No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዶ/ር ገነት ሥዩም - ጠበቃ ተስፊዬ ተገኘወርቅ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 17/18 አስተዲደር ፅ/ቤት - ነገረ ፈጅ አሸናፉ ሥዩም ቀረቡ
ወ/ሮ አመለወርቅ ሙላቴ ጠበቃ ላውጋለት ፀጋ ቀረቡ።
አቶ ባህረ ወ/ጊዮርጊስ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከሕግ ውጪ የተያዘብኝ ቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።
የአመልካች የክስ ይዘትም አመልካች የደርግ መንግስት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በነበራቸው የፕለቲካ አመለካከት ሀገር ውስጥ ለመኖር ባለመቻላቸው ተሰደው ውጭ ሀገር መቆየታቸውን፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 17/18 ክልል ውስጥ የሚገኘውና በካርታ የሚታወቀውን በ1985 ዓ/ም በቁጥር 15/31238 የሆነ የከተማ ቤት የባለቤትነት ደብተር ከከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የተሰጣቸው መሆኑን፣ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት የቤት ቁጥሮች 268፣ 269 እና 270 በሚል መለያ ሰጥቶ ለ2ኛ፣ 3ኛ እና ለአቶ ዘሚካኤል ኃይላ አከራይቶ ጥቅም እያገኘበት መሆኑን፣ ቤቱን 1ኛ ተጠሪ እንዱያስረክባቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥተውም ፈቃደኛ ሁኖ ያለመገኘቱን ገልፀው ቤቱን ለሕጋዊ ባለቤት እንዱያስረክብ፣ ተከራዮችም ቤቱን እንዱለቁ እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስም አከራካሪው ቤት በህግ በመንግስት መወረሱንና በፍርድ ቤት ስልጣን ስር የማይወድቅ መሆኑንና አመልካች ክስ ለማቅረብ የማይችለ መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ ቤቱ በሕግ የተወረሰ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ላልች ተጠሪዎችም ቤቱን ለረዥም አመታት ተከራይተው የሚጠቀሙበትና በ1ኛ ተጠሪ የሚተዲደር መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በ1ኛ ተጠሪ በኩል የቀረቡትን መቃወሚዎችን ውድቅ አድርጎ ፍሬ ጉዲዩን መርምሮ የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት አመልካች መሆናቸው ተረጋግጧል በማለት ቤቱን ተጠሪዎች ለአመልካች ሉያስረክቡ ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪዎች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩና 1ኛ ተጠሪ ተጨማሪ ማስረጃ እንዱያቀርብ ከተደረገ በሁዋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች አለኝ የሚለት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር መምከኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ወስኗል። ከዚህም በሁዋላ አመልካች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተስርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 345(1ለ)) ድንጋጌን ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በ1985 ዓ/ም ለአመልካች የተሰጠው የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ በክርክር ላይ እያለ ደብተሩ መክኗል ተብል አመልካች ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ መብት የላቸውም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የነበረው የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ሕጉን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ውሳኔው ሉጸና ይገባል ሲለ በፅሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል፣ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኗ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰረቱ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት ንብረታቸው መሆኑን መጥቀሳቸውንና ይህንኑ መብታቸውን ያሳያል ያለትንና በ1985 ዓ/ም በከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ተሰጠኝ ያለትን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ለማስረጃነት ማቅረባቸውን፣ የአሁኑ ተጠሪዎች ባቀረቡት መከላከያ መልስ አመልካች በቤቱ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም፣ አከራካሪው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/1967 መሰረት ተወርሶ 1ኛው አመልካች ለረዥም አመታት የሚስተዲድረው መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት መከራከራቸውን፣ ይህንኑ የተጠሪዎችን ክርክር የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገው በአመልካች በኩል የቀረበውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተርና ቤቱ ምትክ ያልተገኘበት ወይም ካሳ ያልተከፈለበት ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቀርቧል በሚል ምክንያት መሆኑን፣ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ የይግባኝ ክርክር ሲደረግ ደግሞ 1ኛ ተጠሪ አመልካች አለኝ የሚለትን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር የተሰረዘ መሆኑንና ማስረጃው ሳይቀርብ የቀረበትን ምክንያት ገልፆ ማስረጃው እንዱቀርብ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ የባለቤትነት ደብተሩ መምከኑን የሚያሳየውን የ1ኛ ተጠሪ ማስረጃ ተቀብል ጉዲዩን በመመርመር የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ የሻረው መሆኑን ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ ከሣሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሰረት አዘጋጅቶ ከሚያቀርበው የክስ ማመልከቻ ጋር በክሱ መሰማት ወቅት ለጉዲዩ ማስረጃ ይሆኑኛል የሚሎቸውን የሰውም ሆነ የጽሁፍ ማስረጃዎችን ዝርዝርና ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጮቻቸውን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 ድንጋጌ ያሣያል። የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 234 ድንጋጌ ሲታይም በተከሳሹ ላይ ተመሳሳዩን ግዳታ ይጥላል። በተለይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 137/3/ የሰነድ ማስረጃዎችን በተመለከተ ማንኛውም ተከራካሪ ወገን ከአቤቱታው ጋር በማያያዝ ወይም ከቀነ ቀጠሮ በፉት ወይም በመጀመሪያው ቀን ቀጠሮ ካልቀረበ በቀር ማስረጃው ላቀርብ ወይም ይቅረብልኝ ተብል ሉጠየቅ እንደማይችል ተመልክቷል። ይሄው ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኘው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 256 ስር በተመለከተው አኳኋን ማስረጃዎቹ ሣያቀርቡት የቀሩት ከባድና በቂ በሆነ ምክንያት መሆኑን ፍ/ቤቱ ሲረዲ ብቻ ነው።
የማስረጃ አቀራረብን በተመለከተ በሥነ ሥርዓት ህጉ የተመለከተው ላላው ደንብ የይግባኝ ሰሚውን ፍ/ቤት ሥልጣን የሚመለከት ነው። በዚህም መሰረት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 345 ድንጋጌ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በራሱ አስተያየት ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው ማናቸውም ዓይነት ሰነድ ወይም ምስክር ወይም ላላ ዓይነት ማስረጃ በተጨማሪነት እንዱቀርብለት የማዘዝ ህጋዊ ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ ያሣያል። የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 145/1/ ድንጋጌም በልላ ፍ/ቤት የሚገኝ ሰነድ የፁሁፍ ማስረጃ ወይም ፍርድ የተሰጠበት መዝገብ ለውሣኔው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍ/ቤቱ በራሡ አነሣሽነትም ሆነ በተከራካሪዎቹ ጠያቂነት እንዱቀርብለት ማዘዝ የሚችል ስለመሆኑ ያስረዲል።
ከላይ እንደተገለፀው ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በቤቱ ላይ መብት ወይም ጥቅም የላቸውም በማለት ውሣኔ የሰጠው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 345((1(ለ)) ድንጋጌ መሰረት የ1ኛ ተጠሪን የተጨማሪ ማስረጃ ጥያቄን ተቀብል ነው። ፍርድ ቤቱ የማስረጃው መቅረብ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ተገቢ መሆኑን ማረጋገጡን የውሳኔው ይዘት ያሳያል። ይሁን እንጂ የአመልካችን የባለቤትነትን መብት ሰርዟል የተባለው ማስረጃ ግን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ በኋላ የተሰረዘበት አግባብ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑን አመልካች ክርክር እንዱያቀርቡ እድል የተሰጠ ስለመሆኑ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በግልጽ አያሳይም።
በአስተዲደር አካለ የሚሰጥ የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ይህንኑ የምስክር ወረቀት በስሙ የተፃፈለት ሰው የንብረቱ ባለቤት ስለመሆኑ ሕጉ ግምት የሚወስድበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል። ይህ ድንጋጌ ሕጉ የሚወሰደው ግምት ስለመኖሩ፣ ይኸው ግምት ግን አሳሪ ያለመሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ጋር ተዲምሮ ሲነበብ ያስረዲል። በልላ አገላለፅ በአስተዲደር አካለ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ነው ተብል የምስክር ወረቀት መስጠት ማስረጃውን ድምዲሚ ወይም አሳሪ (Conclusive Evidence) የሚያደርገው አይደለም። ይልቁንም ይኸው ማስረጃ የተሰጠበት አግባብ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት ስለመሆኑ ማስረዲት ከተቻለ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ስር የተመለከተው ሕጋዊ ግምት ሉስተባበል የሚችል (rebuttable legal presumption) መሆኑን ከድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በልላ በኩል የአስተዲደር አካለ የሰጠውን የባለቤትነት የምስክር ወረቀት በልላ ጊዜ መሰረዙ ከታወቀ ማስረጃው የተሰረዘበት አግባብ ከሕግ ውጪ መሆን ያለመሆኑ ተጣርቶ ውሳኔ የሚሰጥበት እንጂ ይኸው አካል ካርታውን አምክኗል ስለተባለ ብቻ ማስረጃው ክርክር ሳይደረግበት ተቀባይነት የሚያግኝበት የሕግ አግባብ የለም። የአስተዲደር አካለ የሰጠውን የባለቤትነት ምስክር ወረቀት በልላ ጊዜ ሲሰርዝ ማስረጃው የተሰረዘበት ሰው የአስተዲደር አካለን እርምጃ ክርክር ሉያቀርብበት አይገባም፣ በፍርድ ቤትም ሉጣራ የሚገባው አይደለም ከተባለ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት በአንቀፅ 40(1 እና 2) የተረጋገጠውን የንብረት መብት ዋስትና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው ነው። አንድ ሰው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1206 መሰረት በንብረቱ ላይ የሚያቀርበው የመፊለም ክስ ተገቢው መጣራት ተደርጎና የመከራከር መብቱ በአግባቡ ሳይጠበቅለት ውድቅ የሚሆንበት አግባብም የለም። ፍርድ ቤት እውነትን ለማውጣት ከፍተኛ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጋቸውን ስለ ማስረጃ አቀራረብና አቀባበል የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። እነዚህ ድንጋጌዎች ዲኝነት ላሰጥ የሚገባው የክርክሩ አካሄድ በተሟላ አኳኋን ሲመራ መሆኑንም ያስገነዝባለ። የክርክሩ አካሄድ ሳይሟላ የሚሰጥ ዲኝነት ሕጋዊ አይሆንም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ በአመልካች የተያዘው የባለቤትነት ማስረጃ ወረቀት በየካቲት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. የመከነን መሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተጨማሪ ማስረጃነት እንዱቀርብ መደረጉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 345(1(ለ)) ድንጋጌን የጣሰ ነው ልባል የሚችልበት አግባብ የላለ ቢሆንም የአመልካችን የባለቤትነት ማስረጃ አመከነ የተባለው ማስረጃ የመከነበት አግባብ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑ፣ የቤቱ ትክክለኛ ባለቤት ማን እንደሆነ ግን ተገቢው ማጣራት ሳይደረግ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ቤቱ የአመልካች አይደለም ተብል መወሰኑ ፍርድ ቤቶቹ የክርክሩን አመራር ከላይ በተመለከቱት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ የማስረጃ አቀራረብ ደንቦች አለመምራታቸውንና ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1195፣ 1196 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ጉዲዩን ያለመመልከታቸው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ ውሣኔ የሰጡት የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓት ድንጋጌዎች በማይደግፈትና የፍርድ አካሄደ ባልተሟላበት ሁኔታ በመሆኑ በየእርከኑ ባለ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ እና ትዕዛዝ ሙለ በሙለ ሉሻሩ የሚገባና የስር ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ሁለንም መከራከሪያ ነጥቦችንና የአመልካችን የባለቤትነት መብት አምክኗል የተባለው ማስረጃ የመከነበትን ሕጋዊ አግባብ እንዱሁም በአጠቃላይ የአከራካሪው ቤት ሕጋዊ ባለቤት ማን ነው? የሚለውን ጭብጥ በመያዝና ተገቢውን ማጣራት ሁለ በማድረግ ጉዲዩን እንደገና በመመልከት ውሳኔ እንዱሰጡበት ማድረጉ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ ጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ፣ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ መጋቢት 22 ቀን 2002 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ እንዱሁም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ ጥር 29 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ሙለ በሙለ ተሽረዋል።
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ ክርክሩን ቀጥል አመልካች አለኝ የሚለትን የባለቤትነት ደብተር 1ኛ ተጠሪ የካቲት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ያመከነበት አግባብ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑን፣ የቤቱ ሕጋዊ ባለቤት ማን እንደሆነ ግራ ቀኙ አለን የሚሎቸውን ማስረጃዎችን በመስማትና ተገቢነት አላቸው የሚሎቸውን ማስረጃዎችን ሁለ በማስቀረብ ጉዲዩን እንደገና ተመልክቶ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።