No summary available.
መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት- ነ/ፈጅ ናሆም ሸዋንግዛው ቀረቡ ተጠሪ፡- ባላ ገጠር ልማት ድርጅት - ጠበቃ በሻዲ ገመቹ አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አመልካች ሰጠ የተባለው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና (performance Bond) የሚገዛበት የሕግ ክፍልን የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ የመድን ውልን መሰረት ያደረገ ነውና በንግድ ሕግ ቁጥር 674 በይርጋ ቀሪ ሆኗል ሲል የግልግል ጉባኤ በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሣኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩ የሚገዛው በፍትሐ ብሓር በተመለከተው የዋስትና ድንጋጌዎች እንጂ በንግድ ሕጉ በተመለከቱት ባለመሆኑና ይርጋውም የአስር አመት ጊዜ ሁኖ ያላለፈበት ነው ተብል በጉባኤው ውሣኔ መሻሩን በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ቦንድ ለስራ ተቋራጩ የተሰጠው አረቦን /Premium/ ማስከፈል በመሆኑ፣ ይህንን ቦንድ የሰጠው የመድን ድርጅት መሆኑን እና እንደመቼውም የመድን ውልች ኮንትራክተሩ ለሶስተኛ ወገን ጥቅም መድን የገባ መሆኑ ተረጋግጦ እየለ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ሕጋዊ ድጋፍ የላላቸው ምክንያቶች /ትንታኔዎችን/ በመስጠት የግልግል ጉባኤው አብላጫ ድምጽ የሰጠውን ውሣኔ መሻሩ በንግድ ሕግ ቁጥር 654 እና በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቁትን አሰራሮችን የሚፃረር ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች ሰጠ የተባለው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ቦንድ የሚገዛው በንግደ ሕጉ ስለመድን በተመለከቱት ድንጋጌዎች ነው ወይስ በፍትሐ ብሓር ሕጉ ስለ ዋስትና በተመለከቱት ድንጋጌዎች ነው የሚለው ጭብጥ ተይዞ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱያቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በጽሐፍ መልሱን ሰጥቷል።
ተጠሪ ለሰበር ችልት በሰጠው መልስም ተጠሪ ለሚያስራው መንገድ የጨረታ አሸናፉ የሆነው አክሱም ኮንስትራክሽን በኮንስትራክሽን ውለ አንቀጽ 6 መሰረት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና /Performance bond/ ለማቅረብ በገባው ግዳታ መሰረት የአሁን አመልካች ስራ ተቋራጩ ለሚያደርሰው ማናቸውም የውል ቃለ አለመጠበቅ እስከ ብር 1,101,890 ኃላፉነት በመውሰድ ጥቅምት 10 ቀን 1989 ዓ.ም የተፈረመ የመልካም ሥራ ዋስትና ለተጠሪ መስጠቱን፣ ኮንትራክተሩ በውለ የገባውን ግዳታ ባለመውጣቱ በቀረበው ክስ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካች የተሰጠው ሰነድ በፍ/ብ/ሕጉ የተመለከተው ዋስትና ሁኖ በንግድ ሕጉ የሚገዛ የመድን ሽፍን አይደለም በማለት በ10 ዓመት በይርጋ አይታገደም ሲል የጉባኤውን ብይን መሻሩ ሕጋዊ ነው፤ ሰነደ የተፃፈው “surety” ተብል እንጂ “insurer” አለመባለን፣ ሕንፃ ተቋራጩ “contracter” እንጂ “insured” ተብል አለመገለጽን፤ ላልችም በውለ ውስጥ የተጠቀሱት የተዋዋዮች ወገኖች ስያሜ በፍ/ብ/ሕግ የተጠቀሰውን እንጂ በንግድ ሕጉ የተጠቀሰውን “መድን ሰጪ” እና “መድን ተቀባይ” ያልተባለ መሆኑን፣ የግዳታ አቀባበል ባሕርያትም የመድን ውልን የሚመለከት መሆኑን አመልካች በግልጽ “ዋስ” ተብል መግለጽን፤
