No summary available.
የካቲት 27 ቀን 2004ዓ.ም.
ዳኞች፡- መሥፍን ዕቁበዮናስ አማረ አሞኘ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ (አ.ማ) - አቶ ብርሃኑ ታደሰ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ አቶ አዱሱ ደሬሳ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ለሰበር ችልት የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍትሐብሕር መዝገብ መስከረም 24 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍ/ብሓር ይግባኝ ችልት በይግባኝ መዝገብ መጋቢት 10 ቀን 2000 ዓ.ም.
የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ችልት ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ ለብድር ውል የተሰጠ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የሚያስከትለውን ኃላፉነት የሚመለከት ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ፣ በዚህ ክርክር ተሳታፉ ያልሆነው አቶ መሐመድ አብደላ አንደኛ ተከሳሽ፣ አመልካች ሁለተኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ከሳሽ (ተጠሪ) ለሥር ፍ/ቤት ታህሳስ 7 ቀን 1997 ዓ/ም ባቀረበው የክስ ማመልከቻ፤ ሁለተኛ ተከሳሽ (አመልካች) ደንበኛ አንደኛ ተከሳሽ አቶ መሐመድ አብደላ፤ ከከሳሽ ድርጅት የወሰደውንና መጠኑ ብር 1,930,066.61 (አንድ ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺህ ስድሳ ስድስት ብር ከስድሳ ሳንቲም) የብድር ገንዘብ አልከፈለም። ሁለተኛ ተከሳሽ አንደኛ ተከሳሽ በብድር የወስደውን ገንዘብ የማይከፍል ከሆነ እሱ እስከ ብር 1,600,000 (አንድ ሚሉዮን ሥድስት መቶ ሺህ ብር) የሚከፍል መሆኑን በቁጥር YO/BOF/0478/00 በማረጋገጥ ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና የግዳታ ሰነድ ሰጥቶኛል። አንደኛ ተከሳሽ እዲውን በብድር ውለ መሰረት አልከፈለም።
ሁለተኛ ተከሳሽ በሰጠው የዋስትና ግዳታ መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ያልከፈለውን ብድር ዕዲ እንዱከፍለኝ ብጠይቀው ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ሁለተኛ ተከሳሽ ለብድሩ አከፊፈል በሰጠው ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና ግዳታ መሰረት አንደኛው ተከሳሽ ያልከፈለውን የብድር ገንዘብ ዕዲው ተከፍል እስከሚለቅ ድረስ ከሚታሰብ 13.5 ፏርሰንት ወለድና በዚህ ክስ ምክንያት ተከሳሽ ያወጣውን ወጪ ጨምሮ ተከሳሽ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ከሳሽ ክሱን ያስረደልኛል የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎችና የማስረጃ ዝርዝር መግለጫ ከክሱ ጋር በማያያዝ ያቀረበ መሆኑን የሥር ፍ/ቤት በውሳኔው አስፍሯል።
ሁለተኛ ተከሳሽ (አመልካች) መቃወሚያና መከላከያ መልስ ለሥር ፍ/ቤት አቅርቧል። ሁለተኛ ተከሳሽ የተቋቋመው ለንብረት፣ ለሰው አካልና ህይወት፣ ለኃላፉነት የመድን ዋስትና ለመስጠት ነው። የተከሳሽ ባለ አክሲዮኖችና የአስተዲደር ቦርደ በማያውቁት ሁኔታ ከመድን ሥራ ውጭ ተበዲሪውን ዕዲ ለመክፈል የተሰጠው ዋስትና ግዳታ ሰነድ ከሁለተኛ ተከሳሽ መመስረቻ ጽሁፍ መተዲደሪያ ደንብ፣ ስለ መድን ሥራ ፈቃድ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 86/1986 እና በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ከተደነገገው ውጭና ሁለተኛ ተከሳሽ ከተቋቋመበት መሰረታዊ ዓላማ ውጭ የሆነ ተግባር ነው። ሁለተኛ ተከሳሽ ተራ የመድን ሽፊን ሰጭ የኢንሹራንስ ድርጅት ነው። የገንዘብ ዋስትና ሰነድ በተለይም ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚከፈል የዋስትና ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተቋቋመ ልዩ የዋስትና ኩባንያ የሚሰጥ እንጂ በተራ መድን ድርጅት ሚሰጥ የዋስትና ሰነድ አይደለም።
