No summary available.
የካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ተክለድንግል ገ/ሚካኤል ተጠሪ፡- የፋ/ሥ/ም/ፀ/ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ሕግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የሙስና ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካችና በላልች ስምንት ሰዎች ላይ በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።የአሁኑ አመልካች የተከሰሱት በአንድ መዝገብ በተከፈተ ክስ ሲሆን የክሱ ይዘትም አመልካቹ በ1996 ዓ/ም በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀ)፣33 እና 407(1(ሀ)(ሐ))፣(2) እና (3) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና በመንግስትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ በስር ፍርድ ቤት ቀደም ሲል አዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ተመድቦ ሲሰራ በነበረበት ወቅት በስራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የአዱስ አበባ ከተማ ማስተር ፔላን ከስራ ሲታገድ በሲዱ በመገልበጥና በኮምፑዩተር በመታገዝ በከተማው ውስጥ ያለትን ክፍት ቦታዎችን በመለየትና ቀደም ሲል በነበረው ስርዓት ለማኅበራት ይፈቀድ የነበረውን የቤቶች ፔላን ቶፕልጂ በወቅቱ በከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የሚሰራባቸውን የቤቶች አይነት በፔላን በማዘጋጀት ሕጋዊ ያልሆኑ ማህበራትን ከሕግ ውጪ በማደራጀትና ቦታን በመስጠት የሙስና ወንጀል ፈጽሟል ተብል በአንደኛ ተራ ቁጥር ተከሳሽ ከነበረው ከአቶ በሃይለ ለማ ድንቁ ጋር በጥቅም በመመሳጠር በሐሰትና በተቀነባበረ ዘዳ "ሻላ" የሚባል ሃሰተኛ የመኖሪያ ቤት የሕብረት ስራ ማህበር እንዱቋቋም አድርጎ በሀሰተኛ መንገድ የተዘጋጀው የማህበሩን ፊይል ከስር ሁለተኛ ተከሳሽ(ወ/ሮ ደሃብ ገ/ሕይወት) ጋር የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር በ1998 ዓ/ም የካ ክፍለ ከተማ ማህበር ማደራጃ ፅ/ቤት ውስጥ እንዱገባ በማስደረግና የማህበሩ አባላትም የተሳሳተ ግንዛቤ እንዱኖራቸው እና ማህበሩን ሕጋዊ አስመስል በማቅረብና በሁለተኛ ተከሳሽ በኩል ሃሰተኛውን ማህበር ሕጋዊ አስመስል እንዱነገር አድርጎ 248 የማህበሩ አባላት በሕገ ወጥ መንገድ መሬት እንዱያገኙ በማድረግና ቦጋለ የተባለውን ሐሰተኛ እና ሕገ ወጥ ማህበር ፊይልም ከ1ኛ ተከሳሽ በመቀበል ለሁለተኛ ተከሳሽ ሰጥቶ ወደ ክፍለ ከተማው ማህበራት ማደረጃ ፅ/ቤት እንዱገባ አድርጎ በሁለቱም ሐሰተኛ ማህበራት ሕገ ወጥ ጥቅም በማግኘት፣በማስገኘትና በመንግስትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዲት በማድረስ የሙስና ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነው።ጉዲዩ አግባብነት ባለው ስነ ስነ ሥርኣት ተመርቶ አመልካች ክሱን በመካድ በመከራከራቸውም አቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ተመርምረውም አመልካች "ሻላ" የሚባል የመኖሪያ ቤት ሕብረት ማህበር ሉቀመንበር ለመሆናቸው አቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰነድ ማስረጃ ማስረዲቱ መረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ገልፆ ይህንኑ እንዱከላከለ ተደርጎ አመልካች በበኩላቸው አለኝ ያሎቸውን ማስረጃዎችን ለመከላከያ ማስረጃነት አቅርበዋል።ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች በመከላከያ ማስረጃዎቹ የአቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ሉያስተባብለ ያልቻለ መሆኑን በመግለፅ በአቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ ተጠቅሶ የቀረበባቸውን ድንጋጌ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 113(2) መሰረት ዝቅ አድርጎ አመልካችን በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ))፣33 እና 407(1(ሀ)) ስር ጥፊተኛ አድርጎአል።