No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 8 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ጀማል አማን - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ተዋበች ፈረዳ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የእርሻ መሬት ይዞታና የመጠቀም መብትን የሚመለከት ነወ።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአርሲ ዞን የጉፊ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ ብር 1020 /አንድ ሺህ ሃያ ብር/ ተበድሬ በወለድ አግድ ሶስት ቀርጥ የሚሆን መሬት ህዲር 1ዐ ቀን 1990 ዓ.ም በተፃፈ ውል ሰጥቸዋለሁ። መሬቱን እንዱለቅልኝ ብጠይቀው እንቢተኛ ስለሆነ በፍርድ ተገድድ ይልቀቅልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። አመልካች መሬቱን ብር 1ዐ2ዐ ተቀብላ ከሰጠችኝ በኋላ በገንዘቡ ችግሯን ከተወጣች በኋላ መሬቱን እንዱለቅላት መጠየቁ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ ከሰጠችው ሶስት ቀረጥ መሬት አንድ ቀርጥ መሬት ብቻ ለተጠሪ ይልቀቅላት በማለት ወስኗል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ውለ ለህግ ተቃራኒ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የለውም። አመልካች ተጠሪ መሬት ላይ የሰራውን ቤት አንስቶ መሬቱን ለተጠሪ ያስረክብ በማለት የወረዲውን ፍርድ ቤት ውሣኔ በመሻር ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
ተጠሪ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመግለፅ የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርባለች ። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
ግንቦት 24 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ መሬቱን ይዞ አስራ አንድ ዓመት እንደቆየና የተጠሪ ክስ በይርጋ የሚታገድ ሆኖ እያለ መሬቱን እንድለቅ መወሰኑ ስህተት አለበት። ግምቱ ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/ የሚያወጣ ባህር ዛፍ ተክየበት እያለ እንድለቅ መወሰኑ ተገቢ አይደለም። ስለዚህ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ሰበር ችልት ፍርድ ቤት ውሣኔ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ አመልካች መሬቱን የያዘው በውል ነው። ስለዚህ ይርጋን መከራከሪያ ማድረጉ ተገቢ አይደለም። አመልካች ብር 1ዐ2ዐ /አንድ ሺህ ሃያ ብር/ ስለከፈለ መሬቱን ይዞ የሚቆይበትና የእኔን የመሬት ባለይዞታነትና ተጠቃሚነት መብት የሚያሳጣበት ምክንያት የለም። ስለዚህ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ የክልለ አዋጅ ቁጥር 13ዐ/1999 ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1810 እና 1845 በመጥቀስ ክሱ በይርጋ ይታገዲል የሚል የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል ጉዲዩን እንደመረመርነው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ? ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካች ከተጠሪ ጋር ህዲር 1ዐ ቀን 199ዐ ዓ.ም አድርጌዋለሁ የሚለውን ውል ይዘትና መሰረታዊ ባህሪ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የተለያየ ንብረት አፍርቸበታለሁ የሚለው የእርሻ መሬት የተጠሪ ህጋዊ ይዞታ መሆኑን አልካደም። አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ችግር አጋጥሟት እኔ ብር 1ዐ2ዐ /አንድ ሺህ ሃያ ብር/ ለችግር ማቅለያ እንዱሆናት ሰጥቻት ተጠሪ የእርሻ መሬቱን እኔ እንድጠቀምበት ሰጥታኛለች። የእርሻ መሬቱንም ከሰጠችኝ አስር ዓመት ያለፈው ስለሆነ ተጠሪ የእርሻ መሬቴን ይልቀቅልኝ በማለት ያቀረበችው ክስ በይርጋ ይታገዲል በማለት ነው። በእኛ በኩል አመልካች ከተጠሪ ጋር ህዲር 10 ቀን 1990 ዓ.