እንዱሁም ስለ “performace bond” እና “bond” በተለያዩ የሕግ መዝገብ ቃላት እና በመረጃ መረብ የተሰጡትን ትርጓሜዎች እና መሰረት ልማት በሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተዘጋጀ “የሲቪል ስራ ፔሮጀክቶች የውል እስታንዲርድ” አካል በተደረገው ፋዱክ ሰነድ /FIDIC/ የተሰጠውን ትርጉም የሚያሳየው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የደረሰበት ድምዲሜ ተገቢ መሆኑን በመዘርዘር ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል ሲል ተከራክሯል። አመልካች በበኩለ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቅርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ለጭብጡ ምላሽ ለመስጠት ያመች ዘንድም የኮንስትራክሽን ስራ ልዩ ባህሪይን መመልከት የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ሰነድ ወይም (ቦንድ) ትርጉሙን ማየትና የዚህን ሰነድ ዓላማ ከኢንሹራንስ ውል ልዩ ባህርይ አንፃር ማየቱ አግባብነት ያለው ሁኖ ተገኝቷል።
እንደሚታወቀው የኮንስትራክሽን ውል መንገድ፣ ሕንፃ፣ የሃይል ማመንጫ፣ የአውሮፔላን ማረፉያ፣ የባቡር ሐዱድ፣ የውሃና ግድብና ቁፊሮ እና ላልች የሲቪል ምህንድስና ስራዎች ለማስገንባትና ለመገንባት የሚደረግ ውል ሲሆን የውለ አመሰራትና ውጤት በፍትሐ ብሓር ሕግና ላልች አግባብነት ባላቸው ሕጎች የሚገዛ ነው። የኮንስትራክሽን ውል ባሕርይው ሲታይ በተዋዋይ ወገኖች ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን በበርካታ የውል ትስስሮች የተያያዘና ውለን ለመዋዋልም ሆነ ለመፈፀም ብዙ ስራዎችን የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ አፈፃፀሙ ረዘም ያለና ተገቢውን ጊዜ የሚያስፈልገው መሆኑ ይታመናል።
ወደ መልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ሰነድ /ቦንድ/ ትርጉሙንና ዓላማ ስንመጣ ደግሞ ታዋቂው የብላክስ ልው የሕግ መዝገበ ቃላት፡- “Peroformance bond is a bond given by a surety to ensure the timely performance of contract, a third parties agreement to guarantee the completion of construction contract upon the default of the general contractor. Also termed as completion bond, surety bond contract bond.” Suretyship bond a contractual arrangement between the surety, the principal and the oblige where by the surety agrees to protect the oblige if he default in perfoming the principals’’ contractual obligation.” The bond is the instrument which binds the surety” በማለት የሚተረጉመው ሲሆን ከዚህም በቀላለ መረዲት የሚቻለው የመልካም ሥራ አፈፃፀም /ቦንድ/ ሰነድ በውለ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውል ስለመፈፀሙ ለማረጋጥ የሚሰጥ ሰነድ፣ ሶስተኛ ወገን የሆነ አካል ስራ ተቋራጩ የኮንስትራክሽን ውለን ካልፈፀመ ስራው በውል መሰረት እንዱፈፀም የሚሰጠው የዋስትና ሰነድ መሆኑን፣ ቃለም የአፈፃፀም /ማስጠንቀቂያ/ ሰነድ፤
