No summary available.
የካቲት 27ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማዉ ወላ ዓሉ መሐመድ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቅድሚያ ግዥ መብት ጥያቄ የሚስተናገድበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪ በጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍ/ቤት በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም የአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ አመልካች ስድስት ክፍል ቤቶች የካርታ ቁጥሩ 968/አንቀፅ/ 96 የሆነውን በነቀምቴ ከተማ በዲርጌ አስተዲደር ክፍል ውስጥ የሚገኘውን በዚህ ሰበር ችልት ከተራ ቁጥር ሶስት እስከ ተራ ቁጥር ስድስት ለተጠቀሱት በብር 360,000.00 (ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ) ሽጠው ስም በማዛዋወር ላይ እንዲለ ሰምተው ከነቀምት ከተማ አስተዲደር ላይ አጣርተው ይህን ቤት ለመግዛት ቀዲሚ መብት እንዲለቸው ማመልከታቸውን፣ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች ተጠሪ የንግድ ድርጅታቸውን ከመግዛታቸው በፉት የአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ንብረት የነበረ ሆኖ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በእዲ ይዞ ይኸው አካል በሕግ አግባብ የሸጠላቸው መሆኑን፣ በዚህ አግባብ በገዙት ንብረትም የባለቤትነት ማስረጃ የካርታ ቁጥር 352/አንቀጽ/2000 በሆነው ተሰጥቷቸው ከተራ ቁጥር ሶስት እስከ ተራ ቁጥር ስድስት የተጠቀሱት አመልካቾች ከገዙት ቤት ጋር በግድግዲ፣ በጣሪያውና በአንድ ምሰሶ ተያይዞ የተሰራ መሆኑን፣ ይህን ቤት አሳልፍ ለሶስተኛ ወገን መሸጥ ማለት አንድን ቤት ለሁለት ከፍለው መሸጥ መሆኑንና ይህም የተጠሪን መብት የሚጎዲ መሆኑን ዘርዝረው ገዥዎች የገዙትን ዋጋ ተጠሪ ከፍለው በቀዲሚነት የመግዛት መብታቸው እንዱጠበቅላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መከላከያ መልስም በተጠሪና በሻጮች መካከል በቤቶቹ ላይ የጋራ መብት ስለመቋቋሙ የሚያሳይ ውል የላለ መሆኑን፣ የቤቱ ጣሪያና ግድግዲ አንድ ስለመሆኑ የቀረበ ማስረጃ የላለ መሆኑን፣ የግዥና የሽያጭ ውለም ተመዝግቦ የባለቤትነት ማስረጃ ሉሰራ ቁጥር ስለመስጠታቸውና ተጠሪ የቅድሚ ግዥ ጥያቄ ለማቅረብ መብት የላላቸው መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማና ጉዲዩን ተገቢ ነው ባለው መንገድ ከአጣራ በኋላ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1281 መሰረት በቤቱ ላይ የጋራ መብት ማቋቋማቸው መረጋገጡን፣ እንዱህ ከሆነ ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1261፣ 1386 እና 1388 ድንጋጌዎች መሰረት ተጠሪ በግዥ የተላለፈውን ቤት በቀዲሚነት የመግዛት መብት እንዲላቸው የሚያሳይ መሆኑን ገልፆ ተጠሪ የቤቱን ዋጋ ከፍለው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት ይግዙ ሲል ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም የኸው ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ሰርዞታል። ከዚህም በኋላ አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ በድምጽ ብልጫ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ በቤቱ ላይ የቀዲሚነት መብት አላቸው ተብል በበታች ፍ/ቤቶች የተወሰነው በቤቱ ላይ ግራ ቀኙ ያቋቋሙትን መብት አይነት፣ መብቱ የተቋቋመበትን መንገድና ጊዜ እንዱሁም የጋራ መብት ያላቸው ሰዎች የቀዲሚነት መብት የሚኖራቸው ምን ምን ሕጋዊ ሁኔታዎች ሲሟለ ነው የሚለውን ሕጋዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ምልከታ ያላደረገና በክርክሩ ሂደት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ውጪ የተሰጠ ስለመሆኑ ዘርዝረው ውሳኔው እንዱሻርላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ቤቶች ለመግዛት የቅድሚያ መብት አለው የተባለው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በፅሁፍ በሰጡት መልስ የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ ስለጋራ ባለሀብቶች የተደነገጉትን የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ያገናዘበ በመሆኑ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ውሳኔው እንዱፀናላቸው የተከራከሩ ሲሆን አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በክርክሩ ሂደት ክስ ሉመሰርቱ የቻለት የአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ስድስት ክፍል ቤቶች የካርታ ቁጥሩ 968/አንቀጽ/ 96 የሆነውን በነቀምቴ ከተማ በዲርጌ አስተዲደር ክፍል ውስጥ የሚገኘውን በዚህ ሰበር ችልት ከተራ ቁጥር ሶስት እስከ ተራ ቁጥር ስድስት ለተጠቀሱት በብር 360,000.00 (ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ) ሽጠው ስም ለማዘዋወር ላይ እንዲለ ሰምተው ከነቀምት ከተማ አስተዲደር ላይ አጣርተው ይህንን ቤት ለመግዛት ቀዲሚ መብት እንዲለቸው በማመናቸው መሆኑን፣ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች ተጠሪ የንግድ ድርጅታቸውን ከመግዛታቸው በፉት የአሁኑ 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ንብረት የነበረ ሆኖ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በእዲ ይዞ የኸው አካል በሕግ አግባብ ለተጠሪ የሸጠላቸው መሆኑን፣ በዚህ አግባብ በገዙት ንብረትም የባለቤትነት ማስረጃ የካርታ ቁጥር 352/አንቀጽ/2000 በሆነው የተሰጣቸው መሆኑን፣ ይኸው ቤት ከተራ ቁጥር ሶስት እስከ ተራ ቁጥር ስድስት የተጠቀሱት አመልካቾች ከገዙትና ለክርክሩ ምክንያት ከሆኑት ቤቶች ጋር በአንድ በኩል በግድግዲ በአንድ በኩል ደግሞ ብልኬት የተሰሩ ስለሆኑ የወረዲው ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የምስራቅ ወለጋ ዞን ስራና ከተማ ልማትና ጽ/ቤት በባለሙያ አረጋግጦ ማስረጃ የሰጠ መሆኑን ነው።
1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ለላልች አመልካቾች ሸጡ የተባለት ቤትና ተጠሪ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገዙ የተባለበት ቤት የተያያዙበት ግድግዲና ጣሪያ የጋራ ባለሀብትነት መብት በሕግ አግባብ የተቋቋመ ነው። በህጉ መሰረት የተፈጠረ የጋራ ባለሀብትነት ደግሞ የሚገዛው አግባብነት ባለው ህግ ነው። ከፍ/ህ/ቁ 1259-1277 ያለት ድንጋጌዎች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው። የፍ/ህ/ቁ 1260/1/ ድንጋጌ የሚገልጸው ደግሞ እያንዲንደ የጋራ ባለሀብት ድርሻውን ለመሸጥ ወይም በላልች መንገድች የማስተላለፍ ወይም ለማስያዝ መብት ያለው መሆኑን ነው። በመሆኑም እነዚህ ስልጣኖች ላልች የጋራ ባለሀብቶች እየተቃወሙ ቢሆን እንኳን ባለድርሻው የጋራ ባለሀብት የሚተገብራቸው፣ በህግ የተጠበቁ ናቸው።
በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1281(1) ድንጋጌ ስር እንደተመለከተው ያንድ ቤት ልዩ ልዩ ፍቆች ወይም ለመኖሪያ የተመደቡ ክፍልች (አፒርታማ) የልዩ ልዩ ባለሀብቶች ንብረት በሆኑ ጊዜ ተቃራኒ የሆነ ሰነድ ከላለ ከእነዚህ ሀብቶች አንደ ክፍል ለአንደኛው ባለንብረት የግል አገልግልት የሚጠቅም እንዱሆን ከተደረገው በቀር የመሬቱና የላላውም የቤቱ ክፍልች የጋራ ንብረት እንደሆኑ የሚቆጠሩ ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1289(1) ድንጋጌ ስር ደግሞ እያንዲንደ የጋራ ባለንብረት የአንድነት ሀብት ባልሆነው ክፍል ንብረቱ ላይ ህግ ለባለሀብቱ የሚሰጣቸው መብቶች እንደሚኖሩት ተመልክቷል። በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1289(2) ድንጋጌ በተለይ ሲታይ ደግሞ የግለ የሆነውን ለመኖሪያ የተመደቡትን ክፍልች (አፒርታማ) ወይም ፍቅ ለመሸጥ፣ ለማስተላለፍ፣ ለማከራየት ወይም በዋስትና ለማስያዝ ባለሀብት መብት እንዲለው ተደንግጓል። በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1290 ደግሞ የአንድነት ያልሆኑት ክፍልች ላይ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1289 ስር የተመለከቱት መብቶች ያለት ባለሀብት የተጣለበት ገደብ መኖሩ ተመልክቷል። ይህም ምንጊዜም የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የተመደበበትን