No summary available.
የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1ኛ/ ሐሰን አማን መሐመድ ጠበቃ ሚሉዮን አበራ 2ኛ/ ብርሃን መኯንን ደሣለኝ ተጠሪ፡- የፋ/ሥ/ፀረ-ሙስና ኮሚሽን- ዐቃቤ ሕግ- ዋልተንጉስ ፍቅሬ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ በተጠሪ መስሪያ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቁና ክስ ሉመሰረትባቸው የሚገባቸውን የወንጀል ድርጊቶችን እንዱሁም በተጠሪ መስሪያ ቤት ስልጣን ስር የማይወድቅ ጉዲይ በኮሚሽኑ አቃቤ ሕግ ክስ ሉመሰረት የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነው።
የሥር ፍ/ቤት የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ የመሰረተው ክስ በሁለት ምድብ የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው ክስ፡- የወ/ሕግ አንቀጽ 32/ሀ/ እና 379/1ሀ/ን ጠቅሶ አመልካቾች በላልች ሀሰተኛ ሰው ስም የተዘጋጀ የጅምላ ንግድ ፈቃድ አስመስለው አዘጋጅተው ለጨረታ አቀርበው ተወዲድረዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ክስ ደግሞ የወ/ሕግ አንቀጽ 32/1ሀ/እና 696/ሐ/ የተመለከተውን ተላልፈው በ1ኛው ክስ ላይ የተጠቀሰውን ሰነድ ሐሰተኛነቱን ደብቀው ለጨረታ በማቅረብ የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽኑን አታለው በመንግሥት ላይ የብር 707,805.00 ጉዲት በማድረሣቸው ተከሰዋል የሚል ነው። ጉዲዩ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የአቃቤ ሕጉን ክሶች ለአመልካቾች አንብቦላቸው እንዱረደት ከአደረገ በሁዋላ አመልካቾች በክሱ ላይ ተቃውሞ በማቅረባቸው ጉዲዩን መርምሮ ተከሣሾች ሁለም በግል የሚተዲደሩ እንደመሆናቸው የመንግሥት ሰራተኛ ተጣምሮ ባልተከሰሰበት ሁኔታ የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ በተከሣሾች ላይ ክስ ለመመስረት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 404/3/ አንፃር ስልጣን የለውም በማለት መዝገቡን በአብላጫ ድምጽ ዘግቶ ተከሣሾች ከእስር እንዱለቀቁ ትእዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ብይን የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ጉዲዩን አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ማቅረቡ ሕጋዊ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን ሽሮታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ ከመንግሥት ሰራተኞች ጋር ሣያጣምር በግለሰቦች ላይ ክስ ለመመሥረት የሚችልበት የሕግ አግባብ ሳይኖር የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤትን ብይን መሻሩ ያላግባብ ነው በማለት ውሳኔው እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮ በአመልካቾች ላይ የቀረበው ክስ የመንግስት ሰራተኞች ባይሆኑም የተጠሪ መስሪያ ቤት የማስተናገድ ስልጣን አለው ተብል በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በፅሐፍ በሰጠው መልስ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ክስ ያቀረበው ክሱን ለማቅረብ በተሰጠን ስልጣን ነው፣በተለይ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 379 የሙስና ወንጀል መሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 404/4/ ላይ በግልጽ የተደነገገ ሲሆን ይህም ድንጋጌ የመንግሥት ሰራተኛን ብቻ የሚመለከት አይደለም፣አንቀጽ 379 መሰረት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 375 እስከ 378 የተደነገገውን በአንቀጽ 375 ደግሞ "ማንም ሰው…." ብል ነው የሚጀምረው፣ ስለሆነም አንቀጽ 379 ጠቅሰን ክስ ለማቅረብ ሥልጣን ያለን ሲሆን አንቀጽ 696/ሐ/ አጣምረን የከሰስነው ድርጊቱ በ1ኛ ክስ ከጠቀስነው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 379 ጋር ተያይዞ የተፈፀመ በመሆኑ በማስረጃም ሆነ በውሣኔ አሰጣጥ የሚረዲ በመሆኑ እንጂ 696/ሐ/ በአመልካቾች ላይ የጠቀስነው ስልጣን አለን በሚል አይደለም፣ ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪ የወ/ሕግ አንቀጽ 379 በመጥቀስ በአመልካቾች ላይ ክስ መመሥረት ይችላል በማለት መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል።
የአሁኑ አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የስር ፍ/ቤት አመልካቾችን የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ ከአቀረበባቸው ክስ መዝገቡን ዘግቶ ያሰናበታቸው በወ/ሕግ አንቀጽ 404/3/ መሰረት ከመንግሥት ሰራተኛ ውጭ የሆነ ሰው ከመንግሥት ሰራተኛ ጋር ተጣምሮ ካልተከሰሰ ወይም ለመንግሥት ሰራተኛ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ከሰጠ ወይም ለመስጠት ከተስማማ ብቻ በመሆኑ እና ተከሣሾች የመንግሥት ሰራተኞች ስላልሆኑ ወይም ከመንግሥት ሰራተኛ ጋር ተጣምረው ባልተከሰሱበት ሁኔታ የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ ክስ ሉያቀርብባቸው አይችልም በሚል መሆኑንና ይህንን የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያልተቀበለው ደግሞ በመንግስት ሰራተኛ ባልሆነ ሰውም የኮሚሽኑ አቃቤ ሕግ የሙስና ክስ ለማቅረብ ሥልጣን አለው፣የሙስና ድርጊት ያልሆነውን የወንጀል ድርጊትም ከሙስና ወንጀል ጋር አጣምሮ ክስ ለማቅረብ የሚችልበት የሕግ አግባብ አለ በሚል ምክንያት መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 404/4/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው መንግሥታዊ ወይም ወታደራዊ ሰነድችን አስመስል ማዘጋጀት እንደሙስና ወንጀል እንደሚቆጠር መደንገጉን ነው።ይህን እንደሙስና ወንጀል የተደነገገውን ድርጊት ሉፈጽመው የሚችለው ማን እንደሆነ ለማወቅ ደግሞ በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል በአንቀጽ 375 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች ማየትን የግድ ይላል። እነዚህ ድንጋጌዎች በወንጀል ሕጉ በሕዝብ ጥቅሞችና በማህበራዊ ኑሮ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀልች በሚገዛው አራተኛ መፅሐፍ፣በሕዝብ አመኔታ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀልች ርዕሥ ስር፣ሐሰተኛ ሰነድችን መፍጠር፣ሰነድችን ወደ ሐሰተኛነት መለወጥና ማጥፊትን በሚመለከት ምዕራፍ ስር የተቀመጡ ሆነው የአንቀጽ 375 ድንጋጌ በግዙፍ የሚፈጸም ሐሰት በሚል ርዕስ የተቀረጸ ሁኖ የመጀመሪያው ፒራግራፍ ማንም ሰው በሚል ሐረግ የሚጀመር ሁኖ በንዐስ ድንጋጌዎቹ ስር የተመለከቱት የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች መኖራቸው ሲረጋገጥ የወንጀል ተጠያቂነት መኖሩን በግልጽ ያሳያል። በአንቀጽ 379 ድንጋጌ በንዐስ አንቀፅ አንድ ሥር ከተመለከተው ይዘትም የመንግሥት ሰራተኛ የሆነውን እና ያልሆነውን ማንኛውንም ሰው የሚመለከት መሆኑና በዚሁ አንቀጽ ንዐስ ቁጥር ሁለት ስር ያሰፈረው ደግሞ የመንግሥት ሰራተኛን ብቻ የሚመለከት ስለመሆኑ መረዲት የሚቻለው ጉዲይ ነው። ስለሆነም በአንቀጽ 379(2) ስር የሰፈረው ከመንግሥት ሰነድች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ያለው ሆኖ ሰነድችን አስመስል ማዘጋጀት ወይም ወደ ሐሰት መለወጥን ተግባር ያከናወነውን የመንግሥት ሰራተኛ በግልጽ መለየቱ በአንቀፁ ንዐስ ቁጥር አንድ ስር የተመለከተው ደግሞ ሰነደ የመንግሥት ሆኖ አስመስል ያዘጋጀው ወይም የለወጠው ማንኛውም ሰው ላሆን እንደሚችል ግልጽ ነው።
አመልካቾች አስመስለው አዘጋጁት የተባለው የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫ መንግሥታዊ ሰነድን እንደመሆኑ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩበት ወንጀልም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 379 "ን" የሚመለከት ነው። የወንጀል ሕግ አንቀጽ 379 "ን" የሚሸፍን ድርጊት ደግሞ የሙስና ወንጀል ነው ተብል በሕግ ተደንግጓል። እንዱህ ከሆነ ደግሞ በተሻሻለው የፋዳራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 433/1997 መሰረት የሙስና ወንጀልችን የመመርመና የመክሰስ ሥልጣን የተሰጠው የፋዳራለ ሥነ ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ነው።በመሆኑም ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት በአመልካቾች ላይ የቀረበውን 1ኛ የወንጀል ክስ የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ የመክሰስ ስልጣን አለው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን መሻሩ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም።
