No summary available.
ሐምል ዐ4 ቀን 2ዐዐ4 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1ኛ/ አፈወርቅ ላሉሳ ጉዲይ ተከታታይ በትናትናው ዕለት ቀርበው 2ኛ/ ውብሸት ደምል ውሳኔውን መዝገብ ቤት ይስሙ ተብሎል።
ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ዐ/ሕግ - አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው የአሁን አመልካቾች በተከሰሱበት የግድያ ወንጀል ጥፊተኛ የመባላቸውን አግባብነት ተመልክቶ ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት በሚል የቀረበ ነው።
የአሁን አመልካቾች በ1997 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 የተመለከተውን በመተላለፍ አማረ ሙለጌታ የተባለውን አስቀድሞ ለመግደል በነበራቸው ሀሳብ ሚያዝያ 05 ቀን 2003 ዓ.ም ከላሉቱ 6፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በአዋሳ ከተማ በተለያዩ ሆቴልች በመዘዋወር መጠጥ በማጠጣት በስካር እራሱን እንዱስት ካደረገ በኋላ በታቦር ክ/ከተማ በወጋኔ ዋጮ ቀበላ ልዩ ስፍራው ማውንት አላብ ት/ቤት ፉት ለፉት በመውሰድ 2ኛው ተከሳሽ የአሁን ሁለተኛ ተጠሪ እራሱን እንዲይከላከል ሲያደርግ 1ኛ ተከሳሽ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በስለት የግራ ደረቱን ከወጋው በኋላ የፈፀሙት ወንጀል እንዲይገለፅ በሞትና ጣር ያለውን ሆስፑታል የወሰደና ሆስፑታል ግቢ እንደገባ ህይወቱ በማለፈ በፈጸሙት ከባድ የግፍ አገዲደል ወንጀል ተከሰዋል የሚል የወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል። ተከሳሽም ክደው በመከራከራቸው፤ የዐ/ህግ ማስረጃ ተሰምቷል። በዚህም ማስረጃ መሰረት እንዱከላከለ፤ ተደርጎ እነርሱም በተራቸው፣ የመከላከያ ማስረጃ አቅርበው አሰምተዋል።
ይህንኑ የግራ ቀኙን ክርክር ሲሰማ የቆየው ፍ/ቤትም በወ/መ/ቁ. 10239 ሐምል 28 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት ከድርጊቱ በፉት እና በኋላ፤ በድርጊቱ አፈፃፀም ጊዜ ተደርገዋል የተባለትንና በዐ/ህግ ማስረጃ የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች በቀጥታ የወንጀለን ድርጊት ተከሳሾች የፈፀሙት ናቸው በማለት የሚያስረደ ባይሆንም፤ ድርጊቱ በተከሳሾች የተፈፀመ ለመሆኑ በአካባቢ ማስረጃነታቸው በቂና ለድምዲሜ አጥጋቢ መነሻ ሆነው ተገኝተዋል። ስለሆነም ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጫለሁ ካለ በኋላ ይሁን እንጂ በዚህ አኳኋን የተረጋገጠው ማስረጃ እንደ ክሱ ዝርዝር ሁኔታ ተከሳሾች አስቀድሞ በነበራቸው ሀሳብ ተነሳስተውና ተዘጋጅተው የፈፀሙት መሆኑን ለማረጋገጥ የሚችል ሆኖ አልተገኘም ይልቁንም አድራጎታቸው በወ/ሕግ ቁጥር 540 ሥር የሚወድቅ ሆኖ ስለተገኘ በዚሁ ድንጋጌ ሥር ጥፊተኛ ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።
በቅጣት አጣጣል ረገድም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት እና የድርጊቱን አፈፃፀም በማገናዘብ እያንዲንዲቸው በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ወስኗል። ይህም ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልለ ሰበር ሰሚ አጣሪ ችልት ቀርቦ ውሳኔው የሚነቀፍበት ምክንያት የላለ መሆኑ ተገልፆ የአሁን ተጠሪዎች በመሰናበታቸው ለዚሁ ሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
