No summary available.
ሐምል 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፉሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሰው ግድያና የማታለል ወንጀል ስራ መፈጸሙ በተረጋገጠበት አጥፉ ላይ የወንጀለ ውጤት ስለመሆናቸው የተረጋገጡት ንብረቶች ለመንግስት ውርስ መሆን የሚችለ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተነሳው በአሁኑ አመልካቾችና በላልች ሁለት ግለሰቦች በጠቅላላው በስድሰት ሰዎች ላይ የአሁኑ ተጠሪ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተባቸው ክስ መነሻ ነው።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ተከሣሽ የሆነው ያሁኑ 1ኛ አመልካች ታምራት ገለታን በተመለከተ ተጠሪ ያቀረበባቸው ስድስት ክሶች ሲሆኑ ከእነዚህ ክሶች 1ኛው ክስ፡- አመልካች በ1949 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ሀ)) 522(1ሀ እና ሐ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ጊዜአትና ቦታዎች በጥንቆላ ተግባር ሰዎችን ከታመሙበት የበሽታ አይነት አድናለሁ በማለት ከተለያዩ ነገሮች የተቀመመ ውህድ በማጠጣት አቶ ተስፊ ተሾመ (አቶ ተስፊ ወረኢለ)፣ ኢብራሂም ባርጌቾ፣ የአባቱ ስም ያልታወቀ ፈጠነ የተባለ ግለሰብ፣መሐመድ አረጋ፣ እና መካ አብዱላጊ የተባለትን ግለሰቦች በግፍ ገድሎል የሚል ሲሆን 2ኛው ክስ ደግሞ በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ሀ)) እና 539(1ሀ(ሐ)) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛው ክስ ላይ በተገለጸው አኳኋን ሟች ወሰኔ ፈረደን በግፍ ገድሎል የሚል ነው።3ኛ ክስ ደግሞ በ1949 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1ሀ)፣27(1) እና 522(1(ሐ)) የተመለከተውን በመተላለፍ ከኤች አይ ቪ ቫይረስ አድናለሁ በማለት ለወ/ሮ ቬነስ ዩሐንስ በጊዜው የምትወስደውን ዘመናዊ መድኃኒት እንድትተው በማድረግ ውህደን በተደጋጋሚ በመስጠት በከፍተኛ ህመም ወስጥ እንድትወድቅ በማድረግ በውጪ አገር ህክምና የዲኑ በመሆኑ በግፍ ሰው ለመግደል ሞክረዋል የሚል ሲሆን ላልች ሶስት ክሶች ደግሞ የማታለል ተግባሮችን የሚያሳዩ ናቸው።ይኸውም 4ኛው ክስ በ1949 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1ሀ) እና 656(ሀ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከ1991 ዓ.ም. የአባቱ ስም ካልተጠቀሰው መንግስቱ ከተባለው የግል ተበዲይ በጥንቆላው እምነት ስር እንዱወድቅ በማድረግ በማታለል ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ) ፣ከአቶ አረጋ ይማምና ከወ/ሮ ረሑማ ሰኢድን በጥንቆላው ስር እንዱወድቁና ልጃቸውን ወደ ውጪ ለመላክ ሲለ ቤት እንዱሸጡ በማድረግ ብር 13,000.00 መውሰዲቸውን፣ ከአቶ አብድረልሐሚድ መሀመድና ከወ/ሮ ማረያም አብደላሂ ደግሞ በጥንቆላው እምነት ስር እንዱወድቁ በማድረግ ብር 20,000.00 መውሰዲቸውን፣ከአቶ ተስፊዬ ታዬ እና ከአቶ ደረሰ ሰሙም በተመሳሳይ ዘዳ ሜሪኩሪ የተባለ ነገር ስለመሆኑ በጥንቆላው እንደአረጋገጡና እንዱገዙ በማድረግ የግል ተበዲዮች በብር 400,000.00 ከገዙት በኋላ ከራሱ ዘንድ እንዱያስቀምጥ በማድረግ መውሰዲቸውን፣ከአቶ አቶ ራሚ ያሲን ደግሞ በማታለል ብር 150,000.00 መውሰዲቸውን፣ ከአቶ እስማኤል ያሲንና ጀማል ከተባለት ወንድማማቾች ደግሞ በተመሳሳይ የማታለል ዘዳ ብር 60,000.00(ስልሳ ሺኅ) መውሰዲቸውን የሚገልጽ ሲሆን 5ኛ ክስ በ1996 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና 696(1(ሐ)) ስር የተመከተውን በመተላለፍ በጥንቆላው ዘዳ በማታለል ወ/ሮ ወላንሳ አብርሃን መኖሪያ ቤታቸውን በስጦታ እንደሰጧቸው በማስመሰል አስፈርመው ቤቱንና ቦታውን መውሰዲቸውን የሚገልጽ ነው።6ኛው ክስ ደግሞ በ1949 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 589(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በጥንቆላው ዘዳ በማስፈራራት የግል ተበዲይ ታየች ማሞ፣ ወ/ሮ ሜላት ሽፈራውን፣ ቬነሱ ዩሐንስን በተለያዩ ጊዜያት የግብረ ስጋ ግንኙነት ከ1ኛ አመልካች ጋር እንዱፈፅሙ አድርገዋል የሚል ነው።