No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 9 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ተጠሪ አመልካቾች በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ ለ እና አንቀፅ 33 እና በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን በመተላለፍ በወንጀል ግብረ-አበርና ልዩ ተካፊይ በመሆን ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ይዘው የመገኘት ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ ባቀረበው የወንጀል ክስ ክርክር በሥር አንደኛ ተከካሽ የሆነው አንደኛ አመልካች የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ከተቀጠረበት ከመስከረም 1984 ዓ.ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ድረስ የታክስ አስተዲደርና ገቢ ሰብሳቢ ሆኖ የተለያየ የደረጃ እድገት እያገኘ እንደሰራ ገልፆ፣ አንደኛ አመልካች በሕጋዊ መንገድ በመንግስት ሥራው የሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከብር 90,220 /ዘጠና ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ብር/ የሚበልጥ አይደለም። ነገር ግን ተከሶሾች፡-
ሁለተኛ ተከሳሽ ዲሸን ባንክ በሑሳብ 01 ብር 332,363.63 /ሦስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ ሦስት ብር ከስልሣ ሶስት ሣንቲም/ ተቀምጦ ይገኛል።
አንደኛ ተከሳሽ በዲሸን ባንክ በሂሳብ 238200114004 ብር 1,646,371.24 /አንድ ሚሉዮን ስድስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አንድ ብር ከሃያ አራት ሣንቲም/ በስሙ የሚገኝ ሲሆን
አንደኛ ተከሳሽ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ብር 46,802.11 /አርባ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሁለት ብር ከአስራ አንድ ሣንቲም/ በስሙ የሚያንቀሳቅሰው ገንዘብ አለው
ተከሳሾች በልጃቸው በደስታ ወርቅነህ ስም ብር 55,931.92 /ሃምሣ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ አንድ ብር ከዘጠና ሁለት ሣንቲም/ ግምት ያለው የመኖሪያ ቤት አላቸው። በጠቅላላው ተከሳሾች ብር 2,081,468.90 /ሁለት ሚሉዮን ሰማንያ አንድ ሺ አራት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ ምንጩ ያልተወቀ ሀብት ያላቸው በመሆኑ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ ክሱን ሉያስረደ ይቻላለ የሚላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል።
አመልካቾች ክሱ ከደረሳቸውና እንዱረደት ከተደረገ በኋላ የወንጀለን ድርጊት አልፈፀምንም ጥፊተኞች አይደለንም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካቾች በበኩላቸው በተጠሪ ክስ የተዘረዘረው ገንዘብ ሕጋዊ ምንጭ የሚሎቸውን በመዘርዘር አቅርበዋል።
አመልካቾች- በወንድገነት ወረዲ አባያ ቀበላ ከ1984 ዓ.ም ከቤተሰብ የተሰጣቸው 2.5 ሄክታር መሬት ያላቸው መሆኑንና ጫት የተከለ በመሆኑ በዓመት ከመቶ ስልሳ ሺህ ብር በላይ እንደሚያገኙ፣
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የተጠሪንና የአመልካቾችን ክስና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ አመልካቾች የተጠሪን ክስና ማስረጃ ያስተባበለ መሆኑን ገልፆ ከተሰሱበት ወንጀል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነሥርዓት ሕግ 149 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት በነፃ አሰናብቷቸዋል። ተጠሪ ይግባኝ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጨማሪ ማጣሪያ ካደረገና ተጨማሪ ምስክሮች ከሰማ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔን አፅንቷል። ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአመልካቾችን የመከላከያ ማስረጃ ታዓሚነትና ክብደት የላለው በመሆኑ የተጠሪን ክስና ማስረጃ ለማስተባበል አይችልም በማለት አንደኛ አመልካች በሶስት ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ክስ የቀረበበት ንብረት እንዱወረስ፣ ሁለተኛ አመልካች በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ፣ ቅጣቱ እንዱገደብና በስሟ ያለና ክስ የቀረበበት ገንዘብ እንዱወረስ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች ታህሣሥ 5 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የማረም እንጂ ፍሬ ጉዲይ የማጣራት ስልጣን አልተሰጠውም። ዐቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሰውን ገንዘብ ከየት እንዲገኘው አስረድተን እያለ ፍርድ ቤቱ የእኛን የመከላከያ ማስረጃ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የእግድ ትዕዛዝ የተሰጠበት ገንዘብም እንዱወረስ መደረጉ ተገቢነት የለውም።
