No summary available.
ሰኔ 22 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ጀማል መሐመድ - ጠበቃ አቶ ጥላሁን ምትኩ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዓቃቤ ህግ - አቶ ታምራት ጥላሁን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመዝገብ ጥር 10 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ፍርድና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ በሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል መጀመሪያ ፍ/ቤት ነው። ጉዲዩ የእምlት ማጉደል ወንጀል የሚመለከት ነው። በስር ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ተከሳሽ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን በመተላለፍ ለራሱ ብልጽግና ለማግኝት አስቦ መስከረም 6 ቀን 2003 ዓ.ም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል በአራዲ ክ/ከተማ ጥበበ ሆስፑታል ፉት ለፉት ከሚገኘው አይከል የኪራይና የኮንትራት የትራንስፕርት ድርጅት ወደ ጎንደር ለመላክ ከአቶ ገ/መስቀል በርሓ የተረከባቸውን ጠቅላላ ግምታቸው ብር 181,675 (አንድ መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ብር) አመልካች ግንኙነቱ የሚስከትልበትን ግዳታና ኃላፉነት አጓድል ቢገኝ በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል ወይስ አይሆንም? የሚለትን ጥያቄዎች መታየት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
አመልካች የተጠሪ ምስክር በሆኑት አቶ ተክለብርሃን በርሄ ንብረት የሆነ በአንድ ካርቶን የታሸገ እቃ ወደ ጎንደር እንዱልክለት የተጠሪ ሁለተኛ ምስክር ዲቆን ገብረመስቀል በርሓ መስከረም 6 ቀን 2003 ዓ.ም ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተኩል እቃውን እንደታሸገ እሱ ባለቤት ሲያስረክበው እቃውን ወደ ጎንደር ለማጓጓዝ በመስማማት እቃውን እንደታሸገ ሰራተኞቹ አመልካች ባለበት መረከባቸውንና እቃውን ጎንደር ድረስ ለማጓጓዝ ከላኪው ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሣ ብር) የተቀበለ መሆኑ ተረጋግጧል። አንድ ሰው ዋጋ በመቀበል አንድን እቃ የታሰበበት ሥፍራ ለማድረስ የሚገባው ግዳታ የእቃ ማጓጓዝ ውል እንደሆነ አግባብነት ያላቸውን የህግ፣ ማእቀፍች በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። ይህም ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትና ከላይ የተገለጹት ተግባራት የግል ተበዲይና አንደኛ የተጠሪ ምስክር በሆኑት አቶ ተክለብርሃን በርሄና በአመልካች (በአይከል የኪራይና የኮንትራት የትራንስፕርት ድርጅት) መካከል ህጋዊ ውጤት ባለው የእቃ ማጓጓዝ ውል የተቋቋመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
አቶ ተክለ ብርሃን በርሄና በአመልካች (በአይከል የኪራይና የኮንትራት የትራስፕርት ድርጅት) መካከል የተቋቋመው ህጋዊ ውጤት ያለው የእቃ ማጓጓዝ ውል የእቃው ላኪ ለአጓጓዥው መክፈል ያለበትን የአገልግልት ክፍያ የፈጸሙ ሲሆን አመልካች በውለ መሰረት በልምድ መሰረት የሚገባውን ሙለ ጥንቃቄ እቃውን ማጓጓዝና በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታ ይኖርበታል። አመልካች በገባው የእቃ ማጓጓዝ ውል መሰረት በካርቶን ታሽጎ የተሰጠውን እቃ በሙለ ጥንቃቄ ማጓጓዝ፣ በካርቶን የታሸገውን እቃ በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን ያልተወጣ መሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አመልካች በገባው የእቃ ማጓጓዝ ውል መሰረት በካርቶን ታሽጎ የተሰጠውን አቃ በሙለ ጥንቃቄ ማጓጓዝ፣ በካርቶን የታሸገውን እቃ በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን አለመወጣቱ አመልካችን በፍታብሓር ተጠያቂ ከመሆን አልፍ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንኡስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን በመተላለፍ በእምነት ማጉደል ወንጀል የሚያስጠይቃቸው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን መሰረታዊ ነጥብ ነው።
