No summary available.
የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መስፍን ዕቁበዮናስ አማረ አሞኜ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ (አ.ማ) አቶ ብርሀኑ ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- ዲሸን ባንክ (አ.ማ) ነገረ ፈጅ አቶ ዮናታን አስፊው ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍታሐብሓር መዝገብ የካቲት 27 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታሐብሓር ይግባኝ ችልት በይግባኝ መዝገብ ሐምል 30 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ችልት ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ ለብድር ውል የተሰጠ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የሚያስከትለውን ኃላፉነት የሚመለከት ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አንደኛ ተከሳሽ፣ አመልካች ሁለተኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ከሳሽ (ተጠሪ) ለሥር ፍርድ ቤት ነሐሴ 30 ቀን 1997 ዓ.ም ባቀረበው የክስ ማመልከቻ፤
ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ከከሳሽ በብድር ከወሰደው ገንዘብ ውስጥ የከፈለው ተቀናንሶ ብር 5,494,328.29 (አምስት ሚሉዮን አራት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) ውስጥ ሁለተኛ ተከሳሽ (አመልካች) መጠኑ 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የሚደርስ የብድር ገንዘብ ተበዲሪው የማይከፍል ከሆነ እሱ የሚከፍል መሆኑን በማረጋገጥ መጋቢት 17 ቀን 1993 ዓ.ም የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ የሰጠ ሲሆን ይህንኑ የገንዘብ የዋስትና ሰነድ፣ የካቲት 5 ቀን 1994 ዓ.ም፣ መጋቢት 11 ቀን 1995 እና የካቲት 22 ቀን 1996 ዓ.ም አድሶታል። አንደኛ ተከሳሽ ብር 5,494,328.29 (አምስት ሚሉዮን አራት መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሀያ ዘጠኝ ሳንቲም) ዕዲ አለበት። ሁለተኛ ተከሳሽ በሰጠው ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና ግዳታ መሰረት እንዱከፍለኝ ብጠይቀው ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ሁለተኛ ተከሳሽ ለብድሩ አከፊፈል በሰጠው የዋስትና ግዳታ መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ከሚፈለግበት ዕዲ ውስጥ 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺ ብር) ገንዘቡ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ አሥራ አራት ፏርሰንት ወለድና በዚህ ክስ ምክንያት ከሳሽ ያወጣውን ወጭ ጨምሮ ተከሳሽ እንዱከፍል ይወሰንልኝ። ከሳሽ ክሱን ያስረደልኛል የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎችና ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ከክሱ ጋር በማያያዝ ያቀረበ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በውሳኔው አስፍሯል።
በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው (አመልካች) የመጀመሪያ ክስ መቃወሚያና የመከላከያ መልስ አቅርቧል። ሁለተኛ ተከሳሽ ድርጅቱ የተቋቋመው ለንብረት፣ ለሰው አካልና የሕይወት፣ ለኃላፉነት የመድን ዋስትና ለመስጠት ነው። የሁለተኛ ተከሳሽ ባለ አክሲዮኖችና የአስተዲደር ቦርደ በማያውቁት ሁኔታ ከመድን ሥራ ውጭ የአንደኛ ተከሳሽን የብድር ዕዲ ለመክፈል የተሰጠው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ከሁለተኛ ተከሳሽ መመስረቻ ጽሁፍ፣ የመተዲደሪያ ደንብ፣ ስለ መድን ሥራ ፈቃድ የወጣውን ህግ የሚጥስ በመሆኑ ሁለተኛው ተከሳሽ ኃላፉነት የለበትም። የሁለተኛው ተከሳሽ ሥራ አስኪያጅ በፍታብሓር ህጉ፣ በአፍሪካ ኢንሹራንስ (አ.ማ) መተዲደሪያ ደንብና በንግድ ሕጉ የተዘረዘሩትን የአስተዲደር ተግባራትን ከማከናወን ውጭ ላልች ልዩ ተግባራትን ማከናወን እንደማይችል በግልጽ ተቀምጧል። የሁለተኛ ተከሳሽ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰጠውን የገንዘብ ዋስትና ሰነድ በመቀበል ለከሳሽ የፈጸመው ተግባር ከጅምሩ ሕጋዊ ውጤት የላለውና ፍርስ በመሆኑ ከሳሽ ሁለተኛ ተከሳሽን የሚከስበት ምክንያት የለም።
በኢንሹራንስ ውል ምክንያት የሚቀርብ ማንኛውም ክስ ሉጠየቅ የሚችለው ጉዲቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ መሆኑ በንግድ ህጉ በግልጽ ተደንግጓል። ከሳሽ ክሱን ያቀረበው ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ።
የሁለተኛ ተከሳሽ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ሰጥቷል የሚባል ቢሆን ሰነደ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1725(ሀ) እና የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1727(ለ) በሚደነግጉት መሰረት በሁለት ምስክሮች ያልተፈረመ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና ፈራሽ ነው። ከሳሽ በሁለተኛ ተከሳሽ ተሰጥቶኛል የሚለው ሰነድ ገንዘብ መጠኑ ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) መሆኑን ያሳያል። ከሳሽ ሁለተኛው ተከሳሽ በሰነድ ከሰጠው ዋስትና በላይ እንዱከፈለው ያቀረበው ክስ የህግ መሰረት የለውም። ከሳሽ ብድሩን ለወሰደው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ተበድሮ የወሰደ መሆኑን የሚሳይ ማስረጃ አላቀረበም። ከሳሽ እዲው ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ የሚታሰብ አሥራ አራት ፏርሰንት ወለድ ሁለተኛ ተከሳሽ እንዱከፍለው ያቀረበው ክስ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 2479 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎች የሚጥስና የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ ያሰናብተኝ።
ከሳሽ ከሁለተኛ ተከሳሽ ተሰጥቶኛል የሚለው የዋስትና ሰነድ ከሳሽ ከተበዲሪው ጋር ያደረገው ብድር ውል የተደረገበት ጊዜና የብድሩ መጠን የሚገናኝ ባለመሆኑ ሁለተኛ ተከሳሽ በኃላፉነት አይጠየቅም። የከሳሽ አድራጎት የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ስለ ገንዘብ ዋስትና ሰነድች ያወጣውን መመሪያ በመጣስ የተፈጸመ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ሆኖ እንዱሰናበት በማለት ተከራክሯል። ተከሳሽ ክሱን ለመከላከል ይጠቅሙኛል የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ከመልሱ ጋር በማያያዝ ያቀረበ መሆኑንና ማስረጃ ዝርዝር መግለጫ እንዲቀረበ ከሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተረድተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ተበዲሪውን ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የብድር ሂሳብ መግለጫ ከሳሽ እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ የብድር የሂሳብ መግለጫ ቀርቦለታል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሁለተኛ ተከሳሽ ሥራ አስኪያጅ ወጭ አድርጎ በሰጣቸው የገንዘብ ዋስትና ሰነድች በኃላፉነት ይጠየቃል ወይስ አይጠየቅም? ሁለተኛ ተከሳሽ በኃላፉነት የሚጠየቅ ቢሆን የመክፈል ኃላፉነቱ ምን ያህል ነው? የሚለትን ጭብጦች መሥርቷል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሳሽ የገንዘብ ዋስትና ሰነድችን መስጠት ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ የሆነ ተግባር አይደለም። ተከሳሽ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ክልከላ እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የሰጣቸው ገንዘብ ዋስትና ሰነድች ሕጋዊ ውጤት ያላቸው ናቸው። የተከሳሽ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና ሰነድችን የመፈረም ሥልጣን በንግድ ህጉ የተሰጠው በመሆኑና ሁለተኛ ተከሳሽ በህጉ መሰረት የሥራ አስኪያጁን ሥልጣን ያልገደበ በመሆኑ፣ ሥራ አስኪያጁ ለከሳሽ ፈርሞ በሰጣቸው የገንዘብ ዋስትና ሰነድች በኃላፉነት ይጠየቃል። ከሳሽ ክሱን ያቀረበው በንግድ ህጉ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ገደብ ከማለፈ በፉት ስለሆነ የከሳሽ ክስ በይርጋ አይታገድም። አንደኛ ተከሳሽ ከሚፈለግበት ዕዲ ውስጥ ሁለተኛ ተከሳሽ ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ከሣሽ ማስጠንቀቂያ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለከሳሽ በአንድነትና በነጠላ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍታሐብሓር ችልት አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ችልት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካች ነሐሴ 15 ቀን 2000 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር ማመልከቻ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸውን ክርክሮች በማጠናከር ተከራክሯል። አመልካች የተቋቋመው አጠቃላይ የመድን ሥራና የረዥም ጊዜ የመድን ዋስትና ለመስጠት ነው። አመልካች ከመድን ሥራ ውጭ የብድር ዕዲ ለመክፈል የዋስትና ግዳታ ሰነድ ለመስጠት አይችልም። ገንዘብ ዋስትና መስጠት በአመልካች መመስረቻ ጽሁፍና የመተዲደሪያ ደንብ፣ ስለ መድን ሥራ ፈቃድ ከወጣው አዋጅ ቁጥር 86/1986 ድንጋጌዎች ውጭና አመልካች ከተቋቋመበት መሰረታዊ ዓላማ ውጭ የሆነ ለባንክ ብቻ የተፈቀደ ተግባር ነው። ተጠሪ ይህንን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የፈጸመው ተግባር ህገ-ወጥና ምንም አይነት ተጠያቂነት አያስከትልም። የአመልካች ዋና ሥራ አስኪያጅ በድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብና በንግድ ሕግ ቁጥር 363 ንዐስ አንቀጽ 1 የተዘረዘሩትን የአስተዲደር ተግባራትን ከማከናወን ውጭ ላልች ልዩ ተግባራትን ማከናወን እንደማይችል ተመልክቷል። የአመልካች ዋና ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ እንዱፈርም በንግድ ህግ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3 ልዩና ግልጽ የሆነ ሥልጣን አልተሰጠውም። ሥራ አስኪያጁ የሰጠው የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የኢንሹራንስ ፕሉሲ አይደለም። የስር ፍርድ ቤት የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የኢንሹራንስ ፕሉሲ አንድና ተመሳሳይ አድርጎ በመውሰድ ከጅምሩ ሕጋዊ ውጤት የላለውና ፍርስ የሆነውን፣ ተግባር ህጋዊ ውጤት አለው በማለት የተሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የሰጠው የዋስትና ሰነድ ኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው በማለት የህግ ትርጉም ከሰጠ በኋላ አመልካች ያቀረበውን ሁለት ዓመት የይርጋ መከራከሪያ ውድቅ ማድረጉ እርስ በርሱ የሚቃረንና ወጥነት የላለው ነው። በአመልካች ተሰጠ የተባለው የዋስትና ሰነድ በሕግ የተደነገገውን ፍርም የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና ፈራሽ ነው።
የዋስትና ሰነደን የሰጠው በተጠሪና ብድሩን በወሰደው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ተበድሮ ከመውሰደ በፉት ነው። በአመልካችና በተበዲሪው መካከል የብድር ውል ከመፈረሙ በፉት የወጣ ሰነድ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት ሉኖረውና አመልካችን የሚያስገድድ አይደለም። የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሳኔ ከላይ የዘረዘርናቸውን ተደራራቢ መሰረታዊ የህግ ሥህተቶች የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል።
ለአመልካች የሰበር አቤቱታ ተጠሪ ጥር 15 ቀን 2001 ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች በሕግ ያልተከለከለ ሁለንም የመድን ሥራዎች ለመሥራት ይችላል። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 23/2000 እና 24/2004 ለገንዘብ ዕዲ የሚሰጥ ዋስትና በመድን ድርጅቶች የሚሰራ ተግባር መሆኑን በመግለጽ ትርጉም ሰጥቶበታል። አመልካች ክፍያ እየተቀበለ መድን አገልግልት የሚሰጥ በመሆኑ የድርጅቱ ማኔጅንግ ዲይሬክተር ተገቢውን አረቦን በማስከፈል የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የመስጠት ሥልጣን አለው፡ ከዚህ በተጨማሪ ንግድ ህጉ አንቀጽ 35 የድርጅቱ ማኔጅንግ ዲይሬክተር የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የመስጠት ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ የሚደነግግ በመሆኑ የአመልካች ማኔጅንግ ዲይሬክተር የፈፀመው ተግባር ህጋዊ ውጤት አለው። አመልካች ክሱ ሁለት ዓመት የይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ያቀረብኩትን መከራከሪያ የስር ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የህግ መሰረት የለውም። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በወጣው 23/2002 ለገንዘብ ዕዲ ስለተሰጠ የዋስትና ሰነድ መመሪያ አውጥቷል። አመልካች ሰነደን የሰጠው 1993 ዓ.ም ሲሆን ሰነደን በየዓመቱ ሲያድስ ቆይቶ ይህንኑ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ መስከረም 5 ቀን 1997 የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 3 መሰረት እንዱራዘም ያደረገ በመሆኑ የይርጋ ጊዜ ገደቡ አላለፈም። አመልካች የዋስትና ሰነደ በሕግ የተደነገገውን ፍርም የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና ፈራሽ ነው በማለት ያቀረበው ውለ የመድን ፕሉሲ አወጣጥ ፍርም የሚያሟላ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሳኔ የህግ ስሕተት የላለበት በመሆኑ ሰበር ችልቱ በማጽናት እንዱያሰናብተኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች በሰበር አቤቱታው ያነሳቸውን ነጥቦች በማጠናከር ጥር 22 ቀን 2001 ዓ.ም. የተጻፈ ስድስት ገጽ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ በሰበር ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው በመጀመሪያ አመልካች የሰጠው የገንዘብ ዋስትና ሰነድ ህጋዊነትና የሰነደን ሕጋዊ ባሕሪና ሰነደ ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ነው ወይስ አይደለም? በሚለት ነጥቦች ላይ ግራ ቀኙ ያቀረቧቸውን ክርክሮች ቅድሚያ በማየት መወሰን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም አመልካች የሰጠሁት የገንዘብ ዋስትና ሰነድ ምንም አይነት ኃላፉነትን የማያስከትልና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የላለው ነው በማለት ያቀረባቸው መከራከሪያዎች የህግ መሰረት ያላቸው ናቸው ወይስ አይደለም? የሚለውን መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ የሚከተለትን ዝርዝር ጭብጦች በቅደም ተከተል አይተናል። በሰበር የታዩት ዝርዝር የህግ ጭብጦችም፡- 1/አመልካች የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መስጠት አመልካቹ የኢንሹራንስ ኩባንያ ከተፈቀደለት፣ ከተቋቋመበትና ህጋዊ ህልውና አግኝቶ ከተመዘገበበት የንግድ ዓላማ ውጭ የተፈጸመ ተግባር በመሆኑ፣ በህግ ተጠያቂ ልሆን አይገባኝም በማለት ያቀረበው ክርክር፣ የሕግ መሰረት አለው ወይስ የለውም?
