No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣስ 4 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የመከላከያ ወታደራዊ ተከላካይ ጠበቃ- ሃምሣ አለቃ ተስፊዬ ቦያለው ቀረቡ ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ክልል ዐቃቤ ህግ አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የመከላከያ ሰራዊት አባል በመደበኛ ፍርድ ቤት የቀረበበትን የወንጀል ክስ ለመከላከል የሚያስችለው የህግ ድጋፍ መስጠትን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የመከላከያ ሰራዊት አባል በሆኑት ሀምሣ አለቃ ቴውድሮስ ሃይለስላሴ በፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 361/11ሀ በመተላለፍ ባለ አንድ መቶ ሐሰተኛ የብር ኖት (100) ይዘው ተገኝተዋል የሚል የወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል። ተከሣሳሹ የተከሰሱበት የወንጀል ክስ ተገቢውን የህግ ድጋፍ እንዱያደርግና በተከላካይ ጠበቃ እንዱታገዝ የመከላከያ ሰራዊት መከላከያ ጠበቃ መድቧል። የዞኑ አቃቤ ህግ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መከላከያ ሚኒስቴር ተከላካይ ጠበቃ የሚያቆመው በመደበኛ ፍ/ቤት በሚያስከስሱ ወንጀልች ሣይሆን በጦር ፍ/ቤት በሚያስከስሱ ወንጀልች ብቻ ነው። ስለዚህ የመከላከያ ወታደራዊ ተከላካይ ጠበቃ ተከሳሹን ወክል ለመከራከር አይችልም የሚል መቀወሚያ አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት የዞኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን መቃወሚያ በመቀበል የመከላከያ ወታደራዊ ተካላካይ ጠበቃ ለተከሳሹ የህግ ድጋፍ የመስጠት በተከላካይ ጠበቃነት ቆሞ ለመከራከር አይችልም የሚል ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅረቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የልዩ ዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን አፅንቶታል። አመልካች የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነውን ተከሳሽ እንድንከላከል የበታች ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 27/1988 ድንጋጌዎችን የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወታደራዊ ተከላከይ ጠበቃ እንዱታገዙ አዋጅ ቁጥር 27/1988 የሚፈቅደው በወታደራዊ ፍርድ ቤት በሚከሰሱበት ጊዜ ብቻ ስለሆነ ለተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ ለማቆም ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የህግ ትርጉም ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የመከላከያ ሰራዊት አባል ያሆኑት ሃምሣ አለቃ ቴድሮስ ሀይለስላሴ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 361 ንዐስ አንቀጽ 1(ሀ) የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ፈፅሟል የሚል የወንጀል ክስ በተጠሪ በኩል ቀርቦበታል።
የመከላከያ ሰራዊት አባለ የተከሰሱበት ወንጀል ከአስር ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 361 ንዐስ አንቀጽ 1 (ሀ) ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል።
አዋጅ ቁጥር 27/88 በአዋጅ ቁጥር 123/90 እንደተሻሻለ ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈፃሚነት ያለው የህግ ማእቀፍ ሲሆን በዚህ መዝገብ የተያዘው ጭብጥ የአዋጅ ድንጋጌ ብቻ ሣይሆን የህገ መንግስቱን አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 5 ተፈፃሚነት መመርመር የሚጠይቅ ነው። ተከላካይ “ስለማቆም” የሚል ርእስ ያለው የአዋጅ ቁጥር 27/1988 አንቀፅ 35 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ፤ “ራሱ ተከላካይ ጠበቃ ለማቆም ለማይችል ከአምስት ዓመት በማያንስ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ ሰው መንግስት ተከላካይ ጠበቃ ይመደብለታል የሚል ይዘት ያለው ሲሆን የእንግሉዘኛው ቅጅ “the state shall provide a defence counsel to a person charged with an offence punishable by