No summary available.
ጥቅምት 24 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ውልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አለመልካች፡- ጎልደን ሮዝ አግሮ ፊርምስ ኃ/የተ/የግ ማህበር - የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡- አቶ ሐሉፍም ተስፊ ማሪያም - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍረድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የጉዲት ካሣን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረው በፋደ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ነው። ቀረቦ የነበረው ክስ የሰላዲ ቁ. 3-24690 ኢት እና የልዩ ተጏታች/ተሳቢ/ ሰላዲ ቁ. 3-09435 ኢት የሆነ የከሣሽ ተሸከርካሪዎች ናይትሪክ አሲድ የተባለ በኮንቴነር የታሸገ የተከሣሽ ንብረት/ጭነት/ ናይኮን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወይም ታሪንሶ አፍሪካን ትራንዚት በሚባል ተወካይ አማካይነት በከሣሹ ተሸከርካሪዎች ተጭኗል።
ጭነቱን ወደ አዱስ አበባ ለማጓጓዝ እንደተጀመረ በኢትዮጵያ ጅቡቲ ድንበር አካባቢ ሲደርስ አሲድ የተጫነበት ኮንቴነር በየአቅጣጫው ማፍሰስና ማንጠባጠብ ጀምርዋል። በዚህም በዋናው የከሣሽ ጎታች (power unit) ተሸከርካሪ ላይ መጠነኛ ጉዲት የደረሰ ሲሆን ልዩ ተጎታቹ /ተሳቢ/ ግን በአሲደ ሳቢያ በጉማው፣ በቸርኬው፣ ፕንሲውና በላልች አካላት ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዲት የደረሰበት በመሆኑ በአገልግልት ላይ ማዋል እንደማይችል የባለሙያው ሪፕርት አረጋግጧል።
በዚህ የተነሣ ተከሣሽ ከከሣሹ ጋር ባደረገው ድርድር መሰረት ዋናውን ተሸከርካሪ በጥገና የሚያስፈልገውን ወጪ እንደሚከፈል ወይም እንደሚያሰራ ልዩ ተጎታቹ ግን ከጥቅም ውጪ ስለሆነ ባለሙያው ባቀረበው ሪፕርት መሰረት ዋጋውን እንደሚከፍል በጊዜው በቃል ተሰማምቷል። በመሆኑም ልዩ ጎታች ላይ ለደረሰው ጉዲት ለጥገና የሚያስፈልገውን ብር 26,154 (ሃያ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሣ አራት ብር ) ልዩ ተጎታች ወይም ተሳቢ ለመተካት የገበያ ዋጋ ብር 265,000 (ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) እንዱሁም የተቋረጠ ገቢ 68,427.70 (ስልሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሃያ ሰባት ብር ከሰባ ሣንቲም) ይሆናል። ባጠቃላይ ተከሣሽ ብር 359,581.70 (ሦስት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ አንድ ከ ሰባ ሣንቲም) ከእነ ህጋዊ ወለድ ጭምር እንዱከፍል እንዱወስንበት በማለት ነው።
ተከሣሽ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተከሣሽ የዕቃው ተረካቢ እንጂ ላኪ አይደለም፣ ታሪንሶ አፍሪካ ትራንዚት ሰርቪስ ወይም ኒካን ኃለ/የተ/የግል ማህበር የተከሣሽ ወኪልች አይደለም፣ ተከሣሽ ለደረሰው ጉዲት ለከሣሽ ለመክፈል የገባው አንዲችም ስምምነት የለም፣ ተከሣሽ በከሣሽ ንብረቶች ወይም አሮጌ ተሽከርካሪዎች ላይ ለደረሰው ጉዲት በአዱስ ለመተካት ኃላፉነት የለበትም፣ ከሣሽ በሰላዲ ቁ. 3.09435 ኢት ተሳቢ ዋጋ ብር 265 000 ነው ያለውን በተመለከተ ሉከፍል የሚገባው የካሣ መጠን በተሸከርካሪው ዋጋ ላይ ለአገልግልት ዘመን ታስቦ የሚሆነውን የእርጅና እና የአሞርታይዘሸን ቅናሽ ታስቦ ለሚኖረው የተሸከርካሪ ዋጋ ነው እና ተቋረጠ ለተባለው ገቢ በአመታዊ ገቢው መሰረት ከግብር አስገቢ መሥሪያ ቤት የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
የፋ/የመ/ደረጃ ፍርድ ቤት ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ በኋላ ተከሣሽ ለቀረበው ክስ ኃላፉነት አለበት? ወይስ የለበትም? የሚለውን ጭብጥ ከያዘ በኋላ ዕቃውን በከሣሽ መኪና /ተሸከርካሪዎች/ ላይ ያስጫነው የናይኮን ኃለ/የተ/የግል ማህበርም ሆነ ታሪንስ አፍሪካን ትራንዚት ሰርቪስ የተከሣሽ ወኪልች መሆናቸውን ባለማስረዲቱና ተከሣሽ የደረሰውን ጉዲት ለመካስ የተዋዋለ ስለመሆኑ የሚያመለክት ማስረጃ ባለመኖሩ ተከሣሽ ለክሱ ኃላፉነት የለበትም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን በማስቀረብ ግራ ቀኙን ካከራከር በኋላ የአሁን አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት ከወሰነ በኋላ የካሣውን መጠን በተመለከተ ከሣሽ ቀረብኝ የሚለውን ገቢ በተመለከተ የቀረበውን ነጥብ ውድቅ በማድረግ በሁለቱም ተሸከርካሪዎች ደረሰ የተባለውን በአጠቃላይ ብር 291,154 (ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አራት ብር) ጉዲቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 9% ወለድ ጋር የአሁኑ አመልካች ለአሁኑ ተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል። የአሁን አመልካች በዚህ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348(1) መሰረት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአመልካች ጠበቃ በቀን 30-12-2002 ዓ.ም በሦስት ገጽ የፃፈው የቅሬታ ፍሬ ሃሣብ ተጠሪ ለባለቤቱ ለማድረስ የተረከበውን እቃ በአግባቡ ሳያደርስ በመቅረቱ ሉጠየቅ ሲገባው አሲደ ተሸከርካሪዎቼ ላይ ፈሷል በማለት ያቀረበው ክስ ስለአጓጓዥ ግዳታዎች ተብለው በንግድ ሕጉ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች የሚፃረር በመሆኑ ኃላፉነት አለበት ቢባል እንኳ የተሸከርካሪዎቹ የአገልግልት ዘመን እርጅና ተቀናሽ ሳይደረግ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ነው።
ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ በጠበቃው አማካኝነት ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ የ3 ገጽ መልስ ያቀረበ ሲሆን ፍሬ ሃሣቡ የአጓጓዥን ኃላፉነት በተመለከተ ተሸከርካሪው በመገልበጥ ወይም በመገጨት የደረሰ አደጋ ሳይሆን በዕቃው በራሱ አስተሻሸግ ጥፊት በመሆኑ እና የደረሰውን ጉዲት አግባብነት ባለው ባለሙያ አመልካችም ሆነ ተጠሪ ያስገመቱት በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት ያለው አይደለም በማለት ተከራክሯል። የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም፡- አመልካች የራሱ ንብረት በሆነውና በተጠሪ ተሸከርካሪዎች ላይ በተጫነው ናይትሪክ አሲድ መፍሰስ ምክንያት ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት? ወይስ የለበትም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ የተያዘው ጉዲይ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
የአመልካች ንብረት የሆነው እና በመፍሰስ በተጠሪ ተሸከርካሪዎች ላይ ጉዲት አድርሷል የተባለው ናይትሪክ አሲድ በኮንቴነር እንደታሸገ ከጅቡቲ ወደብ በተጠሪ ተሸከርካሪዎች ላይ ያስጫነው አካል ናይኮን ኃላፉነቱ የተ/የግል ማህበር ወይም ታሪንሶ አፍሪካን ትራንዚት ሰርቪስ የአመልካች ወኪል ስለመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ያረጋገጠው ጉዲይ ከመሆኑም በላይ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ አከራካሪ አልሆነም። የንግድ ህግ አንቀጽ 561 እና ተከታዮቹን በምንመለከትበት ወቅት የማጓጓዝ ሂደቶችን በሚመለከት ተሣታፉ አካላት መካከል ላኪ፣ ተቀባይና አጓጓዥ ኃላፉነቶች በሰፉው ተደንግጎ ይገኛል።
በዚህ ጉዲይ ጉዲት አድርሷል የተባለው የአመልካች ንብረት የሆነው ናይትሪክ አሲድ አደገኝነት ያለው ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ከመሆኑ አኳያ በአግባቡ መታሸግ ያለበት ስለመሆኑ ግራ ቀኙን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም በአግባቡ መታሸጉን ማረጋገጥ ያለበት ወገን ደግሞ የላከው ስለመሆኑ በንግድ ሕግ ቁ. 578(2) ሥር የተደነገገ በመሆኑና በዚህ ጉዲይ ደግሞ ላኩ ሉባለ የሚገባቸው ከጅቡቲ ወደብ እቃውን ያስጫኑት የአመልካች ወኪልች በመሆናቸው እና አመልካች እንደ የእቃው ባለቤትነት ይሄ መርዘማነት ያለው ንብረት ከመጫኑ በፉት በአግባቡ ስለመጫኑ የማስረዲት ኃላፉነቱ የተጣለበት በመሆኑ ይሄንን ኃላፉነቱን ባለመወጣቱ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በልላ በኩል አመልካች ከላይ የተጣለበትን የህግ ኃላፉነት ስለመወጣቱ ካለማስረዲቱም በላይ የአሁን ተጠሪ የተጫነው ናይትሪክ አሲድ በአግባቡ ያለመታሸጉን እያወቀ የጫነ ስለመሆኑ እና በዚሁም የተነሣ ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክርም ሆነ ያረጋገጠው ፍሬ ነገር የላለ በመሆኑ ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በዚሁ መሰረት የፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍታሐብሓር ሕግ ቁ. 2069(1)ን በመጥቀስ አመልካች ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ማመልከቱ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው የህግ ድንጋጌ ያለመሆኑን ይሄ ችልት የተረዲው ሲሆን ከውጤቱ አኳያ ግን ከላይ በዚህ ችልት እንደተመለከተው አመልካች ኃላፉነት አለበት ወደ ሚለው መደምደሚያ የደረሰ በመሆኑ ምክንያቱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 342 መሰረት በመለወጥ የተሰጠውን የኃላፉነት ውሣኔ ተቀብለናል። በዚህ መሰረት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የፋ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጡትን የኃላፉነትና የካሣ መጠን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ጠ/ፍርድ ቤት በመዝ. ሐምል 20 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 78535 ህዲር 3 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች በተጠሪ ተሽከርካሪዎች ላይ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉነት አለበት ብለናል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዚህ ችልት በቀን 11-2-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
በትውስት የመጣው የመዝ.ቁ.05737 የሆነ መዝገብ ወደ መጣበት ይመለስ።
No topics extracted.