ስለዚህ በሰበር ታይቶ ይሻርልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ መጋቢት 2 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አመልካቾች ያቀረቡትን የፍሬ ጉዲይ ክርክር የመመርመር ሥልጣን የለውም። ይህ የሚታለፍ ቢሆን አመልካቾች የወንጀል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ በተለይም በይግባኝ በሚሰማበት ጊዜ ያመጡት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ውድቅ ያደረገው በአግባቡ ነው። አመልካቾች ወንጀለን የፈፀሙ መሆኑ ተረጋግጧል። ስለዚህ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
አመልካች መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ይህም ፍሬጉዲይ በማጣራትና ማስረጃ በመመዘን ሂደት በክልለ ፍርድ ቤቶች ወይም ላላ የዲኝነት ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት የፈፀሙት ስህተት ቢኖር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችልት ፍሬጉዲይ አጣርቶና ማስረጃ መርምሮና መዝኖ የማረም ሥልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን ነጥብ እንድናይ የሚያስገድደን ሆኖ አግኝተነዋል። በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዳሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀጽ 3/ለ/ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዲዮች ላይ የተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ለማረም በሰበር ችልት የማየት ስልጣን እንደሚኖረውና ክርክሩ በሕግ እንደሚወሰን ይደነግጋል። በ1994 ዓ.ም ተሻሽል የወጣው የክልለ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 75 ንዐስ አንቀፅ 2/ሐ/ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የማረም ሥልጣን ያለው መሆኑን በግልፅ ይደነግጋል። የክልለ የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 43/1994 አንቀፅ 5 ንዐስ አንቀፅ 3 የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበትን በክልል ጉዲዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሣኔ በሰበር የማየት ሥልጣን ያለው መሆኑን ይደነግጋል። ከላይ የጠቀስናቸውን የፋዳራል ሕገ-መንግስት፣ የክልለ ሕገ-መንግስት፣ የክልለ አዋጅ ቁጥር 43/1994 ድንጋጌዎች ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ፍሬጉዲይ የማጣራት፣ ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን የሚሰጡ ሆነው አላገኘናቸውም። ስለሆነም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የተጠሪንና የአመልካቾችን ማስረጃ በዝርዝር በመመርመርና በመመመዘን የተጠሪን ማስረጃ የወንጀል ክሱን የማስረዲት ብቃትና ታማኝነት አለው።
የአመልካቾች ማስረጃ ታዓሚነትና ክብደት የላለው ነው በማለት የደረሰበትን መደምደሚያና፣ የግራ ቀኙን ማስረጃ መርምሮና መዝኖ የደረሰበትን መደምደሚያ መሰረት በማድረግ በአመልካቾች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ከላይ የገለፅናቸውን ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በያዝነው ጉዲይ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በዝርዝር የግራ ቀኙን ማስረጃ በመመዘንና በመመርመር ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ቢሆንም በውሣኔው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 በተከራካሪ ወገኖች ከሚጥለው የማስረዲት ግዳታ /Burden of proof/ አንፃር አመልካቾችና ተጠሪ በሕግ የተጣለባቸውን ግዳታ ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም? የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካቾችና በተጠሪዎች መካከል ያለውን አከራካሪ የፍሬጉዲይ ጭብጥ ለመወሰን መጣራት የሚገባቸውን ፍሬጉዲዮች በማጣራትና የግራ ቀኙን ማስረጃ የሕጉ ድንጋጌ የሚጥልባቸውን የማስረዲት ግዳታ መሰረት በማድረግ በመመርመርና በመመዘን ውሣኔ ሰጥተዋል ወይስ አልሰጡም? የሚለትን ጭብጦች በውስጡ የያዘ መሆኑ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ከሰጠው ውሣኔ ተረድተናል።
ከላይ የገለፅናቸውን ጭብጦች የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልት በአግባቡ በማየት ውሣኔ የሰጡባቸው መሆን ያለመሆኑን ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካቾች የተከሰሱበት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 33 እና አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 ተጠሪና አመልካች ያለባቸውን የማስረዲት ግዳታ /Burden of proof/ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካቾች የተከሰሱበትን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 33 እና አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 ዝርዝር ይዘት ተመልክተናል።
“ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ” የሚል ርዕስ ያለው የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 በንዐስ አንቀጽ 1 “የመንግስት ሰራተኛ የሆነ ወይም የነበረ ማንም ሰው /ሀ/ የኑሮ ደረጃው አሁን ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ሥራ ወይም በልላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ሕጋዊ ገቢ የበለጠ እንደሆነ ወይም፣ /ለ/ ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ አሁን ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ሥራ ወይም በልላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ሕጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ፣ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ እንዳት ሉኖረው እንደቻለ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ በእጁ እንዳት ሉገባ እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዲ በስተቀር እንደሁኔታው የንብረቱ መወረስ ወይም ለባለቤቱ መመለስ እንደተጠበቀ ሆኖ በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ነገሩ ከባድ ሲሆን ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በመቀጮ ይቀጣል” የሚል ይዘት ያለው ነው።
ተጠሪ አንደኛ አመልካች ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ጉዲይ በወንጀል ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ በክልለ በተለያየ ደረጃ የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ እየሰራ ያገኘው የተጣራና የታወቀ ገቢ ብር 90,220 /ዘጠና ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ብር/ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ እንዲለው በክሱ ከገለፀ በኋላ አመልካቾች በስማቸው በተለያዩ ባንኮች ባላቸው ሂሳብና በልጃቸው ስም የገዙት ቤት ብር 2,081,468.90 /ሁለት ሚሉዮን ሰማኒያ አንድ ሺህ አራት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ ያላቸው በመሆኑ ምንጩ ያልተወቀ ሀብት ይዘው ተገኘተዋል በማለት ክስ ያቀረበ ሲሆን ተጠሪ አንደኛ አመልካች የመንግስት ሰራተኛ በነበረበት ጊዜ ያገኝ የነበረውን ገቢ፣ ሁለተኛ አመልካች የቤት እመቤት መሆናቸውንና ንብረቱ በጥሬ ገንዘብ ያለ በስማቸው ያለ መሆኑንና አመልካቾች በልጃቸው ስም ቤት ያላቸው መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ እንዲቀረበ ፍሬጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
አመልካቾች በበኩላቸው በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ የተገኘው ገንዘብና ቤቱን የሰሩበትን ሀብት ምንጭ ለማስረዲት የመከላከያ ማስረጃዎች እንዲቀረቡ ከሥር ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልቱ ከሰጡት ውሣኔ ተረድተናል።
እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አመልካቾች ተጠሪ ያቀረበውንና በማስረጃ ያረጋገጠውን ፍሬጉዲይ ማለትም በግልፅ ከሚታወቀውና አንደኛ አመልካች ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ሰራተኛነት ያገኝ ከነበረው ሕጋዊ ገቢ በላይ በባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው የተገኘው ጥሬ ገንዘብና በልጃቸው ስም ቤት የሰሩበት ሀብት ማለት ብር 2,081,468.90 /ሁለት ሚሉዮን ሰማኒያ አንድ ሺህ አራት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ ትክክለኛ ምንጭ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነት አለባቸው ወይስ የዐቃቤ ሕግን ክስና ማስረጃ ሉያስተባብለ የሚችለ አንድ አንድ ፍሬጉዲዮችን ለፍርድ ቤት ማቅረባቸው በቂ ይሆናል ወይስ አይሆንም የሚለውን ነጥብ በወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ከተደነገገው የማስረዲት ግዳታ አንፃር መመርመር አስፈላጊ ነው።
ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀፅ 1/ሀ/ እና /ለ/ ድንጋጌዎች ለመረዲት የሚቻለው ዐቃቤ ሕግ የመንግስት ሰራተኛ የሆነው ወይም የነበረው ሰው ያገኝ የነበረውና የሚያገኘው ገቢ ምን ያህል እንደሆነና የመንግስት ሰራተኛው በራሱ ስምም ሆነ በቤተሰቡ ስም ከሕጋዊ ገቢው ውጭ ይዞት የሚገኘውን የገንዘብና የንብረት ግምት የማስረዲት ግዳታ ያለበት መሆኑን በግልፅ ተደንግጓል። በልላ በኩል የመንግስት ሰራተኛ የነበረው ሰውና ከእሱ ጋር በልዩ አባሪነት የተከሰሰ ሰው የመንግስት ሰራተኛው ሲያገኝ ከነበረውና ከሚያገኘው ገቢ በላይ ይዞት የተገኘው ገንዘብ ወይም ሀብት ትክክለኛው ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዲት ግዳታ እንዲለበት በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 ሶስተኛው ፒራግራፍ፣ “….የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ እንዳት ሉኖረው እንደቻለ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ በእጁ እንዳት እንደገባ ለፍርድ ቤቱ ካላስረዲ በስተቀር” ምንጩ ያልተወቀ ሀብት ይዞ በመገኘቱ /በመገኘታቸው/ ጥፊተኛ ተብለው በሕጉ የተደነገገው ቅጣት ሉጣልባቸው እንደሚችል በግልፅ ይደነግጋል። ከዚህም የምንረዲው ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ከሚታወቀው ሕጋዊ ገቢ በላይ ነው በማለት በክሱ የገለፀውንና በማስረጃ ያረጋገጠውን ሀብት ትክክለኛ ምንጭ የማስረዲት ግዳታ /Burden of proof/ በተከሳሾች ላይ የሚወድቅ መሆኑን ነው። የተከሳሾች የማስረዲት ግዳታም ዐቃቤ ሕግ በክሱ ከገለፀውና በማስረጃ ካረጋገጠው ውጭ ተከሳሾች ላላ ገቢ የሚያገኙበት ሥራ ወይም የገቢ ምንጭ ያላቸው መሆኑን ብቻ ለፍርድ ቤቱ በማሳየት የሚወሰን ሳይሆን፣ በዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከተረጋገጠው ገቢ ውጭ በእጅ እንደተገኘ የተረጋገጠው ገንዘብና ሀብት ትክክለኛ ምንጭ ምን እንደሆነ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነት ያለበት መሆኑን ከወንጀል ሕግ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀፅ 1 ሶስተኛው ፕራግራፍ ድንጋጌ አቀራረፅና ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አንደኛው አመልካች የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ከሚያገኘው ደመወዝ /ሕጋዊ ገቢ/ በላይ በስማቸው በተከፈተ የባንክ ሂሳብና በልጃቸው ስም ቤት የተሰራበትና እንደያዙት የተረጋገጠው በአጠቃላይ መጠኑ ብር 2,081,468.90 /ሁለት ሚሉዮን ሰማኒያ አንድ ሺህ አራት መቶ ስልሣ ስምንት ብር ከዘጠና ሣንቲም/ የሆነ ገንዘብና ሀብት ምንጩ በአንደኛ አመልካች ስም በወንድገነት ወረዲ አባዮ ቀበላ ካለው 2.5 ሄክታር የመሬት ይዞታ ላይ ካለሙት የጫትና የቡና ሰብል ሽያጭ፣ በሁለተኛ አመልካች ስም 0.25 ሄክታር መሬት ላይ ካለሙት የሸንኮራ አገዲ እንደሆነ፣ ከፉለን በብድር ከግለሰብ ያገኙት መሆኑንና ከፉለ የጋራራሙ ላንቶ የእንስሳት ማድለብና ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና የጋልማ ባህላዊ ልጅ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንዲቀረቡ ከሥር ፍርድ ቤትና ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ችልት ውሣኔ ተገንዝበናል።
ሆኖም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካቾች ያቀረቧቸው ማስረጃዎች አንደኛ አመልካች ከሚሰራው የመንግስት ስራ በተጨማሪ ላላ የገቢ ምንጭ የነበረው መሆኑን የሚያሣዩ ማስረጃዎች መሆናቸውን በመመልከት ብቻ መጣራት የሚገባቸው ፍሬጉዲዮችን ሳያጣሩና በተለይም አመልካቾች በዐቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ከሕጋዊ ገቢያቸው በላይ የያዙ መሆናቸውን ብር 2,081,468.90 ያገኙበትን ትክክለኛ የገቢ ምንጭ የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀፅ 1 በሚደነግገው መሰረት የማስረዲት ግዳታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ በሕጉ በአመልካቾች ላይ የተጣለውን የማስረዲት ግዳታ /Burden of proof/ መሰረት በማድረግ ተገቢውን ማጣራት አድርገው መርምረውና መዝነው ውሣኔ የሰጡ አለመሆናቸውን ከውሣኔያቸው ይዘት ለመረዲት ችለናል። ምክንያቱም /ሀ/ አመልካቾች በስማቸው እንዲለና ጫት፣ እንሰት፣ ቡናና ሸንኮራ አገዲ እያለማን ገቢ እናገኝበታለን ያለት 2.25 ሄክታር መሬት በተመለከተ አመልካቾች የእርሻ መሬቱ ባለይዞታ ናቸው ወይስ አይደለም? የእርሻ መሬቱ ባለይዞታ ከሆኑ የእርሻ መሬቱን በይዞታነት የያዙት መቼ ነው? መሬቱን በማልማት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ተክልች በማልማት ምርት ገቢ ማግኘት የጀመሩት መቼ ነው? ከመሬቱ የሚገኘው ገቢና መሬቱን ለማልማትና ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የሚወጣው ወጭ ምን ያህል ነው? አመልካቾች ከመሬቱ ተጣርቶ የሚደርሳቸው ገቢ ምን ያህል ነው የሚለው ፍሬጉዲይ በአግባቡና በገለልተኛ ባለሙያ ተጣርቶ ባልታወቀበት ሁኔታ ከቀበላና ከዞኑ ግብርና ጽ/ቤት የተፃፈ ደብዲቤዎችን ብቻ መሰረት በማድረግ አመልካቾች ከእርሻ የሚያገኙት ገቢ መጠን ከፍተኛ እንደሆነ መወሰኑ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀፅ 1 በአመልካቾች ላይ የሚደነግገውን የማስረዲት ግዳታ /Burden of proof/ መሰረት በማድረግ ጉዲዩ ተጣርቶ የተወሰነ አለመሆኑን የሚያሣይ በመሆኑ፣ /ለ/ አመልካቾች በባንክ ሑሳባቸው ውስጥ ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ ብር 1,120,500 /አንድ ሚሉዮን አንድ መቶ ሃያ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በአንደኛው አመልካች ስም የተቀመጠ ከፉለ የጋራራሙ ላንቶ የእንስሳት ማድለብ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ገንዘብ ከፉለ ደግሞ የጋልማ ባህላዊ ልጅ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሆኑን ለማስረዲት የማህበራቱ ቃለጉባኤና አባላት በማስረጃነት ያቀረቡ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤትና ከይግባኝ ሰሚው ችልት ውሣኔ ተገልጿል። ሆኖም በመጀመሪያ ደረጃ ኃላፉነታቸው የተወሰኑ የግል ማህበራት የሚመሰርቱት የማህበሩ ዋና ገንዘብ ልክና የማህበሩ ዋና ገንዘብ በሙለ መግባቱን የሚያስረዲ መግለጫ ሲቀርብ መሆኑ በንግድ ሕጉ አንቀፅ 519 ንዐስ አንቀጽ /መ/ እና /ሰ/ በአስገዲጅነት የተደነገገ በመሆኑ እነዚሀ የንግድ ማህበራት ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው ተመዝግበው ከሆነ ሲመዝገቡ ያስመዘገቡትና ገቢ ያደረጉት የማህበሩ ዋና ገንዘብ ምን ያህል ነው? ማህበራቱ በካፑታልነት ካሰመዘገቡት ካፑታል በላይ በአመልካቾች ስም ለማህበር መመስረቻ የተዋጣው ገንዘብ አለ በማለት የሚፅፈቸው የተለያዩ ማስረጃዎች ሕጋዊ ተቀባይነት፣ ያላቸው ናቸው ወይስ አይደለም? የሚለት ነጥቦች ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አመሰራረት፣ መዋጮ አከፊፈል፣ የማህበሩ ዋና ገንዘብና ገንዘቡ ገቢ ስለሚሆንበት ሁኔታ የተቀመጡ ሕጋዊ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ፣ መጣራት የሚገባቸው ፍሬጉዲዮች ተጣርተውና ማስረጃዎቹ አመልካቾች በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 ያለባቸውን የማስረዲት ኃላፉነት መሰረት በማድረግ ተጣርተው ውሣኔ የተሰጠበት ሆኖ አላገኘንም።
ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ችልት ከላይ የዘረዘርናቸውን መጣራት የሚገባቸውን ፍሬጉዲዮች ሳያጣራና አመልካቾች ያቀረቧቸው ማስረጃዎች በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 የተጣለባቸውን የማስረዲት ግዳታ /Burden of proof/ የተወጡ መሆኑን ያለመሆኑን የሚያሣዩና አግባብነት ያላቸውን ሕጎች መሰረት ያደረጉና ተቀባይነት ያላቸው ናቸው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመመስረት ውሣኔ ያልሰጡበት በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የተጠሪንና የአመልካቾችን ማስረጃ በዝርዝር በመመርመርና በመመዘን የሰጠው ውሣኔም ሆነ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት ከላይ በዝርዝር የገለፅናቸውን ፍሬጉዲዮችን ሳያጣራና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ የአመልካቾችን ማስረጃ ተቀባይነት ሳይመረምሩ የሰጡት ውሳኔ የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 419 ንዐስ አንቀጽ 1 ድንጋጌዎችና ከላይ የዘረዘርናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች የሚጥሱና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው ናቸው በማለት ወስነናል።
የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት ከዚህ በፉት ጉዲዩን ያላዩት ዳኞች በመሰየም በዚህ ፍርድ በተራ ቁጥር 2/ሀ/ እና /ለ/ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማጣራትና የማስረጃዎቹን ተቀባይነት፣ ክብደትና ተዓሚነት በመመዘን በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 149/1/ መሰረት ፍርድ እንዱሰጥበት ጉዲዩን መልሰንለታል።
የውሣኔው ግልባጭ ይላክለት።
No topics extracted.