No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 2 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገብረ ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ስማቸው ልንገርህ ዓለሙ በማ/ቤት ስለሆነ አልቀረበም ተጠሪ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ዐቃቤ ሕግ አቶ ደስታ ንጉሴ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርተው ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የኮንትሮባንድ ወንጀልን የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀፅ 32 ንዐስ አንቀፅ 3 እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 91 ንዐስ አንቀፅ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ፣ ዋና ወንጀል አድራጊ በመሆን መስከረም 2 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በታቦር ክፍለ ከተማ አላሙራ ከሚባለው ሥፍራ ከመካነ መቃብሩ ወደ ሪፈራል ሆስፑታል በሚያስሄደው መንገድ ላይ በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረው ያሽከረክረው በነበረው የመለያ ቁጥር 3-39349/አ.አ/ በሆነው አይሱዙ መኪና የታክስ መጠኑ ብር 22ዐ,939.98 /ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሣ ዘጠኝ ከዘጠና ስምንት ሣንቲም / የሆነ 11,508 /አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ሥምንት ኪል ግራም/ የሆነ ህንድ አገር የተሰራ የጉምሩክ ቀረጥና ሥርዓት ያልተፈፀመበት ስኳር እንዱሁም በሥር ፍርድ ቤት ሶስተኛ ተከሣሽ የነበረው በሚያሽከረክረው የመለያ ቁጥሩ 3-32136 አ.አ በሆነ አይሱዙ መኪና የታክስ መጠኑ 1ዐ,297.80 /አንድ መቶ አስር ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሰማኒያ ሣንቲም / የሆነ መጠኑ 5753 /አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሣ ሶስት ኪል ግራም/ የሆነ ህንድ አገር የተሰራ የጉምሩክ ቀረጥና ሥርዓት ያልተፈፀመበት ስኳር አስጭኖ ሲያጓጉዝ የፋዳራል ፕሉስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የተያዘ በመሆኑ የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው።
አመልካች ወንጀለን አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት የሰውና የፅሐፍ ማስረጃ አቅርቧል። የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በክሱ በተገለፀው ጊዜና ሥፍራ አመልካች ሶስተኛው ተከሣሽ የነበረው የመለያ ቁጥሩ 3-32136 /አ.አ/ ከጋቤና ውስጥ ከሶስተኛው ተከሣሽ ጋር ቁጭ ብል ሁለተኛው ተከሣሽ በሚያሽከረክረው የመለያ ቁጥሩ 3- 39349 በሆነው አይሱዙ መኪናና ሶስተኛው ተከሣሽ በሚያሽከረክረው አይዙሱ መኪና መጠኑ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተገለፀው የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈፀመበት ህንድ አገር የተሰራ ስኳር እንደጫኑ በቁጥጥር ሥር ያዋለ መሆኑንና አመልካች በመጀመሪያ ሲያዝ ተሳፊሪ ነኝ ያላቸው ቢሆንም በማግስቱ ህጋዊ ነጋዳ መሆኑንና ህጋዊና ቀረጥ የከፈለ መሆኑን የገለፀላቸው መሆኑን ስኳሩን ሻሸመኔ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ እንዱራገፍ ማድረጋቸውን በዝርዝር መሥክረዋል።
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች ሹፋሮች መሆናቸውንና እያንዲንዲቸው በብር 17ዐዐ /አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር/ አመልካች የሚከፍላቸው መሆኑን ተስማምተው ዕቃውን እንደጫኑ ወዱያውኑ እንደተያዙ የተናገሩ መሆናቸውን መሥክረዋል። ተጠሪ ዕቃዎቹ ገቢ የሆኑበትን ሰነድ ፣ የተከሣሾች መቃወሚያና መንጃ ፈቃድ እንደዚሁም ተከሣሾች /አመልካች ጭምር/ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 27 ንዐስ አንቀፅ 2 ለፕሉስ የሰጡትን የተከሣሽነት ቃል ለሥር ፍርድ ቤት በማስረጃነት ያቀረበ መሆኑን ከውሣኔው ተረድተናል።
አመልካች ወንጀለ ተፈፀመ በተባለበት መስከረም 2 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም የመከላከያ ምስክሮችን ምሣ ጋብዟቸው ከበለ በኋላ አመልካች ስልክ ተደውልለት አናግሮ እንደተመለሰና ሀዋሳ ደቄት የሚጭን ተመላሽ መኪና ስላገኘሁ ይቅርታ አድርጉልኝ ብል ወጥቶ እንደሄደ የመሰከሩ ሲሆን በሥር ፍርድ ቤት ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሽ የነበሩት በምስክርነት ቀርበው የመከላከያ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። የመከላከያ ምስክሮችም አቅርበዋል። ይዘቱም እያንዲንዲቸው ብር 17ዐዐ/አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር/ ሂሣብ አመልካች ሉከፍላቸው ተስማምተው ዕቃውን አዱስ አበባ ቃሉቲ ማሰልጠኛ ፉት ለፉት የጫኑ መሆኑን የሚገልፅ ነው። በሁለቱ አይሱዙ መኪኖች የተጫነውን ስኳር ይዘው የተገኙ ሰዎች የስኳር ኮርፕሬሽን ደንበኞች እንዲልሆኑና ስኳርም እንዲልሸጠላቸው በፅሐፍ የተረጋገጠ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በውሣኔው በማስፈር አመልካች የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈፀመበት መጠኑ በወንጀል ክሱ የተገለፀውን በህንድ አገር የተሰራ ስኳር በባለሀብትነት ጭኖ ሲያጓጉዝ በመገኘቱ ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች የጉምሩክ ቀረጥ ያልተፈፀመበት ዕቃ በመጫን የትራንስፕርት አገልግልት የሰጡ መሆናቸው ተረጋግጦባቸዋል። የመከላከያ ማስረጃቸው የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የሚያጠናክር እንጅ የሚያስተባብል አይደለም በማለት አመልካችና በሥር ሁለተኛ ና ሶስተኛ ተከሣሽ የሆኑት ሰዎች በወንጀል ህግ አንቀፅ 32/3/ እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 91/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ ወንጀል የፈፀሙ ጥፊተኞች ናቸው ብል አመልካች በሥምንት ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 71,ዐ32/ሰባ አንድ ሺህ ሰላሣ ሁለት ብር /እንዱቀጣ ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች ይግባኝ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካችን የይግባኝ ቅሬታ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195/1/ መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ጥር 7 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የተያዘው ስኳር የእኔ ሣይሆን መሀመድ የተባለ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ መጋዘን ያለው ነጋዳ መሆኑን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 27/2/ መሰረት የተከሣሽነት ቃላን ሰጥቻለሁ። የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ወዱያውኑ እንደተያዝኩ እኔ ተጓዥ መሆኔን ዕቃው የእኔ አለመሆኑን እንደተናገርኩ ከመሰከሩ በኋላ በማግስቱ ዕቃው የእኔ ነው ብሎል በማለት የሰጡትን የምስክርነት ቃል በመቀበል ጥፊተኛ መባላ ተገቢ አይደለም። ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች የሰጡት ቃል በእኔ ላይ በማስረጃነት ሉያዝብኝ አይገባም ። የቅጣት ውሣኔውም ተገቢ አይደለም በማለት አመልክቷል። ተጠሪ አመልካች ወንጀል መፈፀሙ ተረጋግጦበታል። አመልካች የክርክር ስልቱን በመለዋወጥ የሥር ፍርድ ቤት ያለበቂ ማስረጃ ፍርድ እንደተሰጠው ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የለውም በማለት ሚያዚያ 3 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። አመልካች ግንቦት 7 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ በተጠሪ የተያዘው ስኳር የጉምሩክ ቀረጥ ያልተፈፀመበት መሆኑን አላስረዲም። በተቃራኒው ማስረጃው ስኳሩ የጉምሩክ ሥርዓት የተፈፀመበት መሆኑን ያሳያል።
ፕሉሶች ቃላ በማስረጃነት እንደሚቀርብብኝ ሣያስጠነቅቁኝ ዕቃው የእኔ ነው ብሎል በማለት የሰጡትን የምስክርነት ቃል መሰረት በማድረግ ጥፊተኛ መባላ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መረምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍ/ቤቶች አመልካች በወንጀል ህግ አንቀፅ 32 እና በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 91 ንዐስ አንቀፅ 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ነው ተብል የተወሰነው የቅጣት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ ለተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት የሥር ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ በወንጀል ክሱ በገለፀው ጊዜ ማለትም መስከረም 2 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም አመልካች በሀዋሳ ከተማ አላሙራ ከተባለው ሥፍራ በመካነ መቃብሩ ወደ ሪፈራል ሆስፑታል በሚያስሄደው መንገድ ሞተር አጥፍተው ተከታትለው ቆመው በነበሩት ሁለተኛው ተከሣሽ በሚያሽከረክረው የመለያ ቁጥር 3-39349 አ.