2/ አመልካች የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ ለማውጣት ሥልጣን ሣይኖረው ፈርሞ የሰጠውን የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ በመቀበል ተጠሪ ለፈጸመው ተግባር ህጋዊ ተጠያቂነት የለብኝም፣ በማለት ያቀረበውን ክርክር በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት የታለፈው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
3/አመልካች የተሰጠው የገንዘብ ግዳታ የዋስትና ሰነድ፣ ስለ ዋስትና ውል የተደነገጉትን ፍርማሉቲዎች የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና በኃላፉነት የማያስጠይቅ ነው፣በማለት ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት ያለፈት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም ?
4/ ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም?
5/አመልካች ለተጠሪ በሰጠው የገንዘብ የዋስትና የግዳታ ሰነድ መሰረት በኃላፉነት ይጠየቃል ወይስ አይጠቅም? በኃላፉነት ይጠየቃል የሚባል ቢሆን የአመልካች የኃላፉነት መጠን ምን ያህል ነው?
1/የመጀመሪያው ጭብጥ አመልካች እንዱሰራው ከተፈቀደለት መድን ንግድ ሥራና ከተቋቋመበትና ህጋዊ ህልውና አግኝቶ ከተመዘገበበት የንግድ ዓላማ ጋር የተያያዘ ነው። አንድ የንግድ ድርጅት በንግድ መዝገብ ውሰጥ ያስመዘገበውንና በጋዜጣ ታትሞ የወጣውን ጉዲይ መከራከሪያ ሉያደርገው እንደሚችልና ሶስተኛ ወገኖች በንግድ መዝገብ የገባውን ጉዲይ አላውቅም ነበር ብለው ማስረጃ ማቅረብ የማይፈቀድላቸው መሆኑን በንግድ ሕጉ አንቀጽ 120 ንኡስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። አመልካች በህግ ከተፈቀደለትና ኩባንያው ከተቋቋመበት የንግድ ዓላማ ውጭ በተፈጸመ ተግባር በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባኝም በማለት የሚከራከረው፣ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 26ና የንግድ ሕጉ አንቀጽ 120 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈጻሚነት ያላቸው በመሆኑ በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባኝም በማለት ነው።
ሆኖም ከላይ የተጠቀሱት የንግድ ሕጉ አንቀጽ 26ና አንቀጽ 120 ንኡስ አንቀጽ 2 ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈጻሚነት የሚኖራቸው በመጀመሪያ አመልካች ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከተጠሪ የተበደረውን ገንዘብ ካልከፈለ አመልካቹ እስከ 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የሚከፍል መሆኑን በመግለጽ የሰጠው የገንዘብ የዋስትና የግዳታ ሰነድ አመልካች እንዱሰራው ያልተፈቀደለት፣ አመልካች ከተቋቋመበት የንግድ ዓላማ ውጭ የሆነ፣ አመልካች ከሚሰራው የመድን ንግድ ሥራ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላለው ወይም አመልካች እንዲይሰራው በህግ በግልጽ የተከለከለ ተግባር መሆኑ ሲረጋገጥ በመሆኑ በመጀመሪያ ይህንን ነጥብ ቅድሚያ በመስጠት አይተነዋል፡ አከራካሪው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) ምን አይነት የህግ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 በእንግሉዝኛ ቋንቋ ትርጉም ሰጥቶታል። የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ፣ በመመሪያ ቁጥር 23 /2002 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 3 ” Financial guarantee bond shall mean an obligation undertaken by an insurance company to pay for the lending bank or another creditors or supplier all outstanding claims arising from the non Payment by debtor or debtors. “ የሚል ትርጓሜ ሰጥቶታል። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ እንደ አውሮፒውያን አቆጣጠር 2002 ዓ.ም ና 2004 በወጣው መመሪያ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) የማውጣት ተግባር እንዲይፈጽሙ በግልጽ ከልክሎል። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) የማውጣት ተግባር እንዲይፈጽሙ በግልጽ የተከለከለ መሆኑን "Insurance companies are prohibited from issuing a Financial Guarantee Bond, by whatever name it may be referred to, in any form what so ever." በማለት በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 1 የደነገገ ሲሆን Insurance companies are prohibited from issuing a Financial Guarantee Bond, by whatever name it may be referred to, in any form wether conditional or otherwise.
በማለት በመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 1 ግልጽ ክልከላ አድርጎበታል፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የመድን ንግድ ሥራ የሚሰሩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) እንዲይሰጡ በመመሪያ በግልጽ ከመከልከለ በፉት በኢንሹራንስ ኩባንያዎች የተሰጡ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች የሚኖራቸውን ህጋዊ ውጤት ባወጣው መመሪያ ግልጽ አድርጓል። በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 ከመከልከላቸው በፉት በኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ የተሰጡ የገንዘብ የዋስትና ግዳታ ሰነድች የጸኑና ሕጋዊ ውጤት ያላቸው መሆኑን በመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 3 በግልጽ ተደንግጓል። በልላ አነጋገር አመልካችና ላልች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 23/2002 እና መመሪያ ቁጥር 24/2004 በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Gurantee Bond) እንዲይሰጡ ከመከልከላቸው በፉት፣ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ የመስጠት ሥራን እንደ አንድ የመድን ንግድ ሥራ አይነት ሲያከናውኑት የኖሩት ተግባር እንደነበርና ይህም ተግባራቸው ህጋዊ ውጤት ያለውና ኃላፉነትን የሚያስከትል መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 86/86 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 4 ድንጋጌና የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች በጣምራ በማንበብ ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በመጀመሪያ መመሪያ ቁጥር 23/2002 በማውጣት፣የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) እንዲይሰጡ የከለከላቸው፣ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መስጠት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከተቋቋሙበት የመድን የንግድ ዓላማ ውጭ የሆነ ሥራ ነው በማለት አይደለም። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የክልከላ መነሻ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የላላውን ሰው ዕዲ ለመክፈል የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ሲሰጡ ተበዲሪው ብድሩን ባለመክፈለ ምክንያት በገቡት የዋስትና ግዳታ መሰረት ለባለመብቱ (አበዲሪው) የከፈለትን ገንዘብ ከባለዕዲው ለማስመለስ የሚያስችላቸው በቂ መያዣ የሚሆን የተበዲሪው ንብረት ወይም ገንዘብ የማይዙ ወይም የማያገኙ በመሆኑና በአገሪቱ አስተማማኝ የሆነ የጠለፊ መድን ዋስትና የላለ በመሆኑ ምክንያት፣ በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ ለመከላከል በማሰብ መሆኑን በመመሪያው መግቢያ ላይ በግልጽ አስፍሮታል።
ከላይ በዝርዝር በተገለጹት ምክንያቶች አመልካች የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ግልጽ መመሪያ በማውጣት፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) እንዲይሰጡ ከመከልከለ በፉት ወጭ አድርጎ ለተጠሪ የሰጣቸው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች (Financial Guarantee Bonds) ከተቋቋመበት የንግድ ዓላማ ውጭ የተፈጸሙ ተግባራት በመሆናቸው ሕጋዊ ውጤት የላላቸውና አመልካችን በኃላፉነት ሉያስጠይቁ የማይችለ ናቸው በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ግልጽ መመሪያ አውጥቶ ከመከልከለ በፉት ለተጠሪ የሰጣቸው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች (Financial Guarantee Bonds)፣አመልካች እንዱሰራ ከተፈቀደለት የመድን ንግድ ሥራና ከተቋቋመበት የንግድ ዓላማ ውጭ የተሰጡ ሰነድች በመሆናቸው ሕጋዊ ውጤት የላቸውም በማለት ያቀረበውን ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
2/ ሁለተኛው ጭብጥ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድቹ ወጭ በሆኑበት ወቅት የአመልካች ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረውን ሥልጣንና ሉፈጽማቸው የሚችላቸው የህግ ተግባሮች ምንድን ናቸው?
