No summary available.
ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ብስራት ወልደመስቀል - ጠበቆች 1. አበበ አሣመረና 2. ሙለጌታ ወንድመአገኝ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዐቃቤ ሕግ - ደሴ መንበር ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ጉቦ ማቀባበል ወንጀልን መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ የመሰረተው ክስ አመልካች የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆነው በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰብ አቶ አትክልት ዘሪሁን ከወንጀል ተጠያቂነት እንዱያመልጡ ለማድረግ በማሰብ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አቃቤ ሕግ የሆኑትን አቶ ተስፊማርያም ገብረ ትንሳኤ በእጁ ያለውን መዝገብ እንዱዘጋና ለዚህም ብር 5000.00 እንዱቀበላቸው በተደጋጋሚ በመወትወት መስከረም 24 ቀን 2003 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 10፡30 ሰዓት ሲሆን በአዱስ አበባ ከተማ በተለምድ ሒያ ሁለት ማዞሪያ ተብል በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ጌታሁን በሻ ህንፃ 3ኛ ፍቅ ባለው ካፋ ውስጥ የህጉና የሙያው ምግባር ከሚፈቅደው ውጪ ለባለስልጣኑ መ/ቤት አቃቤ ህግ አቶ ተስፊማርያም ገ/ትንሳኤ ብር 5000.00 ሲሰጡ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 429 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነው። የስር ፍ/ቤትም አመልካች ክሱ ደርሷቸውና በግልጽ ችልት ተነቦላቸው ክሱን እንዱረደት ካደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃል ጠይቆ ስለድርጊቱ አፈፃፀም አመልካች የክህደት ቃል በመስጠታቸው አቃቤ ህግ አለኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን በማቅረብ ካሰማ በኋላ አመልካች ድርጊቱን መፈጸማቸው መረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ተገንዝቦ የመከላከል መብታቸውን ጠብቆላቸው አመልካች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው አሰምተዋል። ከዚህም በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ያቀረቧቸው የመከላከያ ምስክሮች ቃል የማይታመን እና እርስ በራሱ የሚጣረስ መሆኑን በመግለጽ ውድቅ ከአደረገው በኋላ አመልካችን በተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጎ ቅጣቱን በተመለከተም መጠኑን በቅጣት መመሪያው መሰረት በመመርመር አንድ አመት ከአራት ወር ፅኑ እስራትና በብር ሶስት ሺህ የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙን አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሚያዝያ 10 ቀን 2004 ዓ/ም በተፃፈ አራት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ምክንያቶችን ዘርዝሮ አቅርቧል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- አቃቤ ሕግ ክሱን በማስረጃ በበቂ ሁኔታ አላስደገፈም፣ የድርጊቱን አፈፃፀም የሚሸፍነው ድንጋጌ በዐቃቤ ህግ ተጠቅሶ የቀረበ አይደለም፣ የቅጣት አወሳሰኑም የቅጣት መመሪያውን መሰረት ያላደረገ ነው፣ ቅጣቱ እንዱገደብ የቀረበው ጥያቄም የታለፈው ያላግባብ ነው የሚለትን የቅሬታ ነጥቦች በመዘርዘር ውሳኔው እንዱለወጥ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታመኑ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በፅሁፍ መልሱን አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለው ሆኖ አግኝቶታል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ በዋናነት የቅሬታ ነጥብ ያደረገው የአቃቤ ሕግ ክስ በበቂ ማስረጃ አልተደገፈም፣ የመከላከያ ማስረጃዎች ቃል ውድቅ የተደረገው ያላግባብ ነው የሚለው ነው።
ይሁን እንጂ ይህ ሰበር ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕግ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ አተረጓጎም ስህተትን ማረም እንጂ ፍሬ ነገርን ማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን አይደለም። በመሆኑም አመልካች የአቃቤ ሕግ ክስን ለማስረዲት የቀረቡት ምስክሮች እንደክሱ አላስረደም፣ የሚታመኑ አይደለም፣ የድርጊቱ አፈጻጸም በአግባቡ አልታየም በማለት ያቀረባቸው የቅሬታ ነጥቦች የፍሬ ነገር ክርክሮች በመሆናቸው ይህ ችልት ሉቀበላቸው የሚገባቸው የክርክር ነጥቦች ባለመሆናቸው አልተቀበልናቸውም። በመሆኑም አመልካች ለድርጊቱ ኃላፉነት አለበት ተበል የተወሰነው ወንጀለን መስራቱ ወይም መፈጸሙና ተሰራ ወይም ተፈፀመ የተባለው ወንጀል ደግሞ በአመልካች መፈጸሙ በማያጠራጥር ሁኔታ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። አመልካች ድርጊቱ ተፈፅሟል ቢባል እንኳ ጉቦ ማቀባበል ወንጀልን የሚያቋቁም አይደለም በማለት በሰበር አቤቱታቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
በመሰረቱ አንድ ሰው በወንጀል ሕግ ቁጥር 429 መሰረት ጉቦ ማቀባበል የወንጀል ድርጊት ሉጠየቅ የሚችለው ለራሱ ማናቸውንም አይነት ጥቅም ባያገኝም እንኳ የመንግስት ስራን ለሚያከናውን ሰው ጉቦ ለመስጠት ገንዘብ፣ ዋጋ ያለውን ነገር፣ አገልግልት ወይም ላላ አይነት ጥቅም ከላላ ሰው የተቀበለ እንደሆነ ወይም የራሱን የባንክ ሂሳብ እንደዚህ አይነት ጉቦ ለማቀባበል ያዋለ መሆኑ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(4) መሰረት ሲረጋገጥ ነው።
ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በድንጋጌው ስር የተመለከቱት የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች ወንጀል አድራጊው ገንዘቡን ከላላ ሰው ተቀብል ወይም የራሱን የባንክ ሂሳብ እንደዚህ አይነት ጉቦ ለማቀባበል በማዋል ድርጊቱን የሚፈጽም መሆኑን የሚያሳዩ መሆናቸውን ነው። በያዝነው ጉዲይ አመልካች ለባለስልጣኑ መ/ቤት አቃቤ ህግ ጉቦ ለመስጠት ያለበት ዋናው ምክንያት በወንጀል የተከሰሰውን ላላውን ሰው ከሕግ ተጠያቂነት ለማዲን ሲለ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ከመረጋገጡም በላይ ድርጊቱ የተፈፀመው ላላውን ሰው ከሕግ ተጠያቂነት ለማዲን ካላቸው ፍላጎት ስለመሆኑ በአቃቤ ሕግ ምስክሮች መነገሩን መሰረት በማድረግ የስር ፍ/ቤት አመልካች ገንዘቡን ለማቀባበል የፈፀሙት ድርጊት መሆኑን በውሳኔው ላይ አስፍሯል። በእርግጥም ይኸው ፍሬ ነገር አመልካች ገንዘቡን በወንጀል ከሚፈለገው ሰው ተቀብለው ለባለስልጣኑ አቃቤ ሕግ ለመስጠት ያደረጉት ነው ከሚባል በስተቀር ላላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ለድርጊቱ መፈፀም መሰረት የሆነው ዋናው ነገር ላላውን ሰው ከሕግ ተጠያቂነት ለማዲን ስለመሆኑ ከተረጋገጠ አመልካች ከዚሁ ሰው ገንዘብ ስለመቀበላቸው ያለመረጋገጡ የጉቦ ማቀባበል ድርጊትን አያቋቁምም ወደሚለው ድምዲሜ የሚያደርስ አይሆንም። ይልቁንም ዋናውና መታየት ያለበት የድርጊት ፈፃሚው ፍላጎት (Motive) ነው። ስለሆነም አመልካች በወንጀል የሚፈለግ ሰው በሕግ እንዲይጠየቅ ከመነጨ ፍላጎት ሕገወጥና የሚያስቀጣ ድርጊት እያወቁ በራሳቸው ፍላጎት ያደረጉ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ አድራጎታቸው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 429 ድንጋጌ ስር የሚወድቅ መሆኑን ከዚሁ ድንጋጌ እንዱሁም ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23( (1) እና (4)) እና 58(1(ሀ)) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ሆኖ ስለአገኘን በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርከር አልተቀበልነውም። በመሆኑም በአመልካች የተፈፀመው ድርጊት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 429 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ የሚያሟላ ሆኖ አግኝተናል።
