No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣሥ 20 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሸለማ ነገሰ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ፊይሣ መንግስቱ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኖኖ ቤንጃ ወረዲ ፍርድ ቤት፣ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዲዩ የእርሻ መሬትን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በኖኖ ቤንጃ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ በኖኖ ቤንጃ ቀበላ ውስጥ በሰሰኮ ጎጥ ጋሴ ቀርጫ ተብል ከሚጠራው ቦታ የተለያዩ አትክልቶች አርባ ግንድ ባህር ዛፍ አራት ግንድ ጌሾ አባቴ ተክል ሲጠቀምበት የኖረውን መሬት ተከሣሽ በሥልጣኑ ይዞታል። የሀገር ሽማግላዎች መሬቱን እኩል ያካፈለን ሲሆን መሬቱ የአባቴ በመሆኑና ለእኔ ሉደርሰኝ ስለሚገባ የእርሻ መሬቱን እንዱለቅልኝ በማለት አመልክቷል።
የአሁን አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ክስ የቀረበበትን መሬት ከአሥራ ሁለት ዓመት በፉት የከሣሽ አባት በህይወት እያለ የነበረውን ባህር ዛፍ ገዝቼ መሬቱን በ1981 ዓ.ም. ተመርቼ ይኸው እየተጠቀምኩበት እገኛለሁ። መሬቱ በአለ ኤልፈታ ቀበላ የሚገኝ ሲሆን አባቱ መሬቱን ለቆ ወደ ደጋ ሲባ ቀበላ ሄዶል። መሬቱ የራሴ ነው በማለት ተከራክሯል። የኖኖ ቤንጃ ወረዲ መሬትና የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት አመልካችም ሆነ ተጠሪ በመሬቱ ላይ ግብር እየከፈለ አይደለም። በፉት መሬቱ የከሣሽ አባት ነበር በማለት ማስረጃ በመስጠቱ የወረዲው ፍርድ ቤት ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ጠቃሚ መሆኑን በመገንዘብ የሰው ምስክሮችን ሰምቷል። የቀረቡት ምስክሮች የከሣሽ የተጠሪ አባት 1985 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከዚህ በኋላ ተከሣሽ አመልካች መሬቱን ይዞ የሚገኝ መሆኑን እና ግራ ቀኙ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን የተጠሪ ምስክሮች የመሰከሩ ሲሆን የአመልካች ምስክሮች አመልካች ተመርቸዋለሁ በማለት መሬቱን እንደያዘ ፣ ከቦታው ድረስ ሄደው እንደሚያውቁ መሥክረዋል።
የወረዲው ፍርድ ቤት የእርሻ መሬቱ የከሣሽ አባት የነበረ ስለሆነ ተከሣሽ መሬቱን ይልቀቅ በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታውን አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር ችልት ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታውን አልተቀበለትም።
አመልካች 1981 ዓ.ም መሬቱ ባድ መሆኑን አመልካች ለእኔ ተሰጥቶኛል። አመልካች በህጋዊ መንገድ በይዞታዬ አድርጌ አሥራ ሁለት ዓመት ከተጠቀምኩበት በኋላ ተጠሪ የአባቴ መሬት ነበር በማለት ክስ አቅርቧል ። ከዚህ በፉት በዚሁ ጉዲይ የተጠሪ ወንድም ክስ አቅርቦብኝ የማህበራዊ ፍርድ ቤት መጋቢት 4 ቀን 1994 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቶበታል። ስለሆነም በፍርድ በተቋጨ ጉዲይ ተጠሪ ያቀረበውን ክስ በመቀበል የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ሀምላ 21 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም. በተፃፈ መልስ አመልካች ያነሣው የይርጋ ክርክር ተገቢነት የለውም። መሬቱንም አስራ ሁለት ዓመት አልያዘም። እኔም አካለመጠን ያልደረስኩ ነበርኩ አመልካች የማህበራዊ ፍርድ ቤት ወስኖልኛል ያለው በሥር ፍርድ ያልተነሳ አዱስ ክርክር ነው። ስለዚህ የሰበር አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ሀምላ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለረዥም ጊዜ መሬቱን በይዞታየ አድርጌ እየተጠቀምኩበት ነው በማለት ያቀረበውን ክርክር በማለፍ መሬቱን ለተጠሪ እንዱለቅ የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል።
የተጠሪ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል መነሻ በማድረግ ተጠሪ አመልካች የሟች የአባቱን ይዞታ መሬት እንዱለቅለት ክስ እስካቀረበበት 2ዐዐ3 ዓ.ም. ድረስ ያለው ጊዜ ሲሰላ አመልካች ለአሥራ ስምንት ዓመት የእርሻ መሬቱን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1140 በሚደነግገው መሰረት በእጁ አድርጎ በእውነት ሲያዝበት የኖረ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ያቀረበው ሟች ወላጅ አባቴ በመሬቱ ላይ የነበረው የይዞታና በመሬቱ የመጠቀም መብት በውርስ ለእኔ ተላልፍልኛል በማለት ነው።
እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የአርሶ አደር አባታቸውን ወይም እናታቸውን የእርሻ መሬት ይዞታና የመጠቀም መብት ያላቸው ወራሾች በውርስ ተላልፍልናል የሚለትን መብት ለማስከበር ክስ ማቅረብ የሚችለት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ነው? በልላ አነጋገር የእርሻ መሬት የይዞታና የመጠቀም መብት ለማስከበር በሚቀርብ ክስ ላይ የይርጋ የጊዜ ገደቡ ምን ይሆናል? የሚለው ነጥብ ነው። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር የእርሻ መሬት ባለይዞታ የመሆንና ከይዞታው ያለመፈናቀል መብት ያለው መሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 4ዐ ንዐሰ አንቀፅ 4 በግልፅ ተደንግጓል። የፋዳራል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 እና የኦሮሚያ ክልል ያወጣው የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቀቀም አዋጅ ቁጥር 13ዐ/99 የመሬት ባለይዞታ የሆነና በመሬቱ የመጠቀም መብት ያለው ሰው ለሁለት ዓመት ያህል መሬቱን በመተው ከአካባቢው ከጠፊ የመሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬት የመጠቀም መብቱ ቀሪ እንደሚሆን ይደግጋለ። ሆኖም የህግ ማዕቀፍቹ የእርሻ መሬት ባለይዞታና የመጠቀም መብቴ በልላ ሰው ተደፍሮብኛል የሚል አርሶ አደር የመሬት ባለይዞታነትና የመጠቀም መብቱን ለማስከበር ክስ ማቅረብ ያለበት በስንት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ የፋዳራለ አዋጅ ቁጥር 456/97 እና የኦሮሚያ ክልል አዋጅ ቁጥር 130/1999 በግልፅ አይደነግጉም።