አመልካች የዋና ስራ አስኪያጁን ሥልጣን በህግ የተቀመጡ ሁኔታዎች በማሟላት ገድቧል ወይስ አልገደበም የሚለትንና ላልች ተያያዥነት ያላቸውን ነጥቦች መመርመር የሚጠይቅ ነው። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 86/1986 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 4 እና በአንቀጽ 6 የተደነገጉትን ልዩ መስፈርቶች በማሟላት ተመዝግቦና ፈቃድ አግኝቶ የመድን ንግድ ሥራ የሚያከናውን የአክሲዮን ማህበር (የኢንሹራንስ ኩባንያ) ነው። የመድን ንግድ ሥራ ለማከናወን የተቋቋመና ፈቃድ ያገኘ የአክሲዮን ማህበር የመድን ሥራውን በዋና ኃላፉነት የሚመራለት ሥራ አስኪያጅ የሚኖረው መሆኑ፣ ሥራ አስኪያጁ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የሚወጣውን መስፈርት የሚያሟላ መሆን እንደሚገባውና ሥራውን የሚሰራው በብሓራዊ ባንኩ ስምምነትና ዕውቅና እንደሚሆን፣ የስራ አስኪያጁ ማንነት የትምህርት ደረጃ ችልታና ላልች ዝርዝር ሁኔታዎች ብሓራዊ ባንክ የስራ አስኪያጆችንና ረዲቶችን ዝርዝር ሁኔታዎች ለመመዝገብ ባዘጋጀው መዝገብ የሚመዘገብ መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 86/1986 አንቀጽ 32፣ አንቀጽ 33ና አንቀጽ 34 ድንጋጌዎችን ይዘት በማየት ለመረዲት ይቻላል።
ሆኖም አዋጁ ከላይ የተቀመጡትንና በብሓራዊ ባንክ የሚወጡ መስፈርቶችን ማሟላቱ ተረጋግጦ የኢንሹራስ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው ስለሚኖረው ሥልጣንና ኃላፉነት አዋጁ በዝርዝርና በግልጽ አይደነግግም። አዋጅ ቁጥር 86/1986 “ሥራ አስኪያጅ” ማለት በማናቸውም የማዕረግ ሥም ቢጠራም የድርጅቱን ሥራን ለመምራት በዋና ኃላፉነት የሚጠራ ሰውና ለእርሱ ወይም ለምክትለ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ ላልች የኩባንያው ኃላፉዎች ናቸው፤ በማለት አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 20 ትርጉም ሰጥቶታል። በዚህ ድንጋጌ ለኢንሹራስ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ የተሰጠው ትርጓሜ የሥራ አስኪያጁን ሥልጣንና ኃላፉነት ለመገንዘብ ጠቀሜታ ያለውና አመላካች (indicative) የሆነ ድንጋጌ ነው። ሆኖም ድንጋጌው የኢንሹራስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያለውን ዝርዝር ሥልጣንና ሉፈጽማቸው የሚችላቸው የህግ ተግባሮች ለመወሰን በቂ አይደለም። በመሆኑም የአመልካች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አከራካሪዎቹን የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች በተሰጡበት ጊዜ የነበረውን ሥልጣንና ሉፈጽማቸው የሚችላቸው የህግ ተግባሮች ለመወሰን አግባብነት ካላቸውና ከላይ ከጠቀስናቸው የአዋጅ ቁጥር 86/1986 ድንጋጌዎች በተጨማሪ የአንድ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ በንግድ ሕጉ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፉነት መመርመሩ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
በንግድ ሕጉ መሰረት ስለተቋቋሙ የአክሲዮን ማህበራት ፕሬዝዳንት፣ ዋና ሥራ አስኪያጅና ጸሐፉ ሥልጣን የሚደነግገው የንግድ ሕግ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3 ሥራ አስኪያጁ በአስተዲደሩ ምክር ቤት እንደሚሾምና የስራ አስኪያጁን ሥልጣን በተመለከተ የንግድ ህጉ አንደኛ መጽሐፍ፣ አንቀጽ 34፣ አንቀጽ 35፣ አንቀጽ 109 ንዐስ አንቀጽ 1(ረ) እና አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ (ሰ) ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ በግልጽ ይደነግጋል። የንግድ ሕጉ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3 ስለ ሥራ አስኪያጁ አመዲደብ (ሹመት) የሚደነግገው ክፍል ከላይ በዝርዝር የተገለጹት ማሻሻያዎች በአዋጅ ቁጥር 86/86 ድንጋጌዎች ተደርገውበታል። በልላ በኩል በንግድ ህጉ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3 ስለ ሥራ አስኪያጁ ሥልጣን ተገቢነት እንዲላቸው የተደነገጉት ድንጋጌዎች የአመልካች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅቱ የነበረውን ሥልጣን ለመወሰን ገዥነት ያላቸው ድንጋጌዎች ናቸው። የድንጋጌዎቹን ይዘት ስንመለከት የንግድ ሕግ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 109 ንዐስ አንቀጽ(ረ) የአክሲዮን ማህበሩ (አመልካች) በሥራ አስኪያጅነት የሾመውን ሰው በንግድ መዝገብ ማስመዝገብ እንደሚገባው የሚደነግጉ ናቸው።
የንግድ ሕግ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 2 ከላይ በተገለጹት የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ንግድ ድርጅቱ ባይፈጽም የሚከተለውን ውጤት ይደነግጋል። ድንጋጌው የአክሲዮን ማህበሩ (አመልካች) የሥራ አስኪያጁን ሹመት በንግድ መዝገብ ሳያስገባ ቢቀር እንኳን ሥራ አስኪያጁ ከተሾመበት ቀን ጀምሮ ሥራውን ለማከናወን የሚችል መሆኑን የሚደነግግ ይዘት ነው።
“ስለ ሥራ አስኪያጁ ሥልጣን” የሚል ርዕስ ያለው የንግድ ሕግ አንቀጽ 35“ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያገናኙት ጉዲዮች ሁለ ሥራ አስኪያጁ ከነጋዳው ሥራ ጋር ነክነት ያላቸውን ማናቸውም ግዳታዎች ለመፈረምና የሚተላለፈ ሰነድችን (ኔጎሸብል ኢንስትሩመንትስ) ጭምር መፈረም ሥልጣን እንዲለው ይቆጠራል” በማለት በንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ የሚደነግግ ሲሆን፣ “የንግድ ሕጉ አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ( ሰ) ነጋዳው ወይም የአክሲዮን ማህበሩ የሥራ አስኪያጁ ሥልጣን የቅርንጫፈን ወይም የውክልናውን ሥራ ብቻ በማካሄድ የተወሰነ መሆኑ በንግድ መዝገብ በገባው ቃል ውስጥ የላለ ከሆነ ቅን ልቦና ያላቸው ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ሉሆኑ አይችለም” በማለት ይደነግጋል።
የአንቀጽ 35 ንኡስ አንቀጽ 2 በሥራ አስኪያጁ ሥልጣን ላይ ሕግ አውጭው የተጣለውን ገደብ ምን እንደሆነ የሚደነግግ ሲሆን “ሥልጣን ያለው ሥራ አስኪያጅ በግልጽ ሥልጣን ካልተሰጠው በስተቀር የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መያዣ ማድረግ፣ ንግድ መደብሩን መሸጥ፣ ማከራየት ወይም በዕዲ ማስያዝ አይችልም” በማለት በግልጽ ይደነግጋል።
አመልካች ዋና ሥራ አስኪያጁ የፈጸመው ተግባር ከነበረው ሥልጣን ውጭ ነው በማለት በተጠሪ ላይ ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት የሚኖረው ከሁለት ሁኔታዎች አንደኛው መሟላቱ ሲረጋገጥ ነው። የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጁ ህግ አውጭው አስገዲጅ በሆነው በንግድ ህግ አንቀጽ 35 ንዐስ አንቀጽ 2 የደነገገውን ክልከላ ወይም የስልጣን ገደብ በመተላለፍ አመልካች በግልጽ ሥልጣን ሳይሰጠው በድንጋጌው ከተዘረዘሩት አንደኛውን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ተግባራት የፈጸመ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ነው። ሁለተኛው የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፈቃጅነት ባለው በንግድ ሕጉ አንቀጽ 35 ንዐስ አንቀጽ 1 የተሰጠውን ሥልጣን አመልካች የንግድ ህግ አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ(ሰ) የተደነገገውን መስፈርት በሟሟላት የገደበው ሆኖ እያለ አመልካች ያስቀመጠውን የስልጣን ገደብ በመተላለፍ ሥራ አስኪያጁ ተግባሩን የፈጸመ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
