No summary available.
ሐምል 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ተካልኝ ጌታቸው - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የፋ/ዐ/ሕግ - አቶ አበባው መንግስቱ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ ተጠሪ የአሁኑን አመልካችን ጨምሮ በ6 ተከሳሾች ላይ ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካችም በ5ኛ ክስ 5ኛ ተከሳሽ ነበር። ክሱም ተከሳሾቹ በኢ/ፋ/ዱሪ/ወ ህግ አንቀጽ 32(1)(ለ) እና 692(1) በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ለወንጀለ አፈፃፀም እንዱረዲ ላላ ያልተያዘ አባሪያቸው ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር በ1ኛ ክስ የተጠቀሰውን ቼክ አመነዛዘር ላይ በመመካከር ለዚሁ ይጠቅማል ያለውን 3ኛ ተከሳሽን ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር በማገናኘት፣ 3ኛ ተከሳሽ 4ኛ ተከሳሽን ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር እንዱገናኝ በማድረግ፣ እንዱሁም 4ኛ ተከሳሽ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾችን ከ1ኛና 2ኛ ተከሳሾች ጋር አገናኝቶ በ6ኛ ተከሳሽ አማካይነት በቼኩ ላይ የተጠቀሰው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ወደ ወጋገን ባንክ ጎፊ ቅርንጫፍ በ6ኛ ተከሳሽ በተከፈተው ተንቀሳቃሽ ሂሳብ እንዱተላለፍ ከተደረገ በኋላ 3ኛ ተከሳሽ ብር 100,000፣ 4ኛ ተከሳሽ ብር 100,000 እና 5ኛ ተከሳሽ ብር 50,000 ወስደው ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው በመላ ሀሳባቸው እና አድራጎታቸው በወንጀል ድርጊት እና በሚሰጠው ውጤት ሙለ ተካፊይ በመሆን በፈፀሙት የማታለል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
አመልካችም ወንጀለን አለመፈፀሙንና ጥፊተኛ አለመሆኑን ክድ በመከራከሩ ክሱ የቀረበለት የፋ/ከ/ፍ/ቤት የግራቀኙን ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ በሰጠው ፍርድ 5ኛ ተከሳሽ ከባንኩ ተጭበርብሮ ከወጣው ብር 750,000 ውስጥ ብር 50,000 መውሰደን ለፕሉስ የተከሳሽነት ቃለን ሲሰጥ በቦታው የነበሩ የከሳሽ የደረጃ ምስክሮች መስማታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮች ደግሞ የተከሳሽ ቤት ሲበረበር ከማየታቸው በስተቀር ተከሳሹ ወንጀለን አለመፈፀሙን አላስረደም በሚል በወ/ሕ/ቁ/ 692 (1) ስር ጥፊተኛ ነው በማለት በ3 ዓመት እስራትና በ5,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጣ ወስኖበታል።
ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም የግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/195(2)(ለ)(2) መሰረት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ፍርድ በማጽናቱ አመልካች በከፍተኛው ፍ/ቤት ፍርድ እና በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል በሚል የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡- ክሱን ባቀረብኳቸው የመከላከያ ምስክሮች አስተባብዬ እያለሁ ፍርድ ቤቶቹ ማስረጃዎቼን በአግባቡ ሳይመዝኑ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ያስተላለፈብኝ ተገቢነት ያለው አይደለም በወንጀለ አመልካች አግኝቷል በሚል በማስረጃ የተረጋገጠው ብር 50,000 ሆኖ ከተረጋገጠው ውጪ ብር 250,000 እንደወሰድኩ ተቆጥሮ ከቅጣትና መቀጫ እርከን መነሻው በማጋነን በተሳሳተ ስላት የተወሰነብኝ ስለ ቅጣት አወሳሰን የወጣውን መመሪያ ያልተከተለ ነው የሚለ ናቸው።
ተጠሪ መዝገቡ ለሰበር ያስቀርባል በተባለው ጭብጥ መነሻ በሰጠው መልስ፡- አመልካች የተከሰሰውና ጥፊተኛ ሆኖ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት በአታላይነት ወንጀል በወ/ህ/አንቀጽ 692(1) ስር ሲሆን ከድንጋጌው መረዲት የሚቻለው ወንጀለ ለራስ ተገቢ ያለሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማስገኘት ሉፈጸም የሚችል በመሆኑ አመልካችም በፈጸመው ወንጀል ለራሱ የደረሰው ጥቅም ብር 50,000 ቢሆንም ላልች በወንጀለ የተሳተፈትም ቀሪውን ገንዘብ ተከፊፍለው ለግል ጥቅማቸው ያዋለ በመሆኑ ምክንያት ድርጅቱ ያጣው ብር 750,000 ስለሆነ አመልካችም ራሱ ጥቅሙን ከማግኘቱም ባሻገር ላልችም ጥቅም እንዱያገኙ ሀሳብ የነበረው በመሆኑ ከፍተኛው ፍ/ቤት ቅጣትን በሚወስንበት ጊዜ ላልች ተከሳሾች ያገኙትን ጥቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ጭምር የወሰነ ስለሆነ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም ብሎል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸ ሲሆን እኛም ከፍተኛው ፍ/ቤትም ሆነ የፈ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካች ላይ ያስተላለፈት የቅጣት ውሳኔ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ወደ ተያዘው ጭብጥ ከመመለሳችን በፉት አመልካች ለዚህ ችልት ካቀረባቸው ቅሬታዎች አንደ ክስ የቀረበበትን ወንጀል አለመፈጸሜን በመከላከያ ምስክሮቼ አስተባብዬ እያለሁ ፍርድ ቤቶቹ የግራቀኙን ማስረጃዎች በአግባቡ አልመዘኑም የሚል ነው። ይሁን እንጂ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሆነ የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ማስረጃዎች በማመዛዘን የተጠሪ ማስረጃዎች ያረጋገጡት ፍሬ ነገሮች የአመልካች የመከላከያ መስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻላቸው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፊቸውን መዝገቡ ያመለክታል። የፍሬ ነገር ጉዲዮችን የማጣራት ስልጣን ባላቸው ፍ/ቤቶች በተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መነሻ በተሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ በኢ/ፋ/ዱ/ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80 (3)(ሀ) እና በፋዳራል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የተፈፀመውን ስህተት ከሚያርም በስተቀር የፍሬ ጉዲዮች እንደገና ሉያጣራ የሚችልበት ወይም በስር ፍ/ቤቶች የተሰሙትን ማስረጃዎች የሚመዝንበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ወደ ጭብጡ ስንመለስ አመልካች የሚከራከረው ወስዶል ከተባለው የገንዘብ መጠን አንጻር ቅጣቱ የቅጣት አፈፃፀም መመሪያን የተከተለ አይደለም በሚል ሲሆን ይህንኑ የአመልካችን ክርክር አመልካች ጥፊተኛ ነው ተብል የቅጣት ውሳኔ ከተላለፈበት የወ/ህ/አንቀጽ 692(1) አንጻር መመርመሩ ተገቢነት ያለው ነው። በወንጀል ህግ አንቀጽ 692(1) እንደተደነገገው ማንም ሰው የማይገባውን ብልጽግና ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የላላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣ በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ላላውን ሰው አታልል ራሱን ወይም የሶስተኛውን ወገን ንብረት ጥቅም የሚጎዲ አድራጎት እንዱፈጸም ማድረጉ የተረጋገጠ እንደሆነ የአታላይነት ወንጀል ፈፅሟል ለማለት የሚቻል ይሆናል። በዚህ በተያዘው ጉዲይም አመልካች የግል ተበዲይ የሆነውን የሙገር ሲሚንቶ ሰራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ኢንተርፔራይዝ ማህበርን ገንዘብ ከላልች ወንጀል ፈጻሚዎች ጋር በመሆን በፈጸመው የማታለል ተግባር ገንዘቡ ከተቀመጠበት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንዣ ያዥ ቅርንጫፍ ወደ ወጋገን ባንክ ጎፊ ቅርንጫፍ ብር 750,000 እንዱዛወር በማድረግ ከዚሁ ከተዛወረው ገንዘብ ውስጥም የተለያየ መጠን ያለውን ገንዘብ ተከፊፍለዋል።
በክፍፍል ከደረሰው ገንዘብ ውስጥም አመልካች የወሰደው ብር 50,000 መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን በድንጋጌው መሰረትም ይህን ገንዘብ ለግል ጥቅሙ አውልታል ተብል ይወሰዲል። በዚሁ የወንጀል ድርጊትም ላልች ተከሳሾች ጭምር ጥቅም እንዱያገኙ አድርጓል። በመሆኑም አመልካች ወንጀለን የፈፀመው ለራሱ ጥቅም ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋር የነበሩት ላልች ተከሳሾችም ጥቅም እንዱያገኙ በሚል ስለሆነ ወንጀል የመስራት ሀሳቡ ለራሱ ጥቅም ለማግኘት ብቻ በሚል የተሰራ ነው ተብል ሉወሰድ የሚገባ አይደለም። በመሆኑም የቅጣቱ መጠንም ራሱ በወሰደው የገንዘብ መጠን ብቻ ሳይሆን ከላልች ተከሳሾች ጋር ወንጀል ለመስራትና ውጤቱን ለመቀበል በመስማማት ሆነ ብል ከፈጸመው የወንጀል ድርጊት ከባድነት አንጻር ላሆን ይገባል።
በመሆኑም ከፍተኛው ፍ/ቤት በጠቅላላው ከግል ተበዲይ ማህበር በተወሰደው የገንዘብ መጠን መሰረት የቅጣት ውሳኔ በአመልካች ላይ ያስተላለፈው እና የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ያፀናው ተገቢና መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 95136 በቀን 28/07/2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ፍርድና የፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ/ 67826 በቀን 03/04/2004 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/195(2)(ለ)(2) መሰረት አጽንተናል።
አመልካች ላይ በጠቅላላው ከተበዲይ ማህበር በማታለል ወንጀል በተወሰደው የገንዘብ መጠን የቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት በአግባቡ ነው ብለናል። ስለሆነም ጥፊተኛ ነው በተባለበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 692(1) ስር በ3 ዓመት እስራትና በብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) እንዱቀጣ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ አግኝተናል።
No topics extracted.