ከላይ የተነሳውን ጥያቄ ለመመለስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ድንጋጌ አቀራረጽ ፣ ዝርዝር ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ መመርመሩ አስፈላጊ ነው። የወንጀል ህጉ በንብረት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀልችን በሚዘረዝርበት ምእራፍ ሁለት በልዩ ሁኔታ በተንቀሳቀቃሽ ንብረቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀልችን በሚዘረዝረው ክፍል አንድ ሥር የተደነገገው የዕምነት ማጉደል ወንጀል መሰረታዊ ባህሪ ይዘትና የሚስከትለው ኃላፉነትን የሚዘረዝር ድንጋጌ ነው።
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንዐስ አንቀጽ ድንጋጌ አማርኛ ቅጅ ቃል በቀል ሲነበብ ማንም ሰው ተገቢ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የላላ ሰው የሆነውንና ለአንድ ለተወሰነ ግልጋልት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙለ ወይም በከፉል ለራሱ ያደረገ ፣ ወይም ለላላ ሰው ያደረገ ፣ የወሰደ ፣ የሰወረ ወይም ለራሱ ወይም ላላ ሰው አገልግልት ያዋለ ወይም ይህን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት የፈጸመ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በቀላል እስራት ወይም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል በማለት ይደነግጋል ። የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንዐስ አንቀጽ 3 የተከሣሹ ወንጀል ሃሣብ ግምት የሚደነግግ ሲሆን ይዘቱም ተከሣሹ ሲጠየቅ በእምነት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዕቃ ወይም ጥሬ ገንዘብ ለመመለስ ወይም ለመክፈል ወይም ዕቃው ያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግልት ያዋለው መሆኑን ማስረዲት ካልቻለ ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ያልተገባ ጥቅም ማዋል ሃሣብ እንዲዋለው ይቆጠራል የሚል ይዘት ያለው ነው።
የእግገሉዝኛውን ቅጅ ስንመለከት Breach of Trust የሚል ርዕስ ያለው አንቀጽ 675 Whoever with intent to obtain for Himself or to Procure for a third person an unjustifiable enrichment appropriates , or Procures for another, takes or causes to be taken misappropriates uses to his own benefit or that of a third person or disposes of for any similar act in whole or in part a thing or a sum of money which is the Property of another and which has been delivered to him in trust or for a specific purpose, is punishable , according to the circumstances of the case with simple imprisonment or with rigorous not exceeding five years በማለት በንዐስ አንቀጽ 1 የሚደነግግ ሲሆን ንዐስ አንቀጽ 3 The intent to obtain for himself or to Procure for third person an unjustifiable enrichment shall be presumed where the criminal is unable upon call, to produce or repay the thing or sum entrusted or at the time when he should have returned it or accounted there for በማለት ይደነግጋል።
አመልካች አይከል የኪራይና የኮንትራት የትራስፕርት ድርጅት ያለው በመሆኑ በገባው የእቃ ማጓጓዝ ውል መሰረት በካርቶን ታሽጎ የተሰጠውን እቃ በሙለ ጥንቃቄ ማጓጓዝ በካርቶን የታሸገውን ዕቃ በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሳ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን የሚወጣው እሱ ራሱ ብቻ በግለ ዕቃውን በዕምነትና በአደራ ጎንደር ወስድ በማስረከብ አይደለም። ዕቃውን በወኪለ በሰራተኞቹ ወይም ከላላ ሰው ጋር የዕቃ ማጓጓዝ ውል በመዋዋል ግዳታውን ሉፈጽም የሚችልበት ሁኔታ ሰፉ ነው። ይህም በመሆኑ አመልካች በውለ መሰረት በልምድ መሰረት የሚገባውን ሙለ ጥንቃቄ እቃውን ማጓጓዝና በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን ባይወጣ በውለ መሰረት ዕቃውን ባለማስረከቡ አግባብነት ባላቸው የህግ ድንጋጌዎች በፍትሐብሕር ከሚጠየቅ በስተቀር የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንዐስ አንቀጽ 1 ተላልፎል ተብል በዕምነት ማጉደል ወንጀል ሉጠየቅ የማይችል መሆኑን ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 65 ድንጋጌ ዝርዝር ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 አመልካች በገባው የእቃ ማጓጓዝ ውል መሰረት በካርቶን ታሽጎ የተሰጠውን እቃ በመለ ጥንቃቄ ማጓጓዝ በካርቶን የታሸገውን ዕቃ በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑ በዕምነት ማጉደል ወንጀል ተጠያቂ የሚሆን ስለመሆኑ አይደነግግም። ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንዐስ አንቀጽ አንድ ለተወሰነ ግልጋልት የሚለው አገላለጽ የእቃ ማጓጓዝ ውልን ይጨምራል በማለት የተከራከረ ቢሆንም የድንጋጌው ይዘት አንድ ሰው አንድን ንብረት ለአንድ አገልግልት ለማዋል ኃላፉነት ተረክቦት ንብረቱን ለተባለው አገልግልት ሳያውል ሲቀር በዕምነት ማጉደል ወንጀል የሚጠየቅ መሆኑን የሚመለከት እንጅ በማጓጓዝ ውለ መሰረት በልምድ መሰረት የሚገባውን ሙለ ጥንቃቄ እቃውን በማጓጓዝና በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን ያልተወጣ አጓዥ በዕምነት ማጉደል ወንጀል እንዱጠየቅ የድንጋጌው ይዘት መንፈስና ዓላማ የማያሣይ በመሆኑ በዚህ በኩል ተጠሪ ያቀረበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል አመልካች በካርቶን የታሸገውን ዕቃ የተረከበው በንግድ ድርጅቱ በኩል በማጓጓዝ ውለ መሰረት በልምድ መሰረት የሚገባውን ሙለ ጥንቃቄ በመድረግ እቃውን ማጓጓዝና በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድረሶ ለተቀባዩ ለማስረከብ በማሰብ እንደሆነ በተጠሪ ማስረጃ ጭምር ተረጋግጧል።
ማንም ሰው በዕምነት ማጉደል ወንጀል የሚጠየቀው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት ወይም ባለማስገኘት በማሰብ የላላ ሰው የሆነወንና ለአንድ ለተወሰነ አገልግልት የተሰጠውን ዋጋ ያለው ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙለ ወይም በከፉል ለራሱ ያደረገ ወይም ለላላ ሰው ያደረገ የወሰደ ያስወሰደ የሰወረ ወይም ለራሱ ወይም ለላላ ሰው አገልግልት ያዋለ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
የአመልካች አድራጎት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንዐስ አንቀጽ 3 በሚደነግገዉ የወንጀል ሃሣብ ግምት የማይሸፈን መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት ለመረዲት ይቻላል።
አንድ ሰው በወንጀል ጥፊተኛ ተብል የሚቀጣው የህግ የግዙፍ ተግባርና የሞራል ሁኔታ መሟላቱ ሲረጋገጥ እንደሆነ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 23 ተደንግጎል። በያዝነው ጉዲይ ከላይ የዘረዘርነው የህግ የሃሣብ ሁኔታዎች አልተሟለም ። ይህ ሁኔታ መሟላቱን ሳያረጋግጡ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንኡስ አንቀጽ 1 የተመለከተውን በመተላለፍ የዕምነት ማጉደል ወንጀል የፈጸመ ጥፊተኛ ነው በማለት አመልካች በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እሥራት እንዱቀጣ የሰጡት ውሣኔ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ድንጋጌ አቀራረጽ ዝርዝር ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 1ዐ ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ፍርድና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በሰኔ 7 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በወንጀለኛ መቀጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ለ/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በገባው የእቃ ማጓጓዝ ውል መሰረት በካርቶን ታሽጏ የተሰጠውን እቃ በሙለ ጥንቃቄ በማጓጓዝ በካርቶን የታሸገውን ዕቃ በተወሰነው ጊዜና ሥፍራ አድርሶ ለተቀባዩ የማስረከብ ግዳታውን አለመወጣቱ አመልካችን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 675 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሰረት በዕምነት ማጉደል ወንጀል የሚያስጠይቀው ባለመሆኑ በነጻ ይሰናበታል በማለት ወስነናል።
አመልካች ከቀረበበት ወንጀል ክስ በነጻ ተሰናበተ በመሆኑ ከእስር እንዱለቀው ለክፍለ ማረሚያ ቤት ይጻፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.