ከላይ በሕግ የተቀመጡትን ሁለት መስፈርቶች መሰረት በማድረግ የአመልካችን ክርክር መዝነናል። የአመልካች ዋና ሥራ አስኪያጅ ተበዲሪው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከተጠሪ ተበድሮ የወሰደውን ገንዘብ በብድር ውለ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ፣ አመልካች በዋስትና ሰነደ እስከገለጸው ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የሚከፍል መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ፈርሞ የሰጠ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤትም ሆነ በሰበር አከራካሪ አይደለም። ይህ የአመልካች ሥራ አስኪያጅ የፈጸመው ተግባር፣ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 86/86 አንቀጽ 4 ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ወጭ አድርጎ የመስጠት የመድን ንግድ ሥራ አይነት እንደሆነ ትርጉም ሰጥቶበታል።
እንደዚሁም የአመልካች ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነደን የፈረመው የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ወጭ እንዲያደርጉ በመመሪያ ከመከልከለ በፉት ስለመሆኑ በሥር ፍርድ ተረጋግጧል።
የአመልካች ሥራ አስኪያጁ የፈጸመውና በዚህ ጉዲይ አከራካሪ የሆነው ተግባር የአመልካችን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መያዣ ማድረግ ወይም ንግድ መደብሩን መሸጥ ወይም ማከራየት ወይም ኩባንያውን በዕዲ የማስያዝ ተግባር አይደለም። ስለሆነም አመልካች የንግድ ሕግ ቁጥር 35 ንዐስ አንቀጽ 2 በመጥቀስ ሥራ አስኪያጁ የፈጸመው ተግባር ፈራሽና ሕጋዊ ውጤት የላለው ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የድንጋጌውን ይዘት ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። ሁለተኛው አመልካች “የንግድ ሕጉ አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ (ሰ) የተደነገገውን መስፈርት በማሟላት የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ እንዲይፈርም ወይም ተመሳሳይ በሆነ ላላ አገላለጽ የዋና ሥራ አስኪያጁን ሥልጣን ያልገደበ መሆኑንና በሥራ አስኪያጁ ሥልጣን ላይ አድርጌአለሁ የሚለውን ገደብ ወይም ቅነሳ በንግድ መዝገብ በገባው ቃል ውስጥ ያላስመዘገበ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ተረጋግጧል። አመልካች የዋና ሥራ አስኪያጁ ሥልጣን የተገደበ መሆኑንና ሥልጣኑ መገደቡ በንግድ መዝገብ በገባው ቃል ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቅርቦ ያላስረዲ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ይህም በመሆኑ ዋና ሥራ አስኪያጁ አመልካች እንዱሰራው በወቅቱ ተፈቀደውለት የነበሩ የመድን የንግድ ሥራዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ተግባራት የመፈጸም ሙለ ስልጣን እንደነበረው ግምት የሚወሰድ መሆኑን ከንግድ ሕግ አንቀጽ 35 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል። የንግድ ሕጉ አንቀጽ 36 ድንጋጌዎችም ይዘታቸው ግልጽና ይህንኑ የሚያጠናክሩ ናቸው።
አመልካች የዋና ሥራ አስኪያጁ ስልጣን የቀነሰ መሆኑን በንግድ መዝገብ ሳያስመዘግብ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሥልጣን በአመልካች መተዲደሪያ ደንብ ተገድቧል። ሥራ አስኪያጁ በመተዲደሪያ ደንብ ከተሰጠው ሥልጣን ውጭ የፈጸመው ተግባር ህጋዊ ተጠያቂነት የለብኝም በማለት ሶስተኛ ወገን የሆነውን ተጠሪን ለመቃወም ያቀረበው ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው መሆኑን መርምረናል። አንድ የአክሲዮን ማህበር በንግድ መዝገብ እንዱያስመዘግባቸው ህግ ግዳታ ያደረገበት ጉዲዮች በንግድ ሕጉ አንቀጽ 323 ንዐስ አንቀጽ 3 ተደንግገዋል። በአዋጅ ቁጥር 86/86 አንቀጽ 6 እና በንግድ ህጉ አንቀጽ 323 ንዐስ አንቀጽ 2 የአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሐፍ፣ ማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ ላልች አስፈላጊ መረጃዎች ማሕበሩ ህጋዊ ህልውና እንዱገኝና እንዱመዘገብ ሥልጣን ላለው አካል ከሚቀርበው ማመልከቻ ጋር ተያይዘው መቅረብ እንዲለባቸው ይደነግጋለ። የአመልካች ክርክር የድርጅቱ የመመስረቻ ጽሐፈና መተዲደሪያ ደንቡን የአክሲዮን ማህበሩ እንዱመዘገብ ከሚያቀርበው ማመልከቻ ጋር አያይዘው መቅረባቸው ብቻውን የአክሲዮን ማህበሩ በመመስረቻ ጽሐፈና በመተዲደሪያ ደንቡ ውስጥ የተካተቱትን ሁለንም ጉዲዮች በንግድ መዝገብ በገባው ቃል ውስጥ እንዲስመዘገበ የሚያስቆጥረው ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ እንድናይ የሚያስገድድ ነው።
አክሲዮን ማህበሩ በንግድ መዝገብ ውስጥ እንዱመዘገብለት ሥልጣን በሕግ ለተሰጠው አካል በሚያቀርበው ማመልከቻ እንዱገልጻቸው በህግ የሚገደደው፤ የማህበርተኞች ስም፣ ዜግነት አድራሻና ለመግዛት የፈረሙት የአክሲዮኖች ብዛት፣ የማህበሩ መጠሪያ፣ የማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤትና ያለት ከሆነ የቅርንጫፍች ሥፍራ፣ ማህበሩ የቆመበት ጉዲይ፣ የተፈረመና ገቢ የሆነውን ገንዘብ ልክ፣ የአክሲዮኑ ዋጋ ብዛቱ፣ አይነትና የአክሲዮኑ ልዩነት፣ በአይነት የተደረጉ መዋጮዎች ዋጋና የአገልግልት አይነት፣ አስተዲዲሪዎቹን ብዛት ሥልጣን እንደዚሁም ለማህበሩ እንደራሴ የመሆን አኳኋን፣ የተቆጣጣሪዎች ብዛትና ማህበሩ የሚቆይበትን ጊዜ መሆኑን የንግድ ሕጉ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 313 ከንዐስ አንቀጽ 1 እስከ ንዐስ አንቀጽ 7፣ ከንዐስ አንቀጽ 10 እስከ ንዐስ አንቀጽ 12 የተደነገጉት ድንጋጌዎች በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። እንደዚሁም የአክሲዮን ማህበሩ ሥራ አስኪያጅ የሾመ መሆኑንና የሥራ አስኪያጁን ማንነት ካልሆነ በስተቀር የስራ አስኪያጁ ሥልጣን ወሰን በንግድ መዝገብ በሚገባው ቃል ውስጥ ማስመዝገብ ህጉ ግዳታ ያላደረገው ተግባር መሆኑን ከንግድ ህጉ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3፣ አንቀጽ 34 ንዐስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 109 ንዐስ አንቀጽ(ረ) ድንጋጌዎች አቀራረጽ ይዘት ለመረዲት ይቻላል። በልላ በኩል የአክሲዮን ማህበሩ የሚጠቅመው ሆኖ ካገኘው የሥራ አስኪያጁ ሥልጣን መገደብና የስራ አሰኪያጁ ሥልጣን ላይ የተደረገውን ገደብ በንግድ መዝገብ ውስጥ በሚጻፈው ቃል እንዱገባለትና እንዱመዘገብለት በግልጽ በሚያቀርበው ማመልከቻ ውስጥ በመግለጽ፣ የስራ አሰኪያጁ ሥልጣን የተገደበ መሆኑ በግልጽ በንግድ መዝገብ በተመዘገበው ቃል ውሰጥ እንዱመዘገብ ካላደረገ በስተቀር በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሉያደርገው እንደማይችል ከንግድ ህጉ አንቀጽ 36 እና አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ (ሰ) ድንጋጌዎች አቀራረጽና ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