ከሳሽ ይህንን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የፈጸመው ተግባር ህገወጥ ነው። ስለሆነም ከሳሽ ላቀረበው ክስ ሁለተኛ ተከሳሽ በኃላፉነት የሚጠየቅበት ከውል ወይም ከህግ የመነጨ ኃላፉነት የላለበት በመሆኑ ከሳሽ ሁለተኛ ተከሳሽን የሚከስበት ምክንያት የለም።
የሁለተኛ ተከሳሽ ዋና ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ እንድፈርም ልዩና ግልጽ የሆነ ሥልጣን አልተሰጠውም። ከሳሽ ሥልጣን የላለው መሆኑን እያወቀ ዋና ስራ አስኪያጁ የፈረመውን የገንዘብ ዋስትና ሰነድ በመቀበል የፈጸመው ተግባር ከጅምሩ ሕጋዊ ውጤት የላለውና ፍርስ በመሆኑ ከሳሽ ተከሳሽን የሚከስበት ምክንያት የለም። በኢንሹራንስ ውል ምክንያት የሚቀርብ ማንኛውም ክስ ሉጠየቅ የሚችለው ጉዲቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ መሆኑ በንግድ ህጉ አንቀጽ 674 ንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። ከሳሽ ክሱን ያቀረበው ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል። የሁለተኛ ተከሳሽ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለከሳሽ ዋስትና ሰነድ ሰጥቷል የሚባል ቢሆን የዋስትና ሰነደ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1725(ሀ) እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1727(ለ) በሚደነግጉት መሰረት በሁለት ምስክሮች ያልተፈረመ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና ፈራሽ ነው። ከሳሽ አንደኛ ተከሳሽ በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ተበድሮ የወሰደ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም። ከሳሽ ተበዲሪው አንደኛ ተከሳሽ ምን ያህል እንደከፈለና ምን ያህል ዕዲ እንደሚፈለግበት የሑሳብ መግለጫ አላቀረበም። የከሳሽ ክስ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል።
የከፍተኛ ፍ/ቤት አንደኛ ተከሳሽ ዕዲውን ያልካደ በመሆኑ የብድር ገንዘቡን የመክፈል ኃላፉነት አለበት። ሁለተኛ ተከሳሽ ከወሰደው የብድር ገንዘብ እስከ ብር 1,600,000 (አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ለመክፈል የዋስትና ሰነድ ሰጥቷል። ሁለተኛ ተከሳሽ ዋስትና ሰነደ ከመጀመሪያው ፈራሽና በህግ ፉት ውጤት የላለው ነው በማለት ያነሳቸው ክርክሮች የህግ ድጋፍ የላቸውም። ከሳሽ ሁለተኛ ተከሳሽ በሰጠው የዋስትና ግዳታ ሰነድ መሰረት ገንዘቡን እንዱከፍለው መጋቢት 30 ቀን 1994 ዓ/ም እና ጥቅምት 8 ቀን 1995 ዓ.ም. ማስጠንቀቂያ የሰጠ መሆኑን ስላስረዲ ክሱ በይርጋ ቀሪ አይሆንም። የወለድ መጠኑም በብሄራዊ ባንክ የወጣውን የወለድ ተመን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ሁለተኛው ተከሳሽ ያቀረበው ክርክር ተገቢ አይደለም። ሁለተኛ ተከሳሽ አንደኛ ተከሳሽ ከከሳሽ ወስድ ካልከፈለውና ክስ ከቀረበበት የብድር ገንዘብ ውስጥ ብር 1,600000 (አንድ ሚሉዮን ሥድስት መቶ ሺህ ብር) የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍታብሄር ይግባኝ ችልት አቅርቧል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍታብሄር ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
አመልካች ለዚህ ችልት የሰበር አቤቱታ ያቀረበው የከፍተኛው ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ነው። አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረባቸውን መከራከሪያዎች በሰበር አቤቱታው በመዘርዘር አቅርቧል። መጋቢት 27 ቀን 2000 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር ማመልከቻ አመልካች የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መስጠት በአመልካች መመስረቻ ጽሁፍ፣ በመተዲደሪያ ደንቡ፣ ስለ መድን ንግድ ሥራ ፈቃድ በወጣው አዋጅ ቁጥር 86/1986 ድንጋጌዎች ከተፈቀደው ውጭ የሆነ ተግባር ነው።
