No summary available.
ሰኔ 04 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ያሬድ ሲሳይ ከጠበቃ ግሩም አየለ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- አልግሪን አግሮ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጠበቃ ውቤ ጓዲ ቀረቡ መዝገቡ ያደረው ለውሣኔ ሲሆን ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የማህበር ይፍረስልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፋ/የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረበው ክስ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ማህበሩ የሚፈርስበት በቂና ትክክለኛ ምክንያት የላለ በመሆኑ የቀረበውን ክስ ወድቅ በማድረግ ውሣኔ መስጠቱ እና የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይሄንኑ ውሣኔ በማጽናቱ የተፈጸመው መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች በማመልከቱ የቀረበ ነው።
አመልካች ሐምል 11 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጸፈ ባቀረበው አቤቱታ ተፈጸመ ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት በማንሳት የተከራከረ ሲሆን ፍሬ ሃሣቡ፡- የበታች ፍርድ ቤቶች ማህበሩ አይፈርስም ወደ ሚለው ድምዲሜ የደረሱት ኃ/የተ/የግል ማህበር የተቀመጠውን የማፍረሻ ምክንያት ሳይሆን ስለማህበሮች በጠቅላላው የተመለከተውን በመሆኑ ፣ እንደዚህ ዓይነቱ ማህበር ፍጹም የሆነ መስማማት የሚጠይቅ ሁኖ እያለ እና አለመግባባቱ ፍርድ ቤት በደረሰበት ሁኔታ ብርቱ ጭቅጭቅ የለም በሚል መወሰኑ፣ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ማህበሩን በውክልና ማስተዲደራቸው እና በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 8.11 ስር 3ኛ ወገን ሉወከል የሚችለው በሁለም ጉዲዮች ሳይሆን አስፈላጊ ሁኖ በታየ ጊዜ ብቻ በመሆኑ፣ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ የማያውቅ፣ ኦዱት ተደርጎ የማያውቅ፣ ስራ አስኪያጅ ማህበሩን ሀብት ለግል ጥቅማቸው የሚያውለት ሁኖ እያለ እና ጉዲዮችን በሽምግልና ታይቶ እልባት ማግኘት ባልቻለበት ሁኔታ ማህበሩ ሉፈርስ አይገባም በሚል ውሣኔ መስጠቱ አግባብነት የላለው በመሆኑ ማህበሩ እንዱፈርስ፣ ስራ አስኪያጅ ደግሞ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለባት እንዱባል እና ሂሣብ እንዱጣራ የሚል ነው።
ጉዲዩ ያስቀርባል ተብል ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ታዞ መስከረም 15 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በሰጠው መልስ አንድ ማህበር ሲፈርስ በቂና ህጋዊ ምክንያቶች ሉሟለ የሚገባቸው ስለመሆኑ በጠቅላላውም ሆነ በልዩ የማህበራት ማፍረሻ የንግድ ህግ ድንጋጌዎች ስር ተመልክቶ እያለ ይሄንን ባላሟላ መልኩ የቀረበው ክስ ተቀባይነት ማጣቱ በአግባቡ በመሆኑ፣ ማህበራት ደግሞ ከተቋቋሙበት ዓላማ አኳያ ያለበቂ ምክንያት የሚፈርሱበት አግባብ ባለመኖሩ፣ ድርጅቱም አመልካች እንደሚለው የከሰረ ሳይሆን ስራውን በአግባቡ እያከናወነ ያለ በመሆኑ፣ በድርጅቱ ውስጥም ብርቱ ጭቅጭቅ አለ ለማለት የማይቻል በመሆኑ እና ስራውንም በአግባቡ እያከናወነ ያለ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ማህበሩ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው በሚል ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ፍርድ ቤቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደመረመረውም ጉዲዩ ለዚህ የሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ሲባል ተይዞ የነበረው ጭብጥ አከራካሪው ማህበር አይፈርስም የተባለበትን አግባብ ለመመርመር በሚል በመሆኑ ከዚሁ ቀደም ሲል ተይዞ ከነበረው ጭብጥ አኳያ ታይቶ እልባት ማግኘት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች ማህበሩ እንዱፈርስ የጠየቀበት ምክንያት ስራ አስኪያጁ ከባንክ ቤት ለማህበሩ ስራ መበደር ያለባትን ገንዘብ ያህል ያልተበደረች ስለመሆኑ፣ የማህበሩን ገንዘብ ለግል ጥቅሟ አውላለች፣ ማህበሩም ኪሣራ ላይ ስለመሆኑ ማህበሩን በውክልና ማስተዲደሯ እና አለመግባባት ስለመፈጠሩ በማመላከት እንደሆነ መመልከት ይቻላል። ጉዲዩን የተመለከቱት የበታች ፍርድ ቤቶች ለማህበር መፍረስ ምክንያት ሁነው የቀረቡት ነጥቦች በማስረጃ አልተረጋገጡም፣ ብርቱ ጭቅጭቅ አለ ለማለት የማያስችለ፣ ከስራ አስኪያጅ ጋር አለመግባባት በራሱ ብርቱ ጭቅጭቅ ተብል ማህበርን ሉያፈርስ የሚችል አይደለም በሚል እና የማህበሩን ስራ አስኪያጅነት በውክልና ማስተዲደርን በተመለከተም በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 8/1/ ስር የተፈቀደ በመሆኑ አልተቀበልነውም በሚል ውሣኔ ተሰጥቷል።
