No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዲት ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር ባለቤት ዶ/ር ጤናዬ አብተው አልቀረቡም ተጠሪ፡- 1.የኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ፅ/ቤት- ነ/ፈጅ ታምሬ ሀይላ ቀረበ 2. ሲቫ ሳንቴ አሉማሉ ኤስአ/በፈንሳይ አገር የተመዘገበ- ጠበቃ ጥላሁን ደስታ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአመልካች መስሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት በሚሰጡት ውሳኔዎች ቅሬታ ያለበት ወገን አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ሉያቀርብ የሚገባበትን ሥርዓት የሚመለከት ነው።ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች ናቸው።የአሁኑ አመልካች በ1ኛ ተጠሪ መሰሪያ ቤት ላይ የመሰረቱት የክስ ይዘት ባጭሩ፡-አመልካች በሕንድ ሀገር ከሚገኝ አሺሽ ላይፍ ሳይንስ ከተባለ ድርጅት "VEREVIN" የተባለ የእንስሳት መድኃኒት እያስመጣ በኢትዩጵያ ለማከፊፈል ሙለ እውቅና ያለው መሆኑን፣ ይህን "VEREVIN" የሚለውን ስምና ተጨማሪ ALS የሚል በቀይ ሳጥን ያለመስቀል የሰራን ምስል በንግድ ምልክትነት እንደሚዘገብልን በማለት ለተከሳሽ አመልክተው ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ገልጾ ይኸው የንግድ ምልክት እንዱመዘገብላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም አመልካች የንግድ ምልክት ምዝገባ እንዱደረግለት ከማመልከቱ በፉት "VEREVIN" ተመሳሳይነት ያለው የንግድ ምልክት ለእንስሳት መድሃኒትነት ምርት ተጠሪ በመመዝገቡ ምክንያት የአመልካችን ጥያቄ አሳካሪ የንግድ ምልክት በሚል መነሻነት አለመመዝገቡን ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።የአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪም ወደ ክርክሩ በጣልቃ ገብነት ተካፊይ ሁኖ በሰጠው መከላከያ መልስ አመልካች እንዱመዘገብለት የጠየቀው የንግድ ምልክት ጣልቃ ገቡ ካስመዘገበና "VEREBIN" ተብል ከሚታወቀው ጋር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ ሉመዘገብለት አይገባም በማለት ተከራክሯል።ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ እና ተገቢ ነው ባለው መንገድ ከአጣራ በሁዋላ አመልካች እንዱመዘገብላቸው የጠየቁት ምልክት በአጻጻፈና በአጠራሩ ከጣልቃ ገቡ ምልክት ጋር ተቀራራቢ እንደሆነና ተጠቃሚውን ሉያሳክር እንደሚችል መረጋገጡን ገልፆ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።፡በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸሮ የአመልካች የንግድ ምልክት እንዱመዘገብላቸው ተብል ተወስኗል።ከዚህም በኋላ ተጠሪዎች ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የአመልካች የንግድ ምልክት ሉመዘገብ አይገባም ተብል መወሰኑ የአዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀጽ 2(4)፣3 እና 8(4) ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው በማለት ውሳኔው እንዱሻርላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ወደ ኢትዬጵያ እያስመጣ የሚያከፊፍለው ምርት "VEREVIN" የሚባለው በሕንድ ሀገር ተመዝግቦና ተመርቶ የሚሰራጭ ሲሆን 2ኛ ተጠሪም ወደ ኢትዮጵያ እያስመጣ የሚያከፊፍለው ምርት "VEREBIN" የሚባለው በፈረንሳይ ሀገር ተመዝግቦና ተመርቶ የሚሰራጭ ከመሆኑ አኳያ የአመልካች ምርት በኢትዬጵያ ውስጥ አይመዘገብም ተብል በ1ኛ ተጠሪ መከልከለን ከ2ኛ ተጠሪ ምርት ጋር ተቀራራቢ በመሆኑ ተጠቃሚውን ያሳክራል ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የመወሰን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 501/1998 አንጸር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ጉዲዩ በቀጥታ ክስ መቅረቡና በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መታየቱ ባግባቡ መሆን ያመሆኑ ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ቀጥታ ክስ መሆኑንና ጥያቄአቸውም 1ኛ ተጠሪ አለመዘግብም ያለው የንግድ ምልክት እንዱመዘገብ እንዱወሰንላቸው መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 320/1995 አንቀጽ 6(1) መሰረት የንግድ ምልክት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማመልከቻዎችን በመቀበል አግባብ ባለው የአእምሯዊ ንብረት ሕግ መሰረት ምርመራ በማካሄድ ውሳኔ የመስጠትና በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 36 መሰረት በተመዘገበ የንግድ ምልክት ላይ የሚነሱ ክርክሮችን በማየት ፈራሽ የማድረግ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን የተጠቀሱት ድንጋጌዎች በግልፅ ያስገነዝባለ።አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17(1) ድንጋጌ ሲታይም አመልካች መስሪያ ቤት ስለንግድ ምልክቱ ምዝገባ በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው ቅሬታውን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል አስቀምጧል።የአዋጁ አንቀጽ 49 ሲታይ ደግሞ ስልጣን ያለው ፍርድ ቤትን ያሳያል።በዚህ ድንጋጌ መሰረት በአዋጁና አዋጁን ለማስፈጸም በአዋጁ አንቀጽ 47 መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣው ደንብ በተመለከቱት ጉዲዩችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችንና ተዛማጅ ጉዲዮችን የማየት ስልጣን የሚኖራቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ናቸው በሚል የሚደነግግ ነው።እንግዱህ በሕጉ ረገድ ያለው የውሳኔ አሰጣጥና የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት ከላይ የተጠቀሰው ሲሆን ሕጉ አመልካች መስሪያ ቤት በሚሰጠው የመጨረሻ ውሰኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት(The Right to Appeal) እንዲለው በግልፅ ከማስቀመጡ ውጪ ጉዲዩ በቀጥታ ክስ የሚቀርብበት ጉዲይ ስለመሆኑ የሚያመላክተው ሁኔታ የለም።በልላ በኩል አግባብነት ያላቸው የአእምሯዊ ንብረት ሕጎች ሲታዩ 1ኛ ተጠሪ መስሪያ ቤት በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሚሰጣቸው አስተዲደራዊ ውሳኔዎች ቅሬታ ያለው ወገን ቅሬታውን ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ የሚችለው በይግባኝ ስርዓት ስለመሆኑ እና ይህን ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ደግሞ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 25/1988 ከአእምሯዊ ንብረት ሕጎች ጋር ተጣምሮ ሲታይ የሚያስገነዝበን ጉዲይ መሆኑን ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ላይ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝን ፍርድ ቤት የሚያስገደድ የሕግ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ነው።
የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17(1) ድንጋጌ ርእሱ ሲታይ አማርኛው "ይግባኝ የማቅረብ መብት" በሚል የተቀመጠ ሲሆን የእንግሉዝኛው ቅጂ ደግሞ "The Right to Appeal" በሚል የተቀመጠ ነው።እንግዱህ ሕጉ በይዘቱና በቅርጹ ይህን የሚመስል ከሆነ ይግባኝ የሚለው የሕጉ አገላለፅ ለየትኛው ፍርድ ቤት ነው ጉዲዩ መቅረብ ያለበት የሚለውን ጥያቄ ይፈታ ዘንድ የይግባኝ ትርጉሙንና የአቀራርብ ሥርዓቱን በአጠቃላይ ማየቱን፣የአመልካች መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የወጣውን ሕግና ለመስሪያ ቤቱ ስልጣን የሚሰጡ ላልች ተዛምጅነት ያላቸው ሕጎች የሚያስቀምጡትን የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት መመልከቱና ግንዛቤ መውሰደ ተገቢ ይሆናል።
