No summary available.
ጥቅምት 13 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ግልባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አ.ማ - የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የመድን ውልን መሰረት ያደረገ የገንዘብ ክፍያ ይተካልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካች የመድን ሽፊን የሰጣቸውን የደንበኛውን የኩርቱ ኢንተርናሽናል ኃ.የተ.የግል ማህበር ንብረት የሆኑትን 1,200 ጎማዎችን ተጠሪ ለማጓጓዝ የተረከበ ቢሆንም እነዚሁ ጎማዎች ተጠሪ በባህር ላይ በደረሰ ግጭት መጥፊታቸውን በመግለፁ አመልካች ከደንበኛው ጋር ባለው የመድን ውል መሰረት ለጠፈት ጎማዎች ግምት ብር 269,293.20 (ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ብር ከሃያ ሳንቲም) ወጪ አድርጎ ለደንበኛው መክፈለን ገልፆ ተጠሪ ባለው የመጓጓዣ ውል መሰረት ለአመልካች ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ከተለያዩ ወጪዎችና ኪሳራዎች ጋር እንዱተካለት ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ ለአመልካች ክስ በሰጠው መከላከያ መልስም አመልካች ክስ ለመመስረት የሚያስችለው መብትና ጥቅም የላለው መሆኑን ለክሱ ኃላፉነት የላለበት መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ጎማዎቹ በባህሩ ላይ ሉወድቁ የቻለት በባህር ላይ በደረሰው የግጭት አደጋ ምክንያት ነው፣ ጉዲቱ የደረሰው በአጓጓዡ ጥፊት ወይም በአጓጓዡ ወኪልች ወይም ሰራተኞች ጥፊት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎ ተጠሪን ከክሱ ነጻ አድርጎታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ ጎማዎቹን በአግባቡና በጥንቃቄ ሳይጭናቸው በመቅረቱ ግጭቱ በደረሰበት ጊዜ ተወርውረው ባህር ውስጥ የገቡ መሆኑ እየታወቀና ይህንኑ ሁኔታ ከባህር ሕጉ አንቀፅ 196(2) ድንጋጌ ይዘት ጋር ፍርድ ቤቱ ማገናዘብ ሲገባው ተጠሪን ከክሱ መለ በመለ ነጻ መልቀቁ ሕጋዊ አይደለም በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ተጠሪ ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የአመልካች ደንበኛ (ኩርት ኢንተርናሽናል ኃ.የተ.የግል ማህበር) ንብረት የሆነውን 1,200 ጎማዎችን አጓጉዞ ለማድረስ መረከቡንና ጎማዎቹ በባህር ላይ በነበረው ጉዞ በደረሰው ግጭት ምክንያት የጠፈ መሆኑ ግራ ቀኙ ያልተካካደት ፍሬ ነገር መሆኑን ነው። አመልካች ተጠሪ ላይ ክስ ሉመሰርት የቻለው ባለበት የመድን ውል ለደንበኛው በንብረቱ ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሳ ከከፈለ በኋላ ገንዘቡ እንዱተካለት ነው። ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው ኃላፉነት የለብኝም በማለት ሲሆን ለዚህ በቀዲሚነት የሚያቀርበው ክርክር ጎማዎቹ በባህር ላይ በደረሰው የመርከቦቹ ግጭት አደጋ የጠፈ እንጂ በተጠሪ ችግር ወይም ሰራተኞች ጥፊት አይደለም በማለት ነው።