አመልካች ለተጠሪ የሰጠው የዋስትና ሰነድ ህገ ወጥና ምንም አይነት ተጠያቂነት እንደማያስከትል በመዘርዘር ያቀረብኩትን ክርክር የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት በማለፍ መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። የአመልካች ዋና ስራ አስኪያጅ በድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብና በንግድ ህግ ቁጥር 363 ንዐስ አንቀጽ 1 የተዘረዘሩትን የአስተዲደር ተግባራትን ከማከናወን ውጭ ላልች ልዩ ተግባራትን ማከናወን እንደማይችል ተመልክቷል።
የአመልካች ዋና ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ እንዱፈርም በንግድ ህግ አንቀጽ 348 ንዐስ አንቀጽ 3 ልዩና ግልጽ የሆነ ሥልጣን አልተሰጠውም። የድርጅቱ ማኔጂንግ ዲይሬክተር የሰጠው የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የዋስትና ውል፣ መያዥያ ውል የመዋዋል ሥልጣን የላለው በመሆኑ ውለ ከጅምሩ ህጋዊ ውጤት የላለውና ፍርስ ነው።
የስር ፍ/ቤት አመልካች የሰጠው የዋስትና ሰነድ ነው በማለት በተመሳሳይ ጉዲይ ላልች ችልቶች የኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው በማለት ከሰጡት የህግ ትርጉም የተለየ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የዋስትና ሰነደ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ነው የሚባል ከሆነ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን የሁለት ዓመት የይርጋ መከራከሪያ ውድቅ ማድረጉ የህግ ስህተት ያለበት ነው። በአመልካች የተሰጠው የዋስትና ሰነድ በህግ የተደነገገውን ፍርም የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና ፈራሽ ነው በማለት ያቀረብኩትን ክርክር ህጉን በተሳሳተ መንገድ በመተርጏም የታለፈ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሉታረም ይገባዋል። አመልካች የዋስትና ሰነደን የሰጠው በተጠሪና ብድሩን በወሰደው በስር ፍ/ቤት አንደኛ ተከሳሽ የነበረው መሐመድ በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ተበድሮ ከመውሰደ በፉት ነው። በአመልካችና በተበዲሪው መካከል የብድር ውል ከመፈረሙ በፉት የወጣ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ህጋዊ ውጤት የሚኖረውና አመልካችን የሚያስገድድ አይደለም በማለት ያቀረብኩት ክርክር መታለፈ መሰረታዊ ህግ ስህተት ያለበት ነው። የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጡት ውሳኔ ከላይ የዘረዘርናቸው ተደራራቢ መሰረታዊ የህግ ስህተቶች የተፈጸሙበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱሻርልኝ በማለት አመልክቷል።
አመልካች መጋቢት 27 ቀን 2000 ዓ/ም ጽፍ ላቀረበው የሰበር ማመልከቻ ተጠሪ ጥር 15 ቀን 2001 ዓ/ም ጽፍ ባቀረበው መልስ የአመልካች መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 4 አመልካች የተቋቋመው ከላልች ስራዎች በተጨማሪ አጠቃላይ መድን ሥራና የረዥም ጊዜ መድን ዋስትና ለመስጠት እንደሆነ ይገለጻል። አመልካች በህግ ያልተከለከለ ሁለንም የመድን ስራዎች ለመስራት ይቻላል። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ኢንሹራንስ ድርጅቶች ስለሚሰሩት አጠቃላይ የመድን ስራና የረዥም ጊዜ የመድን ዋስትና ሪፕርት የሚያደርጉበትን ለመወሰን ባወጣው መመሪያ የገንዘብ ዕዲ ለመክፈል የሚሰጥ ዋስትና በጠቅላላ የመድን ስራ ዘርፍ ውስጥ ከሚካተቱት ተግባራት አንደኛው እንደሆነ ይገለፃል። ለገንዘብ ዕዲ የሚሰጥ ዋስትና አንደ የመድን አገልግልት መሆኑ ለጽንሰ ሀሳቡ በህግ መዝገበ ቃላት የተሰጠው ትርጉም ያሳያል።
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 23/2000 እና 24/2004 ለገንዘብ ዕዲ የሚሰጥ ዋስትና በመድን ድርጅቶች የሚሰራ ተግባር እንደነበር በመግለጽ ትርጉም ሰጥቶበታል።