የዋስትና ሰነድ፣ የውል ሰነድ በሚለ ቃላቶች ሉተካ የሚችል መሆኑን፣ የዋስትና ሰነድ ሰጪ ዋስ ተብል የሚጠራ ሶስተኛ ወገን መሆኑን፣ ይህም በባለገንዘብ እና በባለ እዲ መካከል የተደረገን ውል አፈፃፀም ለመጠበቅ የሚገባ ግዳታ መሆኑም፣ እና ዋሱ ግዳታ የገባበት ሰነድ መጠሪያም ቦንድ የሚባል ሰነድ መሆኑ ነው። ከላይ የተመለከተው የሕግ መዝገብ ቃላት የቃለ ፍቺ ስለ መልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ጉዲይ ሁለት ውልች የሚደረጉ መሆኑን እና ሶስት ወገኖች መኖራቸውን ያመልክታል። ይህንን ዓይነት የዋስትና ሰነድ /ቦንድ/ የማውጣት ወይም በመስጠት የሚታወቁት በዋናነት ባንኮች እና መድን ድርጅቶች እንደሆኑም ያመለክታል።
በአገራችን የሕግ ማእቀፍ ውስጥ ያለትን አግባብነት ያላቸውን ሕጏች ስንመለከትም ስለ ቴምብር ቀረጥ አከፊፈል የወጣው አዋጅ ቁጥር 110/1990 አንቀጽ 2/2/ የአማርኛ ቅጂ፡- “ማገቻ” ማለት የተወሰነ ነገር በመፈፀሙ ወይም ባለመፈፀሙ አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚያገባበት ማንኛውም ሰነድን ይጨምራል” በማለት ሲያስቀምጥ የእንግሉዝኛ ቅጂው ደግሞ፡- “Bond includes any instrument…whereby a person obliges him self to pay money to another” በሚል አስቀምጦታል።
በዚህ አዋጅ “ቦንድ ወይም ማገቻ” ሰፊ ያለ ትርጉም የተሰጠው ሲሆን በተግባር የሚታወቁት በርካታ የቦንድ ዓይነቶች እንዲለና እነዚህም በትርጉም ውስጥ ሉሸፈኑ እንደሚችለ ተጠቃሹ አዋጅ ያሳያል። በዚህ መሰረት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና /performance bond/ bid bond ወይም /የጨረታ ሰነድ/ bail bond /የዋስትና ወረቀት/ /Treasury bond/ /የግምጃ ቤት ሰነድ/ የመሳሰለት ትርጉሙ ሉያጠቃልል ይቻላል። እነዚህ ሰነድች የተወሰነ የገንዘብ ነክ ግዳታ መፈጠሩን የሚያመለክቱ የገንዘብ ሰነድች አሉያም እንደ አግባቡ የዋስትና ሰነድች ሆነው ሉያገለግለ የታሰቡ መሆናቸውን ከትርጉማቸው ይዘትና መንፈስ መረዲት ይቻላል። የዋስትና ሰነድ ማለት ለፊይናንስ ቃል ኪዲን ወይም የፊይናንስ ግዳታን ለመፈፀም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ነገር ሲሆን፣ የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፊ ሰነድንና ቦንድን ይጨምራል በማለት በአዋጅ ቁጥር 57/1989 አንቀጽ 2(18) 18 ትርጉም ሰጥቶታል። ይህንኑ አዋጅ ቁጥር 57/1989 ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቀጥር 648/2001 አንቀጽ 2(20) ስር ደግሞ የዋስትና ሰነድ ማለት የፊይናንስ ቃል ኪዲን ወይም የፊይናንስ ግዳታ ለመፈፀም የሚሰጥ ወይም የሚያዝ ማንኛውም ሰነድ ሲሆን፣የግምጃ ቤት ሰነድን፣ የተስፊ ሰነድንና ቦንድን ይጨምራል የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል።
እንግዱህ ከላይ በተጠቀሱት አዋጆች ስለቦንድ ትርጉም የተሰጠ ሲሆን አከራካሪውን ጉዲይ ሉገዙ ይችላለ ተብለው በተከራካሪ ወገኖች ለክርክር መሰረት በሆኑት የፍትሐ ብሓር ሕጉና የንግድ ህጉ ግን በዚህ ረገድ በግልጽ የተቀመጡ ወይም አመልካች የሆኑ ድንጋጌዎች የለም። በአንድ ጉዲይ ቀጥተኛ ተፈጽሚነት ያለው ሕግ ስለአንድ ቃል ግልጽ የሆነ ትርጓሜ ያለማስቀመጡ ከታመነ በስራ ላይ ባለት ሕጎች ውስጥ ያለውን ትርጉም መፈተሽና ለአከራካሪው ቃል ትርጓሜ መስጠት የሚፈቀድ ስለመሆኑ የሕግ አተረጓጉም ደንቦች የሚያሣዩት ነጥብ ነው። በመሆኑም የአመልካች ነገረ ፈጅ ስለአመልካች የስራ አፈፃፀም ትርጉም ለመስጠት የኢንሹራንስ ውለን ከሚገዙ ሕጏች ውጪ ያለትን ላልች ሕጎችን ለውሣኔው መሰረት ማድረግ ተቀባይነት የላለው ነው በማለት የሚያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት የላለው ሁኖ አግኝተናል። ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱት ሕጎችን መሰረት በማድረግም የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና መሰረታዊ ባሕርይ ከኢንሹራንስ ውልና ከዋስትና ውል ማነፃፀሩ ጉዲዩን የሚገዛውን የሕግ ማእቀፍ ለመለየት የሚያስችል ሁኖ አግኝተናል።
በዚህም መሰረት ስለ የመድን /ኢንሹራንስ/ ውል ምንነት እና አፈፃፀሙን ስንመለክት ደግሞ በ1952 ዓ/ም በወጣው የንግድ ሕግ በአንቀጽ 654 እስከ 712 ተደንግጏ እናገኛለን። የመድን ውልች በጽሐፍ ከመደረጋቸውም በላይ “ፕሉሲ” በሚል ልዩ ሰነድ ላይ መደረግ ያለባቸው መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1725(ለ)፣1720፣1727 እና 1719(2) እንዱሁም ከን/ሕ/ቁጥር 657(1) ድንጋጌዎች መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የመድን ውለ የሚፀናው ሲፈረም መሆኑን የተመለከትን ሲሆን በመድን ስራ ትልቁ ነገር ተብል ሉወሰድ የሚችለው የአረቦን ጉዲይ ሲሆን መድን ሰጪዎች በመድን ገቢዎች ላይ ለሚደርሰው አደጋ ካሣ የመክፈል ግዳታ የሚገቡት ከመድን ገቢዎች በአረቦን መልክ ገንዘብ ስለሚሰበሰቡ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
በመድን ውል ከሚታወቁት ነጥቦች መካከል አንደ የመድን ጥቅም /insurable interest/ የሚባለው ሲሆን ይህም ከመድን ሰጪው ካሣ የሚቀበለው ጉዲት በደረሰበት እለት ጉዲት በደረሰበት ንብረት ወይም እቃ ላይ የመድን ጥቅም ያለው ሰው መሆኑን የሚያስገነዝበን ሲሆን የመድን ጥቅም የላለው ሰው ካሣ ለመጠየቅ የሚያስችለው የሕግ መሰረት የለውም። የመድን ጥቅም ያለው ሰው ሲባል እንግዱህ በደረሰው አደጋ ወይም ጉዲት በትክክል የተጎዲ ወይም ሉጎዲ የሚችል ሰው ስለመሆኑ ይታመናል። ጠቅለል ተደርጏ ሲታይ በን/ሕ/ቁጥር 654(1) ስር እንደተመለከተው የኢንሹራንስ ውል ኢንሹራንስ ሰጪ ተብል የሚጠራ ሰው ፔሪሚየም ተከፍልት አንድ አይነት አደጋ ሲደርስ ተጠቃሚ ተብል ለሚጠራ ሰው የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል የሚገባው ግዳታ ሲሆን በንብረት ወይም በሰው ሕይወትና ጤንነት ወይም በልላ መብት ላይ የአደጋው መድረስ የውለን ውጤት ለማስገኘት መሰረታዊ ሁኔታ በመሆኑ የአደጋው አይነት ብዙ በመሆኑ በኢንሹራንስ የሚሸፈነው አደጋ በውለ ላይ የተመለከተው ብቻ ይሆናል። በአንፃሩ የዋስትና ውል የፍ/ብ/ሕጋችን አንቀጽ 1920 እስከ 1951 ተደንግጓል።
እነዚህን የሕግ ድንጋጌዎች በማነፃፀር የዋስትና ውል ልዩ ባህርያትን ስንመለከት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1921 ድንጋጌ የዋስትና ውል በችሮታ ላይ የተመሰረተ ግዳታ መሆኑን፤ እንዱህም ሲባል ዋሱ ዋስ በመሆኑ የሚያገኘው ጥቅም የላለ በመሆኑ አንድ ሰው ባለእዲው ሳይጠይቅ ወይም ሳያውቅ ዋስ መሆን እንደሚችል መመልከቱ ግንኙነቱ የግድ ጥቅም ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን የሚያሣይ ነው። የዋስትና ውል ላላው ልዩ ባሕርይ ውለ ደባል መሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1926(1) ስር እንደተመለከተው አቢይ ግዳታ ሲቀር የዋስትናው ግዳታ አብሮ የሚቀር መሆኑ የተደነገገ በመሆኑ የዋስትና ውል እንዱኖር በዋስትና ሉረጋገጥ የሚልች ግዳታ መኖር አለበት።