2ኛውን ክስ በተመለከተ የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተው ስልጣን አለኝ ብል ሣይሆን ከ1ኛው ክስ ጋር ግንኙነት ያለውና ማስረጃውም የሁለቱ አንድ ነው በሚል እንደሆነ በስር ፍርድ ቤትና ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከተካሄደው ክርክር ተረድተናል። ኮሚሽኑ በዚህ መልኩ የሱ ስልጣን ያልሆኑ ነገር ግን ከመሰረተው የሙስና ወንጀልች ጋር አጣምሮ ክስ ማቅረቡ ደግሞ ከወንጀል ሥነ ስርዓት ሕግ ዓላማጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ጉዲይ ነው። ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነሥርአት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 434/1997 ነው። በዚህ አዋጅ መሰረት የሙስና ክስ የሚመራበት ሥርዓት ተዘርግቷል።ይሁን እንጂ አዋጁ የኮሚሽኑ አቃቤ ሕግ በእራሱ ስልጣን ስር የማይወድቅ ነገር ግን የሙስና ወንጀል ፈፅሟል ተብል የተከሰሰ ሰው ከዚሁ ጋር አንድ ላይ መከሰስ ያለበትን የወንጀል ድርጊት አንድ ላይ ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ በግልፅ ያስቀመጠው ድንጋጌ የለም። ሆኖም ተጠቃሹ አዋጅ በአንቀጽ 55 ስር የወንጀል ሥነሥርአት ህግ፣ የፍትሀ ብሄር ሥነሥርአት ህግ፣ የወንጀል ህግና ላልች አግባብነት ያላቸው ህጎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተቃረኑ ድረስ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል በሚል ደንግጎ በአዋጁ አንቀፅ 58 ስር የተሻሩና ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎችን ለይቶ ሲያስቀምጥ የጸረሙስና የልዩ ስነስርአትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁ 236/1993 እንደተሻሻለ መሻሩን፣ ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ላልች ሕጎች በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዲዮች ላይ ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው ደንግጓል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የምንችለው በአንድ ጉዲይ ላይ ክስ ለማቅረብ ስልጣን ያለው አካል በሕጉ ከተሰጠው ስልጣን ጋር አንድ ላይ የሚታይና ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ስልጣኑ ከሆነው ጉዲይ ጋር ስልጣኑ ያልሆነውን ጉዲይ ክስ ለማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ የሚደነግጉ የወንጀል ስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸው መሆኑን ነው። ስለሆነም ጉዲዩን የሚያየው ፍ/ቤት ከሙስና ወንጀል ክስ ጋር ተጣምሮ የቀረበውንም የወንጀል ክስ የማየት ስልጣን እስካለው ድረስ ሁለንም ክሶች አጣምሮ ቢያይ የፍ/ቤትን፣ የከሣሽን እና የምስክሮችንም ጊዜና ጉልበት የሚቆጥብ በመሆኑ የሚደገፍ ስለመሆኑ ከላይ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 110 ድንጋጌ ሁለተኛው ፒራግራፍ ይዘትና መንፈስ ጋር አጣምረን ስናነበው የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ዋናውና ቁልፍ ነገር የጉዲዩ መታየት በትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጡ ላይ ሉያስከትለው የሚችለው አለታዊ ውጤት የላለ መሆኑ መረጋገጡ ላይ ነው። ሲጠቃለልም ከላይ በተዘረዘረጉት ሕጋዊ ምክንያቶች የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የኮሚሽኑ ዐቃቤ ሕግ በአመልካቾች ላይ ያቀረበውን ክስ ለማቅረብ ሥልጣን አለው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ብይን በመሻር የተዘጋው መዝገብ ተንቀሳቅሶ ጉዲዩ እንዱቀጥል ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ታህሳስ 20 ቀን 2003 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕግ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/2ሀ/ መሰረት ጸንቷል።
መዝገቡን ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.