በመሰረቱ በባህር ላይ እቃ አመላለሽ ያለበትን ኃለፉነት በተመለከተ የባህር ሕጉ በቁጥር 196 ስር ያስቀመጠ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት እቃ አመላላሽ ሁለት ሰፉና ዋና ዋና ግዳታዎች አለት። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ አንድን መርከብ በሙለ በመከራየት (ቻርተር ፒርቲ) እቃን የሚያጓጉዝ ባለመርከብ ስላለበት ግዳታ የባህር ሕጉን ቁጥር 138 በማጣቀስ የሚደነግግ ሲሆን የአንቀፁ ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ በመርከቡ ላይ የተጫኑትን እቃዎች በጥንቃቄና በሚገባ ለመጫን፣ ለአጠባበቃቸው በሚገባ አቀማመጥ እንዱደረደሩ፣ ስለጉዞዋቸው፣ ስለ ጥበቃቸው፣ ስለ መልካም አያያዛቸውና ስለ ማራገፈ መልካም አፈጻፀም ግዳታ ያለበት መሆኑን በአስገዲጅ ሁኔታ ይደነግጋል። በመሆኑም አጓዡ በሕጉ የተጣለበትን እነዚህን ግዳታዎች ካልተወጣ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ያስረዲል።
በጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ ውስጥ አመላላሹ ኃላፉነት የለበትም ተብል የተደረገው ውል የማይፀና ስለመሆኑም የባህር ሕግ ቁጥር 205 በግልፅ ይደነግጋል። የአመላላሹ መከላከያ ሉሆኑ የሚችለ ሕጋዊ ምክንያቶች በባህር ሕጉ ቁጥር 197 ስር የተመለከቱት ምክንያቶች ናቸው።
ከላይ የተመለከቱት የባህር ሕግ ድንጋጌዎች የአመላላሽን ኃላፉነት ሉያስከትለና ቀሪ ሉያደርጉ የሚችለ ሕጋዊ ምክንያቶችን የሚደነግጉ ሲሆን ኃላፉነትን በተመለከተ ቀሪ ከሚያደረጉ ምክንያቶች ውስጥ አመላላሽ በእቃው ጉዲት የደረሰው በባህር ላይ በደረሰው የግጭት አደጋ (accident of the Sea) መሆኑ፣ ከአመላላሹ ጥፊት ወይም በእርሱ ወኪልችና አሽከሮች ቸልተኝነትና ጥፊት ምክንያት ያለመሆኑና በአግባቡ ማስረከቡን መረጋገጡ ስለመሆኑም ያስገነዝባለ። የእቃው እርክክብ ተፈጽሟል የሚባለው ደግሞ መቼና በምን ሁኔታ ሲፈጸም እንደሆነም ድንጋጌዎቹ በተለይ ከባህር ሕጉ ቁጥር 180(3) ጋር ተዲምረው ሲነበቡ ያሳያለ።
በዚህም መሰረት በጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ የተረጋገጠ የማመላለሻ ውልን የሚመለከቱ ልዩ ድንጋጌዎች የሚጸኑት በተለይ በመርከብ ላይ በተጫኑት የንግድ እቃዎች የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ ወይም ይህን በመሰለ ላላ አይነት ሰነድ በተረጋገጡ የጭነት ማመላለሻ ውልች ብቻ መሆኑ፣ የመርከብ መከራየት ውል ሰነድ ባለው ጉዲይ ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን፣ ነገር ግን መርከቡ የተከራየው በኪራይ ሰነድ (በቻርተር ፒርቲ) የሆነ እንደሆነ የሚሰጠው የጭነት የማስታወቂያ ደረሰኝ ወይም ይህን የመሳሰለው ላላ ሰነድ በአመላላሹና በሰነድ አምጪው መካከል ያለው ግንኙነት ከሚመራበት ጊዜ አንስቶ በዚሁ በሚሰጠው የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኝ ላይ ድንጋጌዎቹ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ፣ የሚፀኑትም እቃዎቹ ከመርከብ ላይ ከተጫኑበት አንስቶ እስከሚራገፈበት ጊዜ ብቻ ስለመሆኑ የተጠቀሰው ድንጋጌ ያሳያል። የዚህ ቁጥር ንዐስ ቁጥር ሶስት በተለይ ሲታይም "…..ከመርከቡ ላይ ከተጫኑበት አንስቶ እስከሚራገፈበት ጊዜ ብቻ ነው።
"በሚል በኃይል ቃል ማስቀመጡ አመላላሹ በማራገፍ ሂደት ለሚከሰቱ ጉዲቶቹም ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በግልጽ የሚሳይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ተጠሪን ለጉዲቱ ኃላፉነት አለበት በማለት የሚከራከረው ጎማዎቹ በባህር ላይ እንዱወድቁ የሆነው ተጠሪ ጎማዎቹን በመርከቡ ላይ በጥንቃቄና በሚገባ በመጫን፣ በሚገባ አቀመማጥ እንዱደረደ ማድረግ (stow) ያለበት ስለመሆኑ በባህር ሕጉ አንቀፅ 196(2) ስር የተመለከተውን ግዳታ አልተወጣም የሚል ምክንያት በመጠቀስ ነው። የስር ፍርድ ቤት ይህንኑ የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው በማስረጃነት የቀረበው የባለሙያ ሰርቬይ ሪፕርት ጎማዎቹ ወደባህር የገቡት በመርከቦቹ ግጭት መሆኑን እንደሚያሳይ፣ አመልካች ጎማዎቹ በልላ ምክንያት የጠፈ ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክር የላለ መሆኑንና በባህር ሕጉ አንቀጽ 197(1(ሐ)) ስር በባህር ላይ ለደረሰው ጉዲት ወይም ድንገተኛ መሰናክል ምክንያት ለደረሰ ጉዲት አመላላሹ ኃላፉነት እንደላለበት መደንገጉንና ጉዲቱ በልላ ምክንያት የተከሰተ ነው ከተባለም በባ/ሕ/ቁጥር 197(1(ከ))ስር አመላለሹ ኃላፉነት የሚኖርበት በአመላላሹ ጥፊት ወይም በእርሱ ወኪልችና አሸከሮች ቸልተኝነትና ጥፊት ምክንያት መምጣቱ ሲረጋገጥ መሆኑንና በአመልካችና በተጠሪ መካከል ባለው ክርክር ግን የአመላላሹ ጥፊት ወይም የእርሱ ሰራተኞች ቸልተኝነት መኖሩ ያለመረጋገጡን በመተንተን ነው። ከዚህ ሁለ መገንዘብ የሚቻለው አመልካች ተጠሪ በሕጉ የተጣለበትን ግዳታ አልተወጣም በማለት ክስ የመሰረተ እንደመሆኑ መጠን ይህንኑ ሉያስረዲ የሚችል ለጉዲዩ አግባብነትና ጥንካሬ ያለውን ማስረጃ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ነው።
ተጠሪ በውለ የተጣለበትን ግዳታ በመወጣት ሂደት ውስጥ በነበረበት ጊዜ በተለይም ጎማዎቹ በመርከቡ ሲጫኑ ጥንቃቄ ባለማድረግ በተገቢው አኳኋን ያልደረደራቸው ከሆነና በዚህ ምክንያት ጎማዎቹ በመርከቦቹ ግጭት ጊዜ ወደባህሩ ተወርውረው የገቡ ናቸው ተብል በአመልካች ክርክር እስከቀረበና በተጠሪ ደግሞ የአመልካች ክርክር እስከተካደ ድረስ የአመልካችን ክርክር የማስረዲት ግዳታ የራሱ ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ክርክሮች የማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ሥርዓት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ከላይ እንደተገለጸው ለጉዲዩ ተገቢ ነው የተባለው የባለሙያ ሰርቬይ ሪፕርት ቀርቦ በማስረጃነቱ ሉሰጠው የሚችለው ክብደት በስር ፍርድ ቤት ታይቶ ማስረጃው የተጠሪን ጥፊት ሉያስረዲ የማይችል መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ባለው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትም ተቀባይነት አግኝቷል። ስለሆነም በጉዲዩ ላይ የቀረበው ማስረጃ ክብደቱ ተመዝኖ የተጠሪን ጥፊት ሉያስረዲ አይችልም ተብል ፍሬ ነገርን በሚያጣሩና ማስረጃን በሚመዝኑ ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ ከተደረሰ ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም በመሆኑ ሉለውጠው የሚችልበት አግባብ የለም። ለማስረጃው የሚሰጠው ዋጋ የስር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ነው ከተባለ ደግሞ በባ/ሕ/ቁጥር 196(2) እና 197(1(ሐ)) እና (ከ)) ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ ተጠሪ ለጉዲዩ ኃላፉ የሚሆንበት ሕጋዊ አግባብ የለም። በአጠቃላይ ተጠሪ አጓጓዥነቱንና እቃው በመርከቦቹ ግጭት ምክንያት ከመርከብ ወደ ውሃ በመውደቅ ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ሳይክድ ኃላፉነት የለብኝም በማለት ያቀረበው ክርክር በአመልካች ማስረጃ ተጠሪን ተጠያቂ ሉያስደርግ በሚችል በበቂ ማስረጃና ሕግ ያልተደገፈ መሆኑን በማረጋገጥ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሰጡ መሆኑን የተገነዘበን በመሆኑ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፋ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 20 ቀን 2002 ዓ.ም. የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ሙለ በሙለ ፀንቷል።
No topics extracted.