የሰበር ቅሬታቸውም ይዘት የእያንዲንዲችንን አድራጎት ለይቶ ያስረዲ የዓይን ምስክር አልቀረበብንም፤ አልተመሰከረብንም ምስክሮች የአካባቢ ናቸው። ሆነ ተብል ለተፈፀመ ድርጊት ተጠያቂነት የለብንም። ዐ/ሕግ ክሱን አሻሽላለሁ በማለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ እንደጥያቄው አሻሽል አለማቅረቡ ሲታወቅ ለጊዜውም ቢሆን ክሱ ተቋርጦ መሰናበት ይገባን ነበር። በክሱ ላይ ላልች ግብረአበሮች እንዲለ በመገለፁ እነርሱ ህግ ፉት ሉቀርቡ ባለመቻላቸው ብቻ እኛ ተሸክመን ሟችን ባደረስን መከሰሳችን አግባብነት የለውም ጥፊተኛ ናችሁ ከተባልንም ወጣትነታችንን፣ የወንጀል ሪከርድ ያልቀረበብን፣ የሟችን ህይወት ከደረሰበት አደጋ ለማትረፍ ያደረግነው ጥረት ሁለ ሳይመዛዘን የተጣለው ቅጣት የበዛ ነው ሉቀነስልን ይገባል የሚል ነው።
የክልለ ዐ/ህግ በዚህ ሰበር ጉዲይ በተጠሪነቱ ቀርቦ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ በሥር ፍ/ቤት የተደረገውን ክርክር መሰረት ያላደረገ መሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው እንዱፀና ጠይቋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል እንደመረመርነውም በወንጀል ጉዲይ የተከሰሰን ሰው ወንጀለን ስለመፈፀሙ መቅረብ የሚገባው የማስረጃ ዓነይት ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያላቸውን ፍሬ ነገሮች ለማስረዲት የሚችል ድርጊቱን ሲፈፅሙ አያቻለሁ፣ ሰምቻለሁ ወዘተ የሚል ቀጥተኛ ማስረጃ ብቻ ነው የሚል የተደነገገ ህግ በህግ ሥርዓታችን አይገኝም ይልቁንም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 137 እንደተደነገገው በማስረጃነት ላቀርብ የሚችለው ስለተያዘው አከራካሪ ነጥብ /ጭብጥ/ ማስረጃው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ስለጉዲዩ የሚያውቀውን ዝርዝር የምስክርነት ቃል ሁለ የሚጨምር ነው።
ስለሆነም በዚህ ረገድ አመልካቾች በእኛ ላይ ቀርበው የተደመጡት ምስክሮች የዓይን ምስክሮች ሳይሆኑ የአካባቢ ናቸው። ስለሆነም ማስረጃው ተቀባይነት የለውም በሚል አንድምታ ያቀረቡት ክርክር ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም።
ለሟች ሞት መንስኤ የሆነው ተግባር በአመልካቾች የተፈፀመ ስለመሆኑ ማስረጃው አረጋግጧል እስከተባለ ድረስ የትኛውን ተግባር የትኛው ተከሳሽ እንደፈጸመ ለይቶ ያስረዲ ማስረጃ አልቀረበብንም የሚለውም ክርክር ቢሆን የየግላቸው የወንጀል ተሳትፍ ተለይቶ አለመታወቁ በሐሳብም ሆነ በተግባር በመተጋገዝ በግብረአበርነት ከፈፀሙት ድርጊት ነፃ ናቸው ከሚል መደምደሚያ ሉያደርስ የሚችል አይደለም። እንዱሁም ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽላለሁ በማለት ሳያሻሽል ክርክሩ በቀረበው ክስ ቀጥል ከሆነ እንደትዕዛዙ አሻሻል ባለማቅረቡ ምክንያት የወንጀለ ክሱ ለጊዜው ሉዘጋ እንደሚችል ስለዚሁ አግባብነት ባለው የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. አልተመለከተም ክሱ ተሻሽል አለመቅረቡ የማሻሻያ ጥያቄው በከሳሽ በዐ/ሕግ ተነስቶ የነበረ ከመሆኑ አንፃር በተከሳሾች ላይ ጉዲት አድርሷል ለማለት አያበቃም ክሱ እንደፍርደ በትዕዛዝ ባለማሻሻለ ምክንያት በክርክሩ አካሄድ የመከራከር መብታቸውን እንዳት እንዲጣበበ እና በምን አኳኋን የፍትህ መጓደል እንደደረሰም አላስረደም።
በልላ በኩል ስለዋናው ጉዲይ ለሟች ሞት መንስኤ የሆነውን፣ ተግባር ማን ፈፀመው? ለሚለው ዐብይ አከራካሪ ነጥብ ተከሳሾች በዕለቱ ዕለት አብረው ማምሸታቸውን፣ ከሁለተኛው ተከሳሽ ጋር፤