የአመልካች ድርጅት መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 4(3) አመልካች የተቋቋመው በአጠቃላይ የመድን ሥራና የረዥም ጊዜ መድን ዋስትና ከመስጠት በተጨማሪ ለኢንቨስትመንት አመች በሆኑ ላልች ሥራዎችን መስራትና እነዚህን የንግድ ዓላማ ለመተግበር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያግዝ ማንኛውንም የንግድ ሥራ እንደሚሰራ የሚያረጋግጥ በመሆኑ አመልካች የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መስጠት ይችላል። አመልካች ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ያቀረቡትን መከራከሪያ የስር ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው። ተጠሪ አመልካች የሰጠውን የብድር ክፍያ የዋስትና ግዳታ ሰነድ የኢንሹራንስ ፕሉሲ ወይም የሚተላለፈ ገንዘብ ሰነድ ነው በማለት ክስ አላቀረበም። ስለዚህ የይርጋው ጊዜ የሚታሰበው በፍታብሄር ህግ ቁጥር 1845 በተደነገገው መሰረት በመሆኑ ክሱ በይርጋ አይታደግም። አመልካች የዋስትና ሰነደ በህግ የተደነገገውን ፍርም የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለው ነው ያለው አግባብነት የለውም። የዋስትና ሰነደ በፍታብሄር ህግ ቁጥር 1922፣ በፍታብሄር ህግ ቁጥር 1925 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 1725 የተደነገገውን ፍርም ያሟላል አመልካች የዋስትና ሰነደን የሰጠው በተጠሪና ብድሩን በወሰደው በስር አንደኛ ተከሳሽ በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ተበድሮ ከመውሰደ በፉት ስለሆነ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም።
የአመልካች ዋና ስራ አስኪያጅ የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የመፈረም ሥልጣን አለው። የአመልካች ዋና ስራ አስኪያጅ በንግድ ህጉ አንቀጽ 33 እና አንቀጽ 35 የገንዘብ ዋስትና ሰነድ የመስጠት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ የሚደነግጉ በመሆኑ የአመልካች ክርክር የህግ ድጋፍ የለውም።
የአመልካች ስራ አስኪያጅ የዋስትና ሰነድ የመፈረም ሥልጣን የለውም የሚባል ቢሆን፣ አመልካች የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1808 ንዐስ አንቀጽ 2 በሚደነግገው መሰረት በሁለት ዓመት የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ያላቀረበ በመሆኑ በሰበር ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ለውም።
በአጠቃላይ አመልካች በስር ፍ/ቤት መከራከሪያ አድርጎ ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው። ስለሆነም የሰበር ችልት የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት እንዱያሰናብተኝ በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በሰበር አቤቱታው ያነሳቸውን ነጥቦች በማጠናከርና ጥር 22 ቀን 2001 ዓ.ም የተፃፈ አምስት ገጽ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ በሰበር ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው በዚህ መዝገብ ግራ ቀኙ የሚከራከሩባቸው ጉዲዮች ይህ ሰበር ችልት በሰበር መ.ቁ.40187 አስገዲጅ የህግ ትርጉም የሰጠባቸው ናቸው።
በዚህ መዝገብ አመልካችና ተጠሪ ያቀረቧቸው ክርክሮች ውሳኔ ሉያገኙ የሚገባቸው የህግ ጭብጦች የሚከተለት ናቸው።
አመልካች የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መስጠቱ አመልካቹ የኢንሹራንስ ኩባንያ ከተፈቀደለት፣ ከተቋቋመበትና ህጋዊ ህልውና አግኝቶ ከተመዘገበበት የንግድ ዓላማ ውጭ የተፈፀመ ተግባር በመሆኑ፣ በህግ ተጠያቂ ልሆን አይገባኝም በማለት ያቀረበው ክርክር፣ የህግ መሰረት አለው ወይስ የለውም?
አመልካች የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ የዋስትና ሰነድ ለማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው ፈርሞ የሰጠውን የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ በመቀበል ተጠሪ ለፈጸመው ተግባር ህጋዊ ተጠያቂነት የለብንም፣ በማለት አመልካች ያቀረበው ክርክር መታለፈ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
አመልካች ለተጠሪ የተሰጠው የገንዘብ ግዳታ የዋስትና ሰነድ፣ ስለ ዋስትና ውል የተደነገጉትን ፍርማሉቲዎች የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና በኃለፉነት የማያስጠይቅ ነው፣ በማለት ያቀረበው ክርክር መታለፈ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም?