አመልካች የተከሰሱባቸውን የወንጀል ድርጊቶችን ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ሕግ አለኝ ያሎቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ቀርበው ከተሰሙና ከተመረመሩ በኋላ የአመልካች የመከላከል መብታቸው ተጠብቆላቸው ማስረጃዎቻቸው ከተሰሙ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው ሉያስተባብለ አልቻለም በሚል ምክንያት አመልካችን በስድስቱም ክሶች ጥፊተኛ በማድረግ በጠቅላላው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዱቀጡ፣ አመልካች ካፈሯቸው ንብረቶች መካከል በአዱስ አበባ ትራንስፕርት ቅርንጫፍ መ/ቤት የምዕራብ ዞን ፅ/ቤት በቁጥር ምዕ/ዞን/12069/200 በቀን 21/11/2001 በጻፈው ደብዲቤ በገለፀው መሰረት የሰላዲ ቁጥር 2-60978 አ.አ እና 2-49372 አ.አ የሆኑ ተሽከርካሪዎች፣ አቢሲኒያ ባንክ ሐምል 27 ቀን 2001 በጻፈው ደብዲቤ በኡራኤል ቅርንጫፍ በአመልካች ስም በቁጠባ ሂሳብ ቁጥር 2151 መኖሩ የተገለጸውን ብር 153,351.72፣በፍቼ ከተማ ቀበላ 04 ሆቴልና በቀበላ 03 የሚገኝ ከልማት ባንክ የተገዛ ቦታ በቁጥር 145/ፒ-58/02 በቀን 22/11/2001 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዲቤ በአመልካች ስም መኖሩ የተረጋገጠው ንብረት፣ በአዲማ ከተማ የሚገኘው ቤት የፍትሒብሓር ክርክርን ውጤት በጠበቀ መንገድ፣ ብዛቱ 131 ሆኖ 1445 ግራም ወርቅ፣ ብርና ላልች አርቲፉሻልችን ለመንግስት ውርስ እንዱሆኑ በሚል የተወሰነ ሲሆን ለመንግስት ውርስ እንዱሆኑ በተባለት ንብረቶች የሶስተኛ ወገኖች መብት መጠበቅ ያለበት ስለመሆኑም ተገልፆ ተወስኗል።የአሁኖቹ 2ኛ አመልካች(ደረጀ ስሜ) እና 3ኛ አመልካች (አዱሱ ሱልጣን)ን በተመለከተ ደግሞ በ4ኛው ክስ ላይ የተገለፀውን የማታለል ወንጀል መፈፀማቸው ብቻ ነው የተረጋገጠው ብል በወንጀል ሕግ አንቀጽ 692(1) መሰረት እና በተጨማሪም በ1949 ዓ.ም፣ የወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 6ዐ6 ጠቅሶ ጥፊተኛ በማድረግ በ2ኛው አመልካች ላይ የ5 ዓመት ጽኑ እሥራት እና ብር 5ዐዐዐ መቀጮ፣ በ3ኛ አመልካች ላይ የ4 ዓመት ጽኑ እሥራት እና የብር 3ዐዐዐ መቀጮ ሲወሰን በአሁኗ 4ኛ አመልካች (ኤልሣቤጥ አበራ) በሚመለከት ደግሞ በ5ኛው ክስ ላይ የተገለፀውን የማታለል ወንጀል መፈፀሟ ሉረጋገጥባት ችሎል በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 692(1) መሰረት ጥፊተኛ በማድረግ የአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት ቅጣት እና የብር 3ዐዐዐ መቀጮ ወሰኖበታል።ላልች ተከሳሾች ላይም ተገቢ ነው ያለውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል።
ከዚኅም በኋላ ሁለም አመልካቾች በተወሰነባቸው የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪም በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለዚሁ ፍርድ ቤት ይግባኙን አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የአቃቤ ሕጉን ይግባኝ ውድቅ ሲያደርግ የ1ኛውን አመልካች ይግባኝ በተመለከተ በክሶቹ ላይ ተላልፎል ተብለው የተጠቀሱበት የሕግ አንቀጾች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 113/2/ መሰረት ተለውጠው 1ኛው አመልካች(ታምራት ገለታ) በ1ኛው ክስ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 58/1/ እና 523 መሰረት፣ በ2ኛው ክስ በአዱሱ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 58 እና 54ዐ መሰረት እንዱሁም በ3ኛው ክስ በሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 58/1/ለ 27/1/ እና 523 መሰረት ጥፊተኛ ልባል ይገባል በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠባቸውን ድንጋጌዎች ያሻሻለ ሲሆን በላልች ድንጋጌዎች ስር የተሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔ ግን እንዲለ በማፅናት ቅጣቱን በተመለከተ ተደራራቢ የሆኑ ወንጀልች መገኘታቸው ሲረጋገጥ ቅጣት ሉወሰን የሚችለውን መርህ መሰረት አድርጎ ከአሰላ በኋላ በጠቅላላው አመልካች በ25(ሃያ አምስት) አመታት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ በመወሰን በንብረት አወራረስ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ደግሞ በውርስ የተገኘ ንብረት እንዲይወረስ ጠቅሶ ሙለ በሙለ አጽንቶታል። በ2ኛ አመልካችና (ደረጄ ስሜ) እና በ4ኛ አመልካች(ኤልሣቤጥ አበራ) ላይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነው የእሥራት ቅጣት በማሻሻል የእሥራቱ ቅጣት በአንድ ዓመት እንዱቀንስላቸው ተደርጎ ታሥረው የቆዩበት ጊዜ የሚታሰብላቸው ሆኖ እያንዲንዲቸው በአራት ዓመት ጽኑ እሥራት እንዱቀጡ የወሰነ ሲሆን በ3ኛ አመልካች (አዱሱ ሱልጣን) የተሰጠው ቅጣት ግን እንዲለ እንዱፀና፣ በቀለ ገለታ የተባለው ደግሞ በነፃ እንዱሰናበት ሲል ወስኗል።