ም የተዋዋለው ውል በመሰረታዊ ይዘቱ አመልካች ለተጠሪ በሰጣት ብር 1ዐ2ዐ /አንድ ሺህ ሃያ ብር/ መክፈያ እንዱሆን ተጠሪ ሶስት ቀርጥ መሬት ላልተወሰነ ጊዜ እንዱጠቀምበት ግዳታ የገባች መሆኑን የሚያሣይ ነው። ውለ በመሰረታዊ ይዘቱም ሆነ በባህሪው ተጠሪ በመሬቱ ላይ ያላትን የመጠቀምና የይዞታ መብት ለዘለቄታው ለአመልካች በብር 1020 /አንድ ሺህ ሃያ ብር/ ለመሸጥ የተስማማች መሆኑን የሚያሣይ ነው።
መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የመንግስትና የህዝብ ሀብት መሆኑ በህገመንግስቱ አንቀፅ 4ዐ ንዐስ አንቀፅ 3 ተደንግጓል። መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት ሆኖ ማናቸውም ኢትዮጵያ አርሶ አደር የመሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬት የመጠቀምና ከይዞታው ያለመፈናቀል መብት ያለው መሆኑ በህገመንግስቱ አንቀጽ 40 ንዐስ አንቀፅ 4 በግልፅ ተደንግጓል። መንግስት የአርሶ አደሮችን የመሬት ባለይዞታ የመሆን መሬት የመጠቀምና ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብት ህጋዊና ተግባራዊ ለማድረግ የፋዳራል የገጠር መሬት አስተዲደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/93 እና በኦሮሚያ ክልል አዋጅ ቁጥር 130/99 በማውጣት ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።
በአዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀጽ አንድ አርሶ አደር የእርሻ መሬቱን ከሶስት ዓመት በላይ በኮንትራት መስጠት እንደማይችል የደነገገ ሲሆን ማንኛውም አርሶ አደር መሬቱን በኮንትራት ለላላ ሰው ሲሰጥ ውለ ሉያሟላቸው የሚገባቸውን ጉዲዮች ይዘረዝራል። ከዚህ በተጨማሪ የአንድ አርሶ አደርን የመሬት ይዞታና በመሬት የመጠቀም መብት በውል በመውሰድ በመሬቱ ላይ ቋሚና ተንቀሣቃሽ ሀብት ያፈራ ሰው ንብረቱን አፍርሶ በመውሰድ መሬቱን የመልቀቅ ግዳታ እንዲለበት በአዋጅ ቁጥር 130/99 አንቀፅ 6 ተደንግጓል።
አመልካች ከተጠሪ ጋር አድርጌዋለሁ የሚለው ውል በመሰረታዊ ይዘቱና ሞራላዊ ባህሪው በህገመንግስቱ አንቀፅ 4ዐ ንዐስ አንቀፅ 3 እና በህገመንግስት አንቀፅ 40 ንዐስ አንቀፅ 4 የተደነገገውን የአርሶ አደሮች የመሬት ባለይዞታ የመሆንና በመሬት የመጠቀምን ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብት የሚጥስ ከሆኑ በኋላ የፍደራል መንግስት ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 456/97 እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 130/99 ድንጋጌዎች የሚቃረን ህገወጥ የሆነ ውል ነው። ውለ ህገወጥ ውል በመሆኑ ተጠሪ ውለ እንዱፈርስ ያቀረቡት ጥያቄ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። ስለሆነም አመልካች ብር 1ዐ2ዐ /አንድ ሺ ሃያ ብር/ በመክፍል የተጠሪን ሶስት ቀረጥ የእርሻ መሬት ለዘለቄታው ለመውሰድ የተዋዋለው ውል ህገወጥ ውል በመሆኑ ውለ ፈራሽና ውጤት አልባ ነው በማለት የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ የህገ መንግስቱንና የፋደራለ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 456/97 እና የኦሮሚያ ክልል ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 130/99 ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የተሰጠና የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ሀምላ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.