No summary available.
የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማዉ ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዋት ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፍዚያ ቃዱ - የቀረበ የለም መዝገቡ የተቀጠረው፤- ለምርመራ ሲሆን፣ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የፍ/ቤት ውሳኔ በተከራካሪ ወገኖች ከቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ክልል ወሰን ሉያልፍ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ለይቶ ተገቢውን ዲኝነት በመስጠት በሚል የቀረበ ነው። የጉዲዩም መነሻ የአሁን አመልካች በሥር የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በግዥ ባገኘሁት የንግድ ድርጅት ላይ የአሁን ተጠሪ ሁከት የፈጠሩብኝ ስለሆነ የተፈጠረው ሁከት ይወገድልኝ በማለት ክስ መሥርቷል።
ተጠሪም ባመለከተው ክርክር የተነሳበት ንብረት ሉገመት ስለሚቻል ተገምቶ ተገቢው የዲኝነት ገንዘብ ተከፍልበት ላቀርብ ሲገባ ይህንኑ ሥርዓት አሟልቶ የቀረበ አይደለም። በተጠሪ በኩል የቀረበው ውል የብድር እንጂ የሽያጭ አይደለም። መፃፍ ስለማልችል በተንኮል የተዘጋጀ ካልሆነ በቀር በእኔ የተደረገ አይደለም ስለሆነም ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱ ጉዲዩን ተመልክቶ በህግ ፉት በማይፀና ውል ንብረቱ በእጅ ገብቷል ማለት ስለማይቻል እና በህግ ማሟለት የሚገባውን ሂደት ባላሟላ ውል ደግሞ በሁከት ክስ ማስፈጸም አይቻልም።
ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ሥ./ሥ/ሕ/ቁ 33(2) መሰረት ውድቅ ነው የሚል ዲኝነት ሰጥቶበታል።
በዚህም የወረዲው ፍ/ቤት ውሳኔ ይግባኝ ተጠይቆበት በበላይ ፍ/ቤቶች የሰበር ሰሚ ችልቱን ጨምሮ በየደረጃው ተቀባይነትን አላገኘም።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ዲኝነት ላይ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚልበትን ዝርዝር ነጥቦች አመልካች በመጥቀስ የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ የተነሳ ሲሆን፤ ተጠሪም ከላይ በመግቢያው ላይ በተጠቀሰው ነጥብ ላይ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጎ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክራቸውን አጠናቀዋል። የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በከሳሽነት የተሰየመ ወገን አንድ ንብረት በአንድ ህጋዊ ተግባር ሳቢያ ወደ እጄ ገብቷል በይዞታ ላይ እያለ ሁከት ተፈጠረብኝ የሚል ክስ ትክክለኛውን የሁከት የህግ ፅንሰ ሀሳብ ተከትል ማቅረቡ ከተረጋገጠ፤ ለዚሁ ክስ በተከሳሽነት የተሰየመው ወገን ከተሰማ በኋላ በፍ/ቤቱ ላሰጥ የሚገባው ዲኝነት ሁከት ተፈጥሯል ይወገድ፤ ወይም የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት የሚወሰን እንጂ በከሳሹ እጅ ሉገባ የቻለበትን ህጋዊ ተግባር ለመመርመር የሚያበቃ ወይም የሚያስችል ምክንያት አይኖርም። ከሳሹ የክሱን ምክንያት ዘርዝሮ ሉያገኝ የሚገባውን ዲኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 224 ሲጠይቅ፤ ውሳኔው ይህንኑ የጠየቀውን ዲኝነት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለይቶ ማዘዝ ስለሚገባ የወረዲው ፍ/ቤት ሁከት የተፈጠረ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም ካለ የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት መወሰን ሲገባው ከዚህ አልፍ በልላ የክርክር መስመር ታይቶና ተጣርቶ ሉወሰን የሚገባውን ጉዲይ ሁለ አካቶ ያለ ቦታው የሽያጭ ውለ ዋጋ ያለው ነው? ወይስ አይደለም? በሚለው ላይ ዲኝነት መስጠቱ ከተጠየቀው ዲኝነት ክልል የወጣ በመሆኑ ሥነ-ሥርዓታዊ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል የአሁን አመልካችም በክስ ማመልከቻው ዘርዝሮ ያቀረበው እና የጠየቀው ዲኝነት ተዲምሮ ሲታይ በሽያጭ ውል ምክንያት በእጁ የገባው የንግድ ድርጅት በተጠሪ ተወስድበት ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 226 (3) እንደተመለከተው የተወሰደን እና ተለይቶ የታወቀን ንብረት ለማስመለስ የተፈለገ እንደሆነ የዚህኑ ንብረት ዋጋ ተገምቶ የሥረ-ነገር ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ተገቢውን በመክፈል ክሱን አቅርቦ በዚሁ የክስ መስመር ተገቢውን ክርክርና ንጥጥር ተደርጎ ተገቢውን ዲኝነት ማግኘት ሲገባ በሥር የወረዲው ፍ/ቤት ክስ የቀረበበት መንገድ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149 እንደተመለከተው በሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ሉስተናገድ የሚገባው ጉዲይ በንብረት ላይ የተፈጠረን ሁከት ለማስቆም (cessation of intereference) ወይም ከሁከት መፍጠር ተግባሩ እንዱታገድ (injuction) ለመጠየቅ እንጂ የተወሰደን ንብረት እንደገና ወደ እጁ ለማስገባት የሚያስችል አይደለም።
ከእነዚህ ሁለት ሐተታዎች አንጻር የስር ፍ/ቤቶች በየደረጃው በጉዲዩ ላይ የሰጡት ዲኝነት ህጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ ባለማግኘታችን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
No topics extracted.
በዚህ ጉዲይ የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ በ26/4/03፤ ይግባኝ ሰሚው የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ16/5/2003 ዓ.ም. እና የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ11/08/2003 ዓ.ም የሰጡት ዲኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የአሁን ተጠሪ ክርክር ያስነሳውን ንብረት በሽያጭ ውል ካገኝ በኋላ በተከሳሽ ድርጊት ከእጁ ወጥቶ ከተገኘ ወይም በተከሳሽ ቁጥጥር ሥር ይገኛል ካለ የህንኑ የሽያጭ ውል ያለውን መነሻ አድርጎ ንብረቱን መልሶ ወደ እጁ ለማስገባት እንደ ሥርዓቱ ዲኝነት የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው ብለናል። ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤት ይተላለፍ።
በዚህ የሰበር ችልት ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክር ሳቢያ ለወጣው ማናቸውም ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።