No summary available.
መጋቢት 13 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሤ አመልካቾች፡- ከፊለ ሰፈነ - ጉዲይ ተከታታይ አስቀናው ከፊለ ቀረበ ተጠሪ፡- የአማራ ክልል ዓ/ሕግ - የቀረበ የለም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በሰሜን ጎንደር አስተዲደር ዞን ደምቢያ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። የጉዲዩ መነሻ ተጠሪ በአመልካች ላይ የተመሰረተው ክስ ነው። አመልካች የተከሰሱት በ1996 ዓ/ም በወጣው የወ/መ/ሕግ አንቀጽ 438 ስር የተመለከተውን በመተለለፍ ከመንግስት ስራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሕግ በተፈቀደው ውጭ አስቦ መጋቢት 22 ቀን 2003 ዓ/ም ደምቢያ ወረዲ ጫሂት ከተማ ላይ ምክትል ሳጅን ሙለጉጃም ሙለአለም የተባለችው የትራፉክ ተቆጣጣሪ ፕሉስ ሆና በመስራት ላይ እንዲለች አመልካች የታርጋ ቁጥር ኮድ 3-28371 አ.አ የሆነች አይሱዚ የጭነት መኪና እያሽከረከረ ወደ ጎንደር አቅጣጫ ሲመጣ በተደረገ ቁጥጥር መንጃ ፈቃድ ሳይዝ በማሽከርከር በሕግ አግባብ ክስ አዘጋጅታ ስትሰጠው የክስ ቻርጅ አልቀበልም በማለት እምቢተኛ በመሆን በድጋሚ ሚያዚያ 11 ቀን 2003 ዓ/ም ደንቢያ ወረዲ ቆላድባ ከተማ 01 ቀበላ በተደረገው የትራፉክ ደንብ መተላለፍ የክስ ቻርጅ የያዘ እንዱወስድ ቢጠየቅም እምቢተኛ በመሆኑ የመንግስት ስራን የማሰናከልና የመተባበር ግዳታ መጣስ የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል በሚል ነው። አመልካች የወንጀል ድርጊቱን በመካድ የተከራከረ ሲሆን አቃቤ ሕግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን ማስረጃዎችን አቅርቦ አስምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካች እንዱከላከል ተደርጎ የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት ምስክሮችን ከአሰማ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የአመልካች መከላከያ ማስረጃ የአቃቤ ሕጉን ማስረጃ ለማስተባበል ብቃቱ የላለው መሆኑን ዘርዝሮ ውድቅ አድርጏ አመልካችን በአቃቤ ሕጉ ተጠቅሶ በቀረበበት ክስ ጥፊተኛ በማድረግ በአንድ አመት ከስድስት ወር እስራት እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኃላ በአመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኛነት ውሣኔ ሙለ በሙለ ሲጽና የቅጣት ውሣኔው ግን ተሻሽል አመልካች በአንድ አመት እስራት እንዱቀጣ ተደርጓል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ድርጊቱን ስለመፈፀሙ ሳይረጋገጥና ተረጋግጧል ቢባል እንኳ ድርጊቱ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 438 ስር የማይሸፈን ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የሰጡት ያላግባብ ነው በማለት ውሣኔው እንዱሻርላቸው ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 438 ስር ጥፊተኛ ተብል የመቀጣቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መንዘብ የተቻለው አመልካች የተከሰሰው የትራፉክ ተቀጣጣሪ ፕሉስ ሆኖ በመስራት ላይ የነበረችው የትራፉክ ፕሉስ ጽ/ቤት ባልደረባ አመልካች የታርጋ ቁጥር ኮድ 3- 28371 አ.