No summary available.
ጥር 01 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ፊሲል በላይነህ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ፋዳራል ዐቃቤ ሕግ - አደናይ ተ/ብርሃን ቀረቡ መዝገቡ ተመረምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በሕግ አግባብ የተወከለ ሰው በውክልና ስልጣኑ ከወካዩ የተረከባቸውን ንብረቶች ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ ሲረጋገጥ በወንጀል የሚጠየቅበት አግባብ መኖር ያለመኖሩን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ የተጀመረ ነው። የክሱ ይዘትም አመልካች በ1996 ዓ.ም.
የወጣውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል መቅጫ ሕግ አንቀጽ 676(2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት በማሰብ ሚያዚያ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. ሰዓቱ በውል በማይታወቅበት በአራዲ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15/16 ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ስጋ መደዲ አከባቢ የግል ተበዲይ ወ/ሪት አዱስ አያል የካቲት 20 ቀን 2001 ዓ/ም ውክልና ሰጥታው በውክልና መሰረት የንግድ ድርጅት ለሁለት አመት ኮንትራት ይዞ ሲሰራ፡- 1ኛ/ የቤት ኪራይ አስራ ስምንት ሺህ ብር፣ 2ኛ/ ቪዱዮ ካሜራ አስራ ሁለት ሺህ ብር የሚያወጣ፣ 3ኛ/ አንድ ብርድ ልብስ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር የሚያወጣ፣ 4ኛ/ የተለያዩ ንብረቶች ግምታቸው አስራ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር የሚያወጡ በአጠቃላይ ግምት ብር 48,000.00 (አርባ ስምንት ሺህ ብር) የሚያወጡ ንብረቶችን ተረክቦ መልስ ሲባል አልመልስም በማለት በፈጸመው ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው። አመልካች ጉዲዩ የፍትሒብሓር እንደመሆኑ መጠን በወንጀል የሚጠየቁበት አግባብ የለም በማለት የክስ ተቃውሞ አቅርበው የነበሩ ሲሆን ይኸው ተቃውሞ ውድቅ ሆኖ ግን ስለእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቅ የድርጊቱን አፈፃፀም በተመለከተ የክህደት ቃለን ሰጥቷል። አቃቤ ሕግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን አቅርቦ ካሰማ በኋላ አመልካች የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት የመከላከያ ምስክሮችን አሰምቷል። የሥር ፍርድ ቤትም ጉዲዩን መርምሮ አመልካች በመከላከያ ምስክሮች የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ሉያስተባብለ አልቻለም በሚል ምክንያት ክስ በቀረበበት ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጎ በአምስት አመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል። አሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውን ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዲዩ የፍትሒብሓር ጉዲይ ከሚሆን በስተቀር በወንጀል የሚያስጠይቅበት አግባብ የለም፣ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች እንደክሱ አላስረደም፣ የመከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ የተደረገውም ያላግባብ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች በወንጀል ጥፊተኛ ተብለው የመቀጣታቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለትም ቀርቦ በጽሐፍ በሰጠው መልስ አመልካች ጥፊተኛ የተባለት በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ተመዝነው በመሆኑ በሰበር ችልት የሚታይ አይደለም፣ ቅጣቱም ለድርጊቱ ተመጣጣኝና የቅጣት መመሪያውን መሰረት አድርጎ የተሰጠ በመሆኑ ሉጸና ይገባል የሚል ነው።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀለን የሚያቋቋሙት ሕጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 414/1996 የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(2) በግልጽ ደንግጓል። እንግዱህ አንድን ድርጊት ወንጀል ነው ብል ለመወሰን ሕጋዊ፣ ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች ተጣምረው መገኘት የግድ ይላል። ሕጋዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ ለጉዲዩ አግባብነት አለው ተብል የተጠቀሰውን ድንጋጌ ለማቋቋም ሙለ በሙለ መሟላት ያለባቸውን ነጥቦች የሚመለከት ሲሆን ግዙፊዊና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች የሚባለት ደግሞ እንደየቅደም ተከተላቸው ከድርጊት ማድረግ ወይም አለማድረግና ከሐሳብ ክፍል ጋር በሕጉ አንቀጽ 24፣ 57 እና 58 ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን የሚመለከቱ መሆኑ ይታመናል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመጣ አመልካች ጥፊተኛ የተባለት መውሰዲቸው የተረጋገጠውን ንብረት ግምቱ በአቃቤ ሕግ ክስ ማመልከቻ የተጠቀሰውን ያህል ባይሆንም በወኪልነት ስልጣናቸው ከግል ተበዲይ የተረከቡት ሆኖ እንዱመልሱ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ምክንያት ነው።
ይህ ፍሬ ነገር ጉዲዩን በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ በሚያውቁት የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ማስረጃዎች ያላስተባበለ መሆኑም በበታች ፍርድ ቤቶች በሚገባ መረጋገጡን ውሳኔው ያሳያል። አመልካች የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል የሚታመን አይደለም፣ የመከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው በማለት የሚያቀርበው ክርክር ሲታይም የማስረጃ ምዘና ጉዲይ በመሆኑ ለዚህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌ መሰረት ከተሰጠው የመሰረታዊ ሕግ ስህተት ማረም ስልጣን ስር የማይወድቅ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም አመልካች በዚህ ረገድ የሚያቀርቡት ክርክር ከሰበር ችልቱ ስልጣን አንጸር ሲታይ ተቀባይነት ያለው ባለመሆኑ አልፈነዋል። አመልካች የግል ተበዲይን ንብረት በውክልና ስልጣናቸው ወስደው ሉመልሱ ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ተረጋግጧል ከተባለ ይህ አድራጎት የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆን ያለመሆኑን መመልከቱ ተገቢ ይሆናል።
አንድ ወኪል ከወካዩ በውክልና ስልጣኑ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ ፈቃደኛ ካለሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 676(2) ድንጋጌ የሚጠየቅ ስለመሆኑ ተጠቃሹ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። ስለሆነም በውክልና ስልጣኑ መሰረት አደራ የተቀበለ ተዋዋይ ወገን እምነት አጉድሎል ተብል በወንጀል የሚጠየቅ ስለመሆኑ ስለእምነት ማጉደል የሚደነግጉት የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችም ያሳያለ።
በመሆኑም በወንጀል ሕግ አንቀጽ 676(2) መሰረት ወንጀል ነው ተብል የተጠቀሰው የወኪለ ድርጊት በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ከወንጀል ህግ አንቀጽ 23(2) እና ተጠቃሹ የወንጀል ህግ አንቀጽ 676(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ በግልጽ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በዚህም መሰረት አመልካች ለጉዲዩ በወንጀል ጥፊተኛ የተባለው የፍትሒብሓር ይዘት ብቻ ባለው ጉዲይ ነው ለማለት ስላልተቻለ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የወ/መ/ሕ/አንቀጽ 23(2) እና 676(2) ደንጋጌዎችን ያገናዘበ ሆኖ በመገኘቱ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ብለናል።
ቅጣቱን በተመለከተም የቅጣት አጣጣል መርሆዎችን የጣሰ ነው ለማለት አልተቻለም። በእነዚህ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 13 ቀን 2003 ዓ.ም.
የጸናው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2)) ጸንቷል።
አመልካች በወንጀል መጠየቃቸው በአግባቡ ነው ብለናል።
በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መፅናቱን በማወቅ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈፅም ለማረሚያ ቤት ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.