አ በሆነ መኪናና ሶስተኛ ተከሣሽ ያሽከረክረው በነበረው የመለያ ቁጥሩ 3-32136 አ.አ በሆነ አይሱዙ መኪና ጋቤና ውስጥ ቁጭ ብል በቁጥጥር ሥር ያዋለ መሆኑን ፣ መኪኖቹ የጉምሩክ ቀረጥ ያልተፈፀመበት ህንድ ሀገር የተሰራ ስኳር ጭነው መገኘታቸውን አመልካችንና ላልቹን ተከሣሾች በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሄደት የፋዳራል ፕሉስ አባላት መኪናው ላይ ያለው ዕቃ ባለሀብት ማን እንደሆነ ሲጠይቋቸው ለእያንዲንዲቸው ብር 17ዐዐ ለመክፈል ተስማምቶ አመልካች ያስጫነው ዕቃ መሆኑን ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች የገለፁ መሆኑን አመልካች በወቅቱ ተሣፊሪ ነኝ ያለ መሆኑንና በማግስቱ ዕቃው ቀረጥ የተከፈለበት የእኔ ንብረት ነው ያለ መሆኑን ይህንን የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ አመልካች ባቀረበው የመከላከያ ማስረጃ ያላስተባበለና ማስረጃው በሰነድ ማስረጃዎችና ላልቹ ተከሣሾች ያቀረቡት የመከላከያ ምስክሮች ቃል የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የሚያጠናክር ይዘት ያለው መሆኑን በውሣኔው በግልፅ አስፍሯል።
ዕቃውን አመልካችንና ዕቃውን የጫኑትን ሹፋሮች በቁጥጥር ሥር ያዋለት የተጠሪ ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል በሁለት አይሱዙ መኪና ተጭኖ የነበረው የጉምሩክ ቀረጥ ያልተከፈለበት ህንድ አገር የተሰራ ስኳር በመኪናዎቹ እንደተጫነ በቁጥጥር ሥር ከማዋላቸው በፉት ስለነበረው አጠቃላይ ሁኔታ አመልካችን ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች በመኪናዎቹ ላይ ከተጫነው ስኳር ጋር በቁጥጥር ሥር ሲያውሎቸው የነበረውን ሁኔታና አመልካችን ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሽ በቁጥጥር ሥር አውለው ወደ ካንኘ ሲወስዶቸው ስለነበረው ሁኔታ /circumstance/ እና ከዚህ ሂደት አመልካች ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች ያሳዩት የነበረውን የባህሪ ሁኔታ ይፈፅሙት የነበሩትን ድርጊትና በቃላት ሲገልፁ ስለነበረው ሀሣብ አስረድተው የተመለሱ ናቸው። በልላ አነጋገር የተጠሪ ምስክሮች በወቅቱ ስለነበረው አጠቃላይ ሁኔታ /circumstantial evidence/ ሰጥተው የተመለሱ ናቸው። በአገራችን የህግ ሥርዓት ምስክሩ ስለአጠቃላይ ሁኔታዎች በአይኑ የታዘበውን በጆሮው የሰማውንና የሚያውቀውን ፍሬ ጉዲይ ሉስመሰክር እንደሚችልና የምስክሩም ቃል ህጋዊ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 137 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ለመረዲት ይቻላል።
አመልካችና የተጠሪ ምስክሮች አመልካች የጉምሩክ ቀረጥ ያልተፈፀመበት ስኳር ጭነው በማከታተል ቆመው በቁጥጥር ሥር ከዋለት መኪናዎች ውስጥ በአንደኛው ማለትም ከሶስተኛ ተከሣሽ ጋር ሶስተኛው ተከሣሽ ሲያሽከረክረው ከነበረው የመለያ ቁጥሩ 3-32136/አ.አ/ ከሆነው አይሱዙ መኪና ውስጥ ቁጭ ብል እንዲገኙት ፣ ወዱያውኑ ሲጠይቁት ተጓዥ ነኝ በማለት መናገሩንና በቁጥጥር ሥር ውል ከሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች ጋር ወደ ካንኘ እንደተወሰደ ካንኘ ታስሮ አድሮ በማግስቱ ዕቃው የእኔ ነው ህጋዊ የጉምሩክ ሥርዓት ተፈፅሞበታል በማለት መግለፁን ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሣሾች ለእያንዲንዲቸው ብር 17ዐዐ /አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር/ ለመክፈል ተስማምቶ ዕቃውን ያስጫናቸው አመልካች መሆኑን በቁጥጥር ሥር በሚውለበት ጊዜ እንደገለፀላቸው በማረጋገጥ የሰጡት ምስክርነት ቃል የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ / circumstantial evidence / እንደሆነና ይህም አመልካች በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 27/2/ ከሚሰጠው የተከሣሽነት ቃል የተለየ የማስረጃ አይነት መሆኑን ሣያገናዝብ ማስረጃው ተቀባይነት