እንዱሁም የዋስትና ውል ግልጽና የማያሻማ ግዳታ መሆን እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1922(1) እና (2) ድንጋጌዎች የተቀመጠ ሲሆን ከዚህ ድንጋጌ በስተጀርባ ያለው ምክንያትም ዋስትና አንድ ሰው ራሱ በግል ተጠያቂ ለማይሆንበት ግዳታ ለላላ ሶሰተኛ ወገን ብል የሚሰጠው ማረጋገጫ በመሆኑ ግዳታ ገቢው በግልጽ ተረድቶ ግዳታ ውስጥ እንዱገባ በማድረግ ኃላፉነቱን መሸከም ተገቢ መሆኑ የሚታመን ነው። የዋስትና ውል ግዳታ ከዋናው ግዳታ እኩል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1924(1) ስር የተመለከተ ሲሆን ውለ ለባለ ገንዘቡ ብቻ የሚሰጥ ማረጋገጫ በመሆኑ ውጤት የሚኖረው በተዋዋዮቹ ማለትም በዋሱና በባለ ገንዘቡ መሃል ነው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1922 (3) ስር እንደተመለከተው ላላው የዋስትና ውል ልዩ ባሕርይ የዋስትና ውለ የዋሱን ግዳታ መጠን በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት መሆኑ ሲሆን የዋስትና ገንዘብ መጠን ዋስትና ውል ላይ በግልጽ ካልተቀመጠ ዋስትናው ውጤት የለውም። ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1920 እስከ 1951 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች የዋስትና ውል ማለት ሁለት ሰዎች ባደረጉት የባለገንዘብነትና የባለእዲነት ግዳታ ግንኙነት ውስጥ ከእነዚህ ተዋዋዮች ውጭ የሆነ ላላ ሶስተኛው ባለእዲው እዲውን በመለ ወይም በከፉል ያልከፈለ መሆኑ ከተረጋገጠ ወይም ግዳታውን በውለ በተመለከተው አኳኋን በአግባቡ ያልተወጣ ከሆነ እኔ በባለእዲው ሥፍራና አቋም ሁኜ እዲውን እከፍላለሁ ወይም ግዳታውን እወጣለሁ ሲል ለባለገንዘቡ ማረጋገጫ የሚሰጥበት በሕግ አግባብ መቋቋሙ ከተረጋገጠ ከስተጀርባው ለአፈፃፀሙ የሕግ ጥበቃ የሚያገኝ ውል ነው።
ላላው ከላይ እንደተመለከትነው የዋስትና ግዳታ ሰነድ ብዙ ሰነድችን ሉይዝ የሚችል መሆኑ ከላይ የተመለከተ ሲሆን የገንዘብ ዋስትና ግዳታ (financial Gureantee Bond) የሚጠቅስ ነው። ይህ ሰነድ ምን አይነት የህግ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 በእንግሉዘኛ ቋንቋ ትርጉም የሰጠበት መሆኑን፣ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ፣ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 1ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 ዓ.ም አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ3 “Financial guarantee bond shall mean an obligation undertaken by an insurance company to pay for the lending bank or another creditors or supplier all outstanding claims arising from the non payemt by debtor or debtors” የሚል ትርጓሜ ያለው መሆኑ፣ ይህ ሰነድ በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 1(1) እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 ዓ.