካቾች ያቀረቡትን ክስ ውድቅ ያደረጉት በአንድ በኩል የባለሀብትነት ማረጋገጫ ካርታ በሚመለከተው የአስተዲደር ባለስልጣን የተሰጠው ሰው የንብረቱ ባለሀብት ተብል የሚገመት ስለመሆኑ እና በዚሁም መሰረት የአመልካቾች አውራሽ በ1998 ዓ/ም ካርታ በስማቸው በዚሁ አከራካሪ ቤት ላይ የተሰጣቸው በመሆኑ የዚሁ ቤት ባለሃብት ተደርገው የሚወሰደ ስለመሆኑ በማመላከት በልላ በኩል ደግሞ በ1998 ዓ/ም ተስጥቶ የነበረው ይሄው ካርታ የሚመለከተው መስተዲደር አካል ግራ ቀኙ በክርክር ላይ ባለበት ወቅት መጋቢት 16 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰረዘ በመሆኑ ባለሃብትነታቸውን የሚያረጋግጠው ካርታ በመሰረዙ ምክንያት መብት የላቸውም በማለት ውሳኔ የሰጠ ስለመሆኑ ከውሳኔው ይዘት መገንዘብ ይቻላል። በዚህ ነጥብ ላይ የተነሳውን ክርክር ስንመለከት በእርግጥ አንድ የሚመለከተው የአስተዲደር ክፍል የሚሰጠው የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሄንን የምስክር ወረቀት ለያዘ ሰው ባለሃብት ስለመሆኑ ግምት የሚያሰጠው ስለመሆኑ ከፍትሐብሕር ህግ ቁ. 1195/1/ ይዘት መገንዘብ ይቻላል። በልላ በኩል አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ የተሰጠው አግባብነት በላለው መልኩ በሆነ ጊዜ ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ ማስተባበል የሚቻል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ህግ ቁ. 1196 ስር የተደነገገ በመሆኑ እና ስራውን በአግባቡ ያልተወጣ የሚመለከተው የአስተዲደር ክፍል ኃላፉነት ሉያስከትልበት የሚችል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ህግ ቁ. 1198 ስር ተመልከቷል። ከእነዚህ ሁለ አጠቃላይ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው አንድ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የተሰጠ የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለሃብትነትን በተመለከተ የህግ ግምት የሚያሰጥ ቢሆንም በልላ ተቃራኒ ማስረጃ ሉስተባበል የሚችል፣ በተቃራኒው ከሚቀርቡት ማስረጃዎች ጋር ሉመዘን የሚችል እንጅ ማስተባበያ ላቀርብበት የማይችል ወሳኝ /conclusive evidence/ ያለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተመሳሳይ አንድ የሚመለከተው የአስተዲደር አካል የምስክር ወረቀት ሲሰጥ ተገቢውን ስርዓት እና ደንብ መከተል እንዲለበት ሁለ የተሰጠን የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሲሰረዝ አግባብነት ያላቸውን ስርዓቶችን መከተል ያለበት ስለመሆኑ እና የዚህ አፈፃፀም ሂደትም በአግባቡ ስለመፈጸሙ ወይም አለመፈጸሙ በፍርድ ቤት ላታይ የሚችል ስለመሆኑ ከፍትሐብሕር ህግ ቁ. 1195 እስከ 1198 ድረስ ካለት ድንጋጌዎች ዓላማ፣ ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም ግራ ቀኙ በክርክር ላይ ባለበት ወቅት ለአመልካቾች አውራሽ ተሰጥቶ የነበረው የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በሚመለከተው የአስተዲደር አካል ተሰርዟል በመባለ ብቻ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ውድቅ መደረጉ ተቀባይነት ያለው አካሄድ ሆኖ አልተገኘም። የበታች ፍ/ቤቶች ማድረግ ያለባቸው የቀረበው ክስ የባለሃብትነት ክርክር እስከሆነ ድረስ በግራ ቀኙ የሚቀርቡትን ማስረጃዎች በመመዘን እና የካርታውን መምከን በተመለከተም የእርምጃው አግባብነት ባጠቃላይ ከቀረቡት ማስረጃዎች ጋር ተመዝኖ የሚታይ ሆኖ እያለ በንብረቱ ላይ ተሰጥቶ የነበረው ካርታ በመምከኑ ብቻ ክሱን ውድቅ ማድረግ ከላይ የተመለከቱትን የፍትሐብሕር ህግ ድንጋጌዎች ዓላማ እና ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
No topics extracted.
በልላ በኩል አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት አከራካሪው ቤት የአውራሻቸው አያት የአቶ ወንድተገኝ በላይነህ የምርጫ ቤት እንጂ በመንግስት የተወረሰ ቤት አይደለም በማለት ሲሆን 3ኛ ተጠሪ በበኩለ ቤቱ የተወረሰ ቤት ነው በማለት ተከራክሯል። በዚህ ነጥብ ላይም የበታች ፍ/ቤቶች አከራካሪው ቤት የተወረሰ ስለመሆኑ ወይም የተወረሰ ስላለመሆኑ ጭብጥ በመያዝ ያጣሩት ነጥብ የላለ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። የሚያከራከረው ቤት የተወረሰ ስለመሆን ወይም አለመሆን ክርክር በተነሳ ጊዜ ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ የሚቀርቡትን ማስረጃ በመመልከት የተወረሰ ነው ወይም ያልተወረሰ ቤት ነው በማለት ውሳኔ ሉሰጡበት የሚችለ ስለመሆኑ ከዚህ በፉት ይሄ ሰበር ሰሚ ችልት በመዝ.ቁ.24627 ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ ፍ/ቤቶች በተመሳሳይ በዚህም ጉዲይ መወሰን የሚችለ ስለመሆኑ ግልፅ ነው።
በአጠቃላይ የበታች ፍ/ቤቶች ከላይ እንደተመለከተው ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ጭብጦች በመያዝ እና በግራ ቀኙ ማስረጃ ሳያጣሩ ውሳኔ መስጠታቸው በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.246 እስከ 248 ድረስ ያለትን የጭብጥ አመሰራረት እና ክስ ማጣራትን በተመለከተ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ነው ብለናል።
በአጠቃላይ የበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ የደረሱት ተገቢውን ጭብጥ በመያዝ እና በማጣራት ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.95545 በቀን 17-5-2003 ዓ.ም. በዋለው ችልት እና የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.76167 በቀን 11-8-2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348 (1) መሰረት ተሸሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ መካከል አከራካሪውን ቤት በተመለከተ በፍርድ ሐተታው በተመለከተው መሰረት ተገቢውን ጭብጥ በመያዝ እና በግራ ቀኙ ማስረጃ በማጣራት ውሳኔ እንዱሰጥበት በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
3.በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።