No summary available.
ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ደረጀ ጎሳዬ - ጠበቃ ወገኔ ካሳሁን ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አቃቤ ሕግ የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ለዋስትና የተያዘ ገንዘብ ይመለስልኝ ጥየቄን የሚመለከት ነው። አመልካች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል በሶስት ምድብ የተከፈለ ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤቱ ለአመልካች የዋስትና መብቱን ጠብቆለት አመልካች ብር 500,000.00(አምስት መቶ ሺህ ብር) አስይዞ የተጠበቀለትን የዋስትና መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ ሲፈልግ በቼክ ጉዲይ በወንጀል ተከሶ የእስር ቅጣት በመፈረደ ምክንያት ማረሚያ ቤት በመግባቱ የዋስትና መብቱን ሉጠቀምበት ያለመቻለን ገልጾ በክርክር ሂደት ላይ ላለው ጉዲይ ያስያዘው የዋስትና ገንዘብ እንዱመለስለትና ጉዲዩን ከማረሚያ ቤት እየተመላለሰ እንዱከታተል ይደረግ ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል። አቤቱታው በዚህ መልክ የቀረበለት የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የአመልካችን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል። በዚህ ትዕዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ጉዲዩ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 75 መሰረት ይግባኙ የቀረበበት መሆኑን ገልፆና ይህ ድንጋጌ የሚያገለግለው የዋስትና መብት ሲነፈግ ይግባኝ ለማቅረብ ነው የሚል ምክንያት ይዞ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች በልላ ወንጀል በተፈረደው ፍርድ መሰረት ማረሚያ ቤት የሚቆይ በመሆኑ ለላላ ጉዲይ የተጠበቀው የዋስትና መብት ተግባራዊ የማይሆን መሆኑ ግልጽ ስለሆነ ለጉዲዩ የተያዘው ገንዘብ እንዱመለስ መጠየቁ ተቀባይነት የሚያጣበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች በልላ መዝገብ ፍርደኛ በመሆኑ ከማረሚያ ቤት ተመላልሶ መከራከር የሚችል ቢሆንም ለዋስትና ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለትም ተጠሪ ቀርቦ በጽሐፍ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የዋስትና ገንዘብ ያስያዘው በተጠሪ መስሪያ ቤት አቃቤ ሕግ የተለያዩ የጉምሩክ ሕግ ድንጋጌዎች ተላልፎል ተብል በቀረቡት ሶስት ክሶች የዋስትና መብት በፍርድ ሲጠበቅለት ሲሆን በልላ በኩል ደግሞ በቼክ ጉዲይ ተከሶ የአራት አመት ከስድስት ወር ፍርደኛ ሆኗል። ገንዘቡ እንዱመለስለት የሚጠይቀውም ፍርድ ቤት ያለውን የጉምሩክ ወንጀል ክርክርን ከማረሚያ ቤት በመመላለስ የሚከታተል መሆኑን በመገንዘብ ነው።
በመሰረቱ ዋስትና ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑንና ይህ መብት በልዩ ሁኔታ በሕጉ ክልከላ ካልተደረገ በስተቀር ለተከሰሱ ሰዎች ሉጠበቅ የሚችል መሆኑን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 19(6) ድንጋጌ በግልፅ ያሳያል። በሕጉ አግባብ የዋስትና መብት ሲፈቀድ ደግሞ የተከሳሹ ፍርድ ቤት መቅረብ እውን እንዱሆን ተከሳሹ ገንዘብ እንዱያስይዝ ወይም ላላ ዋስትና እንዱያቀርብ የሚደረግ መሆኑን የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 69(1) ድንጋጌ ያስረዲል። የዋስትና መብት የተፈቀደለት ተከሳሽ መብቱን ለመቀጠም የማያስችል ሕጋዊ ምክንያት ያለው መሆኑን በመግለፅ መብቱን ለመጠቀም ካልፈለገ ደግሞ መብቱ የራሱ ይሆናል። በፍርድ ቤት የተፈቀደለትን የዋስትና መብት ያለመጠቀም ፍላጎት ደግሞ የዋስትና መብት እንደተፈቀደ ወይም ከተፈቀደና ተከሳሹ መብቱን መጠቀም ከጀመረ በኋላም ሉመጣ ይችላል። ሕጋዊ ምክንያት እስካለው ድረስ በማንኛውም ደረጃ ተከሳሹ በሕጉ አግባብ የተፈቀደለትን የዋስትና መብት የመተው ፍላጎቱ ሉጠበቅለት የሚገባው ጉዲይ እንጂ ይህንኑ መብቱን ለመከላከል የሚያስችል ግልጽ ድንጋጌ የለም። ፍርድ ቤቱ ትኩረት ሉያደርግና ሉቆጣጠረው የሚገባው ቁልፍና ዋናው ነገር በፍርድ ቤት ክስ የቀረበበት ሰው ቀጠሮውን ተከታትል የሚቀርብበት ትዕዛዝ መስጠቱ ነው። ይህ ደግሞ የተከሳሽን የዋስትና መብት በማክበር ተገቢውን ዋስትና በማስጠራት ወይም ተከሳሹ ማረሚያ ቤት ሆኖ ሉፈፀም የሚችል ስለመሆኑ ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 68 እና 69 ድንንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። ስለሆነም አንድ ተከሳሽ የዋስትና መብቱ ከተከበረለት በኋላ በሕጋዊ ምክንያቶች መብቱን በመተው ጉዲዩን ማረሚያ ቤት ሆኖ ለመከታተል ፍላጎት ያለው መሆኑን ሲገለጽ ሉነፈግ አይገባም። የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የአመልካችን የዋስትና ገንዘብ ይመለስልኝ ጥያቄ ያልተቀበለው አመልካች በዋስ የተለቀቀበት መዝገብ እልባት ያላገኘና ማረሚያ ቤት በልላ ወንጀል ገብቷል የተባለውም በውሳኔ ይሁን በልላ ምክንያት አልተረጋገጠም በሚል ሲሆን የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ ይግባኙ የሚቀርበው የዋስትና መብት ሲከለከል ነው በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ አመልካች በልላ ወንጀል ፍርደኛ መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች በተደረገው ክርክር የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 75”ን” ለአቤቱታው መሰረት ማድረጉም አቤቱታውን ለማስተናገድ ፍርድ ቤቱ አልችልም ብል ውድቅ ለማድረግ ሥነ ሥርዓታዊ ምክንያት ላሆን አይችልም። ፍርድ ቤቶቹ አመልካች እልባት ያላገኘውን ጉዲይ ከማረሚያ ቤት በመመላለስ የፍርድ ቤትን ቀነ ቀጠሮውን አክብሮ የሚከታተልበት አግባብ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ትዕዛዝ በመስጠት ይህንኑም እንዱፈፅም ለማረሚያ ቤቱ ማስተላለፍ ሲገባቸው ሕጋዊ መሰረት የላላቸውን ምክንያቶችን በመያዝ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ከአመልካች የንብረት መብትና መብቱ ሉያስገኝ የሚችለውን ፍሬ ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 68 እና 69 ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 08 ቀን 2003 ዓ/ም የጸናው ትዕዛዝ ተሽሯል።
አመልካች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በቀረቡት ክሶች ያስያዘው የዋስትና ገንዘብ እንዱመለስለት ብለናል። አመልካች በዚህ መዝገብ የተያዘውን ጉዲይ ማረሚያ ቤት ሆኖ እንዱከታተል የማሰሪያ ዋራንት ለማረሚያ ቤት ይፃፍ። የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ለአመልካች ገንዘቡን እንዱያስመልስ ብለናል።
No topics extracted.