በመሆኑም አመልካች የስራ አስኪያጁ ሥልጣን የተቀነሰ ወይም የተገደበ መሆኑን በንግድ መዝገብ በሰፈረው ቃል ወሰጥ ሳያስመዘግብ የድርጅቱን መተዲደሪያ ደንብ ውስጥ የስራ አስኪያጁ ሥልጣን የተቀነሰ መሆኑን በመጥቀስ ያቀረበው ክርክር፣ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 36 ንዐስ አንቀጽ 1 የሥራ አስኪያጁ ሥልጣን ያለው ሰው የአንድ ቅርንጫፍ ሥራ ለማስኬድ ብቻ ሥልጣን በመስጠት ሥልጣኑን የተወሰነ ለማድረግ ይቻላል፤
ስለሆነም እንደዚህ ያለው የስልጣን መቀነስ ማስታወቂያ በንግድ መዝገብ ካልተመዘገበ በስተቀር በዚህ ህግ አንቀጽ 121 መሰረት መቃወሚያ ላሆንባቸው አይችልም በማለት በግልጽ የደነገገውን የሚተላለፍና፣ በተለይም በንግድ ህጉ አንቀጽ 121 ንኡስ አንቀጽ(ሰ) እና የንግድ ህጉ አንቀጽ 36 ንዐስ አንቀጽ 2 ላላው አይነት የስልጣን መቀነስ በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ላሆንባቸው አይችልም።
በማለት ለሶስተኛ ወገኖች በግልጽ የሰጠውን ጥበቃ ያላገናዘበና የሕግ ድጋፍና መሰረት የላለው ነው። ሕግ አውጭው እነዚህን ድንጋጌዎች የደነገገው በግብይት ሂደት ውስጥ ከአመልካች ጋር ውል የሚዋዋለ ሰዎች የድርጅቱን መተዲደሪያ ደንብ መመርመርና ማንበብ እንደማያስፈልጋቸውና ድርጅቱ በንግድ መዝገብ ያስመዘገባቸውን ፍሬ ጉዲዮች ብቻ በማየት ከአመልካችጋር በቅን ልቦና የሚዋዋለ ሶስተኛ ወገኖች ውለታው በህግ ተፈጻሚነት የሚኖረው መሆኑን በማረጋገጥ ከፍ ያለ ጥበቃ ለመስጠት ነው። በአጠቃላይ ከላይ በዘረዘርናቸው ምክንያቶች አመልካች የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣን ሳይኖረው የፈረማቸው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች እኔ በኃላፉነት አልጠየቅም በማለት ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢና የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
3/ ሶስተኛ ጭብጥ አመልካች የሰጠውን የገንዘብ ግዳታ የዋስትና ሰነድ፣ ስለ ዋስትና ውል የተደነገጉትን ፍርማሉቲዎች የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና በኃላፉነት የማያስጠይቅ ነው፣ በማለት ያቀረበውን ክርክር የህግ መሰረት ያለው መሆኑን መመርመር የሚጠይቅ ነው። ይህንን ነጥብ ለመወሰን በመጀመሪያ የአመልካች ሥራ አስኪያጅ ፈርሞ የሰጠው ሰነድ በመሰረታዊ ባህሪውና ይዘቱ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው ወይስ የዋስትና ሰነድ የሚለውን ነጥብ ማየት ይጠይቃል። አመልካች ወጭ አድርጎ ለተጠሪ የሰጠው ሰነድ Financial Guarantee Bond በማለት የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 በእንግሉዝኛ ቋንቋ ግልጽ ያደረገውን በኢንሹራንስ ኩባንያ የሚሰጥ የዋስትና ሰነድ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የሰጠው የገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነደን ሉያሟላው የሚገባውን ፍርም፣ የሰነደን ባሕሪና የሚስከትለውን ውጤት ለመወሰን ሕግ አውጭው ለገንዘብ ዋስትና ሰነድ የሰጠውን የህግ ትርጓሜ መመልከቱ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የዋስትና ሰነድን በተመለከተ ሕግ አውጭው በተለያየ ጊዜ ባወጣቸው የህግ ማዕቀፍች ይዞታቸው ተመሳሳይ የሆኑ ትርጓሜዎችን የተጠቀመ መሆኑን ተገንዝበናል። ዝርዝሩን ስንመለከት፡የዋስትና ሰነድ ማለት የፊይናንስ ቃል ኪዲን ወይም የፊይናንስ ግዳታን ለመፈጸም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ነገር ሲሆን፣ የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፊ ሰነድንና ቦንድን ይጨምራል በማለት በአዋጅ ቁጥር 57/1989 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 18 ትርጉም ሰጥቶታል።
በአዋጅ ቁጥር 57/1989 ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 648/2001 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 20 የዋስትና ሰነድ ማለት የፊይናንስ ቃል ኪዲን ወይም የፊይናንስ ግዳታን ለመፈጸም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ማንኛውም ሰነድ ሲሆን፣ የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፊ ሰነድንና ቦንድን ይጨምራል፣ የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል።
ቦንድ የሚለውን የእንግሉዝኛ ቃል ማገቻ የሚል ፍች የሰጠው አዋጅ ቁጥር 110/1990 ማገቻ የተወሰነ ነገር በመፈጸሙ ወይም ባለመፈጸሙ ምክንያት የሚቀር ሆኖ፣ አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበት ማናቸውም ሰነድ ወይም በምስክር የተረጋገጠ ሆኖ፣ ነገር ግን በትዕዛዝም ሆነ ለአምጭው የማይከፈልበት አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበትን ማናቸውንም ሰነድ ይጨምራል በማለት በአንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2 ትርጓሜ ሰጥቶታል።
የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥረ 24/2004 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 3 የሰጠው ትርጉምና ከላይ በጠቀስናቸው የህግ ማዕቀፍች ሕግ አውጭው ተመሳሳይነት ባላቸው አገላለጾች የሰጣቸውን ትርጓሜ ስንመለከት አመልካች ወጭ አድርጎ የሰጠው ሰነድ በመሰረታዊ ባህሪውም ሆነ ይዘቱ የመድን ውል ወይም የኢንሹራንስ ፕሉሲ መሰረታዊ መስፈርት የሚያሟላ ሆኖ አላገኘነውም።
የኢንሹራንስ ፕሉሲ በመሰረታዊ ባህሪው መድን ገቢው የኢንሹራንስ ሽፊን በተሰጠው ጉዲይ ላይ መብት ወይም ጥቅም (Insurable Interest) ያለው መሆኑን ይጠይቃል። በያዝነው ጉዲይ ከአመልካች አከራካሪውን የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ለማግኘት ከአመልካች ጋር ውል የተዋዋለው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋናው ፍላጎቱ ተጠሪ በብድር የሚሰጠውን ገንዘብ ተበዲሪው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባይከፍለው አመልካች የሚከፍለው መሆኑን በማረጋገጥ የሰጠውን የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ተጠሪ በማየትና ስለ ብድሩ አከፊፈል ከተበዲሪው ውጭ የሆነ አስተማማኝ ዋስትና ያለው መሆኑን በማመንና በማረጋገጥ የብድር ገንዘቡን እንዱለቅለት ማድረግና ገንዘቡን መበደር ነው። ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አመልካች የሰጠውን የዋስትና ሰነድ አስይዞ የብድር ገንዘቡን ከወሰደ በኋላ ተጠሪ የሰጠውን ብድር ገንዘብ የመክፈል ግዳታ ያለበት ባለዕዲ ነው። የተበዲሪው ባለዕዲነት አመልካች በሰጠው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መሰረት ለተጠሪ የብድር ገንዘቡን ከከፈለ በኋላም የሚቀጥልና አመልካች ተጠሪን (አበዲሪውን) በመተካት ሉጠይቀውና ሉከታተለው የሚችለው ነው። የአመልካች ደንበኛ የሆነው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጉዲዩ ዘላቂ ባለዕዲ ከመሆን አልፍ ተጠሪ በብድር የሰጠውን ገንዘብ የመከፈል ጉዲይ ላይ መብት ወይም ጥቅም (Insurable Interest) ያለው ወገን ባልሆነበት ሁኔታ በአመልካችና በግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መካከል የተደረገው ውል የመድን ውል ነው ተጠሪ ደግሞ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ተጠቃሚ ነው ብል ለመደምደም አይቻልም ።
