No summary available.
ሰኔ 4 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡-
ጉዲዩ የሙስና ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካቾች እና በላልች ሃያ ሰዎች ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ ሲታይ አመልካቾችና የስር ላልች ሃያ ተከሳሾች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ)፣ (ለ)) እና በተሻሻለው ልዩ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 214/1974 አንቀጽ 23(1(ሀ)(ለ)) እና (2) ድንጋጌዎች ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በስልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብል ሲሆን የስር ፍ/ቤት የአቃቤ ህግ ማስረጃዎቹን ከሰማ በኋላ የአሁኑን አመልካቾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141 መሰረት በነጻ አሰናብቷል። በዚህ ብይን የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የአሁኑ አመልካቾች ድርጊቱን መፈጸማቸውን አቃቤ ሕግ በማስረጃዎቹ አስረድቶ እያለ ምንም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዱሰናበቱ ተብል ብይን መሰጠቱ ያላግባብ ነው በሚል ምክንያት የስር ፍ/ቤትን ብይን ሽሮ አመልካቾች ሉከላከለ ይገባል በማለት ጉዲዩን ለስር ፍ/ቤት መልሶ ልኮለታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካቾች ድርጊቱን ስለመፈፀማቸው አቃቤ ህግ በማስረጃዎቹ አስረድቷል በሚል ምክንያት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ ያላግባብ ነው የሚል ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም የአሁኑ አመልካቾች ከ15% በላይ የዋጋ መረጋጋት ለማድረግ ኤሪክሰን የተባለውን ኩባንያ እንዱያልፍ ጥረት አድርገው ሳይሳካ ቢቀርም የእነሱ ሕገ ወጥ ተግባር በውጭ ግዥ ኮሚቴ ግቡን እንዱመታ ተደርጓል በሚል ጥፊተኛ ናቸው የመባላቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ሲመረምር አስቀድሞ ምላሽ ሉያገኝ የሚገባው አቢይ ነጥብ ሆኖ ያገኘው ጉዲዩ በዚህ ሰበር ችልት ለመታየት ብቁ ነው ወይ? የሚለው ነው።
ከላይ እንደተመለከተው የአሁኑ አመልካቾች በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከመሰረተባቸው የሙስና ወንጀል ምንም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተው የነበሩ ሲሆን ይኸው የስር ፍ/ቤት የአመልካቾች በነፃ መለቀቅ ብይን ግን ይግባኙን በተመለከተው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ተሽሮ አመልካቾች በስር ፍ/ቤት የመከላከያ ማስረጃ እንዱያሰሙ የተወሰነ ሲሆን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይኸው የይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው።
በመሰረቱ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፔቡሉክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን በማናቸውም የመጨረሻ ፍርድ ባገኙ ጉዲዮች ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ይህንኑ ስህተት ማረም ነው። የአቤቱታው አቀራረብ ሥርዓትም በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት ተደንግጓል።
በዚህም መሰረት ጉዲዩ ለሰበር እንዱታይለት የሚፈልግ አቤቱታ አቅራቢ ጉዲዩ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚልበትን ምክንያት በማመልከቻው ላይ ዘርዝሮና ጽፍ ማቅረብ ያለበት መሆኑን፣ ከማመልከቻው በተጨማሪ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ቅጅዎችን በማያያዝ የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠ በዘጠና ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንደአለበት አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 22 በዝርዝር ይደነግጋል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ጉዲይ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሚሰማው አስቀድሞ በሶስት የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች የሚሰየሙበት ችልት ውሳኔው ለሰበር የሚያበቃ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለው ብል ሲወሰን ነው። በድንጋጌው "የመጨረሻ ውሳኔ" የሚለው ሀረግ የሚያስገነዝበው ለሰበር ችልቱ የሚቀርቡት ማናቸውም ጉዲዮች የይግባኝ አቀራረብ ስርዓቱን ያጠናቀቁና የመጨረሻ ፍርድ የተሰጣቸው መሆን ያለባቸው መሆኑን ነው። በመሆኑም የመጨረሻ ፍርድ ያላገኘ ጉዲይ ለሰበር ችልቱ ላቀርብ የሚችለበት አግባብ የለም።