አ የሆነች አይሱዚ የጭነት መኪና እያሽከረከረ ወደ ጎንደር አቅጣጫ ሲመጣ በተደረገ ቁጥጥር መንጃ ፈቃድ ሳይዝ በማሽከረከር በሕግ አግባብ ክስ አዘጋጅታ ስትሰጠው የክስ ቻርጅ አልቀበልም በማለት በተለያዩ ሁለት ቀናት እምቢተኛ በመሆን የመንግስት ስራን የማሰናከልና የመተባበር ግዳታ መጣስ የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል በሚል ሲሆን አመልካች ክድ በመከራከሩ አቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን ምስክሮች ቀርበው በመሰማታቸውና አመልካችም የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት የመከላከያ ማስረጃዎችን ያሰማ ቢሆን የአቃቤ ህግ ማስረጃዎችን ለማስተባበል ያለመቻለ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መገለጽን ነው። በዚህም መሰረት የሥር ፍ/ቤት አመልካቾችን ለድርጊቱ ኃላፉነት ያደረጉት የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች በመሰማትና ቃላቸው ለጉዲዩ አግባብነት፤ ክብደት ያለው መሆኑን በማመን አመልካች በመከላከያ ማስረጃዎች እንዱያስተባብል የመከላከል መብቱን በመጠበቅ የአመልካችን የመከላከያ ማስረጃዎችን ከሰማ በሁዋላ የመከላከያ ማስረጃዎቹ የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ለማስተባበል የማይችለ መሆኑን ዘርዝሮ ቃላቸውን ውድቅ በማድረግ መሆኑን ከውሣኔው ግልባጭ ተገንዝበናል።
በመሆኑም አመልካች የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ክብደትን በተመለከተ ያቀረበውን ቅሬታ ስንመለከተውም ጉዲዩ የማስረጃ ምዘና ጉዲይ በመሆኑና ይህ ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት ለዚህ ችልት በአንቀጽ 80 (3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰርት ለዚህ ሰበር ችልት ከተሰጠው መሰረታዊ ሕግ ስህተት ማረም ስልጣን ስር የማይወድቅ ወይም የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የማያሟላ በመሆኑ የምንቀበለው ሁኖ አላገኘነውም። በፍሬ ነገር ደረጃ አመልካች የትራፉክ ፕሉስ ባልደረባ የትራፉክ ደንብ መተላለፊቸውን በመግለጽ የሰጠችውን ክስ አልቀበልም በማለት እምቢተኛ መሆኑ መረጋገጡን ይዘን ይህ አድራጏት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 438 ስር የሚወድቅ መሆን ያለመሆኑን ስንመለከተው የተጠቃሹ ድንጋጌ አርአስት “የመንግስት ስራን ማሰናከልና የመተባበር ግዳታን መጣስ” በሚል የተቀመጠ ሁኖ ድንጌው ለላልች ሰዎች በመንግስት ስራ ላይ የሚፈፅሟቸው ወንጀልች በሚል “ምዕራፍ ሶስት” ስር የሚገኝ ሲሆን ይህ ምዕራፍ የሚያሳየውን ላልች ሰዎች ከመንግስት ስራ ጋር በተያያዘ መንገድ የሚፈፅሟቸው ወንጀልች በሚደነግገው ክፍል ሁለት ስር ያለ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም በላይ የድንጋጌው ይዘት ሲታይ ማንም ሰው ከመንግስት ስራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሕግ በተፈቀደው ወይም በፍርድ ቤት በተሰጠ ትእዘዝ መሰረት በመንግስት ሰራተኛ ሲጠየቅ ቀርቦ ለማስረዲት፤
ተገቢውን መልስ ለመስጠት፤ ሰነድችን ለማቅርብ ወይም ለማስመርመር ወይም ልዩ ልዩ ቤቶች፣ ቦታዎችን ወይም ነገሮችን ለማስፈተሽ እምቢተኛ ከሆነ በጠቅላላው ለምርመራ ያልተባበረ ወይም በማናቸውም ላላ መንገድ የመንግስት ስራ ያደናቀፈ እንደሆነ ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን ያሣያል። ከድንጋጌው ውስጥ “…… በሕግ በተፈቀደው…..” እና “…… በማናቸውም ላላ መንገድ…….” የሚለት ሐረጎች ሲታዩ የአመልካች አድራጏትም በዚሁ ድንጋጌ የሚሸፈን መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። ምክንያቱም የትራፉክ ፕሉስ የትራፉክ ደንብን የመቆጣጠርና የማስፈፀም ስልጣን በህግ ተለይቶ የተሰጠው ሲሆን ከዚሁ ስራ ጋር በተያያዘ ኃላፉነቱንና ተግባሩን በመወጣት ሂደት ማንም ሰው ሉያስናክለው የማይገባ፣ ይልቁንም የመተባበር ግዳታ ያለበት መሆኑ የሚታወቅ ነውና። ሲጠቃለልም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(-2)) መሰርት ሙለ በመለ ፀንቷል።
ውሣኔው የፀና መሆኑን አውቆ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈጽም ለክፍለ ማረሚያ ቤት ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.