በአንጻሩ አመልካች በሰጠው ሰነድ ከተጠሪ የአጭር ጊዜ የብድር ገንዘብ የወሰደው ግሬስ ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በብድር ውለ በተገለጸው ጊዜ ዕዲውን ካልከፈለ አመልካች እስከ ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የሚደርስ ገንዘብ ለመክፈል በሰነደ ውስጥ ለተገለጸው ጊዜ ብቻ ዋስትና የሰጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
በመሆኑም አመልካች የሰጣቸው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ግሬስ ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከተጠሪ የወሰደውን የብድር ገንዘብ ተበዲሪው ባይከፍል አመልካች እስከ ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ለመክፈል የአንድነትና ያልተነጣጠለ የዋስትና ግዳታ የገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው። ከዚህ አንጻር የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የሰጠው የገንዘብ የዋስትና የግዳታ ሰነድ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ከላይ በዝርዝር የሰጠናቸውን ምክንያቶች ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስሕተት ያለበት ነው።
ከዚሁ ጋር በማያያዝ አመልካች ሰነደ ስለ ዋስትና ውል የተደነገጉትን ፍርማሉቲዎች የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የለውም በማለት ያቀረበውን ክርክር መዝነናል። በመጀመሪያ የዋስትና ሰነደ አመልካች የላላ ሰው ዕዲ ማለትም የግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የብድር ዕዲ ለመክፈል የተሰጠ ሰነድ ነው። ይህም በመሆኑ ሰነደ ስለዋስትና ግዳታ በፍታሐብሓር ሕግ አንቀጽ 1922 የተደነገጉትን መሰረታዊ መስፈርት የሚያሟላ መሆኑ የግድ አስፈላጊ ነው። ሕጉን ሲተረጉሙ ሰነደ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው የሚል የተሳሳተ ድምዲሜ ላይ የደረሱ ቢሆንም አመልካች የሰጠው ሰነድ በፍታሐብሓር ህግ አንቀጽ 1922 ንዐስ አንቀጽ 2 እና ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገጉትን መሰረታዊ ሁኔታዎች የሚያሟላ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ ይዘት ተረድተናል። አመልካች የዋስትና ሰነደ የፍታሐብሓር ሕግ አንቀጽ 1725 ንዐስ አንቀጽ (ሀ) እና የፍታሐብሓር ሕግ አንቀጽ 1727 በተደነገገው መሰረት በተጠሪና በሁለት ምስክሮች አልተፈረመም በማለት ተከራክሯል።
ሆኖም ይህ የአመልካች ክርክር ( Financial Guarantee Bond) እንደ ማንኛውም የዋስትና ውል በተዋዋይ ወገኖች የሚዘጋጅ ሰነድ ሣይሆን የመድን ንግድ ሥራ እንዱሰራ የተፈቀደለት የኢንሹራንስ ኩባንያ በተሰጠው ልዩ ፈቃድ ተጠቅሞ፣ የሚያዘጋጀውና የላላ ሰው ዕዲ ለመክፈል ራሱን ግዳታ ውስጥ የሚያስገባበት የማገቻ ሰነድ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 3 ለገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) የሰጠውን ትርጓሜ ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አላኘነውም። እንደዚሁም አመልካች የሰጠው የማገቻ ሰነድ (Bond) የግድ በምስክሮች መረጋገጥ የላለበት መሆኑን ሕግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 110/1990 በአንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2 ለማገቻ ትርጉም ሲሰጥ “አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበት ማናቸውም ሰነድ ወይም በምስክር የተረጋገጠ ሆኖ ነገር ግን በትዕዛዝም ሆነ ለአምጭው የማይከፈልበት፣ አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበትን ማናቸውንም ሰነድ ይጨምራል” በማለት ከተጠቀመው አገላለጽ እና በወቅቱ ሥራ ላይ የነበረው በአዋጅ ቁጥር 57/1989 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 18 ለዋስትና ሰነድ ከሰጠው ትርጓሜ ለመረዲት ችለናል።
ከዚህ በተጨማሪ የአመልካች ክርክር በአዋጅ ቁጥር 86/1986 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 4 ሥልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ አመልካችና ላልች የኢንሹራስ ኩባንያዎች በማናቸውም ሥያሜ የገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድ (Financial Guarantee Bond) እንዲያወጡ በመመሪያ ከመከልከላቸው በፉት ወጭ ያደረጓቸው የገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድች (Financial Guarantee Bond) የጸኑና ህጋዊ ውጤት ያላቸው መሆኑን ” Financial Guarantee Bond or other unconditional bonds issued by insurance companies and outstanding before the effective date of these directives shall remain enforce until the expiry date or shall be phased out in line with an action plan submitted by each insurance company and agreed with the bank.” በማለት የገለጸውን የመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 3 ድንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ የሚቃረንና የህግ መሰረት የላለው ነው።
ስለሆነም አመልካች ተበዲሪውን ግሬስ ትሬዱንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከተጠሪ የወሰደውን የብድር ገንዘብ ባይከፍል እሱ የሚከፍል መሆኑን በማረጋገጥ የሰጠውን የማገቻ ሰነድ ልዩ ባህሪ ያለውና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚዘጋጅና ወጭ የሚደረግ የማገቻ ሰነድ በመሆኑ አመልካች ሰነደ በሁለት ምስክሮች ስላልተረጋገጠ ሰነደ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