ላላው አመልካች የመሰረታዊ ሕግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት በቅሬታ ነጥብነት ያቀረቡት ክርክር የቅጣት አወሳሰኑን በተመለከተ ነው። አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ የሚያስቀጣው የቅጣት መነሻው እንደነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት፣ ወይም ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በመቀጮ ነው። የበታች ፍ/ቤቶች በአመልካች ላይ ያስተላለፈት የቅጣት መጠን አንድ አመት ከአራት ወር ፅኑ እስራት እና የብር 3000.00 መቀጮ ነው።
በመሰረቱ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ሲታይም የቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች አወሳሰንን በተመለከተ ዘርዘር ያለ ንዐስ ድንጋጌዎችን አካቶ ይዟል። በዚህ አንቀጽ ስር ያለ ንዐስ አንቀጾች የሚያሳዩት ፍ/ቤቱ ቅጣቶቹን የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚወስነው የወንጀል ህጉን ጠቅላላ ክፍል ድንጋጌዎችን እንዱሁም ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው የሚደነግጉት የልዩ ክፍለ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ መሆኑን፣ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሳሱትን ምክንያቶችና የአሳቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ፣ እንዱሁም የወንጀለን ከባድነትና የአፈጻጸሙን ሁኔታዎች በማመዛዘን መሆኑን፣ የወንጀል ህግ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍ/ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስን ያሳያል። የበታች ፍ/ቤቶች በአመልካች ላይ ቅጣት ያስተላለፈት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብለው ከአመዛዘኑና በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ስለመሆኑ ውሳኔው ያሳያል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ለአመልካች ሶስት ምክንያቶችን በቅጣት ማቅለያነት ወስድና ከቅጣት መመሪያውም ጋር አዛምድ ቅጣቱን የጣለው መሆኑን ውሳኔው በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን የቅጣት መጠኑ ከድርጊቱ አፈጻጸም አንጻር ሲታይም በወንጀል ሕጉ ስለቅጣት የተቀመጡትን መሰረታዊ የሆኑ የቅጣት አጣጣል መርሆዎችን ያላገናዘበ ነው ለማለት የሚያስችል ምክንያት አላገኘንም። በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካች ቅሬታ (የቅጣት በዛ ክርክር ከሚሆን ውጪ) በቅጣት አወሳሰን ላይ የተጣሰ መርህ ስለመኖሩ የሚያረጋግጥ ሆኖ አላገኘነውም። እንዱሁም አመልካች ቅጣቱ ሉገደብ ይገባ ነበር በማለት የሚያቀርቡት ክርክርም የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 190፣ 192፣ እና 194 ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ ፍ/ቤት በቅጣት አጣጣለ ጊዜ ግንዘቤ ሉወስድባቸው ስለሚገባቸው ህጋዊ ምክንያቶች ያለገናዘበ በመሆኑ በዚህ ረገድም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት አልተቻለም። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 22 እና 28 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ መጋቢት 21 ቀን 2004 ዓ.ም. የጸናው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ ቁጥር 195(2(ለ(2)) መሰረት ሙለ በሙለ ፀንቷል።
ውሳኔው የጸና መሆኑን አውቆ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈጽም ለማ/ቤቱ ይገለጽለት ብለናል።
No topics extracted.