No summary available.
መጋቢት 1ዐ ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አመልካች፡- ጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ6 አስተዲደር ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ ሶስና ተስፊዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ከፈለ ታረቀኝ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን መሰረት ያደረገን የባለሃብትነት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በአዱስ አበባ ከተማ ጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ6 ክልለ ወስጥ የሚገኝ ቁጥሩ ዐ31 የሆነ ቤት በውርስ ከአባታቸው ያገኙትና የተላለፈላቸው መሆኑንና የአሁኑ ተጠሪ ይገባኛል በማለት የያዘባቸው መሆኑን ገልፀው ቤቱ የግል ቤታቸው መሆኑ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካችም ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስ ቤቱ የተጠሪ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ የላለ መሆኑ ተጠሪ ከስ ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ጠቅሶ ሲያቀርብ በፍሬ ነገር ደረጃ ክርክር ደግሞ አከራካሪው ቤት በአዋጅ የተወረሰና ለተጠሪ የባለቤትነት ደብተር የተሰጣቸው ከአሰራርና ከደንብ ውጪ በመሆኑ ደብተሩ ስልጣን ባለው አካል መመዘኑንና በተሰረዘ ደብተር ደግሞ ተጠሪ ሉያገኙ የሚችለት መብት የላለ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራከሯል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አመልካች በፍርድ ኃይል መብቱን ከአጣ በኋላ የአከራካሪው ቤት የተጠሪን ባለሃብትነት የሚያሳይ ማስረጃ በአስተዲደር አካለ መክኗል በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የላለው መሆኑን ገልጾ ቤቱን አመልካች ለተጠሪ ለቆ ሉያስረክብ ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በሕግ አግባብ ተወርሶ በአመልካች የሚተዲደር ከመሆኑም በላይ ተጠሪ የቤቱ ባለመብት የሚያደርጋቸው ማስረጃ በላለበትና የነበረውም በተሰረዘበት ሁኔታ አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ያስረክብ ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ወረቀት የተሰረዘ መሆኑ እየታወቀ አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ያስረክብ የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባለ ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ተጠሪ በፅሐፍ በሰጡት መልስ አከራካሪው ቤት በውርስ ተላልፍላቸው በሕግ አግባብ የባለቤትነት ደብተር የተሰጣቸው ከመሆኑም በላይ አመልካች በፍርድ ሃይል መብቱን ያጣ መሆኑ ተረጋግጦ በተሰጠው ውሣኔ ደብተሩ ተሰርዟል በሚል ምክንያት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት የሚችልበት አግባብ የለም በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ እንዱፀናላቸው ገልፀው ተከራክረዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅ በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን በፅሐፍ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ክሱን የመሰረቱት አመልካች ቤታቸውን ያላግባብ የያዘባቸው መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን አመልካች ደግሞ ቤቱን በሕግ አግባብ የያዘው መሆኑን ጠቅሶ የተከራከረ መሆኑን ፣ የስር ፍርድ ቤትም አከራካሪው ቤት ባለቤትነት የማን ነው? የሚለውን ጭብጥ ከያዘ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አከራካሪውን ቤት ተጠሪ በውርስ ከአባታቸው ያገኙት መሆኑን ፣ ይህን የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃም ያቀረቡ መሆኑን ፣ ተጠሪ ከላላ ግለሰብ ጋር ባደረጉት ክርክርም ቤቱ የተጠሪ መሆኑን ተረጋግጦ ከመወሰኑም በላይ አመልካች ውሣኔው መብቴን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት አቤቱታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው የቀረ በመሆኑን ፣ ይህ ከሆነ በኋላ አመልካች ተጠሪ በቤቱ ላይ አለኝ የሚለትንና ሚያዚያ ዐ1 ቀን 1994 ዓ.ም. ተሰጠኝ በማለት ያቀረቡት የካርታ ቁጥር 9/05531 መሰረዝ በሕግ አግባብ የተጠሪን ባለሃብትነት ቀሪ የሚያደርግ አይደለም በማለት ውሣኔ መስጠቱን ነው። አመልካች ቤቱ በሕግ አግባብ የተወረሰ ስለመሆኑ ገልፆ በዚህ ረገድም ማስረጃ ያለው መሆኑን ጠቅሶ መከራከሩንም ከውሣኔው ይዘት ተገንዝበናል።
No topics extracted.