ም አንቀጽ 1(3) ለገንዘብ ዋስትና ሰነድ የሰጠው ትርጉምና ከላይ በተጠቀሱት የሕግ ማእቀፍች ሕግ አውጭው የሰጠው ትርጓሜዎች ሲታዩ መሰረታዊ ባህሪውም ሆነ በይዘቱ የመድን ውል ወይም የኢንሹራንስ ፕሉሲ ጋር የማይመሳሰልና መሰረታዊ መስፈርት የሚያሟላ ስላለመሆኑና መገዛት ያለበትም በንግድ ህጉ በተመለከተው የይርጋ ድንጋጌዎች ሳይሆን በፍትሐ ብሓር ሕጉ ዋስትናን በተመለከተ በሚገዙ ሕጏች መሰረት ስለመሆኑ ይህ ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ጉዲይ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በተያዘው ጉዲይ አከራካሪው ነጥብ ሰነደ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ ሳይሆን የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ሰነድ ነው።
በብሓራዊ ባንክ ወጥቶ ተግባራዊ የሆነው ከላይ የተጠቀሰው መመሪያ ስለዚህ ሰነድ የሚሰጠው ትርጉም የለም። መመሪያው ትርጉም የሰጠው ስለገንዘብ ዋስትና ሰነድ ሲሆን ለዚህም “Financial guarantee bond” shall mean a bond payable on demand issued by an insurance company obliging such insurance compamy to pay to a lending bank or another creditor or supplier all outstanding claims arising form non-payment by principal debtor or debtrs; በማለት ከገለፀ በሁዋላ “unconditional bond” shall mean a bond other than financial gurantee bond issued by an insrance company that is payable to the beneficaiary on demand, without any preconditions attached to such payemnt” ሲል ያስቀምጣል። እንዱህ ከሆነ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና የሐረጉ ስያሜ እንዲለ ሲታይ አንድ ሰው አንድን የተለየና የተወሰነ ስራ ለላላ ሰው ለመስራት ግዳታ ከገባ ይኸው ሰው በውለ መሰረት የገባውን ግዳታ መፈፀም የሚችል መሆኑን ለማረጋገጥ ላላው ሰው የሚያቀርበው ውል ነው። በመሆኑም የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ሰነድ ብሓራዊ ባንክ በውለ የተገባው ግዳታ በአግባቡ መከናወን የሚችል በመሆኑን ለማረጋገጥ የሚሰጥ ሰነድ በመሆኑ “uncondtional bond” ተብል በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የሚወድቅ አይደለም።
ከኮንስትራክክሽን ሰዎች ጋር በተያያዘ ተፈጽሚነት አላቸው ከሚባለት ሰነድች መካከል አንደ የ”ፉዱክ” የውል ፍርም ነው። አሰሪ የሆነው ተጠሪና የስራ ተቋራጭ ባደረጉት ውል የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሲቪል ስራዎች ፔሮጀክት ስታንደርድ የውለታቸው አካል እንዱሆን መስማማታቸው በፍሬ ነገረ ደረጃ ተረጋግጧል። በስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴ የሲቪል ስራዎች ፔሮጀክት ስታንዲርድ ደግሞ “The FIDIC form of contract” አካል ነው። ይህ የፋዱክ ውል ፍርሙ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ለኮንስራክሽን ስራው በውለ መሰረት መከናወን ዋስትና የሚሰጥ ሰነድ መሆኑን ያስገነዝባል።