ከዚህ ሁለ መረዲት የሚቻለው አመልካች ማህበሩ እንዱፈርስ ያቀረበውን ምክንያት በፍሬ ነገር ረገድ ያላስረዲ ስለመሆኑ ነው። የቀረቡት ምክንያቶች ደግሞ እስካልተረጋገጡ ድረስ ለማህበሩ ማፍረሻ ምክንያት ተደርገው የማይወሰደ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ማህበር ሉፈርስ የሚችለው ደግሞ ከንግድ ህጉ አንቀጽ 217፣ 218 ፣ 511 እና 543 መመልከት እንደሚቻለው በድንጋጌዎች ስር የተመለከቱት በርካታ ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሁነው በቂ እና ህጋዊ ምክንያት እንደዚሁም በአባላት መካከል ብርቱ ጭቅጭቅ መኖር ያለበት ስለመሆኑ ያመለክታል። በዚህ ጉዲይ ግን የቀረበው ብርቱ ጭቅጭቅ ስለመኖሩ መሰረት ያደረገ ክርክር ሲሆን ይሄ ስለመኖሩ ደግሞ ያልተረጋገጠ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ ድምዲሜ ላይ ደርሰዋል።
አመልካች ለማህበሩ ማፍረሻ ምክንያት ነው በማለት ያቀረበውን ነጥብ እስካላስረዲ ድረስ ደግሞ ማህበሩ የሚፈርስበት በቂ ምክንያት የለም ተብል መወሰደ የሚነቀፍበት አግባብ የለም።
ሆኖም ግን አመልካች በማህበሩ የስራ አስኪያጅ አመራር ላይ የስራው በውክልና መተዲደርን ጨምሮ የተለያዩ ቅሬታዎች እንዲለት ግልጽ ነው። አንድ የኃ/የተ/የግል ማህበር ስራው በአግባቡ አልተመራም በሚልበት ወቅት ባለው የማህበሩ መተዲዲሪያ ደንብ ወይም አግባብነት ባላቸው ህጎች እንዱስተካከል መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 37/1/ ስር ፍትሕ የማግኘት መብትን ከሚመለከተው ድንጋጌ መመልከት ይቻላል። የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ማህበሩን በውክልና አስተዲድራለች ወይስ አላስተዲደረችም? ፣ አስተዲድራ ከሆነስ ከማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ አኳያ እና ከላልች አግባብነት ካላቸው ህጎች ጋር ተገናዝቦ መፍትሓ የሚያገኝ ጉዲይ ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ከቀረበው የማህበር ይፍረስልኝ ጉዲይ ጋር በማያያዝ በመተዲደሪያ ደንቡ የተፈቀደ ነው በማለት ማለፍ ለተነሳው ክርክር አግባብነት ያለው ድምዲሜ ባለመሆኑ እና የማህበሩ የስራ አመራር እንዱስተካከል ከሚቀርብ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ላታይ የሚችል ፤ አሁን ከተነሳው ክርክር ጋር የሚታይ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው አካሄድ ሁኖ አልተገኘም በመሆኑም ይሄም ጉዲይ አመልካች የማህበሩ የስራ አመራር አካሄድን በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርብ አብሮ ታይቶ እልባት ሉያገኝ ሚችል ነው ብለናል። ሆኖም በዚህ የማህበር ይፍረስልኝ የክርክር ነጥብ ላይ ማህበሩ የሚፈርስበት በቂ ምክንያት የለም ተብል ውሣኔ መሰጠቱ ከውጤት አኳያ በአግባቡ ነው ከሚባል በስተቀር የሚነቀፍበት አግባብ አላገኘንም።
ባጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች አከራካሪው ማህበር የሚፈርስበት በቂ ምክንያት አልቀረበም በሚል አመልካች ያቀረበውን ክስ ወድቅ ማድረጉ በአግባቡና የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ.ቁ. 110861 ሐምል ዐ8 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝ/ በቀን 3ዐ/9/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካች ያቀረበው ኃ/የተ/የግል ማህበር ይፍረስልኝ ክስ ወድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው ብለናል። ይሄ ውሣኔ አመልካች የማህበሩን የስራ አመራር ጉድለት በተመለከተ እንዱስተካከል በሚል ከመጠየቅ የሚከለክለው አይደለም።
በዚህ ችልት ሐምል 27 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.