የሰበር አቤቱታው የቀረበውም በዚሁ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ምክንያት ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ አመልካቾች በጥፊተኝነት እና በእስራት ቅጣቱ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል በሰበር ችልቱ አጣሪ ችልት ተቀባይነት ያጣ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ለዚህ ችልት እንዱቀርብ የተደረገው 1ኛ አመልካችን በተመለከተ ንብረቶቹ እንዱወረሱ የተሰጠው ትእዛዝ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 98 ድንጋጌ አንፃር ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተብል ነው። በዚህም መሰረት ለአቃቤ ሕግ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በሰጠው መልስ ንብረቶቹ እንዱወረሱ ትእዛዝ ላሰጥ የቻለው ከወንጀል ፍሬ የተገኙ መሆናቸው ተረጋግጦ ስለመሆኑና ሕጉም የአስገዲጅነት ባህርይ ያለው በመሆኑ ነው በማለት በንብረቶቹ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንዱጸና ዲኝነት የጠየቀ ሲሆን የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው አመልካች ጥፊተኛ የተባለባቸው ልዩ ድንጋጌዎች ስለንብረት መወረስ የማይደነግጉ በመሆናቸው ንብረቶቹ ሉወረሱ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም በማለት የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።እንደመረመረውም የአመልካች ንብረቶቹ እንዱወረሱ በሚል የተሰጠው ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው 1ኛ አመልካች የተከሰሱትና ጥፊተኛ የተባለት በስድስት ክሶች ሁኖ የአመልካች ጠበቃ እንደጠቀሱት ሁለም የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠባቸው ልዩ ድንጋጌዎች በቅጣት አወሳሰን ጊዜ የንብረት መወረስ ስለመኖሩ በግልፅ አያስቀምጡም።እንዱህ ከሆነ የአመልካች ንብረቶቹ የሚወረሱበት አግባብ ስለመኖሩ ሕጉ በልላ መንገድ አስቀምጧል ወይ? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ የማይቀር ነው።ይህን ጥያቄ ለመመለስ የአመልካች ንብረቶች የተያዙበትን አግባብ እና የክሶችን ይዘት መመልከቱ ተገቢ ይሆናል።አመልካች የተከሰሱባቸው ድንጋጌዎች በጥንቆላ ዘዳ ሰዎችን በመግደልና በማታለል ንብረታቸውን ወስደዋል፣ያላግባብም በልጽገዋል በሚል ምክንያት ሲሆን ንብረቶቹ የወንጀለ ፍሬዎች ስለመሆናቸው አቃቤ ሕግ በክሱ በማስረጃ ዝርዝር ገልጾ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው፣ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በውርስ ከአገኙት እና ራሳቸው በግል ጉልበታቸው፣ ገንዘባቸው እና እውቀታቸው ሉያፈሩ ከሚችለት በላይ ሀብት አካብተው መገኘታቸውን ማረጋገጡን በውሳኔው ላይ በግልጽ አስፍሯል። ይህ የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ በይግባኝ ሰሚው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ችልትም ተቀባይነት ማግኘቱን ውሳኔው ያስገነዝባል። እንዱህ ከሆነ ንብረቶቹ የወንጀል ፍሬ ናቸው የሚለው የበታች ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ ለዚህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት ከተሰጠው የመሰረታዊ ህግ ስህተት ማረም ስልጣን አንጻር ሲታይ በዚህ ችልት የተለየ ድምዲሜ ሉያዝበት ወይም ሉለወጥ የሚችል አይደለም። ምክንያቱም የዚህ ችልት በሕጉ ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን ፍሬ ነገርን ማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን ስላለመሆኑ ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነውና።