አመልካች ለተጠሪ በሰጠው የገንዘብ የዋስትና የግዳታ ሰነድ መሰረት በኃላፉነት ይጠየቃል ወይስ አይጠይቅም? አመልካች በኃላፉነት ይጠይቃል የሚባል ቢሆን የአመልካች የኃላፉነት መጠን ምን ያህል ነው? የሚለት ናቸው።
1/ የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ ይህ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ የሰጠው ሰፉ ትንታኔ በዚህ መዝገብ አመልካችና ተጠሪ ላቀረቡት ክርክር ገዥነት ያለው ነው።
ለጉዲዩ አግባብነት ያለው አዋጅ ቁጥር 86/86 የመድን ንግድ ሥራ ዓይነቶች የሚላቸው ሕግ አውጭው በአዋጁ ትርጉም የሰጣቸውን ጠቅላላ የመድን ንግድ ሥራ፣ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ መድን ንግድ ሥራ፣ የኢንሹራንስ ፕሉሲ(ፕሉሲ)፣ አብይ የመድን ንግድ ሥራ፣ ህይወት መድንና የጠለፊ መድን ሥራዎችን ብቻ እንዲልሆነ « መድን ንግድ ሥራ ዓይነቶች ወይም የንግድ ሥራ ዓይነት ወይም ላልች ሥያሜዎች ባንኩ በዚህ አዋጅ በሚያወጣው መመሪያ የሚደነገግ ትርጉም ይኖራቸዋል» በማለት በአንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 4 በግልጽ ደንግጓል።
ይህ ድንጋጌ አዋጁ ሲወጣ ትርጉም ያልተሰጣቸውና ያልተገለጹ አዋጁ ተግባራዊ በሚሆንበት ሂደት በተቆጣጣሪው የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ትርጉም የሚሰጣቸውና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንዱፈጽሟቸው የሚፈቀደ መድን ንግድ ስራ ዓይነቶች ሉኖሩ እንደሚችለና የንግድ ሥራዎቹም በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ትርጉም የሚሰጣቸው መሆኑን ይደነግጋል። ድንጋጌው የመድን ንግድ ሥራ እንዱሰራ በኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው የኢንሹራንስ ኩባንያ፣ በአዋጁ የተተረጎሙና የተገለጹትን የመድን ንግድ ሥራዎች ብቻ ሳይሆን ላልች በብሓራዊ ባንክ ትርጉም የሚሰጣቸውን፣ የሚገለጹትና የሚፈቀደለትን የመድን ንግድ ሥራ ዓይነቶች ለመስራት እንደሚችል የሚደነግግ ነው።
አከራካሪው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) ምን ዓይነት የህግ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ በመመሪያ ቁጥር 23 /2002 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 በእንግሉዘኛ ቋንቋ ትርጉም ሰጥቶታል። የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ማለት በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 3 " Financial gurantee bond shall mean an obligation undertaken by an insurance company to pay for the lending bank or another creditors or supplier all outstanding claims arising from the non payment by debtor or debtors" የሚል ትርጓሜ ሰጥቶታል። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ እንደ አውሮፒውያን አቆጣጠር 2002 እና 2004 ዓ/ም ባወጣው መመሪያ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) የማውጣት ተግባር እንዲይፈጽሙ ከልክሎል። የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) የማውጣት ተግባር እንዲይፈጽሙ በግልፅ የተከለከለ መሆኑን የደነገገው በመመሪያ ቁጥር 23 /2002 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥር 24/ 2004 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 1 ነው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ብሓራዊ ባንክ መድን ንግድ ስራ የሚሰሩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) እንዲይሰጡ በመመሪያ በግልጽ ከመከልከለ በፉት በኢንሹራንስ ኩባንያዎች የተሰጡ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች የሚኖራቸውን ህጋዊ ውጤት ባወጣው መመሪያ ግልጽ አድርጓል። በኢትጵያ ብሓራዊ ባንክ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 እና በመመሪያ ቁጥር 24/2004 ከመከልከላቸው በፉት በኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ የተሰጡ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች የፀኑና ሕጋዊ ውጤት ያላቸው መሆኑን በመመሪያ ቁጥር 24/ 2004 አንቀጽ 3 በግልጽ ደንግጓል። በልላ አነጋገር አመልካችና ላልች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 23 /2002 እና መመሪያ ቁጥር 24 /2004 በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) እንዲይሰጡ ከመከልከላቸው