ታዋቂው የ" Black's Law Dictionary" ይግባኝ የሚለውን ቃል ሲተርጎም "A proceeding undertaken to have a decision reconsidered by bringing it to a higher authority, especially; the submission of a lower court’s or agency’s decision to a higher court for review and possible reversal. በሚል ያስቀምጣል።ከዚሁ መገንዘብ የሚቻለው ይግባኝ በበታች አካል የተሰጠ የአንድ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም ለበላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ በማቅረብ የስር ፍርደ/ውሳኔ እንደገና የሚታይበትን ወይም እንዱጣራ የሚደርግበትን ወይም ሉለወጥ የሚችልበትን ሥርአት የሚያመላክት መሆኑን ነው።በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 320(1) የተመለከተው ድንጋጌ ሲታይም በፍትሒ ብሓር ወይም በላልች ሕጎች ውስጥ በልላ ሁኔታ እንዱፈጸም የሚያዝ ድንጋጌ ከላለ በቀር ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በፍትሒ ብሓር ፍርድ ቤት በተወሰነበት የመጨረሻ ፍርድ ላይ ይግባኝ ለማለት የሚችለ መሆኑን ይደነግጋል።በዚህ ድንጋጌ መሰረት የይግባኝ ትርጉም በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራካሪ የነበረና በተሰጠው ፍርድ ቅር የተሰኘ ወገን ይህንኑ ቅሬታውን ለበላይ ወይም ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ እንዱሻሻል፣እንዱለውጥ ወይም በጠቅላላው ውድቅ እንዱሆንና ዲኝነቱ ለእሱ እንዱሰጠው ለመጠየቅ የሚያስችል ሥርዓት ነው። በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 ደግሞ የይግባኝ ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ተመልክተዋል።በልላ በኩል አዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀጽ 17(1) ድንጋጌ ስለንግድ ምልክት ምዝገባ ፅ/ቤቱ በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው ቅሬታውን ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ብል ሲያስቀምጥ "የመጨረሻ ውሳኔ" የሚለው ሐረግ አቀራረፁና ይዘቱ የሚያሳየው በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት መሆኑን እንጂ ቀጥታ ክስ የሚቀርብበት አለመሆኑን መገንዘብ የሚቻል መሆኑን ነው።እንዱሁም አመልካች የተቋቋመው አእምሯዊ ንብረትን የሚገዙ ብሓራዊ ሕጎችን የሚያስፈፅም ወይም ተፈጻሚነታቸውን የሚከታተል እንዱሁም አስፈላጊውን አቅም በመገንባት ቀልጣፊና ውጤታማ አገልግልት የሚሰጥ መንግስታዊ አካል ማቋቋም በማስፈለጉ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 320/95 በመግቢያው ያስቀመጠው ጉዲይ ሲሆን የዚሁ አዋጅ አንቀፅ 2 ደግሞ "አእምሯዊ ንብረት" እና "ፒተንት" የሚለትን ቃላት ትርጉም አስቀምጧል።በዚህም መሰረት አእምሯዊ ንብረት ማለት የሰው ልጅ አእምሮ ውጤት በሆኑ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ያለ ሕጋዊ መብት ሲሆን ፒተንትን፣የንግድ ምልክትን፣የምስክር ወረቀትንና ኮፑ ራይትን እንደሚጨምር በአዋጁ አንቀፅ 2(1)ድንጋጌ የተቀመጠ ሲሆን ፒተንት ማለት ደግሞ የፈጠራ ስራን ለማስጠበቅ የሚሰጥ መብት ሲሆን በፈጠራ፣በአነስተኛ ፈጠራና በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/187 መሰረት በፈጠራ፣በአነስተኛ ፈጠራና በኢንደስትሪያዊ ንድፍ የሚሰጠውን የአስገቢ ፒተንት፣የግልጋልት ሞዳል ምስክር ወረቀትና የኢንደስትሪያዊ ንድፍ የምዝገባ የምስክር ወረቀትን እንደሚጨምር በአንቀጽ 2(2) ስር በግልፅ ሰፍሮ እናገኛል።ይህ መስሪያ ቤት ከሚያስፈጽማቸው ሕጎች መካከል አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንደ ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀፅ 2(9 እና 15) ድንጋጌዎች ሲታዩም በአዋጁ በሚገዙ ጉዲዮች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን የመመልከት ስልጣን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስለመሆኑ በግልፅ ያሳያለ።በልላ በኩል የፈጠራ፤የአሰነስተኛ ፈጠራና የኢንደስትሪያዊ ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/1987 ስር የይግባኝ ሰልጣኑ የማዕከላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣን ስለመሆኑ አንቀፅ 2(1) እና 54 ድንጋጌዎች በአንድ ላይ ሲነበቡ የሚያሳዩት ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሁኖ አግኝተናል።