አግልግልት አክብሮ መጠበቅ፣ እንዱሁም የተከፈለ ድርሻ የሆነው ንብረት እንዱያገለግል የተመደበበት ጉዲይም ሆነ የመጠቀሚያውን አይነተኛ ነገር ላልቹን ባለሀብቶች በሚጎዲ ሁኔታ ለመለወጥ ያለመቻል በሕጉ የተጣለበት ገደብ ነው። እነዚህ ድንጋጌዎች በግልጽ የሚያሳዩት አንድን የማይንቀሳቀስ ንብረት በጋራ ባለመብት የሚያደርጋቸው የንብረቱ ክፍል ካለ በዚሁ የጋራ ባለንብረት በሚያደርጋቸው የንብረቱ ክፍል ባለሀብቶቹ የሚኖራቸው መብት ለአንድ ባለሀብት ህጉ የሰጣቸው መብቶች ስለመሆናቸው ነው። በዚህ ረገድ የተደነገጉትን የንብረት ህግ ድንጋጌዎችን ስንመለከት ባለቤትነት ከሁለ የሰፊ መብት መሆኑን ያስገነዝባለ። በህግ የተቀመጡትን ገደቦችንና ወሰኖችን (Restriction and Limitation) ሳያልፍ የአንድ ንብረት ባለቤት በንብረት እንደፈለገው የመጠቀምና የመገልገል መብቱና ነፃነቱ በህግ የተከበረለት ስለመሆኑም ድንጋጌዎቹ ያሳያለ። ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከልም ንብረቱን በህጉ አግባብ ማስተላለፍ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1184 እና 1185 ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባል። በአጠቃላይ የባለቤትነት መብት ከሁለ የሰፊ መብት ሲሆን በህጉ ከተጣለት ገደቦች ውጪ የሚነካ ወይም ለላላ ተላልፍ እንዱሰጥ የሚደረግ መብት አይደለም። ስለሆነም ሕጉ የጋራ ባለሀብት በህጉ ጥበቃ ላደረግለት የሚገባቸው መብቶች ምን እንደሆኑ ለይቶ አስቀምጧል።
በዚህም መሰረት የፍ/ህ/ቁ. 1261፣ 1388 እና 1406 ድንጋጌዎች ይዘት ሲታይ የጋራ ባለሀብቶች ያልተከፈለውን የጋራ ንብረት ከማንኛውም 3ኛ ወገን በፉት፣ ሉሸጥ የታሰበውን ድርሻ አስገድድ ለመግዛት የቅድሚያ መብት ያላቸው መሆኑን ያስረዲል። እነዚህ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1281፣ 1289 እና 1290 ድንጋጌዎች ተግባራዊ የሚደረጉበትን አግባብ የሚገድቡ አይደለም።
ይልቁንም በበንብረቱ ላይ ባለሀብቶች ያላቸው ድርሻ በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1281፣ 1289 እና 1290 ድንጋጌዎች መሰረት የሚገዛ መሆኑ ከተረጋገጥው ውጪ የጋራ የሆነው ሀብት ሉሸጥ ሲታሰብ የጋራ ባለሀብቶች ከማንኛውም 3ኛ ወገን በፉት ሉሸጥ የታሰበውን ድርሻ አስገድድ ለመግዛት የቅድሚያ መብት ያላቸው መሆኑን የሚያስገነዝቡ ናቸው። በመሆኑም አንድ ቤት በአንድ በኩል ግድግዲውና ጣሪያው የተያያዘ መሆኑ በላልች ክፍልች ባለሀብቱ ያለውን መብት በፈለገው የገበያ ዋጋና ግዥ ወይም ለመለወጥ ሳይችል በአንድ በኩል የግድግዲው ባለሀብት ለሆነው ባለሀብት አጠቃል እንዱሸጥ በህግ ገደብ አልተጣለበትም። የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት እንዱገዙት የወሰኑት ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያላቸው የፍ/ብሕ/ቁጥር 1281፣1289 እና 1290 ድንጋጌዎች ይዘት በፍሬ ነገር ደረጃ ቤቱ የተያያዘው በአንድ በኩል በግድግዲና ጣሪያ ስለመሆኑ ከተረጋገጠው ነጥብና ከተጠሪ ዲኝነት ይዘት ጋር በአግባቡ ሳያገናዝቡ እና በተጠሪ ላይ ሉደርስ ይችላል የተባለው ጉዲትም ሳይረጋገጥ ነው። ለአንድ ጉዲይ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ እያለ አግባብነት የላለውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠት ደግሞ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀም ነው። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል
በጉቶ ጊዲ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 24 ቀን 2002 ዓ.ም. ተሰጥቶ በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11851 20710 የካቲት 05 ቀን 2002 ዓ.ም. በትዕዛዝ ፀንቶ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ነሀሴ 12 ቀን 2002 ዓ.ም. በአብላጫ ድምጽ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሸሯል።
በነቀምቴ ከተማ በዲርጌ አስተዲደር ክፍል በካርታ ቁጥር 968/አንቀጽ/ 96 በሆነው በ1ኛ አመልካች ስም ተመዝግቦ ያለው ስድስት ክፍል ቤቶች ለተጠሪ በቅድሚያ የሚሸጡበት የህግ አግባብ የለም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።