imprisonment not less than five years and un able to retain a counsel” በሚል መንገድ የተደነገገ መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት ተገንዝበናል። የአንቀጽ 35 ንዐስ አንቀጽ 2 በዚህ “አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት በተከላካይ ጠበቃነት ለማቆም የሚችለው ከሰራዊቱ አባል መካከል ይሆናል። በማለት በግልፅ ይደነግጋል። ከላይ የተገለፀው የህግ ድንጋጌ ማንኛውም የመከላከያ ሰራዊት አባል በወታደራዊ ፍርድ ቤትም ሆነ በመደበኛ ፍርድ ቤት ከአምስት ዓመት በማያንስ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ፈፅሟል ተብል ክስ ሲቀረብበትና በራሱ ተከላካይ ጠበቃ ለማቆም የማይችል በሆነ ጊዜ መንግስት የህግ እውቀትና ልምድ ያለው የመከላከያ ሰራዊት አባል የሆነ ተከላካይ ጠበቃ በነፃ የማቆምና የመከላከል ግዳታ እንዲለበት የሚደነግግ ነው።
አዋጅ ቁጥር 27/88 አንቀጽ 35 መንግስት ለሰራዊቱ አባላት በነፃ ተከላካይ ጠበቃ በማቆም የቀረበባቸውን የወንጀል ክስ እንዱከላከል በህግ የሚገዲድበትን ዝቅተኛ መስፈርት (minimum standard) የሚደነግግ ሲሆን የአገር መከላከያ ሚኒስትር የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግዲጅ ላይ እያለ ፈፀመውታል ተብል በተከሰሱበት ከ5 አመት እስራት በታች በሚያስቀጣ ወንጀል ተከላካይ ጠበቃ በነፃ ለማቆምና ለመከላከል ከፈለገ በወታደራዊ ፍ/ቤትም ሆነ በማናቸውም ደረጃ በሚገኝ መደበኛ ፍ/ቤት ተከላካይ ጠበቃ በመወከልና በነፃ የቀረበውን የወንጀል ክስ መከላከል የአዋጁ አንቀጽ 35 ድንጋጌዎችን የሚገድቡት እንዲልሆነ ከድንጋጌው አቀራረፅ ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ ለመገንዘብ ይቻላል።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ የአዋጅ ቁጥር 27/1988 አንቀፅ 35 ድንጋጌዎች በወንጀል የተከሰሱ የመከለከያ ሰራዊት አባላት በግላቸው ጠበቃ ለማቆም የማይችለ በሆነ ጊዜ ፍትህ ሉጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም በመንግስት ወጪ የጠበቃ ድጋፍና እርዲታ የማግኘት መብት እንዲላቸው በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 5 የተደነገገውን በማጣብብና በተሻሻለ ሁኔታ የህገ መንግስቱን ድንጋጌ ተፈፃሚ በሚያደርግ መንገድ መተርጏምና ተግባራዊ መሆን አለበት። ስለሆነም ማንኛውም የመከላከያ ሰራዊት አባል ከ5 አመት በማያንስ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል በመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም በወታደራዊ ፍርድ ቤት የወንጀል ክስ በቀረበበት ጊዜና ተከሳሹ በግለ ተከላካይ ጠበቃ ለማቆም የማይችል ሲሆን የመከላከያ ወታደራዊ ጠበቃ ድጋፍ በነፃ ማግኘት በአዋጅ ቁጥር 27/1988 አንቀጽ 35 የተደነገገ የሰራዊቱ አባል መብትና የአገር መከላከያ ሚኒስትር ህጋዊ ግዳታ ሲሆን የሰራዊቱ አባል በአምስት ዓመት በማያንስ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል በመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም በመከላከያ ፍርድ ቤት ክስ በቀረበበት ጊዜ የአገር መካከላያ ሚኒስትር በነፃ የተከላከይ ጠበቃ ድጋፍ የሰራዊት አባል ማግኘት አለበት ብል ካመነ የመከለከያ ወታደራዊ ጠበቃ በነፃ የህግ ድጋፍና እገዛ እንዱያደርግለት በማድረግ መከላከል የሚችል መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 27/1988 አንቀጽ 35 ድንጋጌዎች ይዘትና ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 5 ድንጋጌ ለመገንዘብ የሚቻል ሆኖ እያለ የመከላከያ ሰራዊት አባል በመከላከያ ወታደራዊ ጠበቃ ነፃ የህግ ድጋፍ የሚያገኘው በወታደራዊ ፍርድ ቤት በወንጀል ሲከሰስ ብቻ ነው በማለት ተጠሪ ያቀረበውን የህግ መሰረት የላለው መቃወሚያ በመቀበል ተከሣሹ በመከላከያ ወታደራዊ ጠበቃ ነፃ የህግ ድጋፍ እንዲያገኝ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ብይን ተሽሯል።
አመልካች የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በመደበኛ ፍርድ ቤት በወንጀል በተከሰሱበት ጉዲይ በነፃ የህግ ድጋፍና እገዛ የማድረግና የመከላከል መብት አለው በማለት ወስነናል።
ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የማይነብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.