No summary available.
ታህሣሥ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ ያለአግባብ ከስራ አስኪያጅነት ተነስቻለው የሚል ክስን የተመለከተ ሲሆን የተጀመረው በፋ/የመጀ/ደ/ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ ነው። ቀርቦ የነበረውም ክስ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እንዱሁም 2ኛ ተከሳሽ የ4ኛ ተከሳሽ ተወካይ በመሆን ህዲር 17 ቀን 2001 ዓ.ም አድርገነዋል ባለት ስብሰባ የማህበሩን ደንብ እና መመስረቻ ፅሐፍ በማሻሻል 1ኛ ከሳሽ ከምክትል ስራ አስኪያጅነት እንዱነሱ ተደርጎ የ2ኛ ተከሳሽ ልጅ 3ኛ ተከሳሽ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንዱሆኑ ተደርጎ ቃለ-ጉባኤ የተያዘበት ቀኑ ሳይፃፍበት ከሳሾች ሳይጠሩ የተደረገው ውሳኔ ሀሰተኛ እና ህገ-ወጥ በመሆኑ፣ 1ኛ ከሳሽ ም/ስራ አስኪያጅ የሆነው የግራቀኙን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል በመሆኑ፣ 1ኛ ከሳሽ ከምክትል ስራ አስኪያጅነታቸው መነሳታቸው ያለአግባብና መስተካከል ያለበት መሆኑን በስብሰባ ተማምነን ረቂቅ ማሻሻያ ተዘጋጅቶ በረቂቁ ላይ አስተያዬት ከሰጠን በኋላ በውልና ማስረጃ ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ በመሆናቸው፣ በ1995 ዓ.ም በተደረገው የመመስረቻ ፅሐፍ ማሻሻያ የኩባንያው ጠቅላላ ጉባኤ ከፍተኛ አካል ሆኖ እያለ ከህግ ውጪ የጠቅላላ ጉባኤውን ስልጣን በሙለ ለዋና ስራ አስኪያጅ በህዲር 17 ቀን 2001 ዓ.ም በመሰጠቱ፣ የሑሳብ ሰነድችንም እንዲናይ የተደረግን በመሆኑ ተከሳሽ ከዋና ስራ አስኪያጅነታቸው እንዱነሱ አልያም በአግባቡ እንዱሰሩ። እንደዚሁም ህዲር 17 ቀን 2001 ዓ.ም የተደረገው የመመስረቻና የመተዲደሪያ ደንብ ማሻሻያ ፅሐፍ እንዱሻር፣ 1ኛ ከሳሽ ከምክትል ስራ አስኪጅነታቸው ሉነሱ አይገባም እንዱባልልኝ፣ የሑሳብ ሰነድችን የመመልከት መብታችን እንዱከበርልን የሚል ነው። በቀረበው ክስ ላይ ተከሳሾች መልስ እንዱሰጡበት ታዘው በሰጡት መልስ 1ኛ ተከሳሽን በተመለከተ መተዲደሪያ ደንቡና መመስረቻው በህጉ አግባብ የተደረገና በሚመለከተው አካል የፀደቀ ነው፣ ቀኑም በፀደቀበት ቀን ታትሟል፣ 1ኛ ከሳሽ ም/ስራ አስኪያጅ የሆኑት በተሻሻለው የመመስረቻ ጽሁፍ እና ኩባንያው ሲመሰረትም ስራአስኪያጅ አይደለም፣ 1ኛ ከሳሽ ጥሪ ተደርጎላቸው በስብሰባው ላይ አልተገኙም፣ የመጨረውሻን የስብሰባ አጀንዲ አውቀው የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ በሰነድች ማረጋገጫ ጽ/ቤት ቀርቦ አልፈረሙም፣ ሰነድቹም ተፈርሞባቸዋል፣ አለመግባባት ተፈጥሮ በስምምነት ለመጨረስ ተሞክሮ ሳይሳካ በመቅረቱ በአብላጫ ድምጽ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በመሆናቸው በዚያው መልኩ የተወሰነ በመሆኑ፣ ሰነደን አስፈቅደው ኮፑውን መውሰድ ስለሚችለ ማስጠንቀቂያው ተቀባይነት አለው እና 2ኛው ተከሳሽ ስራቸውን በአግባቡ የተወጡት በመሆኑ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችን በተመለከተ ያቀረቡት መልስ በቀጥታ የአንደኛ ተከሳሽ መልስ ጋር ተመሳሳይ ስለመሆኑ ተመልክቶ ሳይመዘገብ በበታች ፍርድ ቤቶች ታልፍአል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት ግራቀኙን ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ በኋላ አራት የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ ጉዲዩን መርምሮታል። እንደመረመረውም በተደረገው ስብሰባ የመተዲደሪያ ደንቡ ሉሻሻል ስለመቻለ በተመለከተ በንግድ ህጉ ቁ. 536(2) መሰረት የመተዲደሪያ ደንብ ለውጥ ¾ ባላቸው ባለአክሲዮን የድምጽ ብልጫ መወሰን እንዲለበት ስለሚያመላክት እና ተከሳሾች ያላቸው የአክሲዮን ድርሻ 77.50% በመሆኑ የተደረገው የመተዲደሪያ ደንብ ለውጥ ህጋዊ አይደለም የሚባልበት አግባብ የለም፤ አንድ ስራ አስኪያጅ በስብሰባ የቀረቡትን እና የተወሰኑትን ዉሳኔዎች የማሳወቅ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በንግድ ህግ ቁ. 533 ስር የተደነገገ በመሆኑ ይሄንኑ ኃላፉነታቸውን መወጣት ያለባቸው ስለመሆኑ ወስኗል፤
የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች ያደረጉትን ስብሰባ በተመለከተ በሚመለከተው ባለስልጣን ፊርማ እና ማህተም የተረጋገጠ እና ቀንም ያለው በመሆኑ የባለስልጣኑ ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት ቀን ማሻሻያው እንደተደረገ ይቆጠራል በማለት ከሳሾች ቀኑ የማይተወቅ ነው በማለት ያነሱትን ክርክር ውድቅ አድርጓል። በመቀጠልም 2ኛ ተከሳሽ ከስራ አስኪያጅነት እንዱነሱ በከሳሾች በኩል የተነሳውን ክስ ውድቅ ሲያደርግ በልላ በኩል በባለአክሲዮኖች በተደረገው ስብሰባ የ1ኛ ከሳሽ ከምክትል ስራ አስኪያጅነት መነሳትም በተመሳሳይ በምክንያት ያልተደገፈ ባለመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ የተደረገው የመመስረቻ ጽሐፍ ማሻሻያ ክፍል ተሽሯል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
የአሁን አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዲዩ ያስቀርባል በማለት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የፋ/የመጀ/ደ/ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል።
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታ በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የግራቀኙን ክርክር በጽሐፍ ሰምተናል። ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች፣ ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም በመጀመሪያ ደረጃ ምክትል ስራ አስኪያጅ ስራ አስኪያጅን በሚመለከቱ የንግድ ህግ ድንጋጌዎች ሉከራከር አይገባውም በማለት የተነሳውን ክርክር በተመለከተ ስለስራ አስኪያጅ የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ከንግድ ህግ ቁ.525 እና ተከታዮቹን ስንመለከት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ስራ አስኪያጆች ሉሾሙ የሚችለበትን አግባብ ስለሚያስቀምጥ እንደዚሁም ህጉ ለእነዚህ ኃላፉነቶች በእነዚሁ ድንጋጌዎች የሚስተናገደ እንጂ ለእያንዲንደ የተለያዬ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል ተብል ስለማይታሰብ ተቀባይነት ያለው ክርክር አይደለም ብለናል። በመቀጠል አመልካች በቅሬታቸው አጥብቀው የሚከራከሩት በመተዲደሪያ ደንባችን አንቀጽ 2(2.4) ውስጥ ስራ አስኪያጅ በማህበርተኞች ጠቅላላ ጉባዔ የሚሻር ስለመሆኑ ተመልክቶ እያለ ያለበቂ ምክንያት ሉሻር አይገባም መባለ አግባብነት የለውም፣ የተባረረው ያለበቂ ምክንያት ነው ቢባል እንኳ በንግድ ህግ ቁ.527(3) መሰረት ኪሳራ ከሚቆረጥለት በስተቀር ወደ ስራ አስኪያጅነቱ ፍርድ ቤት የሚመልስበት አግባብ የለም። እንደዚሁም በባለ አክሲዮኖች የተደገረገው ስብሰባ ህጋዊ ነው ተብል ተወስኖ እያለ በልላ በኩል ም/ስራአስኪያጅ የተነሳበትን የቃለ-ጉባኤ ክፍል መሰረዙ አግባብነት የላለውና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱሻርልን የሚል ነው።
በልላ በኩል ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው ከምክትል ስራ አስኪያጅነት የተሻርኩት በጠቅላላ ጉባኤ ሳይሆን ተከሳሾች እናት እና ልጅ በመሆን ያደረጉት በመሆኑ የመመስረቻው ጽሐፍ አንቀፅ ተጠቅሶ የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም፣ በንግድ ህግ ቁ. 527(3) ስር የተጠቀሰው ፍርድ ቤት ሉቀበለው የሚችል በቂ ምክንያት ከላለ በስተቀር ስራ አስኪያጅ ሉሻር የማይችል ስለመሆኑ በመመስረቻ ጽሐፍ ስለተቀመጠ ወይም ስላልተቀመጠ ሳይሆን ህግ በመሆኑ ሉተገበር ይገባል።