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካቾች የተከሰሱት በሙስና ወንጀል ሆኖ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነሥርዓት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ነው። በዚህ አዋጅ መሰረት የሙስና ክስ የሚመራበት ሥርዓት ተዘርግቷል። አዋጁ ከደነገጋቸው ጉዲዮች አንደ የይግባኝ መብት ነው። የአዋጁ አንቀጽ 40 የትዕዛዝ ይግባኝን የሚደነግግ ሲሆን ይግባኝ ልባል የሚችለው በአዋጁ አንቀጽ 36(2) መሰረት በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ እንደሚቻል የሚደነግግ ሲሆን በአንቀጽ 36(2) መሰረት የሚሰጡ ውሳኔዎች ደግሞ በቅድመ ክስ ዝግጅት ሂደት ፍ/ቤቱ የማስረጃ ተቀባይነትን በተመለከተ በሚነሳ ጥያቄ፣ መደበኛው የክስ ሂደት ከመጀመሩ በፉት ውሳኔ ሉያገኝ በሚገባው በማናቸውም የሕግ ጥያቄ ላይ ስለመሆኑ ድንጋጌው ያሳያል። ይሁን እንጂ አዋጁ አንድ ሰው በሙስና ወንጀል ተከሶ የኮሚሽኑ አቃቤ ሕግ ማስረጃ እንደክሱ ያስረዲ ስለመሆኑ ፍ/ቤቱ አምኖ የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጥ በዚህ ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የሚቻል ስለመሆኑ በግልጽ ያስቀመጠው ድንጋጌ የለም። ሆኖም ተጠቃሹ አዋጅ በአንቀጽ 55 ስር የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ፣ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ፣ የወንጀል ህግና ላልች አግባብነት ያላቸው ህጎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል በሚል ደንግጎ በአዋጁ አንቀጽ 58 ስር የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎችን ለይቶ ሲያስቀምጥ የፀረሙስና የልዩ ስነስርዓትና ማስረጃ ህግ አዋጅ ቁ. 236/1993 እንደተሻሻለ መሻሩን፣ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ላልች ሕጎች በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዲዮች ላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው ደንግጓል። ከዚህም መረዲት የሚቻለው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ሕጉ ላይ የተመለከቱት የይግባኝ አቀራረብ ስርዓትን የሚደነግጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸው መሆኑን ሲሆን በዚህ ሕግ አንቀጽ 184 እና 185 ስር የተመለከቱት ድንጋጌዎች አንድ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ፍ/ቤቱ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 142(1) መሰረት ብይን ሲሰጥ ይግባኝ ለማቅረብ የሚቻል መሆኑን አያሳዩም። ስለሆነም አመልካቾች በጉዲዩ ላይ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት መከላከያ ማስረጃ ሰምቶ በሚሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ካላቸው በስርዓቱ መሰረት ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ በማቅረብ ጉዲያቸው ከታየና የመጨረሻ ፍርድ ካገኙ በኋላ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአቃቤ ሕግን ማስረጃ በተመለከተ በሰጠው ውሳኔ ላይ ጭምር በስርዓቱ መሰረት የሰበር አቤቱታ አጠቃልለው ከሚያቀርቡ በስተቀር ከወዱሁ የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርቡ በማለት በሰጠው ውሳኔ ላይ የሰበር አቤቱታ ማቅረባቸው ስለሰበር አቤቱታ አቀራረብ የተደነገጉትን ሕጎች ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበ በመሆኑ አቤቱታቸው ለሰበር ብቁ አይደለም ተብል ሉዘጋ የሚገባው ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት አመልካቾች በዋናው ጉዲይ ላይ ያቀረቡትን ቅሬታ መመርመር ሳያስፈልግ መዝገቡን ጉዲዩ ለሰበር ብቁ አይደለም በማለት ዘግተናል። አመልካቾች በአቃቤ ማስረጃ ላይ ያላቸውን ሕጋዊ ቅሬታ በስርዓቱ መሰረት በሚያቀርቡት የሰበር አቤቱታ ወደፉት ከማቅረብ ግን ይህ ውሳኔ አያግዲቸውም ብለናል።
No topics extracted.