No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የትግራይ ክልል አጽቢ ወረዲ ዐቃቤ ሕግ ተጠሪ፡- ተማሪ ሐጎስ ወልደሚካኤል በላለበት ታይቷል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዝገብ በግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአጽቢ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። ጉዲዩ በአንድ የወንጀል ድርጊት ሁለት ጊዜ የመከሰስና የመቀጣት ሕጋዊነትን አስመልክቶ በቀረበ ክርክር ላይ የተሰጠውን የሕግ ትርጉም የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካች ለአጽቢ ወረዲ ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርቦ ተጠሪ በወንጀል ሕግ 540 የተደነገገውን በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስቦ የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት በማለት በም/እምባ ቀበላ አረዋ ከተባለው መንደር ድንጋይ ወርውሮ ሟች ግደይ ገብረየሱስ ጭንቅላታቸውንና አከርካሪያቸውን በመምታት የገደለ በመሆኑ ሆነ ብል የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረበው የወንጀል ክስ ነው። ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ በወንጀል ክሱ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ ሟችን ድንጋይ ወርውሬ መትቻለሁ። ነገር ግን ሟች ድኖ ላላ ጊዜ የሞተ በመሆኑ ለሟች መሞት በኃላፉነት ልጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክሯል። አመልካች የሰው ምስክርና የፅሐፍ ማስረጃ አቅርቧል። ተጠሪ ሟች በድንጋይ ከተመታ በኋላ ሕክምና ተደርጏለት ድኖ የመስኖ እርሻ ሥራ ሲሰራ የነበረ መሆኑን ያውቁልኛል በማለት ሁለት የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ማስረጃ ከሰማና ከመረመረ በኋላ ተጠሪ በወንጀል ሕግ 540 የተደነገገውን በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስቦ ድንጋይ ወርውሮ ሟች ግደይ ገብረየሱስ ጭንቅላታቸውንና አከርካሪያቸውን በመምታት የገደለ በመሆኑ ጥፊተኛ ነው በማለት ተጠሪ በአሥር ዓመት ፅኑ እሥራት እንዱቀጣ ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውቅሮ ምድብ ችልት ይግባኝ አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ከመረመረ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የሚነቀፍበት የሕግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ነጥብ የለም በማለት የተጠሪን ይግባኝ በወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ሰርዞታል።
ተጠሪ አመልካች ከዚህ በፉት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556 ንዐስ አንቀጽ 2 /ሀ/ የተመለከተውን በመተላለፍ የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት በም/እምባ ቀበላ አረዋ ከተባለው መንደር ድንጋይ ወርውሮ በመምታት በግል ተበዲይ አቶ ግደይ ገብረየሱስ ላይ ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት ለወንበርታ ወረዲ ፍርድ ቤት አቅርቦብኝ ጥፊተኛ ተብዬ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም ተቀጥቻለሁ። አመልካች ተጠሪ በተቀጣሁበት ድርጊት በማንሣት በድጋሚ በወንጀል መከሰሱና የበታች ፍርድ ቤቶችም እኔን ጥፊተኛ ብለው ቅጣት መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። አመልካች ተጠሪ በወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 130 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ይህንን ነጥብ መጀመሪያ የክስ መቃወሚያ አድርጏ ያላቀረበ ስለሆነ የሰበር መከራከሪያ ሉያደርገው አይገባም። ተጠሪ ከዚህ በፉት የተከሰሰው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556 ንዐስ አንቀጽ 2 /ሀ/ የተመለከተውን በመተላለፍ አቶ ግደይ ገብረየሱስ ላይ ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል ተብል ነው አሁን የተከሰሰው በወንጀል ሕግ 540 የተደነገገውን በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስቦ ድንጋይ ወርውሮ ሟች ግደይ ገብረየሱስ ጭንቅላታቸውንና አከርካሪያቸውን በመምታት ገድሎል ተብል ስለሆነ የቀረበው ክስ በፉት ከተከሰሰበት ጋር በአንድ ጉዲይ አይደለም በማለት ተከራክሯል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 23ና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 5 በመተርጏም የተከሰሰው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556 ንዐስ አንቀጽ 2 /ሀ/ የተመለከተውን በመተላለፍ አቶ ግደይ ገብረየሱስ ላይ ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል ተብል ጥፊተኛ ተብል የተቀጣ በመሆኑ በድጋሚ በዚያው ድርጊት ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው በማለት የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔን በመሻር ተጠሪን አሰናብቷታል።
