No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ፈትያ አወል - አልቀረቡም ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቢ ህግ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበችውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ አመልካች እኔ ባልተገኘሁበትና የቅጣት አስተያየት ባልሰጠሁበት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ እንዱሰረዝ ያቀረብኩት አቤቱታ ውድቅ ተደርጎብኛል የሚል ይዘት ያለው ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ ከመዝገቡ እንደተረዲነው ተጠሪ አመልካች አዋጅ ቁጥር 104/90 አንቀጽ 20 እና አንቀጽ 18(2) በመተላለፍ የግል ተበዲይን ወደ ኩዬት እልክሻለሁ በማለት ብር 7800 በመቀበል ታህሳስ 1 ቀን 2000 ዓ.ም ወደ ደባይ የላከቻት በመሆኑ በክሱ የተጠቀሰውን አዋጅና የአዋጁን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ወንጀል ፈፅማለች በማለት ክስ አቅርቦ አመልካች ወንጀለን አልፈጸምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክራለች።
ዐቃቤ ህግ ክሱን የሚያስረደለትን ምስክሮች አመልካች ባለችበት አሰምቶ አመልካች የሰውና የፅሁፍ የመከላከያ ማስረጃዎችን አሰምታለች። ከዚህ በኋላ አመልካች ሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም በነበረው ቀነ ቀጠሮ አመልካች ባለመቅረቧ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች በላለችበት ጉዲዩን የሚቀጥል ስለመሆኑ ትዕዛዝ ሰጥቶ ሀምላ 28 ቀን 2003 ዓ.ም አመልካች በክሱ የተጠቀሰውን ወንጀል የፈፀመች ጥፊተኛ ናት በማለት በአስር ወር እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በላለሁበት የተሰጠው ፍርድ ይነሳልኝ (ይሰረዝልኝ) በማለት ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርባ የከፍተኛው ፍ/ቤት የአመልካች ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል። አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርባ ፍ/ቤቱም የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ አፅንቶታል።
አመልካች ሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም በነበረው ቀጠሮና የሥር ፍርድ ቤት ፍርድ በሰጠበት ጊዜ ያልቀረበችው ውጭ አገር ሄዲ ልጇ በመታመሙ ምክንያት ወደኢትዮጵያ የምታደርገው ጉዞ የዘገየ መሆኑን ገልፃ የሥር ፍ/ቤት የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀፅ 4 በሚደነግገው መሰረት ጠበቃዬ እንዲይገኝ በማድረግ የቅጣት አስተያየት ሣይሰጥ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በላለሁበት የተሰጠ ፍርድ በመሆኑ ሉሰረዝልኝ ሲገባ ጥያቄዬ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክታለች። ተጠሪ ክርክር የተካሄደውና ማስረጃ የተሰማው አመልካች ባለችበት ነው። ስለዚህ ፍ/ቤቱ ፍርድ በሰጠበት ጊዜ አመልካች አለመገኘቷ ጉዲዩ በላለችበት ታይቷል የሚያስብል አይደለም። ፍርደ የሚሰረዝበት ምክንያት የለም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርባለች።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሁፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሥር ፍ/ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች ያቀረበችውን የፍርድ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የወንጀል ክሱ በሚሰማበት ጊዜ ወንጀለን ያልፈፀመች መሆኑን በመግለጽ የተከራከረች መሆኑ፣ አመልካች ባለችበት ተጠሪ ማስረጃዎቹን ያሰማ መሆኑንና አመልካችም የመከላከያ ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃዎቿን ያቀረበች መሆኑ ተረጋግጧል። ይህም አመልካች በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 4 በተደነገገው መሰረት የተጠሪን ምስክሮች ቃል የመመርመርና የመጠየቅ መብቷ እና የእሷን የመከላከያ ማስረጃ አቅርባ የማሰማት መብቷ ሙለ በሙለ በተከበረበት ሁኔታ የአመልካችና የተጠሪ ክርክርና ማስረጃ የተሰማ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 4 በሚደነግገው መሰረት የከሳሽን ማስረጃ የመመርመርና የመጠየቅ መብቷ የተረጋገጠላትና የእሷንም የሰውና የፅሁፍ የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበችው አመልካች የከሳሽንና የተከሳሽን ማስረጃ መርምሮ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ በያዘበት ቀን ሣትገኝ መቅረቷ ጉዲዩ በህገመንግስቱ አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 4 የተደነገገው መሰረታዊ መብቷ ባልተሟላበት ሁኔታ ታይቷል ከሚል መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ አይደለም። በወንጀል የተከሰሰ ሰው የዐቃቤ ህግ ማስረጃ ሲሰማ በመገኘት የዐቃቤ ህግን ምስክሮች የመጠየቅና የመመርመር መብቱን በአግባቡ ከተጠቀመና የመከላከያ ምስክሮችንና ማስረጃ ካሰማ በኋላ ቀጠሮውን አክብሮ ፍርድ ቤት ባይቀርብ ዳኞች የከሳሽንና የተከሳሽን ክርክርና ማስረጃ በመመዘን ፍርድ ከመስጠት የሚገድባቸው አይደለም። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው አመልካች ቀጠሮውን አክብራ ባልቀረበችበት ሁኔታ የቅጣት አስተያየት የመስጠት መብቴ ታልፎል በማለት ያቀረበችው ክርክር የህገ መንግስቱን አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 4 እና የወንጀልኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 149 ንዐስ አንቀጽ 1 እና 4 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል አመልካች ጉዲዩን የሥር ፍ/ቤት ተከሳሽ በላለበት በሚታይበት ሥርዓት (defau|t procedure) እንዲየው በመቁጠር ያቀረበችው አቤቱታ መጀመሪያውኑ አንድ ጉዲይ ተከሳሽ በላለበት በ(defau|t procedure) ታየ የሚባለው መቼ ነው? ተከሳሽ በላለበት የወንጀል ክስ ስለሚታይበት ሁኔታ የሚደነግጉት ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 161 እስከ 164 የተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘት ትርጉምና ተፈፃሚነትና ውጤት እንደዚሁም ተከሳሽ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በላለበት ታይቶ የተሰጠው ፍርድ እንዱሰረዝለት ከወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 197 እስከ 202 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ይዘት ትርጉም ተፈፃሚነትና ውጤት ያላገናዘበና ተገቢነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም አመልካች በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዐስ አንቀጽ 4 በተደነገገው መሰረት የተጠሪን ማስረጃ የመመርመርና የመጠየቅ መብቷ በተረጋገጠበትና የሰውና የሰነድ የመከላከያ ማስረጃ የማቅረብ መብቷን ሙለ በሙለ ከተጠቀመች በኋላ ፍ/ቤቱ ፍርድ በሰጠበት ቀን እኔ ስላልተገኘሁ የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ ይሰረዝልኝ በማለት ያቀረበችው አቤቱታ የህግ መሰረት የላለው ነው። ይህ የአመልካች ጥያቄ የህግ መሰረት የላለው ነው በማለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ
No topics extracted.