No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- አቶ ጥላሁን ጎበዜ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የገጠር የእርሻ መሬት ይዞታ ክርክር ሲሆን የተጀመረው በአማራ ብሓ/ክልላዊ መንግሥት በፍገራ ወረዲ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ባቀረበው ክስ የተጀመረ ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ ተከሣሾች በ1989 ዓ.ም በተደረገው የመሬት ሽግሽግ የተመራሁትን ስለያዙበኝ እንዱለቁልኝ በማለት አዋሣኙን በመጥቀስ እንዱወሰንለት ጠይቋል። ተከሣሾች በቀረበው ክስ ላይ መልስ እንዱሰጡበት ታዘው በሰጡት መልስ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መሬት ከ1989 ዓ.ም. በፉትም የራሳቸው የነበረ ስለመሆኑ፣ በ1989 ዓ.ም. የመሬት ሽግሽግ ሲደረግ ለተከሣሾች የተቆጠረ ስለመሆኑ፣ በ1997 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው የሚጠቀሙበት የራሳቻው ይዞታ በመሆኑ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የክልለ የወረዲ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተከሣሾች በዚህ አከራካሪ በሆነው የእርሻ መሬት ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ስለተሰጣቸው ያለአግባብ የተሰጠ የይዞታ መረጋገጫ ከሆነ ይዞታውን ለሰጠው አካል ከማቅረብ ውጭ በቀረበው ክስ መሬቱ የከሣሽ ነው በማለት ማስለቀቅ አይቻልም በማለት በእንደዚህ ዓይነት መልኩ ክስ መቅረቡ ህጋዊ አይደለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የበታች ፍ/ቤት ውሣኔን በመሻር ተከሣሾች ለክርክር ምክንያት የሆነውን የእርሻ መሬት ለከሣሽ (አመልካች) እንዱያስረክቡ ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪዎች በበኩላቸው በዚህ የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የወረዲውን ፍ/ቤት ውሣኔ በማጽናት ውሣኔ ሰጥቷል። የክልለ የሰበር ሰሚ ችልትም የክልለ የጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በአብላጫ ድምጽ በማጽናት ውሣኔ ሰጥቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራ ቀኙን ክርክር በጽሐፍ ሰምተናል። 2ኛ ተጠሪ ባለመቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፍአል።
ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም የበታች ፍርድ ቤቶች በቀረበው ክስ ላይ ውሣኔ የሰጡት ተገቢውን የማጣራት ሂደት በማድረግ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በአማራ ብሓ/ክልላዊ መንግሥት የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 133/98 አንቀጽ 24(4) እና ይሄንን አዋጅ ለማስፈጸም በወጣው የደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 20(4) የይዞታ ማረጋገጫ የያዘ ሰው የመሬቱ ባለይዞታ እንደሆነ እንደሚገመት ይደነግጋል። ይሄ ማለት ግን በህጉ የተቀመጠው የባለይዞታነት ግምት ሉስተባበል የማይቻል በራሱ ብቻ አሳሪ ማስረጃ ስለመሆኑ የተመለከተ ነገር የለም።
በአንድ የፍትሐብሕር ክርከር በህጉ በተለየ ሁኔታ የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓቱ የተገደበ ካልሆነ በጽሐፍ፣ በምስክር፣ በህሉና ግምት፣ በተከራካሪዎች እምነት፣ ወይም በመሒላ ማስረጃ ማስረዲት እንደሚቻል በፍተሐብሓር ህግ ቁ. 2002፣ 1195፣1196 እና በተለያዩ ህጎች ውስጥ የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓቶችን የሚደነግጉ ድንጋጌዎች አጠቃላይ ዓላማ፣ ይዘትና መንፈስ መረዲት ይቻላል። በዚሁ መሰረት አመልካች ተከሣሾች ይዞታዬን ይዘውብኛል እና እንዱለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ ያቀረበ ሲሆን ተጠሪዎችም የራሳቸውን መከራከሪያና በ1997 ዓ.