እነዚህ ሕጎች በአመልካች መስሪያ ቤት ይፈጸማለ ተብለው ከተጠቀሱት ሕጎች መካከል ውስጥ ሲሆን አመልካች መስሪያ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ይግባኙ የሚቀርበው በግልፅ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን ያሳያለ። ከላይ እንደተገለጸው አመልካች መስሪያ ቤትን ያቋቋመው አዋጅ ቁጥር 320/1995 መስሪያ ቤቱን ለማቋቋም ያስፈለገበትን አእምሯዊ ንብረትን የሚገዙ ብሓራዊ ሕጎችን የሚያስፈፅም ወይም ተፈጻሚነታቸውን የሚከታተል አካል ማቋቋም በማስፈለጉ መሆኑን በግልጽ ያስፈረ ሲሆን ይህ ምክንያት አመልካች መስሪያ ቤት ተመሳሳይ የአእምሯዊ ንብረት ጉዲዮችን ለማስተናገድ ስልጣን የተሰጠው አካል ከመሆኑ ተዲምሮ ሲታይ ጽ/ቤቱ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ይታያለ፣ወይም በተወሰኑት ይግባኝ፣በተወሰኑት ደግሞ ቀጥታ ክስ ይቀርብባቸዋል ብል መደምደም የአመልካች መስሪያ ቤትን ሥልጣንና ተግባር ውጤት ያለው ማድረግ ያስችላል ተብል የማይታሰብ መሆኑን አመልካች መስሪያ ቤት የሚያስፈጽማቸው ሕጎች አውደ ንባብ (Contextual interpretation) የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነው።በመሆኑም አመልካች መስሪያ ቤት በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ቅሬታ ያለው ወገን በሕግ የተሰጠው መብት ይግባኝ ማቅረብ እንጂ ቀጥታ ክስ መመስረት አይደለም።በሕጉ የተዘረጋው ሥርዓት ይግባኝ ከሆነ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አግባብነት ባለቸው የፍትሒ ብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በጉዲዩ ላይ የይግባኝ ሥልጣን ያለው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።ሲጠቃለልም የአዋጅ ቁጥር 501/98 አንቀፅ 6፣17፣36 እና 49 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ከይግባኝ ትርጉምና አመልካች መስሪያ ቤት ከተቋቋመበት አላማና አመልካች መስሪያ ቤት የሚያስፈፅማቸው ከአዋጅ ቁጥር 501/98 ውጪ ያለት ላልች ተዛማጅነት ያላቸው ሕጎች ከዘረጉት የይግባኝ አቀራረብ ሥርኣት አንጻር ሲታይ በንግድ ምልክት ምዝገባ ጉዲይ ላይ አመልካች መስሪያ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ያለው መብት በይግባኝ ሥርዓት የሚከበር እንጂ በቀጥታ ክስ የሚስተናገድ አለመሆኑን፣ይግባኙ መቅረብ ያለበት ደግሞ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።ከላይ የተመለከተው የሕግ ትንታኔ ይህ ችልት በሰ/መ/ በቀረበው ተመሳሳይ የሕግ ጥያቄ ላይ የተሰጠ ሲሆን ይህ የሕግ ትርጉም ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ ነው።በመሆኑም በሕጉ አግባብ እስካልተለወጠ ድረስ ለዚህ ጉዲይም ተፈፃሚነት ያለው ሁኖ አግኝናል።በዚህም መሰረት የፍርድ ቤት የስረ ነገር ሥልጣን በተከራካሪ ወገኖች ባይቀርብም በፍርድ ቤቱ አነሳሽነትም መነሳትና ቀድሞ እልባት ማግኘት ያለበት ነጥብ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231(1ለ)) ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለሆነም የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን በቀጥታ ክስ በማየት ማስተናገደም ሆነ ይህንኑ ስህተት ሳያርሙ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶችም በፍሬ ጉዲዩ ላይ የበኩላቸውን ውሳኔ መስጠታቸው ይህ ችልት በሰ/መ/ ከሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል።በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 29 ቀን 2000 ዓ.ም.፣የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. እንዱሁም በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ነሐሴ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሸረዋል።
የንግድ ምልክት ምዝገባ አቤቱታ ላይ አመልካች በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ያለው መብት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ማቅረብ እንጂ ቀጥታ ክስ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረብ አይደለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.