አመልካች ነሐሴ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ለዚህ የሰበር ችልት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556 ንዐስ አንቀጽ 2 /ሀ/ የተመለከተውን በመተላለፍ አቶ ግደይ ገብረየሱስ ላይ ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል ተብል በወንበርታ ወረዲ ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበትና በድርድር ጥፊተኝነቱን አምኖ ጥፊተኛ ተብል ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የተቀጣው የተሳሳተ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው። አቶ ግደይ ገብረየሱስ የካቲት 21 ቀን 2002 በተጠሪ ድንጋይ ተመትተው መጋቢት 30 ቀን 2002 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የሟች አቶ ግደይ ገብረየሱስ ህይወት ለሕልፈት የበቃው ተጠሪ በድንጋይ ጭንቅላታቸው ላይ ባደረሰባቸው ጉዲት ምክንያት መሆኑ በሚኒሉክ ሆስፑታል ተረጋግጧል። ስለሆነም ትክክለኛውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ በወንጀል ሕግ 540 የተደነገገውን በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስቦ ድንጋይ ወርውሮ ሟች ግደይ ገብረየሱስ ጭንቅላታቸውንና አከርካሪያቸውን በመምታት ገድሎል በማለት ያቀረብነውን ክስ ተቀብለው የወረዲው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 23 እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 5 የሚጥስ ነው በማለት በመሻር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በአድራሻው ተፈልጎ ያልተገኘ በመሆኑ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ በወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 193 ንዐስ አንቀጽ 1 መሰረት ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር አመልካች ያቀረበው የሰበር ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ተጠሪ በወንጀል አንቀጽ 540 የተደነገገውን በመተላለፍ ሰው ለመግደል አስቦ ድንጋይ ወርውሮ ሟች አቶ ግደይ ገብረየሱስ ጭንቅላታቸውንና አከርካሪያቸውን በመምታት ገድሎል በማለት በድጋሚ መከሰሱንና ተጠሪ በወረዲው ፍርድ ቤትና በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፊተኛ ተብል መቀጣቱ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 23 እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 5 የሚጥስ ነው በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው የሕግ ትርጉምና ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት በም/እምባ ቀበላ አረዋ ከተባለው መንደር ድንጋይ ወርውሮ የግል ተበዲይ አቶ ግደይ ገብረየሱስን የመታቸው መሆኑን ያልካደ ሲሆን ይህ ፍሬ ጉዲይ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃም ተረጋግጧል። ተጠሪ ይህንን ድርጊት በፈጸመ በሁለተኛው ቀን ማለትም የካቲት 24 ቀን 2002 ዓ.ም አመልካች ለወንበርታ ወረዲ ፍርድ ቤት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 556 ንዐስ አንቀጽ 2 /ሀ/ የተመለከተውን በመተላለፍ በግል ተበዲይ አቶ ግደይ ገብረየሱስ ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቦበት ተጠሪ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፊተኛ ተብል በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የተቀጣ መሆኑን አመልካች ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ባቀረበው ክርክርና ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በግልጽ በማመን አቅርቦታል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ በይዘቱ መጀመሪያ ለወንበርታ ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪ ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ፈጽሟል የሚል ወንጀል ክስ፣ በዓቃቤ ሕግ የቀረበው የተጠሪ ድርጊት በግል ተበዲይ ላይ የሞት አደጋ ማድረሱ ከመታወቁ በፉት ነው። አሁን ግን የተጠሪ ድርጊት በግል ተበዲይ ላይ ሞት አደጋ ማድረሱ በመታወቁ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ሆነ ብል የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት ተጠሪን በድጋሚ መክሰሳችን ሕጋዊና ተገቢ ነው የሚል ነው።