4/ አራተኛው ጭብጥ ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም? የሚል ነው አመልካች የሰጠው ሰነድ የመድን ውል አለመሆኑ ተረጋግጧል። የላላ ሰው ዕዲ ለመክፈል የአንድነት የዋስትና ግዳታ የገባ ሰው የዋናውን ባለዕዲ ግዳታ ነፃ የሚያደርጉ የይርጋና ላልች መከራከሪያዎች በማቅረብ ከኃላፉነት ነፃ እንደሚሆን ከፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1926 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ አቀራረጽ፣ ይዘትና ዓላማ ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በዋሱ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው የይርጋ የጊዜ ገደብ በዋናው ባለዕዲ ላይ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ እንደሆነ፤ በዋናው ባለዕዲ ላይ የተጀመሩ ክሶች ለዋሱ መቆጠር የጀመረለት የይርጋ ዘመን ያቋርጡበታል በማለት ሕግ አውጭው የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1929 የደነገገበትን ምክንያት በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። በአበዲሪው በተጠሪና በተበዲሪው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መካከል የተደረገው ብድር ውል ላይ ተፈጻሚነት ያለው ስለ ውልች በጠቅላላው የሚደነግገው የይርጋ የጊዜ ገደብ ነው። የአመልካች (የዋሱ) ግዳታ ቀሪ የሚሆነው የዋናው ባለዕዲ ግዳታ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት የይርጋ የጊዜ ገደብ ነው። ስለሆነም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የህግ ድንጋጌ በፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1845 የተደነገገው የይርጋ የአስር ዓመት የጊዜ ገደብ ነው። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ንግድ ህግ 674 ንዐስ አንቀጽ 1 እንደሆነ አመልካች ያቀረበውን የይርጋ ክርክር መቀበላቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ቢሆንም በውጤት ደረጃ ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የህግ ድንጋጌ የፍታሐብሓር ህግ አንቀጽ 1845 በመሆኑ አመልካች የይርጋ ክርክር መታለፈ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
5 አምስተኛው ጭብጥ አመልካች ለተጠሪ በሰጠው የገንዘብ የዋስትና የግዳታ ሰነድ መሰረት በኃላፉነት ይጠየቃል ወይም አይጠየቅም? በኃላፉነት ይጠየቃል የሚባል ቢሆን የአመልካች የኃላፉነት መጠን ምን ያህል ነው? የሚለው ነው። አመልካች ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከተጠሪ በብድር የወሰደውን ገንዘብ በብድር ውለ መሰረት ካልከፈለ እስከ ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) የሚደርስ ገንዘብ ለተጠሪ ለመክፈል የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ሰጥቷል። ተበዲሪው ዕዲውን በብድር ውለ መሰረት አለመክፈለ በስር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች ተጠሪ ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላበደረው ብድር የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ የሰጠው ብድር ውለ ከመደረጉ በፉት መሆኑን ገልጾ መጀመሪያውኑ ላልነበረ የብድር ውል የተሰጠ ዋስትና ግዳታ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት የቀረበው ክርክር በፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1925 ንዐስ አንቀጽ 1 ወደፉት ለሚመጣ ወይም በአንድ አይነት ሁኔታ ለሚመጣ ግዳታ ዋስ መሆን ይቻላል በማለት የደነገገውን ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው ነው። አመልካች የሰጠው የዋስትና ግዳታ ሰነድ አመልካች እዲውን በአንድነት ለመክፈል የሚያረጋግጥ መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች ተበዲሪው ግሬስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና ተጠሪ ማጭበርበር ተግባር ፈጽመዋል በማለት ለሰበር በሰጠው የመልስ መልስ ያቀረበው ክርክር ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ መስማት ሥልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ያልተነሳና ያልተጣራ የፍታሐብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329 ንዐስ አንቀጽ 1 የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ይህ ክርክር ለሰበር ችልት በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 80 ንዐስ አንቀጽ 3(ሀ) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 የተሰጠውን ሥልጣን ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች በሰጠው የገንዘብ የዋስትና ሰነድ መሰረት በኃላፉነት ይጠየቃል በማለት የሰጡት ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ ሆኖ አግኝተነዋል።
የአመልካችን የኃላፉነት መጠን በተመለከተ ዕዲን ለመክፈል ዋስ የሆነ ሰው ዕዲው ወለድ የሚያስከፍል እንደሆነ ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በቀር በዋስትናው ውል ውስጥ በተወሰነው ገንዘብ ልክ በወለደም እንደተዋሰ እንደሚቆጠር የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1930 በግልጽ ይደነግጋል። አመልካች የሰጠው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ እስከ ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ድረስ ግዳታ የገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ሰነደ ስለወለድ ተቃራኒ ቃል የላለው መሆኑ ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተገንዝበናል። የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች ለብድሩ ያለበት ዋስትና ግዳታ እስከሰጠበት ብር 3,500,000 (ሶስት ሚሉዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1930፣ የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1924 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1922 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ያደረገና የህግ ስሕተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በበታች በስር ፍርድ ቤት ከታህሳስ 26 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች በህግ የተደነገገውን ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ እንዱከፍል የወሰነው አመልካች በገባው ዋስትና ግዳታ መሰረት ባለመፈጸሙ ምክንያት ኃላፉ ሆኖ በመገኘቱ ነው። በዚህ ጉዲይ ምክንያት ተጠሪ ለዲኝነት የከፈለው ገንዘብና ላልች ወጭዎች አመልካች እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ የፍታሐብሓር ህግ ቁጥር 1931 መሰረት ያደረገ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ከላይ በዝርዘር ባየናቸው ጭብጦች ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ ስላገኘነውና የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የሰጠው ገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው ለይርጋው ክርክር አግባብነት ያለው የንግድ ሕጉ አንቀጽ 674 ንኡስ አንቀጽ 1 ነው በማለት የሰጡት ህግ ትርጉምና ምክንያት መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ቢሆንም በውጤት ደረጃ የደረሱበት መደምደምያ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በእነዚህ ነጥቦች ላይ የሰጡትን የህግ ትርጉምና ምክንያት ብቻ በመለወጥ ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
No topics extracted.