No summary available.
ህዲር 08 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ሀብተወልድ ዘርጋው የጄትሮ የስራ አመራር የማማከር አገልግልት ድርጅት ባለንብረት - ጠበቃ ተስፊ አደኛ ቀረቡ ተጠሪ፤- 1. አቶ ሳሙኤል አሰፊ የጄትሮ ሉደርሺፔ ኤንድ ማኔጅመንት ወይም ዩቶር ሉደርሺፔ ኤንድ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት- ራሣቸው ቀረቡ 2. የንግድ ሚኒስቴር - ነ/ፈጁ ተካልኝ ከድር ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የንግድ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 686/2002 መሰረት የሚሰጣቸው የንግድ ስም ጉዲዮች ውድቅ የሚደረጉበትን አግባብና ቅሬታ ያለው ወገን ሉከተለው ስለሚገባው መፍትሓ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ነው። ክሱ የተመሰረተውም ባሁኑ ተጠሪና በንግድ ሚኒስቴር ላይ ነው። የአሁኑ አመልካች በተጠሪና በንግድ ሚኒስቴር ላይ የመሰረተው የክስ ይዘት ባጭሩ፡በንግድ ሚኒስቴር የተመዘገበውና ያሁኑ ተጠሪ የሚጠቀምበት ጄትሮ ሉደርሺፔ ኤንድ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት (Jethro leadership and managemet institute) የሚለው የንግድ ስም አመልካች ከተጠሪ ቀደም ብለው ካስመዘገቡት ጄትሮ የስራ አመራር የማማከር አገልግልት (Jethro management consultancy service) ከሚለው የንግድ ስም ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም 2ኛ ተጠሪ የአመልካችን ተቃውሞ ሳይቀበል ይሄ ተመሳሳይ የንግድ ስም እንዱመዘገብ ማድረጉ በአመልካች ላይ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር የሚያስከትል መሆኑን ዘርዝረው 1ኛ ተጠሪ "Jethro" በሚለው የንግድ ስም እንዲይጠቀም እንዱወሰንላቸው፣ 2ኛ ተጠሪም ለ1ኛ ተጠሪ የመዘገበውን የንግድ ስም እንዱሰርዝ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪዎችም በተከሳሽነታቸው ቀርበው በሰጡት መልስም የንግድ ስም ፈቃድ በአዋጅ ቁጥር 686/2002 ሲሰጥ ተቃውሞ የሚያቀርበው ወገን ለንግድ ሚኒስቴር ተቃውሞውን በማቅረብ ጉዲዩ ከታየ በሁዋላ ቅሬታ ካለው በይግባኝ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይታያል እንጂ ቀጥታ ክስ የሚመሰረትበት ጉዲይ ባለመሆኑ ጉዲዩ ከፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን ውጪ ነው በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 61”ን” መሰረት በማድረግ ጉዲዩ በይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ እንጂ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀጥታ ክስ የሚስተናገድ አይደለም በማለት መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 231(ሀ)(ለ) መሰረት ዘግቶታል። በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት ጉዲዩን በቀጥታ ክስ የማስተናገድ ስልጣን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁኖ እያለ ጉዲዩ በይግባኝ ነው የሚታየው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የሥር ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 61 መሰረት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የነበረው መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ 2ኛ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 6፣ 7፣ 30 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ የመስጠት ስልጣን ያለው ሲሆን ይህንኑ ስልጣን ተግባራዊ ሲያደርግ የሚያስፈልጉትና ሉከተላቸው የሚገባቸው ስርዓቶች በአዋጁ ተዘርዝረው ተደንግገው እናገኛለን።
የአዋጁ አንቀጽ 2(9) እና (16) ድንጋጌዎች ከአዋጁ አንቀጽ 61 ድንጋጌ ጋር ተጣምረው ሲነበቡ ንግድ ሚኒስቴር የንግድ ስም በመመዝገብ ሂደት የሚቀርበውን አቤቱታ መርምሮ ተገቢ ነው ያለውን አስተዲዲራዊ ውሳኔ መስጠት የሚችል መሆኑን ያሳያለ። በአስተዲደራዊ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን በሕግ ጉዲዮች ብቻ አቤቱታውን ለመደበኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚችል መሆኑን የአዋጁ አንቀጽ 61 ድንጋጌ የሚያስቀምጥ ሲሆን በድንጋጌው አቤቱታው ለመደበኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብበት አግባብ የተመለከተ ቢሆንም አቤቱታው ቀጥታ ክስን ወይም ይግባኝን የሚመለከት ስለመሆኑ በግልጽ ሁኔታ በድንጋጌው ተቀምጧል ለማለት አይቻልም። ይሁን እንጂ በሕጉ ረገድ ያለው የውሳኔ አሰጣጥና የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት ከላይ የተጠቀሰው ሲሆን ሕጉ 2ኛ ተጠሪ መስሪያ ቤት በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን በሕግ ጉዲዮች ላይ ብቻ ለመደበኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት (The right to Appeal) እንዲለው ከማስቀመጡ ውጪ ይግባኙ በፋዳራለ ፍርድ ቤቶች በየትኛው እርከን ለሚገኝ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ግልጽ በሆነና አሻሚነት በላለው አነጋገር አያስቀምጥም። እንዱህ በሆነ ጊዜ ሕጉን መተርጎም ተገቢ ይሆናል።
የአዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 61 ድንጋጌ ርእሱ ሲታይ አማርኛው “በአስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ስለማቅረብ” በሚል የተቀመጠ ሲሆን የእንግሉዝኛው ቅጂ ደግሞ “Submission of Complaints on Administrative Decisions)” በሚል የተቀመጠ ነው። የድንጋጌው እንግሉዝኛ ትርጉም ዝርዝር ሲታይ Any person or a business person or a commercial representative against whom an administrative decision has been taken by the registering 0ffice or the appropriate authority may lodge appeal in connection with his complaints to regular courts only on matters of law. በሚል የተቀመጠ መሆኑን ያስረዲል። እንግዱህ ሕጉ በይዘቱና በቅርጹ ይህን የሚመስል ከሆነ ይግባኝ የሚለው የሕጉ አገላለፅ ለየትኛው ፍርድ ቤት ነው ጉዲዩ መቅረብ ያለበት የሚለውን ጥያቄ ይፈታ ዘንድ የይግባኝ ትርጉሙንና የአቀራረብ ሥርዓቱን በአጠቃላይ ማየቱን፣ የአመልካች መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የወጣውን ሕግና ላልች ተዛማጅነት ያላቸው ሕጎች የሚያስቀምጡትን የይግባኝ አቀራረብ ሥርዓት መመልከቱና ግንዛቤ መውሰደ ተገቢ ይሆናል።
ታዋቂው የ “ Black’s Law Dictionary” ይግባኝ የሚለውን ቃል ሲተረጎም A proceeding undertaken to have a decision reconsidered by bringing it to a higher authority, especially, the submission of a lower court’s or agency’s decision to a higher court for review and possible reversal. በሚል ያስቀምጣል። ከዚሁ መገንዘብ የሚቻለው ይግባኝ በበታች አካል የተሰጠ አንድ ፍርድን ወይም ውሳኔን በመቃወም ለበላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ በማቅረብ የስር ፍርደ/ ውሳኔ እንደገና የሚታይበትን ወይም እንዱጣራ የሚደረግበትን ወይም ሉለወጥ የሚችልበትን ሥርዓት የሚያመላክት መሆኑን ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 320/1/ የተመለከተው ድንጋጌ ሲታይም በፍትሐብሕር ወይም በላልች ሕጎች ውስጥ በልላ ሁኔታ እንዱፈጸም የሚያዝ ድንጋጌ ከላለ በቀር ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በፍትሐ ብሓር ፍርድ ቤት በተወሰነበት የመጨረሻ ፍርድ ላይ ይግባኝ ለማለት የሚችለ መሆኑን ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የይግባኝ ትርጉም በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከራካሪ የነበረና በተሰጠው ፍርድ ቅር የተሰኘ ወገን ይህንኑ ቅሬታውን ለበላይ ወይም ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ እንዱሻሻል፣ እንዱለውጥ ወይም በጠቅላላው ውድቅ እንዱሆንና ዲኝነቱ ለእሱ እንዱሰጠው ለመጠየቅ የሚያስችል ሥርዓት ነው።
በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 ደግሞ የይግባኝ ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ተመልክተዋል። በልላ በኩል አዋጅ ቁጥር 686/2002 አንቀጽ 61 ድንጋጌ 2ኛ ተጠሪ በሰጠው የአስተዲደራዊ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው በሕግ ጉዲዮች ላይ ብቻ አቤቱታውን ለመደበኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ብል ሲያስቀምጥ “አቤቱታ” የሚለው የአማርኛ ሐረግ በእንግሉዝኛው "Appeal" በሚለው ቃል ተተርጎሞ መቀመጡ የሚያሳየው በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚቀርብበት መሆኑን እንጂ ቀጥታ ክስ የሚቀርብበት አለመሆኑን ነው። እንዱሁም በሕጉ አነጋገር በፍሬ ነገር ላይ አቤቱታ ማቅረብ የማይቻል መሆኑ መቀመጡ ቴክኒካዊ በሆኑ ምክንያቶች አስተዲደራዊ አካለ የሚሰጠው ውሳኔ ተገቢነት ያለው መሆኑ ታምኖበት በመሆኑ ፍሬ ነገር ላይ አቤቱታ እንደማይቀርብ ተከልክል በሕግ ነጥብ ላይ ብቻ ቀጥታ ክስ ይቀርብባቸዋል ብል መደምደም የአመልካች መስሪያ ቤትን ሥልጣንና ተግባር ውጤት ያለው ማድረግ ያስችላል ተብል የማይታሰብ መሆኑን 2ኛ ተጠሪ መስሪያ ቤት የሚያስፈጽማቸው ሕጎች አውደ ንባብ (contextual interpretation) የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነው። በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሚሰጣቸው ውሳኔዎች ቅሬታ ያለው ወገን በሕግ የተሰጠው መብት ይግባኝ ማቅረብ እንጂ ቀጥታ ክስ መመስረት አይደለም። በሕጉ የተዘረጋው ሥርዓት ይግባኝ ከሆነ በፋዳራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በጉዲዩ ላይ የይግባኝ ሥልጣን ያለው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩ በቀጥታ ክስ ላታይ የሚችል አይደለም በማለት የሰጡት ብይን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ ስላላገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 05 ቀን 2003 ዓ.ም.
የጸናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
2ኛ ተጠሪ የንግድ ስም ምዝገባን አስመልክቶ በሚሰጠው አስተዲደራዊ ውሳኔ ቅሬታ ያለበት ወገን ያለው መፍትሓ ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንጂ ቀጥታ ክስ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መመስረት አይደለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.