No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 09 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባልስልጣን-አቃቤ ሕግ ትዝታ ዘውዳ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ በወንጀል ጉዲይ በተሰጠ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ለማቅረብ በሕጉ ተለይቶ የተመለከተውን የጊዜ ገደብ የተመለከተ ነው። አመልካች ባሁኑ ተጠሪዎች በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 32(1ሀ) እና የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 91 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የጉምሩክ ስነ ስርዓት ሳይፈጸም አስራ አምስት የቀንድ ከብቶችን ወደ ሱዲን ለማስወጣት ሲለ ሰባት ኪል ሜትር ሲቀራቸው መያዛቸውን ገልፆ አንደኛ ተጠሪ በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተጠሪዎች ደግሞ በግብረ አበርነት የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን ተጠሪዎች ክደው ተከራክረው አቃቤ ሕግ አለን ያላቸውን ማስረጃዎችን አቅርቦ ከአሰማ በኋላ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪዎች የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸማቸው አቃቤ ሕግ በማስረጃዎቹ አላስረዲም በማለት ተጠሪዎችን ምንም መከላከል ሳያስፈልጋቸው ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 141 መሰረት በነፃ አሰናብቷቸዋል። ከዚህም በኋላ አመልካች ይግባኙን ለቤንሻንጉል ጉምዝ ብሓራዊ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት አቅርቦ ጉዲዩ ተጠሪዎችን በመልስ ሰጪነት ያስቀርባል ተብል ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የአመልካች የይግባኝ አቤቱታ አቀራረቡ በወ/መ/ሕ/ስ/ስ/ቁጥር 187(2) ስር የተመለከተውን የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ ጠብቆ ያልቀረበ መሆኑን በማረጋገጥ መዝገቡን ዘግቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ጊዜውን ለመቁጠር መነሻ ያደረገበት ጊዜ ትክክለኛ ያለመሆኑንና ይግባኙን ግንቦት 25 ቀን 2003 ዓ.ም ግልባጩን በመቀበል ሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ያቀረበ ሆኖ እያለ የይግባኝ ግልባጩ ለአመልካች የደረሰው ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ አልፎል ተብል የይግባኝ መዝገቡ መዘጋቱ ሥነ ሥርዓቱን ያልተከተለ መሆኑን እንዱሁም በዋናው ጉዲይ የተሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ ያለመሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው ሉለወጥ ይገባል ሲል መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ የአመልካች የይግባኝ አቤቱታው በወቅቱ ያልቀረበ ነው ተብል በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውድቅ መደረጉ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ለተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ በጭብጥነት የተያዘው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈው በአግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ነው።
የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች የይግባኝ ጊዜ ማቅረቢያ ሳይጠብቅ ይግባኙን አቅርቧል ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዲዩ ላይ ግንቦት 10 ቀን 2003 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቶ አመልካች የይግባኝ መዝገቡ ተገልብጦ እንዱሰጠው ውሳኔ ከተሰጠ በ2ኛው ቀን ማለትም ግንቦት 11 ቀን 2003 ዓ/ም መጠየቁን፣ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ/ም ደግሞ የይግባኝ መዝገቡን ግልባጩን መቀበለንና በዚህ ቀን ሸኚ የተሰጠው መሆኑና አመልካች ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ይግባኝ ማቅረቡ መረጋገጡን መርምሮ እነዚህ ፍሬ ነገሮችን መሰረት በማድረግም በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 187(2) ስር የተመለከተው የሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ ሲሰላ አመልካች ይግባኙን ያቀረበው የሰባት ቀናት ጊዜ ከአለፈ በኋላ መሆኑ ተረጋግጧል በማለት ነው። አመልካች ይህንኑ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ድምዲሜ የተሳሳተ ነው በማለት በዚህ የሰበር ችልት የሚከራከረው ይግባኙ ተገልብጦ የተሰጠው ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ/ም ሳይሆን ግንቦት 25 ቀን 2003 ዓ/ም ስለመሆኑ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በነበረው የቃል ክርክር ጊዜ ተረጋግጧል፣ ማስረጃም ቀርቧል በሚል ነው። ተጠሪዎች ደግሞ ይህ የአመልካች ክርክር እውነትነት የላለው መሆኑን በመዘርዘር የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በፍሬ ነገር የፈፀመው ስህተት የለም በማለት ለዚህ ችልት በጽሁፍ መልስ ሰጥተዋል።
በዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 187(2) ድንጋጌ የውሳኔው ግልባጭ የተሰጠው ሰው ይግባኙን ለማየት ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ይግባኙን ማቅረብ ያለበት ግልባጩ በተሰጠው በሰላሳ ቀናት የጊዜ ገደብ ስለመሆኑ አከራካሪ የሆነ የሕግ ጥያቄ አይደለም።
አከራካሪውና በሰበር ችልቱ ትርጉም ያስፈልገዋል ተብል በአመልካች ጥብቅ ክርክር እየቀረበ ያለው የይግባኝ መዝገቡ ግልባጭ ለአመልካች የደረሰው ግንቦት 25 ቀን 2003 ዓ/ም እንጂ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ/ም በሚል ነው። ይሁን እንጂ ይህ የፍሬ ነገር ክርክር ሲሆን ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች የይግባኝ መዝገብ ግልባጩ የደረሰው ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ/ም ሆኖ በዚሁ ቀን በተጻፈለት ሸኚ ደብዲቤ መሰረት ይግባኙ ሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ/ም መድረሱን አረጋገጠ እንጂ አመልካች እንደሚለው በቃል ክርክር ወቅት ለአመልካች ይግባኙ የተሰጠው ግንቦት 25 ቀን 2003 ዓ/ም ስለመሆኑና ማስረጃም በስር ፍ/ቤት መዝገብ መቅረቡ አለመረጋገጡን በውሳኔው ላይ ገልፆ በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም ሲል ደምድሟል። እንዱህ ከሆነ ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 ድንጋጌዎች መሰረት የተሰጠው ስልጣን ፍሬ ነገርን ማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን ሳይሆን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍ/ቤቶች በሕጉ አግባብ የደረሱበትን ድምዲሜ እንደ እውነት በመቀበል በሕጉ አተረጓጏም ወይም አተገባበር ረገድ መሰረታዊ የሆነ ስህተት ተፈፅሞ ከሆነ ይህንኑ ማረም ነው። በተያዘው ጉዲይም ለጉዲዩ ቀጥተኛ የሆነ ተፈጻሚነት ያለውን የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 187(2) ድንጋጌን በመተርጏም ወይም በመተግበር ረገድ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለ ሲሆን በአመልካች በኩል በቅሬታነት የቀረበው ነጥብም የፍሬ ነገር እንጂ የመሰረታዊ ሕግ ስህተትን መመዘኛ የሚያሟላ ባለመሆኑ ልንቀበለው የምንችለው ሆኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም የአመልካች የይግባኝ ጊዜ አልፎል ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሆኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ መስከረም 10 ቀን 2004 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
የአመልካች ይግባኝ የቀረበው በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 187(2) ድንጋጌ ስር የተመለከተው የጊዜ ገደብ ከአለፈ በኋላ ነው ተብል የይግባኝ መዝገቡ መዘጋቱ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት መስከረም 23 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከተው አካል ይፃፍ።
No topics extracted.