እንደዚሁም በ1995 ዓ.ም በተሸሻለው የመመስረቻ ጽሐፍ ም/ስራአስኪያጅ የሆንኩት ከድርጅቱ ህልውና እና የአክሲዮን አባላቱ መብት ጋር ተያያዥነት ባለው ሁኔታ በመሆኑ ይሄውም 2ኛ አመልካች ስራ አስኪያጅ ሆነው የተጠሪን ድርሻ ጨምሮ የላልች ሁለት ባለአክሲዮኖች እንጀራ እናት በመሆናቸው አድል እንዲይፈጽሙ ታስቦ በመሆኑ የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ነው የሚል ነው።
ጉዲዩ ለዚህ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረዉ ጭብጥ የመልስ ሰጪ ወደ ምክትል ስራ አስኪያጅነት ይመለስ የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል በመሆኑ የተያዘውን ጉዲይ ከዚሁ ጭብጥ አኳያ መመርመሩ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በንግድ ህጉ ቁ. 525 እስከ 537 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች የአንድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ የሚመረጥበት እንደዚሁም የሚሾምበት አግባብ ተደንግጎ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ጉዲዩን ስንመረምረው በመመስረቻ ጽሐፈ አንቀጽ 2(2.4) ስር በጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ ስራ አስኪያጅን ማንሳት የሚቻል ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር በተመለከተ በዚህ መልኩ ማንሳት እንደሚቻል ስምምነት ቢኖርም ያለበቂ ምክንያት እና በአባላት ፍቃድ ብቻ መሰረት በማድረግ ማንሳት የሚቻል ስለመሆኑ በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር ባለመኖሩ ከላይ የተመለከተውን የመመስረቻ ጽሐፍ ድንጋጌ በመጥቀስ የቀረበው ክርክር ከንግድ ህግ ቁ.527(4) ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በእርግጥ የአሁን ተጠሪ ስራ አስኪያጅ ሆኖ የተሾመው በመመስረቻ ጽሐፈ ስለመሆኑ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም፤ በመመስረቻ ጽሐፍ የተመረጠ ስራ አስኪያጅ ለመሻር ደግሞ መመስረቻ ጽሐፍን ለማሻሻል የሚያስፈልገውን የ¾ኛ ካፑታል ድርሻ ባላቸው አባላት መደገፍ ያለበት ስለመሆኑ የንግድ ህግ ቁ.527(1) እና 536(2) አጠቃላይ ንባብ የሚያስገነዝብ ከመሆኑም በላይ በዚህ ጉዲይ ስብሰባውን ያደረጉት የአመልካቾች ወገን 77.50% የካፑታል ድርሻ ያላቸው መሆኑን በማረጋገጥ በላልቹ የመመስረቻ ሰነደን ማሻሻል በተመለከተ ህጋዊ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በማረጋገጥ ተቀብለዋል። ሆኖም ግን ስራ አስኪያጅን ስለመሻር በተመለከተ በንግድ ህግ ቁጥር 527 ስር የተደነገጉትን አንድ በአንድ ስንመለከት ከላይ የተመለከተው እና ስራ አስኪያጅን ለመሻር የሚያስፈልገው ድምጽ በንግድ ህግ ቁ.527(1) ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ሦስት ስር ስራ አስኪያጅ ፍርድ ቤት ሉቀበለው በሚችል በቂ ምክንያት ካልሆነ ሉሻር እንደማይችል፣ የተሻረው ስራ አስኪያጅ ከተሻረበት ጊዜ አንስቶ ስራውን መስራት የማይችል ስለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱም የተሻረበት በቂ ምክንያት ያለመሆኑን የተረዲው እንደሆነ የተሻረው ስራ አስኪያጅ ኪሳራ እንዱያገኝ ለመወሰን ይችላል በማለት ይደነግጋል። ይሄ በንግድ ህግ ቁ.527(3) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ደግሞ ቀደም ሲል ከተመለከተው ከዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ቁጥር አንድ ቀጥል የመጣ በመሆኑ ስራ አስኪያጅን ከስራ ለማንሳት መሟላት እንዲለበት በተለየ የሚደነግገውን ቅድመ ሁኔታዎቹ ስለመሟላት ወይም አለመሟላት መመልከቱ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