ም የተሰጣቸውን የይዞታ ማረጋገጫ አቅርበዋል። ይሄ በሚሆንበት ጊዜ ጉዲዩን የተመለከተው ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያላቸውን ማስረጃ በመስማት እና ከላላ የመንግሥት አካላትም መቅረብ ያለበትን ማስረጃ በመቀበልና የቀረቡትን ማስረጃዎች በማመዛዘን ተገቢውን ውሣኔ መስጠት ሲገባው ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ያቀረቡ በመሆኑ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሣኔ መስጠቱ አግባብነት የለውም። የይዞታ ማረጋገጫም ቢሆን እንደአንድ ማስረጃ ተቀባይነት ያለውና ሉመዘን የሚችል እንጂ ወሣኝ (conclusive evidence) ባለመሆኑ ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ በመቀበል እና ላልች አስፈላጊ ናቸው የሚላቸውን ማስረጃዎች በመቀበል ተገቢውን ውሣኔ መስጠት ሲገባ የይዞታ ማረጋገጫ ሉስተባበል እንደማይቻል ማስረጃ በመውሰድ እንደዚሁም መስተባበል ካለበት የይዞታ ማረጋገጫውን ለሰጠው አካል አቤቱታ በማቅረብ ብቻ እንደሆነና ፍርድ ቤቱ በግራቀኙ ማስረጃ ጉዲዩን ተመልክቶ የመወሰን ስልጣን እንደላለው በመውሰድ የቀረበውን ክስ ህጋዊ አይደለም በማለት ውሣኔ መስጠቱ አግባብነት የለውም።
በልላ በኩል ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የደቡብ ጎንደር ከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ያስቀርባል አያስቀርብም በማለት ተገቢውን ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፉት ለተጠሪዎች የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ የተሰጠበትን አግባብ የወረዲው የመሬት አስተዲደር አካል መግለጫ እንዱሰጥበት ማድረጉ ተጠሪዎች የክርክሩ አካል ባልተደረጉበት ጊዜ በመሆኑ አግባብነት ያለው የማስረጃ አሰባሰብ ስርአት ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም ብለናል። ምክንያቱም ማጣራቱ ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ካመነበት ግራቀኙ የክርክሩ አካል በሆኑበትና የእኩልነት መርህን በጠበቀ መልኩ መከታተልና በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያዬት መስጠት በሚችለበት ሁኔታ መደረግ ነበረበት።
ባጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የእርሻ መሬት የማን ይዞታ ነው?
የሚለውን ነጥብ በግራቀኙ ማስረጃ በማጣራት እንደዚሁም ከላላ የመንግስት አካልም ተጨማሪ ማስረጃ መቀበል አስፈላጊ ከሆነም ይሄው ስርአት ተፈፅሞ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ሲገባው መሰረታዊ የማስረጃ አቀባበልና ምዘና ስርአት ባልተከተለ መልኩ የተሰጠው ውሣኔ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
07860 ሚያዝያ 24 ቀን 2003ዓ.ም በዋለው ችልት፣የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ.25228 በቀን 03-7-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት፣ የደቡብ ጎንደር መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 21099 በቀን 11-10-2003 ዓ.ም.
በዋለው ችልት እና የፍገራ ወረዲ ፍ/ቤት መዝ.ቁጥር ባልተጠቀሰ በቀን 15-4-2001 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች ለክርክሩ ምክንያት በሆነው የእርሻ መሬት ላይ የይዞታ ማረጋገጫ በመያዛቸው ብቻ ሉስተባበል አይችልም በማለት የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው አግባብነት ያለው አካሄድ አይደለም ብለናል። በመሆኑም የፍገራ ወረዲ ፍ/ቤት ግራቀኙ አከራካሪ በሆነው የእርሻ መሬት ላይ ያላቸውን ማስረጃ መስማትና ላልች ተገቢ ናቸው የሚለውን ተጨማሪ ማስረጃዎች ከሚመለከተው የመንግስት አካል በማጣራት ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር በግራቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.