እንግዱህ ክርክሩ በይዘቱ አመልካች ቤቱን ያላግባብ ይዟል የሚለውን የተጠሪን ክስ መሰረት ያደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀድመው ከላላ ግለሰብ ጋር በአደረጉት ክርክር አመልካችም ቀርቦ ክርክር ተደርጎበት ክርክሩ ተቀባይነት አጥቶ ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ነኝ በማለት የአፈጻጸም ክስ ያላቀረቡ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን የስር ፍርድ ቤቱም አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት አቤቱታውን አቅርቦ ተቀባይነት አጥቷል በማለት በፍርድ ሐተታው ላይ ያሰፈረው አገላለፅ የአመልካችና የተጠሪ ማስረጃዎች ተሰምተው ክርክሩ ተደርጎ ፍርደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 360 መሰረት የማይለወጥ ነው ተብል የፀና መሆኑን የሚያሳይ አለመሆኑን የማያስገነዝበን ሁኖ አግኝተናል። ተጠሪ ራሳቸው ክስ ሲመሰርቱ በአመልካች ላይ በአዱስ መልክ ቀጥታ ክስ ማቅረባቸውም በአመልካች ላይ ቀድሞ ያረፈ ፍርድ መኖር ያለመኖር ላይ ጥያቄን የሚያስነሳ መሆኑ ግልፅ ነው። እንዱህ ከሆነ የስር ፍርድ ቤት አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት አቤቱታ አቅርቦ ተቀባይነት ማጣቱን ሳይሆን ይኸው አቤቱታ ተቀባይነት ያጣበት ስርዓት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት የሚቀርበው አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 359 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የተስተናገደ መሆን ያለመሆኑን፣ ተጠሪ ከላላ ግለሰብ ጋር አደረጉ የተባለው ክርክርና የተሰጠው ውሣኔ አመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ሲያቀርብ የተለወጠ መሆን ያለመሆኑን የሚገልፅ መሆኑን ያለመሆኑ ግልጽ ላሆን ይገባ ነበር ። ይኸው ግልጽ አለመሆኑ በእርግጥም አመልካችም በሕግ አግባብ በተካሄደው ክርክር ተሸናፉ ከሆነ በሁዋላ በስራው ባገኘው ሥልጣን በመጠቀም ካርታውን ማምከኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ተይዞ እንዲይታይ የሚያደረግ ሁኖ ነው። ቀድሞ የተወሰነ ውሣኔ ካለም ተጠሪ በአዱስ መልክ ክስ የአቀረበቡት ምክንያትም ሉጣራ የሚገባው እና ሥነ ሥርዓታዊ መሆኑ ምላሽ የሚያስፈልገው ነበር። ተጠሪ በአመልካች ላይ ያስፈረደት ፍርድ የላለ መሆኑን አምነው አዱስ ክስ ከአቀረቡ ደግሞ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው የቤቱ ባለቤት ማን ነው የሚለው ነጥብ ሁኖ የግራ ቀኙ ማስረጃዎች መሰማትና ተገቢ ሆኖ ከተገኘም ፍርድ ቤቱ በራሱ መነሻነት ፍሬ ነገሩን በማጣራት ትክክለኛውን ፍርድ መስጠት ነው። በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የአስተዲደር አካለ የሚሰጠው የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በስሙ ማረጋገጫው የተሰጠው ሰው የምስክር ወረቀቱ ለተጠቀሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት ስለመሆኑ ሕጉ ግምት የሚወስድበት ጉዲይ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195/1/ ድንጋጌ ከሰፈረው ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነጥብ ነው። ይህ ድንጋጌ ሕጋዊ ግምቱ ሉስተባበል የሚችል መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ጋር ተዲምሮ ሲነበብ ያስገነዝባል። በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ድንጋጌ በአስተዲደር አካለ የሚሰጥ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ደምዲሚ ማስረጃ (conclusive evidence) ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ስር የተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች አለ የሚል ወገን በማናቸውም ማስረጃ ሉያስተባብለው የሚችለው ማስረጃ መሆኑን ያሳያል። በልላ በኩል የአስተዲደር አካለ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 መሰረት የሰጠውን የባለሃብትነት ማረጋገጫ ደብተርን በልላ ጊዜ ከሰረዘው ይኸው ተግባሩ በፍርድ ቤት ሉስተናገድ የሚችል አይደለም ልባል የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40/1/2/ እና 37 ድንጋጌዎች አንፃር ተዲምሮ ሲታይ የሚያስገነዝበን ነው። አስተዲደር አካል ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖረው አንዳ የሰጠውን የባለቤትነት ደብተር ከሰረዘ ይኸው አካሄድ ሕጋዊ አይደለም የሚለው ሰው በፍርድ ቤት መብቱን ለማስከበር ክስ ሉያቀርብ የሚገባና ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን በማስረጃ አጣርቶ እና የንብረት ባለቤትነት መብትን ከሚጠብቁ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ ተገቢውን ውሣኔ የሚሰጥበት ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በአዱስ መልክ በቀረበው በተጠሪ ክስ ላይ ተጠሪ አለኝ የሚለትን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር መሰረዙን ገልፆ የተከራከረ ሲሆን ክሱ በአዱስ መልክ የቀረበ እንደመሆኑ መጠን አመልካች ተጠሪ አለኝ የሚለትን ካርታ የሰረዘው በሕጉ አግባብ በተዘረጋው ስርአትና አሰራር ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ በግራ ቀኙ ማስረጃ እና ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ባለው መንገድ ሁለ ተጣርቶ ጉዲዩ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ፣ 1196 እና ከላልች አግባብነት ካላቸው የንብረት መብት ሕጎች ጋር ተዛምድ ታይቶ ሉወሰን የሚገባው ሁኖ እያለ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ አዱስ ክስ ያቀረቡ መሆኑን ወደ ጎን በመተው ወይም ቀድሞ ተጠሪ ከላላ ግለሰብ ጋር ሲያደርጉ በነበሩት ክርክር በአመልካች ላይ የተሰጠው ውሣኔ አመልካች የቤቱ ባለሃብት አይደለም የሚል መሆን ያለመሆኑን በግልጽ ሳያረጋገጥ አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ያስረክብ ተብል መወሰኑ የክርክሩ አካሄድ በተሟላ ሁኔታ ተከናውኖና ተጣርቶ ያለመሆኑን የሚያሳይ ነው። አንድ ክርክር በተሟላ የሥነ ሥርዓት አካሄድ ካልተመራ ደግሞ በውጤቱ የተከራካሪ ወገኖችን መሰረታዊ መብት የመጎዲት አጋጣሚ የሰፊ እንዱሆን የሚያደረግ መሆኑ የሚታመን ስለሆነ ተቀባይነት የላለውና መሰረታዊ የሆነ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ነው። በአጠቃላይ ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉሻር የሚገባውና በፍሬ ነገር ደረጃ በተገቢው መንገድ ያልተጣሩ ነጥቦች ተጣርተው ጉዲዩ እንደገና በስር ፍርድ ቤት ታይቶ እንዱወሰን ማድረጉ ተገቢ ሁኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ ዐ1 ቀን 2002 ዓ.ም.
በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ይጻፍ።