ከላይ እንደተመለከተው የኢንሹራንስ ፕሉሲ አይነተኛ ባህርይ መድን ገቢው የኢንሹራንስ ሽፊን በተሰጠው ጉዲይ ላይ መብት ወይም ጥቅም (insurable interst) ያለው መሆኑን ይጠይቃል።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ከስራ ተቆራጩ ጋራ ባደረገው ውል አከራካሪውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና የግዳታ ሰነድ እንዱቀርብ የፈለገበት አይነተኛ ምክንያት ተጠሪ ለሚሰራው መንገድ የጨረታ አሸናፉ የሆነው አክሱም ኮንስትራክሽን በኮንስትራክሽን ውለ አንቀጽ 6 መሰረት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና /performance bond/ ለማቅርብ በገባው ግዳታ መሰረት የአሁን አመልካች ስራ ተቋራጩ ለሚያደርሰው ማናቸውም የውል ቃል አለመጠበቅ እስከ ብር 1,101,890 ኃላፉነት በመውሰድ ኮንትራክተሩ በውለ የገባውን ግዳታ ባይወጣ በውለ መሰረት ስራው ባለመስራቱ ለሚደርሰው ጉዲት አመልካች የሚከፍለው መሆኑን በማመን ነው።
ተጠሪ የመንገድ ስራውን የሰጠው ተቋራጭ መንገደን በውለ መሰረት ባለመስራት ለተጠሪ ባለእዲ ከመሆን አልፍ አመልካች ለመልካም ስራ አፈፃፀም ለመክፈል በተሰማማው ገንዘብ መከፈል ወይም አለመክፈል ላይ የመድን መብት ወይም ጥቅም (insurable interest) ያለው ወገን አይደለም። በመሆኑም በአመልካችና በአክሱም ኮንስትራክሽን ድርጅት መካከል የተደረገው ውል መድን ውል ነው፣ ተጠሪ ደግሞ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ተጠቃሚ ነው ብል ለመደምደም አይቻልም። በልላ በኩል አመልካች የሰጠው የመልካም ስራ አፈፃፀም ሰነድ ስራ ተቋራጩ በውለ በተመለከተው ጊዜና ሁኔታ የመንገድ ግንባታው ስራውን ካላከናወነ ተጠሪ በመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና ሰነድ የተገለፀውን ገንዘብ ለመክፈል በሰነደ ውስጥ ለተገለፀው ስራ ብቻ ዋስትና የሰጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። በመሆኑም አመልካች የሰጠው የመልካም ሰራ አፈፃፀም ዋስትና የግዳታ ሰነድ ስራ ተቋራጩ ስራውን ባይሰራ አመልካች መጠኑ በሰነደ የተገለፀውን ገንዘብ ለመክፈል የአንድነትና የነጠላ የዋስትና ግዳታ የገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው።
ከዚህም አንፃር አመልካች የሰጠው የመልካም ስራ አፈፃፀም ሰነድ በመሰረታዊ ባሕሪውና ይዘቱ የመድን ውል ሣይሆን ያልተነጣጠለ የዋስትና ግዳታ የገባ መሆኑን የሚያሣይ ሰነድ በመሆኑ ሉገዛ የሚገባው በንግድ ሕጉ በተመለከቱት ድንጋጌዎች ሣይሆን በፍታሐ ብሓር ሕጉ በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት ነው። እንዱህ ከሆነ አመልካች የገባው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ግዳታ ከላይ በዝርዝር በተመለከቱት የፍሬ ነገር እና የሕግ ምክንያቶች የመድን ውል ሳይሆን በፍ/ብ/ሕግ አንቀጽ 1920 እና ተከታዮቹ የሚሸፈን የዋስትና ውል ነው፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1845 ስር የተመለከተው የአስር አመት ይርጋ ጊዜም አላለፈም ተብል የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መጋቢት 30 ቀን 2001 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል
የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ግዳታ የኢንሹራንስ ውል ሳይሆን የዋስትና ውል በመሆኑ የሚገዛው በፍ/ብ/ሕጉ በቁጥር 1921 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ነው ብለናል።
ተጠሪ በአመልካች ላይ የመሰረተው ክስ የአስር ዓመት ጊዜ አላለፈበትም ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ይግባኝ ባይ ዝርዝር የማቅረብ መብት ተጠብቋል።
No topics extracted.