የኢፋዱሪ ሕገ መንግስት መሰረታዊ የወንጀል ሕግ መርህ አድርጎ ከደነገጋቸው ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች አንደኛው አንድ ሰው በአንድ የወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፊተኝነቱ ተረጋግጦ በተቀጣበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና መከሰስና መቀጣት የለበትም የሚለው ነው። ይህ የወንጀል ሕግ መርህ በሕገ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 5 ተደንግጓል። ሕገ መንግስቱ በአንቀጽ 23 ‘’ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነሥርዓት መሰረት ተከስሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፊተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም‘’ በማለት ደንግጓል።
የወንጀል ህግ መርሁ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መርህ ሲሆን አገራችን ባጸደቀችው በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፕለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀጽ 14 ንዐስ አንቀጽ 7 “ No one shall be liable to be tried or punished again for an offence for which he has already been finally convicted or acquitted in accordance with the law and penal procedure of the country ” በሚል መንገድ ደንግጎል።
ሆኖም የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት አተረጓጏም በዕለት ከዕለት የወንጀል ክስ አቀራረብ በሚታዩ ስህተቶች የሚፈጠሩ ችግሮችን ዓቃቤ ሕግ በድጋሚ የወንጀል ክስ በማቅረብ ለማረም በሚፈቅድ ሁኔታ የተቀረጸ ነው ወይስ አይደለም፤ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 ድንጋጌ እንዳት መተርጎምና ተፈፃሚ መሆን ይገባዋል የሚለው ነጥብ አከራካሪ መሆኑን አመልካች ተጠሪ የግል ተበዲይን በድንጋይ ወርውሮ የመታው በግል ተበዲይ ላይ ቀላል የአካል ማጉደል ለማድረስ አስቦ በድርጊቱ ቀላል የአካል ማጉደል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ፈጽሟል በማለት የወንጀል ክስ አቅርቦ ተጠሪ በአመልካች በተከሰሰበት ወንጀል ተከራክሮ ከተቀጣ በኋላ፣ አመልካች ከዚህ በፉት በተጠሪ ላይ የወንጀል ክስ ሳቀርብ የተጠሪ ድርጊት በግል ተበዲይ ላይ ያስከተለውን ወይም ሉያስከትል የሚችለውን ውጤት በማገናዘብም ሆነ አግባብነት ያለውን የወንጀል ሕግ ድንጋጌ በመምረጥና በመጥቀስ የተሳሳትኩ ስለሆነ ተጠሪን ሆነ ብል ተራ የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት በድጋሚ ክስ እንዲላቀርብ የሚከለክለኝ ሕግ የለም በማለት በዚህ መዝገብ ያቀረበውን ክርክር በመመርመር ለመረዲት ይቻላል።
ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 23 አቀራረፅና ይዘት ለመረዲት የሚቻለው አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በድጋሚ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በአንድ ጉዲይ በድጋሚ ያለመከሰስና ያለመቀጣት መብቴን የሚጥስ ነው ብል ለመከራከርና የህገ መንግስቱም ድንጋጌ ተፈፃሚ እንዱሆንለት ለመጠየቅ ሁለት መሰረታዊ መስፈርቶች ሉሟለ ይገባል። የመጀመሪያው ተከሣሹ በተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት በወንጀል ህግና ሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት የተከሰሰ የነበረ መሆኑ ማረጋገጥ ነው።
ሁለተኛው ተከሣሹ ከዚህ በፉት በተከሰሰበት ወንጀል ድርጊት የመጨረሻ በሆነ ፍርድ ጥፊተኛ ሆኖ የተቀጣ ወይም በነፃ የተለቀቀ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው። ዓቃቤ ሕግ በአንድ ተከሣሽ ላይ የወንጀል ክስ ለማቅረብ ወይም ላለመቅረብ የሚሰጠው ውሣኔና የወንጀል ክስ ለማቅረብ ከወሰነ በኋላ ተከሣሹ በኃላፉነት ሉጠየቅ የሚችልበትን የወንጀል ድርጊትና የወንጀል ሕግ ድንጋጌ በወንጀል የፍትህ ሥርዓቱና በወንጀል የፍርድ ሂደት ውስጥ እጅግ ወሣኝና የመጀመሪያውና መሰረታዊ ውሣኔና ክንውን ነው። ዐቃቤ ሕግ በአንድ ተከሣሽ ላይ የወንጀል ክስ ከማቅረቡ በፉት ተከሣሹ አንድ ወንጀል በመፈጸም ሃሣብ የሰራው አንድ የወንጀል ድርጊት ያስከተላቸውን ወይም ሉያስከትላቸው የሚችላቸውን ውጤቶች ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ በማገናዘብና አግባብነት ያላቸውን ህግ ድንጋጌዎች በመለየትና በመጠቀስ የወንጀል ክሱን በጥንቃቄ የማቅረብ ግዳታ እንዲለበት፣ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 24 ንዐስ አንቀጽ 1፣ ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 41፣ አንቀጽ 111 እና አንቀጽ 112 ና ላልች አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል።