እደር አላድርም በሚል ትንቅንቅ ትግል በተከሳሾችና በሟች የነበረ መሆኑ፤ ሟች አላድርም ብል ወደ ቤቱ ሲሄድ ከአጭር በ2 እና ሦስት ደቂቃ በሚቆጠር ጊዜ መከተላቸው፤ በዚህ ጊዜ ሟች በሰው እጅ ተጎድቶ ተከሳሾች ሟችን ተሸክመው ወደ ሆስፑታል ባመጡት ጊዜ ሟች ከአንገቱ ሥር ከደረቱ ላይ በስለት ነገር መወጋቱ፤ ተከሳሽም ፉታቸው ሁለ ሳይቀር ደም በደም የነበረ መሆኑን እና ከምስክሮች የመገረም ቃል አገላለፅ ተነስተው "የሞተው መቼ እሱ ብቻ እኛም ሞተናል አይ የኛ ነገር አበቃ የእኛ ነገር" ተከሳሽ በሚል መናገራቸውን ሁለ ፍ/ቤቱ እንደ በቂ የግምት መነሻ በመውሰድ ሟችን ለህልፈተ ህይወት ያበቃው በተከሳሾች አድራጎት ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የሚያየው ፍ/ቤት ፍሬ ነገርን በማስረጃ የማረጋገጥ፤ በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር በማስረጃነቱ አከራካሪ ነጥብ የሆነውን በማስረዲት ረገድ ያለውን ታማኝነትና ሚዛን የመለካት ስልጣን ባለው ፍ/ቤት የተከናወኑ የዲኝነት ሥራ/ተግባራት በመሆኑ ጉዲዩ የህግ ጥያቄን የሚያስነሳ ሆኖ አይገኝም ምናልባትም የዚህ ማስረጃ አግባብነት ታማኝነትና ሚዛን ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 141 አንፃር ተገናዝቦ መታየቱንና አለመታየቱን በሚመለከት የህግ ጥያቄን ያስነሳል እንኳ ቢባል በዚህ ህግ በተቀመጠው የማስረጃ ሚዛን መለኪያ አኳያ ከላይ የተመለከተው የዐ/ህግ ማስረጃ ይታይ እንኳ ቢባል በህጉ መሰረት ከተቀመጠው ሚዛን የወረደ ስለሆነ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በብይን በነፃ መሰናበት ነበረባቸው የሚለውን የህግ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም።
ተከሳሾች በተራቸው እንከላከላለን በማለት ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃም ቢሆን በዕለቱ ዕለት በሟችና በ1ኛ ተከሳሽ ተፈጥሮ የነበረውን ቂም የሚያመለክትና በድርጊቱ አፈፃፀም ተጠያቂዎች ተከሳሾች እንጂ ላላ ወገን አይደለም የሚለውን በማመላከት የዐ/ሕግ ማስረጃ የሚያጠናክር እንጂ በወ/መ/ሐ/ሥ/ሥ/ቁ/ 149 እንደተመለከተው ከወንጀለ ተጠያቂነት ነፃ ሉያደርጋቸው የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
በቅሬታቸው እንደገለፁት እና ከመደበኛ የሰበር ክርክር አቀራረብ ሥርዓት ውጭ በአቤቱታ እንደገለፁት ተከሳሾች በተከሰሱበት የወንጀል ጉዲይ ላልች ግብረአበሮች የነበሩ ስለመሆኑ ክርክሩ የሚያስረዲ ከመሆኑም በላይ እነዚህ አሁን አመልካቾች የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት ለመፈፀማቸው የወንጀል ህግ ሥርዓት የሚጠየቀውን ሚዛን በጠበቀ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው መሆኑ እስከታወቀ ድረስ በዚህ አኳኋን ያቀረቡት የመከራከሪያ ነጥብ ከኃላፉነት ነፃ ሉያደርጋቸው የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
ቅጣትን በሚመለከት የቀረበውም ክርክር በዚህ ሰበር ችልት ደረጃ እንደገና ሉታረም የሚችልበትን የህግ ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለም።
በዚህ ሁለ ምክንያት በሥር ፍ/ቤቶች በአመልካቾች ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ባለማግኘታችን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
በዚህ ጉዲይ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃውን ጠብቆ በሰበር መ/ በ28/2/2004 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ አፅንተናል።
No topics extracted.