No summary available.
መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- ወ/ሮ በላይነሽ ቢያድግልኝ ቀረበች።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ አስቴር ገበሬ አልቀረበችም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በኮንድሚኒየም ቤት ላይ የተደረገው የሽያጭ ውል እንዱፈርስ በመጠየቅ በቀረበው ክስ መነሻነት የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረችው አመልካች ስትሆን፣ ከተጠሪ ጋር ያደረገችው የቤት ሽያጭ ውል የኮንደሚኒየም ቤት ለተወሰኑ ዓመታት በሽያጭ እንዲይተላለፍ የሚከለክለውን ሕግ በመቃረን የተደረገ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት እንዱፈርስላት ዲኝነት ጠይቃለች። ተጠሪ በበኩልዋ ለክሱ በሰጠችው መልስ ውለ የሚፈርስበት የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ ምክንያት እንደላለ በመግለጽ ተከራክራለች። ከዚህ ላላ ፍ/ቤቱ የሁለቱን ወገኖች ክርክር በመመርመር ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ወስኗል። ጉዲይ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች በ22-11-2003 ዓ.ም. በፃፈችው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የምትልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታ አቅርባለች።
በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የቤቱ ሽያጭ ውለ አይፈርስም የተባለው በሕጉ አግባብ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ይህን ጭብጥ ግራ ቀኝ ወገኖች ካሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርመረናል።
አመልካች ውለ መፍረስ አለበት ለሚለው ክርክር መሰረት ያደረገችው ዋነኛው ነጥብ የሕግ ክልከላ ነው። በእርግጥ ውለ የተደረገው በስህተት እና በድንገተኛ ተንኮል ነው የሚል መከራከሪያም እንዲለት ከመዝገቡ ተመልከተናል። ሕጉ በኮንድሚኒየም (በጋራ ህንፃ) ላይ ቤት በእጣ የደረሰው ሰው እጣው ከደረሰው ቀን ጀምሮ እስከ አምስት ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ ቤቱን መሸጥ አይችልም የሚል እንደሆነ በመግለጽ ስለመከራከርዋም ተገንዝበናል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ያልተቀበለው መሸጥ የሚከለክል በሕግ ደረጃ የወጣ አዋጅ የለም፤ የሚከለክል ደንብ ወይም መመሪያ አለ ቢባል እንኳን ከሣሽ (አመልካች) ቤቱን ለተከሣሽ (ተጠሪ) በሽያጭ ለማስተላለፍ ስምምነትም በሰጠችበት ወቅት የዚህ ግንዛቤ እንደነበራት ግልጽ ነው የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት እንደሆነ ውሣኔው ያመለክታል።
አመልካች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የምትለው በዚህ መልክ የተሰጠውን ውሣኔ ሲሆን፣ ተጠሪ በበኩልዋ ለሰበር አቤቱታው በሰጠችው መልስ አመልካች የጠቀሰቻቸው አዋጅም ሆነ ደንብ ቤቱን እንዲይሸጥ በግልጽ አይከለክለም። አመልካች ቤቱን የሸጠችልኝ ወዲና ፈቅዲ በመሆኑ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክራለች።
ከቀረበልን ክርክር ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው በኮንድሚኒየም (የጋራ ቤት ህንፃ) የተያዘ ቤት እንዲይሸጥ ለተወሰኑ ዓመታት ክልከላ ያደርጋል ተብል የተጠቀሰው “የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራያዊ ሪፕብሉክ የጋራ ህንፃ ቤት ባለቤትነት አዋጅ ቁጥር 370/1995” ነው። ይህ አዋጅ በእርግጥ በጋራ ህንፃ ቤት በእጣ የደረሰው ቤቱ ለላላ ሰው ስለሚሸጥበት ሁኔታ በሚመለከት በግለጽ ያስቀመጠው ድንጋጌ የለም። በልላ በኩል ግን የከተማው አስተዲደሮች አዋጁን ለማስፈጸም የሚረዲ ደንብ ለማውጣት እንደሚችለ በአንቀጽ 42 ግልጽ የሆነ ድንጋጌ ማስቀመጡን ለመገንዘብ ችለናል። በ1952 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1281 እስከ ቁጥር 1360 ያለት ድንጋጌዎች በአዋጅ መሰረት በሚስተዲደር የጋራ ህንፃ ላይ ተፈፀሚ እንደማይሆኑ እንደዚሁም ማንኛውም ሕግ፣ ልማድ ወይም አሰራር በአዋጅ የተደነገጉ ጉዲዮች ላይ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው በአንቀጽ 43 ስለመደንገጉም ተመልክተናል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የሚገኝበት የጋራ ህንፃ (ኮንድሚኒየም) በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ከሚተዲደሩት አንደ ነው። ከላይ የተጠቀሰው አዋጅ ቁ. 370/95 ተፈጽሚ የሚሆነው በአዱስ አበባ እና በድሮው ከተማ አስተዲደሮች ላይ እንደሆነ በአዋጅ አንቀጽ 3 የተደነገገ ሲሆን፣ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ምክር ቤትም በአዋጁ በተሰጠው አዋጁን ለማሰፈጽም የሚረዲ ደንብ የማውጣት ስልጣን መሰረት አዋጅ ቁ. 19/97 አውጥቷል። በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14(2) እንደተመለከተውም በኮንድሚኒየም ቤት ያገኘ (በእጣ የተሰጠው) ሰው የቤቱን ጠቅላላ ዋጋ ከፍል ቢያጠናቅቅ እንኳ ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ የሚችለው ቤቱን ከገዛ (በእጣ ካገኘ) በኃላ አምስት ዓመት ሲሞላው ብቻ ነው። ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን የተለመደ አሰራር ወይም ሕግ በአዋጁ በተሸፈኑ ጉዲዩች ላይ ተፈፀሚነት እንደላለውም በአንቀጽ 21 ተመልክቷል።
እንደሚታየው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ምክር ቤት በወጣው አዋጅ የተቀመጠው የያዘነውን ክርክር የሚመለከተው ድንጋጌ ማለት ነው በኮንድሚኒየም ቤት ያገኘ ሰው ቤቱን ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለማስተላለፍ የሚችልበት አግባብ በሕግ ገደብ ተጥልበታል። በእርግጥ ገደቡ በጊዜ (በዓመታት) የተወሰነ በመሆኑ ጊዜአዊ ቢሆንም፤ ጊዜው ከመድረሱ በፉት የሚደረገው ሽያጭ ግን ሕግን የጣሰ መሆኑ ግልጽ ነው። ስለውለ አመሰራረት በተመለከተ የተደነገገው የፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1678 አንድ ውል የሚፀና ውል ነው ልባል የሚችለው በቂ ሲሆን እርግጠኛነት ባለው በሚቻልና ሕጋዊ በሆነ ጉዲይ ላይ መደረግ እንዲለበት ያመለክታል። በዚህ መዝገብ ለተያዘው አከራካሪ ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው ሃይለ ቃል ውለ ሕጋዊ በሆነ ጉዲይ ላይ መደረግ እንዲለበት የሚገልጽ ነው። ውለ የተደረገበት ጉዲይ ወይም ምክንያት ከሕግ ውጪ የሆነ ነው በተባለ ጊዜም ውለ ይፍርስ ዘንድ ለመጠየቅ እንደሚቻል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1808(2) ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ የሆነውም ይኸው ነው።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን የውል ይውረስልኝ ክርክር ውድቅ ለማድረግ የሰጠው ምክንያት ከዚህ አንፃር ሲታይ ሕጉን በአግባቡ ያለገናዘብ እንደሆነ ነው መገንዘብ የሚቻለው። በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል በሕጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከማብቃቱ በፉት የተደረገ ስለመሆኑ ባለከራከረበት ሁኔታ አይፈርስም ተብል ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ የለም። ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ (የኮንድሚኒየም ቤት) ውል በሕግ ክልከላ የተደረገበት ስለሆነ ፈራሽ ነው ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጭና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.