ከዚህ አንፃር ስንመለከተው በጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለውን የይርጋ ህግ ድንጋጌ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 4ዐ ንዐስ አንቀፅ 4 የተደነገገውን የአርሶ አደሮች የመሬት ባለይዞታነትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ ሁኔታ አግባብነት ያላቸውን የፍታብሓር ህግ ድንጋጌዎች በመተርጎም ውሣኔ መስጠት የሚገባው ጉዲይ ሆኖ አግኝተነዋል። ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያላቸው የፍትሐብሕር ድንጋጌዎች ስንመረምር በመጀመሪያው ድንጋጌ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1149 ንዐስ አንቀፅ 2 የተደነገገው የሁለት ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ ነው። ሆኖም ድንጋጌው በተለያየ መንገድ የይዞታና በመሬት የመጠቀም መብታቸውን በልላ ሰው የተደፈረባቸው አርሶ አደሮች በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን የእርሻ መሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬት የመጠቀም መብት በፍርድ ቤት ተከራክረው በማስከበር ሰፊ ያለ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ በገጠር መሬት ላይ ያለን የባለይዞታነትና በመሬት በመጠቀም በሚቀርብ ክርክር ላይ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1149 ንዐስ አንቀፅ 2 ተመራጭ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል ማንኛውም አርሶ አደር ምክንያታዊ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ በእርሻ መሬት ላይ ያለውን የይዞታና የመጠቀም መብት ለማስከበር ተገቢውን ትጋት የማድረግ ግዳታ ይኖርበታል።
ስለሆነም በላልች የይርጋ የጊዜ ገደብ በግልፅ ባልተደነገገላቸው ጉዲዮች ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ ይህ ሰበር ችልት ለፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1677/1/ እና ለፍትብሓር ህግ ቁጥር 1845 የተደነገገው የአሥር ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ አርሶ አደሮች በህገ መንግስቱ የተከበረላቸውን የመሬት ባለይዞታነትና በመሬት የመጠቀም መብት በፍርድ ከስሰው ለማስከበር ሰፊ ያለ እድል የሚሰጠው የፋዳራል አዋጅ ቁጥር 456/97 እና የኦሮሚያ ክልል አዋጅ ቁጥር 130/1999 መሰረታዊ ጋር የሚጣጣም ሆኖ አግኝተዋል። ስለሆነም ይዞታውን በልላ ሰው የተነጠቀ አርሶ አደር ወይም ወራሾቹ ይዞታው በልላ ሰው ከህግ ወይም ከውል ውጭ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በአስር ዓመት ውስጥ የእርሻ መሬት የባለይዞታነትና የመጠቀም መብቱን ለማስከበር ክስ ካላቀረበ ክሱ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1677/3/ እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1845 በተደነገገው የአሥር ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ ይታገዲል ከሚለው መደምደሚያ ላይ ደርሰናል።
የወረዲ ፍርድ ቤት ወደ ፍሬ ጉዲይ ገብቶ የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ከመስማቱ በፉት በመጀመሪያ አመልካች ባነሣው የይርጋ የጊዜ ገደብ መቃወሚያ ላይ ብይን መስጠት እንዲለበት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 244 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። ተጠሪ አመልካች የአባቱ ይዞታ የነበረውን መሬት እንዱለቅለት ክስ ያቀረበው አመልካች መሬቱን 1985 ዓ.ም ጀምሮ ይዞ አሥራ ስምንት ዐመት ከቆየ በኋላ መሆኑ በተጠሪ ምስክሮች ጭምር ተረጋግጧል። ስለሆነም ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1677/1/ እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1845 የተደነገገው የአስር ዓመት የይርጋ የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ አመልካች መሬቱን እንዱለቅለት ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖ እያለ የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን የይርጋ መቃወሚያ በማለፍ መሬቱን ለተጠሪ እንዱለቅ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኖኖ ቤንጃ ፍርድ ቤት ፣ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ተጠሪ አመልካች መሬት እንዱለቅ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ወስነናል።
አመልካች መሬቱን ለተጠሪ የመልቀቅ ግዳታ የለበትም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.