በመሆኑም ንብረቶቹ የወንጀል ፍሬዎች ስለመሆናቸው ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ባለቸው ፍርድ ቤቶች መረጋገጡን እንዲለ የምንቀበለው ጉዲይ ሁኖ ወደ ሕጉ ስንመጣ ደግሞ በሕጉ ላይ በግልጽ በተደነገገ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ከአንቀጽ 98 ቀጥል በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ንብረቱ በሙለ ወይም በከፉል እንዱወረስ ሉፈርድ እንደሚችል በዚሁ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ አንድ ስር በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን በአንቀጹ ንኡስ አንቀጽ ሁለት ስር ደግሞ የጥፊተኛነት ውሳኔ በተሰጠበት የወንጀል ስራ ወንጀለኛው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያገኘው ንብረት እንደሚወረስ አስገዲጅነት ባለው መልኩ ተደንግጓል። ከአንቀፅ 98(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የንብረት መውረስ ፍርድ ላሰጥ የሚችለው ወንጀለኛው ንብረቱን ያገኘው የጥፊተኛነት ውሳኔ በተሰጠበት የወንጀል ስራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ ስለመሆኑ ነው። በመሆኑም የጥፊተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ የንብረት መወረስ እንደሚኖር በቅጣት መልክ ባያስቀምጥም ንብረቱ የወንጀለ ፍሬ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ ፍርድ ቤቱ የወንጀለኛው ንብረት ለመንግስት ውርስ እንዱሆን የግድ መፍረድ ያለበት መሆኑን ሕጉ በግልጽ ያሳያል።
ከዚህ አንጻር ስንመለከተውም የአመልካች ጠበቃ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 98(1) ድንጋጌን ብቻውን ነጥለው በመጥቀስ የሚያቀርቡት ክርክር የአንቀጹን ንኡስ አንቀፅ ሁለት ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ በክርክሩ ሂደት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ጋር ያገናዘበ ሁኖ አላገኘነውም።ስለሆነም የአመልካች ንብረቶቹ የተገኙት በወንጀል ስራ ስለመሆኑና ንብረቶቹ የወንጀለ ፍሬ ስለመሆናቸው ተረጋግጦ ለመንግስት ውርስ እንዱሆኑ የተሰጠው ውሳኔ በ1949 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 97"ም" ሆነ በ1996 ዓ/ም ከወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 98(2) ድንጋጌዎች ይዘት ሲታይ ሕጉን የተከተለ እንጂ የሚነቀፍ ሁኖ አላገኘነውም።
ላላው ከዚሁ የንብረት መውረስ ውጤት ጋር ተያይዞ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንደተገለፀው ግልጽ ሁኖ መቀመጥ ያለበት ነገር ለመንግስት ውርስ እንዱሆኑ በታዘዙት የአመልካች ንብረቶች የሶስተኛ ወገኖች መብት ካለ የማይነካ መሆኑ ነው። ስለሆነም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠው ግልጽ ውሳኔ እና የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በውርስ የተገኙ ንብረቶች ሉወረሱ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ በንብረቶቹ ላይ ሶስተኛ ወገኖች ያላቸው መብት እንዲይነካ የሚገልጽ በመሆኑ በዚህ ረገድ መብት አለን የሚለትን ሶስተኛ ወገኖች የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔም መብታቸውን የማይነካ መሆኑ ሉታወቅ የሚገባ ሁኖ አግኝተናል። ሲጠቃለልም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለ ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተሻሽል የንብረት ውርስ ውሳኔን ያጸናው የውሳኔ ክፍል በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195(2(ለ-2) መሰረት ጸንቷል።
አመልካች በወንጀለ ተግባር ስለማግኘታቸው የተረጋገጡት ንብረቶች ለመንግስት ውርስ እንዱሆኑ መወሰኑ ሕጋዊ ነው ብለናል። ሆኖም የሶስተኛ ወገኖች መብት ግን የሚነካ ላሆን አይገባም ብለናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/ይ/መ/
No topics extracted.