የስራ አስኪያጅን መሻር በተመለከተ ፍርድ ቤት ሉያምንበት የሚችል በቂ ምክንያት ከላለ በስተቀር ሉሻር እንደማይችል በግልጽ የደነገገ በመሆኑ ፍርድ ቤት ስራ አስኪያጁ የተሻረበትን አግባብ በመመርመር እንደጉዲዩ አግባብ እየተመለከተ ወደ ስራው ሉመልስ የሚችልበት ምንም ህጋዊ አካሄድ የለም በማለት በአመልካቾች በኩል የተነሳው ክርክር በህጉ በግልጽ የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም። በንግድ ህግ ቁ.527(3) ሁለተኛው እና ሶስተኛውን አረፍተ ነገር በተመለከተ ከኃላፉነት የተሻረ ስራ አስኪያጅ ወዱያውኑ እና ለዘለቄታው ስራውን ያቆማል መባለ ስራ አስኪያጁ የተሻረበትን አግባብ ለመመርመር ለፍርድ ቤት የተሰጠውን ስልጣን የሚነካ እና የሚቃረን ካለመሆኑም በላይ ያለአግባብ የተሻረ ስራ አስኪያጅ ፍርድ ቤቱ ኪሳራ እንዱቆረጥለት መወሰን መቻለ ፍርድ ቤቱ ማድረግ የሚችለው ኪሳራን መቁረጥ ብቻ ነው ከሚል ባለመሆኑ እና እንደየ ጉዲዩ አግባብ ለመወሰን እንዱችል ፈቃጅ (permissive) በሆነ መልኩ የተቀመጠ በመሆኑ ፍርድ ቤት ኪሳራ ቆርጦ ከማሰናበት ውጪ ስራአስኪያጁ የተሻረው ያለአግባብ መሆኑን ቢረዲም ወደ ስራው እንዱመለስ የሚወስንበት አግባብ የለም በማለት የተነሳውን ክርክር አልተቀበልነውም። ምክንያቱም ያለበቂ ምክንያት ሉሻር የሚችል ስራ አስኪያጅ እንደሚኖር ሁለ በበቂ ምክንያትም የሚሻር ስራ አስኪያጅ ሉኖር ስለሚችል ፍርድ ቤቶች እንደየጉዲዩ አግባብነት በመመልከት መወሰን እንዱችለ ፈቃጅ በሆነ መልኩ የተቀረጸ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪም ያለበቂ ምክንያት የተሻረም ቢሆን እንደየጉዲዩ አግባብነት ኪሳራ ተከፍልት እንዱሰናበት ላደረግ የሚችልበት ሁኔታም ሉኖር ይችላል ማለት ነው።
በላለ በኩል በንግድ ህግ ቁ. 527(3) ስር የተቀመጠውን ድንጋጌ ከአቀማመጡ አኳያ በተለየ ሁኔታ ስራአስኪያጅን ለመሻር የተመለከተውን ድንጋጌ ያስቀመጠው በዚሁ ድንጋጌ ንኡስ አንቀጽ አራት ስር የተቀመጠው ሲሆን ይሄውም በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ ውስጥ በማህበርተኞች ነጻ ፍቃድ (at the pleasure of the members) ሉሻር የሚችል ስለመሆኑ የተስማሙ እንደሆነ በማለት ይደነግጋል። ሆኖም በእንደዚህ ዓይነት መልኩ የተስማሙ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር የላለ እና አመልካች በቅሬታው ላይ ያነሳው በጠቅላላ ጉባኤ ማንሳት እንደሚቻል በመመስረቻ ጽሐፈ ተመልክቷል የሚል ሲሆን ይሄ ማለት ደግሞ በንግድ ህግ ቁ 527(4) ስር የተመለከተውን የሚያሟላ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል። በዚሁ መሰረት አመልካቾች ተጠሪን ከም/ስራአስኪያጅነት ለማንሳት ያቀረቡት በቂ ምክንያት ያለመኖሩን በበታች ፍርድ ቤት በፍሬ-ነገር የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ በክርክር ሂደት ግልጽ የሆነው ደግሞ ግራቀኙ የሚያስተዲድሩት ድርጅት እንደማንኛውም ተቀጣሪ ስራ አስኪያጅ ሳይሆን በውርስ የተላለፈላቸውና አመልካቾች በአንድ ወገን በመሆን ተጠሪ ደግሞ በልላ ወገን በመሆን የተለያዩ ፍላጎቶች በመከሰታቸው የተጠሪ ከም/ስራአስኪያጅነት አለመነሳት በአግባቡ መሆኑን የሚያጠናክር ነጥብ ነው።
ባጠቃላይ የአሁን ተጠሪ ከምክትል ስራአስኪያጅነት የተነሳው ያለአግባብ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ተመልክተው ወደ ስራው ይመለስ በማለት የሰጡት ውሳኔ በአግባቡና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ ቁ.94715 ህዲር 28 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመጀ/ደ/ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 140096 በቀን 05-9-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ.348(1) መሰረት ጸንቷል።
የአሁን ተጠሪ ከምክትል ስራአስኪያጅነቱ የሚሻርበት ህጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት ጥር 02 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።