ይህም ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ክስ ሲያቀርብ በህግ የተጣለበትን ግዳታ ሣይወጣ ተከሣሹን በቀላል ወንጀል ኃላፉና ተጠያቂ የሚደርግ የወንጀል ድንጋጌ ጠቅሶ ክስ አቅርቦ ተከሣሹም፣ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ በሚፈቅደው መሰረት የእምነት ክህደት ቃልን ከሰጠና ተከራክሮ በቀረበበት የወንጀል ክስ በፍርድ ቤት ጥፊተኛ ተብል ከተቀጣ ወይም በነፃ ከተለቀቀ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ከዚህ በፉት በተጠሪ ላይ የወንጀል ክስ ሳቀርብ የተጠሪ ድርጊት በግል ተበዲይ ላይ ያስከተለውን ወይም ሉያስከትል የሚችለውን ውጤት በማገናዘብም ሆነ አግባብነት ያለውን የወንጀል ሕግ ድንጋጌ በመምረጥና በመጥቀስ ተሳሳቻለሁ በሚል በተከሣሹ ላይ በድጋሚ የወንጀል ክስ ቢያቀርብ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 ና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 5 በምን መንገድ መተርጏምና ተፈጻሚ መሆን አለባቸው የሚለውን ነጥብ እንድንመረምር ያስገድደናል።
በዚህ መዝገብ አመልካች ያቀረበው የዚህ አይነት ክርክር ሲያጋጥም ከሁለም በፉት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌው ሉያሳካው የሚፈልገውን ግብና ዓላማ መሰረት በማድረግ ክርክሩን በመመርመር መወሰን ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ የህገ መንግስቱን አንቀፅ 23 ትርጉምና የተፈፃሚነት ወሰን አስመልክቶ የሚነሱ አከራካሪ ጉዲዮች በህገ መንግስቱ አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቃል ኪዲን ስምምነቶች በተለይም ከዓለም ዓቀፍ የሲቪልና የፕለቲካ መብቶች ሥምምነት አንቀጽ 14 ንዐስ አንቀጽ 7 ይዘት፣ ትርጉምና የተፈፃሚነት ወሰን ጋር ማገናዘብና መረዲት ያስፈልጋል። የዚህ ዓለም ዓቀፍ የወንጀል ህግ መርህ መሰረታዊ ዓላማ የአንዱት አገር መንግስት ህግ አስከባሪ አንድ ጊዜ የወንጀል ክስ አቅርቦበትና ተከራክሮ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት በልላ ጊዜ ተከሳሹን በድጋሚ ለመክሰስና ለማስቀጣት የማይችል መሆኑን በመደንገግ ሰዎችን በአንድ ወንጀል ድርጊት በተደጋጋሚ በሚቀርብ የወንጀል ክስ ስጋት ውስጥ እንዲይወድቁ በመከልከል ለሰዎች የተረጋጋና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና እና ጥበቃ መስጠት ነው።
የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 በአቀራረጹና በይዘቱ በአንድ በኩል ዓቃቤ ህግ ለአንድ የወንጀል ድርጊት በተለያየ ጊዜ የተለያየ የወንጀል ርዕስና የህግ ድንጋጌ በመጥቀስ ወይም ተመሳሳይ የወንጀል ህግ ድንጋጌ በመጥቀስ ተከሳሽ ተከስሶ በፍ/ቤት በተሰጠ የመጨረሻ ፍርድ ነፃ ከወጣ ወይም ከተቀጣ በኋላ በድጋሚ በወንጀል እንዲይከሰስና እንዲይጠየቅ የሚከለክል በልላ አነጋገር የመንግስት የወንጀል ክስ የማቅረብ ሥልጣንን የሚገድብ መሰረታዊ ድንጋጌ ነው። በልላ በኩል ድንጋጌው አንድ ተከሳሽ የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብል ከወንጀል ክሱ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት ጉዲይ ላላ የወንጀል ክስና ተጠያቂነት ይመጣብኛል ከሚል ጭንቀት ሥጋት እንዲይሸማቀቅ ህገ መንግስታዊ ዋስትናና ጥበቃ በመስጠት ተከሳሹ በወንጀል ተከስሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሚ የማይከሰስና የማይፈረድበት ስለመሆኑ ህገ መንግስታዊ ዋስትና ያለው መሆኑን በማረጋገጥ የተረጋጋ ህይወት እንዱኖር የማድረግ ዓላማና ግብ ያለው ነው።
አንድ ሰው በወንጀል ህግና በወንጀል ስነ ስርዓት ተከስሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዲይ ጥፊተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም በነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 130 የተደነገገ ሲሆን ፍ/ቤቱ ያቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 131 ተደንግጓል። ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከስሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሚ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሉነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ብይን የሚሰጡበት የመከራከሪያ ነጥብ በመሆኑ አመልካች ተጠሪ ይህን ነጥብ በወረዲው ፍ/ቤት ሣይነሳ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰበር መከራከሪያ አድርጎ ማቅረቡና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የተጠሪን ክርክር ተቀብል መወሰኑ የህግ መሰረት የለውም በማለት ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
ስለሆነም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አመልካች ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የወረዲው ፍ/ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ አመልካች ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ በመቀበልና በማከራከር የሰጡትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሻሩ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 23 እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 2 ንዐስ አንቀጽ 5 መሰረታዊ ይዘት፣ ዓላማና የተፈፃሚነት ወሰን ያገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.