በፉት፣ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ የመስጠት ሥራን እንደ አንድ የመድን ንግድ ሥራ አይነት ሲያከናውኑት የኖሩት ተግባር እንደነበርና ይህም ተግባራቸው ህጋዊ ውጤት ያለውና ኃላፉነት የሚያስከትል መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 86/86 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 4 ድንጋጌና የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ ቁጥር 4/ 2004 አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች በጣምራ በማንበብ ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ በተጨማሪ የኢትጵያ ብሓራዊ ባንክ በመጀመሪያ መመሪያ ቁጥር 23 /2002/ በማውጣት፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) እንዲይሰጡ የከለከላቸው፣ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ መስጠት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከተቋቋሙበት መድን የንግድ ዓላማ ውጭ የሆነ ስራ ነው በማለት አይደለም። በኢትጵያ ብሓራዊ ባንክ የተደረገው ክልከላ መነሻ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የላላውን ሰው ዕዲ ለመክፈል የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ሲሰጡ ተበዲሪው ብድሩን ባለመክፈለ ምክንያት በገቡት የዋስትና ግዳታ መሰረት ለባለመብቱ (አበዲሪው) የከፈለትን ገንዘብ ከባለዕዲው ለማስመለስ የሚያስችላቸው በቂ መያዥያ ሚሆን የተበዲሪው ንብረት ወይም ገንዘብ የማይዙ ወይም የማያገኙ በመሆኑና በአገሪቱ አስተማማኝ የሆነ የጠለፊ መድን ዋስትና የላለ በመሆኑ ምክንያት፣ በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ ለመከላከል በማሰብ መሆኑን በመመሪያው መግቢያ ላይ በግልጽ አስፍሮታል።
ከላይ በዝርዝር በተገለጹት ምክንያቶች አመልካች የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ግልጽ መመሪያ በማውጣት፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ስያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) እንዲይሰጡ ከመከልከለ በፉት ወጭ አድርጎ ለተጠሪ የሰጠ መሆኑ ተረጋግጧል። አመልካች የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች (Finanicial Gurantee Bonds) መስጠት ከተቋቋምኩበት የንግድ ዓለማ ውጭ የተፈጸሙ ተግባር በመሆኑ ሕጋዊ ውጤት የላለውና አመልካችን በኃላፉነት ሉያስጠይቅ የማይችል ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ ግልጽ መመሪያ አውጥቶ ከመከልከለ በፉት ለተጠሪ የሰጣቸው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች (Finanicial Gurantee Bonds) ፣አመልካች እንዱሰራ ከተፈቀደለት መድን ንግድ ሥራና ከተቋቋመበት የንግድ ዓላማ ውጭ የተሰጠ ሰነድ በመሆኑ ሕጋዊ ውጤት የለውም በማለት ያቀረበውን ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
2/ ሁለተኛው ጭብጥ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድቹ ወጭ በሆኑበት ወቅት የአመልካች ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረውን ሥልጣን የሚመለከት ነው። የስራ አስኪያጁ ሥልጣን የተገደበ መሆኑን በማንሳት ተከራክሯል። አመልካች የዋና ስራ አስኪያጁን ስልጣን መገደብና የስራ አስኪያጁ ስልጣን ላይ የተደረገውን ገደብ በንግድ መዝገብ ውስጥ በሚጻፈው ቃል እንድገባለትና እንድመዘግብለት በግልጽ ባቀረበው ማመልከቻ ውስጥ በመግለጽ፣ የስራ አስኪያጁ ሥልጣን የተገደበ መሆኑ በግልጽ በንግድ መዝገብ በተመዘገበው ቃል ውስጥ እንዱመዘገብ ካላደረገ በስተቀር የህንን መከራከሪያ በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሉያደርገው አይችልም። ይህንንም ከንግድ ሁጉ አንቀጽ 36 አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ (ሰ) ድንጋጌዎች አቀራረጽና ይዘት ለመረዲት ይቻላል። በመሆኑም አመልካች የስራ አስኪያጁ ሥልጣን የተቀነሰ ወይም የተገደበ መሆኑን በንግድ መዝገብ በሰፈረው ቃል ውስጥ አለማስመዝገቡ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል።
