No summary available.
የመጋቢት 26 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ውድማ አበጀ - አልቀረበም።
ተጠሪ፡- የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ዐ/ሕግ አልቀረበም።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፣ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው የአንድ የወንጀል አፈፃፀም ተግባር በሙከራ ደረጃ ላይ ደርሷል የሚባለው መቼ፤ እንዳት ነው? የሚለውን ነጥብ በዚህ የወንጀል ጉዲይ በማስረጃ ከተረጋገጡት የፍሬ ነገር ጉዲዮች ጋር በማናገዘብ ተገቢውን ዲኝነት ለመስጠት በሚል ነው።
የጉዲዩ መነሻ በክልለ የጉራጌ ዞን ዐ/ሕግ በአሁኑ አመልካችና በግብረ-አበሮቹ ላይ ሦስቱም ተከሳሾች በወ/ህ/ቁ 32/1/ /ሀ/፣ 27/1/ እና 671/1/ለ ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በጅማ ወለኔ ቀበላ የሚመላለሱትን ተሽከርካሪዎች ለመዝረፍ የጦር መሣሪያ፣ ጭንብል፣ የእጅ ባትሪ፣ ጩቤ በመያዝ ከመጋቢት 07 ቀን እስከ መጋቢት 08 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ተንቀሳቅሰው ጠብቀው ተሽከርካሪ በማጣታቸው ሲመለሱ በተደረገው ጥቆማ መነሻ በፀጥታ ኃይልች ስለተያዙ በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ሙከራ ወንጀል ተከሰዋል በማለት ያቀረበው ክስ ሲሆን፤ የአሁን አመልካች በተከሳሽነቱ ድርጊቱን አልፈፀምኩም፤ ጥፊተኛም አይደለሁም በማለት ክድ ተከራክሯል።
በማስረጃነትም የሰው ማስረጃና ተከሳሾች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 27 እና 35 መሰረት በምርመራ ጊዜ ለመርማሪ ፕሉስ እና በፍ/ቤት የሰጡት ቃል ቀርቧል። በሰው ማስረጃው የተረጋገጠው መጋቢት 07 ቀን 2001 ዓ.ም ከአንድ የመኪና አሽከርካሪ ሽፍቶች ለመዝረፍ ተሰማርተዋል የሚል ጥቆማ አግኝቼ ወዱያውኑ ስከታተል ማግኘት አልቻልኩም። ተሽከርካሪ በማስቆም በተደረገው ጥብቅ ክትትል እነዚህ ሦስት ሰዎች መታወቂያ ሲጠየቁ የላቸውም። በግንባታ ሥራ ተሰማርተን የግንባታ ቁሳቁስ እጥረት ስለአጋጠመ ወደ መኖሪያችን እየሄድን ነው አለ። ዕቃቸው ሲፈተሽ ግን አንድ የጦር መሣሪያ፣ ጩቤ፣ ጭንብል ተገኝቶባቸዋል የሚል ነው። እንዱሁም በምርመራ ጊዜ በሰጡት የእምነት ቃልም ለዘረፊ ተስማምተው አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት አድርገው ያመቸናል ብለው ወደ አሰቡበት ቦታ በመሄድ ጫካ ውስጥ ከአደሩ በኋላ ባገኙት መኪና ተሳፍረው ሲመለሱ ከያዙት የዘረፊ ቁሳቁስ ጋር በፕሉስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሚገልፅ ነው።
ፍ/ቤቱም ይህንኑ የዐ/ሕግ ማስረጃ እና ተከሳሾች እንከላከላለን ሲለ ያቀረቡትን ማስረጃ በማገናዘብ ከመረመረ በኋላ እንደ ክሱ አቀራረብ ጥፊተኛ ናቸው ካለ በኋላ ከሦስተኛው ተከሳሽ በስተቀር በአሁን አመልካችና ሁለተኛ ተከሳሸ በነበረው ላላ ግብረአበር ላይ የቀረበውን የወንጀል ጥፊተኝነት እና ቅጣት ሪከርድ መነሻ በማድረግ በአሁን አመልካች ላይ የ22 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ጥሎል።
ከዚህም ቀደም ብለው መግደል ወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ ከተባለበት ፅኑ እስራት የ10 ዓመቱን በእስር ሉጨርስ በሚል በአመክሮ መለቀቁን መነሻ በማድረግ የተጣለ ቅጣት እንደሆነ የውሳኔው ግልባጭ ያስረዲል።
በዚህ ውሳኔ ላይ በደረጃው ላለ የበላይ ፍ/ቤቶች እንዱታረም ቅሬታ ቢያቀርብም ቅሬታው ውድቅ በመደረጉ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዲዩን በዚህ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቧል።
በዚህ ችልት ግራ ቀኙ ክርክር ያደረጉበት ነጥብ ይህ አመልካች እና ላልች ግብረ-አበሮች የፈፀሙት ተግባር በሙከራ ወንጀል ሥር ሉወድቅ የሚችል ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ላይ ነው። እኛም በዚሁ ጭብጥ ላይ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ቅሬታ ከሥር ፍ/ቤቶች የውሳኔ ግልባጭ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
እንደመረመርነውም በ1997 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 27 እንደተደነገገው ማንም ሰው አስቦ ወንጀለን ማድረግ ጀምሮ የወንጀለን ድርጊት እስከመጨረሻው ባይከታተልም ወይም ለመከታተል ባይቻልም የወንጀል ድርጊቱ እንዱፈፀም እስከመጨረሻው ተከታትል አስፈላጊ የሆነውን ውጤት ያላስገኘ ቢሆንም የሙከራ ወንጀለን እንደፈፀመ እንደሚያስቆጥረው ተመልክቷል።
በዚህም ጉዲይ በፍሬ ነገር ረገድ እንደተረጋገጠው ከድርጊቱ በፉት ተከሳሾች ሁልጊዜ የዘረፊ ወንጀል በሚፈፀምበት ጫካ መግባታቸው፤ ይህን በተመለከተ በሰው ጥቆማ አማካኝነት በፀጥታ ኃይልች በተደረገው ክትትል ተሳፍረውበት ከነበረው መኪና ከጦር መሣሪያ፣ ጩቤና ጭንብል ጋር መያዛቸው፤ እንዱሁም በእራሳቸው የእምነት ቃል እንደተረጋገጠው ለዘረፊ ወንጀል አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት አጠናቀው ከዚሁ ጫካ ውስጥ ሲጠባበቁ አድረው በማግስቱ በመኪና ተሳፍረው ሲሄደ ለዘረፊ ተግባር ሲለ ከያዙት ቁሳቁስ ጋር መያዛቸው ሁለ ሲታይ አመልካችና ግብረ-አበሮቹ የዘረፊ ወንጀል ለመፈፀም እስከመጨረሻው ተከታትለው ነገር ግን የሚዘረፍ ነገር ባለማግኝታቸው ውጤቱን ያላገኙ መሆኑን አስረጂ ነው። በልላ አገላለፅ በአመልካችና በግብረአበሮቹ በኩል የተፈፀመው ተግባር በእራሱ የዘረፊ ወንጀለን ለመፈፀም ወደ ኋላ ከማይመለሱበት ደረጃ ደርሰው የነበረ መሆኑን አመላካች ነው። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቱ ይህንን ሁለ በማገናዘብ የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ አመልካች ተላልፍታል ተብል በተጠቀሰው ሕግ አነጋገር መሰረት ሆኖ የተገኘ እንጂ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ በቀን 12/06/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ /ለ/ /2/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ይህንኑ እንዱያውቀዉ ውጤቱ ባለበት ማ/ቤት ይገለፅለት። መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.