የለውም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ምክንያቱም የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ በባህሪውና በይዘቱ አንድ ክስተት ከመፈጠሩ በፉት ፣ ክስተቱ ሲፈጠር ወይም ድርጊቱ ሲፈፀምና ክስተቱ ከተፈጠረ ወይም ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ያለትን የአካባቢ ሁኔታዎች በማሣየትና በመግለፅ ዳኞች በጭብጥነት ስለተያዘው አከራካሪ ጉዲይ ልጅካል ድምዲሜ ላይ እንዱደርስ የሚያደርግ የማስረጃ አይነት መሆኑን “ circumstantial evidences is an evidence that tend to prove the matter by providing events or circumstances from which the occurrence of the matter at issue can be reasonably inferred circumstantial evidence not bearing directly the fact in dispute but make clear various attendant circumstances from which the judge might infer the occurrence of the fact in dispute ” በሚል መንገድ በህግ መዝገj ቃላትና በላልች አገሮች የማስረጃ ህግ ድንጋጌዎች የተገለፀውንና የእኛም አገር የህግ ሥርዓት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 137 ንዐስ አንቀፅ 1 ህጋዊ ተቀባይነት ያለው የማስረጃ አይነት መሆኑን በግልፅ የደነገገው መሆኑን ግንዛቤ ወስጥ በሚያስገባ ሁኔታ አመልካች የሥር ፍርድ ቤት የተጠሪ ምስክሮች የሰጡትን የአካባቢ ሁኔታ የሚያስረዲ የምስክርነት ቃል መቀበለ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው አልተቀበልነውም።
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት የተጠሪ ምስክሮች አመልካች አንደኛና ሁለተኛ ምስክር በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፉት ፣ በቁጥጥር ሥር ሲውለና በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ስለነበረው አጠቃላይ ሁኔታ ፣ አመልካችና ተከሣሾች ስለአሳዩት ባህሪ ፣ ስለፈፀሙት ድርጊትና በቃላት ስለገለፁት ሃሣብ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ተጠሪ ካቀረባቸው ላልች የሰነድ ማስረጃዎችና በአመልካችና በሁለተኛና ሶስተኛ መከላከያ ምስክሮች ከሰጡት የምስክርነት ቃል ጋር በማገናዘብና በመመርመርና በመመዘን አመልካች በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 91 ንዐስ አንቀፅ 2 በመተላለፍ የኮንትሮባንድ ወንጀል የፈፀመ ነው በማለት የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማፅናቱ የበታች ፍርድ ቤቶች በህግ የተሰጣቸውን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን በመጠቀም ተገቢ ነው ከሚለት መደምደሚያ ላይ የደረሱ መሆኑን የሚያሣይና የህግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ጥፊተኛ ሆኖ የተገኘበት የህግ ድንጋጌ ከሰባት ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት ፅኑ እስራትና ዕቃዎቹ ላይ ሉከፈል ከሚገባው ቀረጥና ታክስ ጋር በሚመጣጠን የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ መሆኑ በግልፅ ይደነግጋል። አመልካች በሁለት አይዙሱ መኪና ጭኖ ከተገኘው የስኳር መጠን ፣ ከአመልካች የወንጀል አፈፃፀም አንፃር ሲታይ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች በስምንት ዓመት ፅኑ እስራትና በብር 71,032 /ሰባ አንድ ሺህ ሰላሣ ሁለት ብር/ መቀጮ እንዱቀጣ የሰጡት ውሣኔ አመልካችን ቅር እንደሚለው መሰረታዊ የቅጣት አወሳሰን መርሆችን የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያወጣውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 12/ለ-2 መሰረት ሉፀና ይገባዋል በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሓር ፣ ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀፅ 2 /ለ/ 2 መሰረት ፀንቷል።
በአመልካች ላይ የተወሰነው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የፀና መሆኑን አውቆ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈፅም ለክፍለ ማረሚያ ቤት ይፃፍ። መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.