አመልካች በድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብ ውስጥ የስራ አስኪያጁ ሥልጣን የተቀነሰ መሆኑ እንደተገለጸ በመጥቀስ ተከራክሯል። ሆኖም ይህ የአመልካች ክርክር የንግድ ሕጉ በአንቀጽ 36 ንዐስ አንቀጽ 1 ስራ አስኪሃጅነት ሥልጣን ያለው ሰው አንድ ቅርንጫፍ ሥራ ለማስኬድ ብቻ ሥልጣን በመስጠት ስልጣኑን የተወሰነ ለማድረግ ይቻላል፣ ስለሆነም እንደዚህ ያለው የስልጣን መቀነስ ማስታወቂያ በንግድ መዝገብ ካልተመዘገበ በስተቀር በዚህ ህግ አንቀጽ 121 መሰረት መቃወሚያ ላሆንባቸው አይችልም በማለት በግልፅ የደነገገውን ያላገናዘበ ነው። በተለይም የአመልካች ክርክር በግኝት ህጉ አንቀጽ 121 ንዐስ አንቀጽ (ሰ) እና የንግድ ህጉ በአንቀጽ 36 ንዐስ አንቀጽ 2 ላላው አይነት የስልጣን መቀነስ በሶስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ላሆንባቸው አይችልም በማለት ለሶስተኛ ወገኖች በግልጽ የሰጠውን ጥበቃ ያላገናዘበና የህግ ድጋፍና መሰረት የላለው ነው። ሕግ አውጭው እነዚህን ድንጋጌዎች የደነገገው በግብይት ሂደት ውስጥ አክሲዮን ማህበሩ ጋር ውል የሚዋዋለ ሰዎች የድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብ መመርመርና ማንበብ እንደሚያስፈልጋቸውና ድርጅቱ በንግድ መዝገብ ያስገነዘባቸውን ፍሬ ጉዲዮች ብቻ በማየት ከአመልካች ጋር በቅን ልቦናው የሚዋዋለ ሶስተኛ ወገኖች ውለታው በህግ ተፈጻሚነት የሚኖረው መሆኑን በማረጋገጥ ከፍተኛ ጥበቃ ለመስጠት ነው። በአጠቃላይ ከላይ በዘረዘርናቸው ምክንያቶች አመልካች ዋና ሥራ አስኪያጁ ስልጣን ሳይኖረው ለፈረማቸው የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድች በኃላፉነት አልጠየቅም በማለት ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍ/ቤትና በይግባኝ ሰሚው ችልት ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢና የህግ ሥህተት ያልተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
3/ ሶስተኛ ጭብጥ አመልካች ለተጠሪ የተሰጠውን የገንዘብ ግዳታ የዋስትና ሰነድ፣ ስለ ዋስትና ውል የተደነገጉትን ፍርማሉቲዎች የማያሟላ በመሆኑ በህግ ፉት ውጤት የላለውና በኃላፉነት የማያስጠይቅ ነው፣ በማለት ያቀረበውን ክርክር የህግ መሰረት ያለው መሆኑን መመርመር የሚጠይቅ ነው። በመጀመሪያ የዋስትና ሰነደ አመልካች ለላላ ሰው ዕዲ ማለትም የአቶ መሐመድ አብደላ የብድር ዕዲ ለመክፈል የተሰጠ ሰነድ ነው። ይህም በመሆኑ ሰነደ ስለዋስትና ግዳታ በፍታብሄር ህግ አንቀጽ 1922 የተደነገጉትን መሰረታዊ መስፈርት የሚያሟላ መሆኑ የግድ አስፈላጊ ነው። አመልካች የሰጠው የዋስትና ሰነድ መሆኑንና በፍታብሄር ህግ አንቀጽ 1922 ንዐስ አንቀጽ 2 እና ንዐስ አንቀጽ 3 የተደነገጉትን መሰረታዊ ሁኔታዎች የሚያሟለ መሆኑን በስር ፍ/ቤት አረጋግጧል። አመልካች የዋስትና ሰነደ የፍታብሓር ሕግ አንቀጽ 1725 ንዐስ አንቀጽ (ሀ) የፍታብሄር ሕግ አንቀጽ 1727 በተደነገገው መሰረት በተጠሪና በሁለት ምስክሮች አልተፈረመም በማለት ተከራክሯል። ሆኖም ይህ የአመልካች ክርክር (Finanicial Gurantee Bond) እንደማንኛውም የዋስትና ውል በተዋዋይ ወገኖች የሚዘጋጅ ሰነድ ሣይሆን የመድን ንግድ ሥራ እንዱሰራ የተፈቀደለት የኢንሹራንስ ኩባንያ በተሰጠው ልዩ ፈቃድ ተጠቅሞ፣ የሚዘጋጀውና የላላ ሰው ዕዲ ለመክፈል ራሱን ግዳታ ውስጥ የሚያስገባበት የማገቻ ሰነድ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ በመመሪያ ቁጥር 23/2002 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 1 እና በመመሪያ ቁጥር 24/ 2004 አንቀጽ 1 ንዐስ አንቀጽ 3 ለገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) የተሰጠውን ትርጓሜ ግንዘቤ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ አላገኘነውም።
እንደዚሁም አመልካች የሰጠው የማገቻ ሰነድ (Bond) የግድ በምስክሮች መረጋገጥ የላለበት መሆኑን ሕግ አውጭው በአዋጅ ቁጥር 110/1990 በአንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 2 ለማገቻ ትርጉም ሲሰጥ "አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበት ማናቸውም ሰነድ ወይም በምስክር የተረጋገጠ ሆኖ ነገር ግን በትዕዛዝም ሆነ ለአምጭው የማይከፈልበት፣ አንድ ሰው ለላላው ገንዘብ ለመክፈል ግዳታ የሚገባበትን ማናቸውንም ሰነድ ይጨምራል" በማለት ከተጠቀመው አገላለጽና በወቅቱ ሥራ ላይ የነበረው በአዋጅ ቁጥር 57/1989 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 18 ለዋስትና ሰነድ ከተሰጠው ትርጓሜ ለመረዲት ችለናል። ከዚህ በተጨማሪ የአመልካች ክርክር በአዋጅ ቁጥር 86/1986 አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 4 ሥልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሓራዊ ባንክ አመልካችና ላልች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በማናቸውም ሥያሜ የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ (Finanicial Gurantee Bond) እንዲያወጡ በመመሪያ ከመከልከላቸው በፉት ወጭ ያደረጓቸው የገንዘብ ዋስትና ግዳታ ሰነድች (Finanicial Gurantee Bond) የጸኑና ህጋዊ ውጤት ያለቸው መሆኑን " Finanicial Gurantee Bond or other unconditional bonds issued by insurance conpanies and outstanding before the effective date of these directives shall remain enforce until the expiry date or shall be phased out in line with an action plan submitted by each insurance company and agree with the bank" በማለት የገለጸውን የመመሪያ ቁጥር 24/2004 አንቀጽ 3 ድንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ የሚቃረንና የህግ መሰረት የላለው ነው። ስለሆነም አመልካች ተበዲሪው አቶ መሐመድ አብደላ ከተጠሪ የወሰደውን የብድር ገንዘብ ባይከፍል እሱ የሚከፍል መሆኑን በማረጋገጥ የሰጠውን የማገቻ ሰነድ ልዩ ባህሪ ያለውና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚዘጋጅና ወጭ የሚደረግ የማገቻ ሰነድ በመሆኑ፣ አመልካች ሰነደ በሁለት ምስክሮች ስላልተረጋገጠ የዋስትና ሰነደ ህጋዊ ውጤት የለውም በማለት ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
4/ አራተኛው ጭብጥ ተጠሪ ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም? አመልካች የሰጠው ሰነድ የመድን ውል አለመሆኑ ተረጋግጧል። የላላ ሰው ዕዲ ለመክፈል የአንድነት የዋስትና ግዳታ የገባ ሰው የዋናውን ባለ ዕዲ ግዳታ ነጻ የሚያደርጉ የይርጋና ላልች መከራከሪያዎች በማቅረብ ከኃላፉነት ነጻ እንደሚሆን ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 1926 ንዐስ እንቀጽ 1 ድንጋጌ አቀራረጽ፣ ይዘትና ዓላማ ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በዋሱ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖረው የይርጋ ጊዜ ገደብ በዋናው ባለዕዲ ላይ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ እንደሆነ፣ በዋናው ባለዕዲ ላይ የተጀመሩ ክሶች ለዋሱ መቆጠር የጀመረለት የይርጋ ዘመን ያቋርጡበታል በማለት ፍታብሓር ህግ ቁጥር 1929 የደነገጉትን ምክንያት በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። በአበዲሪው በተጠሪና በተበዲሪው አቶ መሐመድ አብደላ መካከል የተደረገው የብድር ውል ላይ ተፈጻሚነት ያለው ስለ ውልች በጠቅላላው የሚደነግገው የይርጋ ጊዜ ገደብ ነው።
የአመልካች (የዋሱ) ግዳታ ቀሪ የሚሆነው የዋናው ባለዕዲ ግዳታ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት የይርጋ የጊዜ ገደብ ነው። ስለሆነም የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የፍታብሄር ህግ ቁጥር 1845 እንደሆነና ተጠሪ ያቀረበውን ክርክር መቀበላቸውና ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
5/ አምስተኛው ጭብጥ አመልካች ለተጠሪ በሰጠው የገንዘብ የዋስትና የግዳታ ሰነድ መሰረት በኃላፉነት ይጠየቃል ወይም አይጠየቅም? በኃላፉነት ይጠየቃል የሚባል ቢሆን የአመልካች የኃላፉነት መጠን ምን ያህል ነው? ሚለው ነው። አመልካች አቶ መሐመድ አብደላ ከተጠሪ በብድር የወሰደውን ገንዘብ በብድር ውለ መሰረት ካልከፈለ እስከ ብር 1,600,000 (አንድ ሚሉዮን ሥድስት መቶ ሺህ ብር) የሚደርስ ገንዘብ ለተጠሪ ለመክፈል የገንዘብ ዋስትና የግዳታ ሰነድ ሰጥተዋል። ተበዲሪው ዕዲውን በብድር ውለ መሰረት አለመክፈለ በስር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች የዋስትና ግዳታ እስከሰጠበት ብር 1,600,000 (አንድ ሚሉዮን ስድስ መቶ ሺህ ብር) ሉከፍል ይገባል በማለት የሰጡት ውሳኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1930፣ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1924 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1922 ንዐስ አንቀጽ 2ን የመሰረት ያደረገና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል። እንደዚሁም የስር ፍ/ቤት በዚህ ጉዲይ ምክንያት ተጠሪ ለዲኝነት የከፈለውን ገንዘብና ላልች ወጪዎች አመልካች እንዱከፍል የተሰጠው ውሳኔ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1931 ን መሰረት ያደረገ ሆኖ አግኝተነዋል። በአጠቃላይ የስር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ከላይ በዝርዝር ባየናቸው ጭብጦች ላይ የሰጡት የህግ ትርጉምና ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍታብሓር መዝገብ መስከረም 24 ቀን 1999 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍታብሓር ይግባኝ ሰሚ ችልት በይግባኝ መዝገብ መጋቢት 10 ቀን 2000 የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
በዚህ ችልት የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፣ ለሚመለከተው ይተላለፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.