ከዚኅም በኋላ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በሁዋላ አመልካችን በአምስት አመት ፅኑ እስራትና በብር 5,000.00(አምስት ሺኅ ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኖባቸዋል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች መስከረም 18 ቀን 2003 ዓ/ም በጻፈት አምስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል።ይዘቱም ባጭሩ፡-አመልካች የመንግስት ሰራተኛ ሳይሆኑ በሙስና መከሰሳቸው ያላግባብ መሆኑን፣በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141 ነጻ በተባለበት ጉዲይም ተመልሶ ጥፊተኛ መባላቸው ስነ ሥርኣቱን ያልጠበቀ መሆኑን፣የስር ፍርድ ቤት በአመልካች እንዱቀርብና ፊርማው እንዱመረመር የተጠየቀውን የሰነድ ማስረጃ በፍረንሲክ ሳያስመረምር አልፍ ውሳኔ መስጠቱም የማስረጃ አቀራረቡና አመዛዘኑ ሥርዓት ሕጉን ያልጠበቀ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ዘርዝርው በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ተሽሮ አመልካች በነጻ እንዱሰናበቱ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች የቤት ስራ ማህበር ሉቀመንበር ናቸው ተብል ጥፊተኛ መደረጋቸው ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎል።በዚህም መሰረት ተጠሪ የካቲት 15 ቀን 2003 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። አመልካች በበኩላቸው መጋቢት 09 ቀን 2003 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለአቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ ከጠቀሷቸው የቅሬታ ነጥቦች መካከል አንደ ተጠሪ ክሱን በማስረጃ አለማስደገፈንና አመልካች እንዱመረመርላቸው የጠየቁት ሰነድ በፍረንሲክ ሳይመረመር እንዱሁም ለተሰሙት የመከላከያ ምስክሮች ቃል ክብደት ሳይሰጥ መታለፊን የሚመለከት ነው።ይሁን እንጂ በዚህ ረገድ የቀረበው ቅሬታ በሰበር ችልት እንዱታይ በጭብጥነት ያልተያዘ ከመሆኑም በላይ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን ማስረጃ በማጣራትና በመመዘን የአመልካችን የመከላከያ ማስረጃዎችን የአቃቤን ህግን ማስረጃዎችን የማስተባበል ብቃት የላቸውም በሚል ያለፈት ነው። በመሆኑም ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሰት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት የተሰጠው ሥልጣን በበታች ፍርድ ቤቶች በተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበውን ቅሬታ ይህ ችልት የሚመረምረው ሁኖ ስላላገኘው አልፈነዋል።
ላላው አመልካች ያቀረቡት ቅሬታ አመልካች የመንግስት ሰራተኛ ሳይሆኑ በሙስና ወንጀል መከሰሳቸው አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7 ድንጋጌን በግልፅ የሚጻረር ነው በሚል ነው።ይሁን እንጂ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ቅሬታ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 33 ድንጋጌን መንፈስና ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የላለው ነው። ምክንያቱም አመልካች በስር ፍርድ ቤት የተከሰሱት የመንግስት ሰራተኞቾ ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በመንግስትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዲት አድርሰዋል በሚል ከመሆኑም በላይ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 33 መሰረት አንድ ሰው የመንግስት ሰራተኛ ባይሆንም በሙለ ፈቃደና እውቀቱ የሙስና ወንጀል ሙለ ተካፊይ መሆኑ ከተረጋገጠ በሙስና የሚከሰስበት አግባብ መኖሩ የተደነገገ ነውና።
በዚህ ችልት እንዱታይ የተያዘውና አመልካች በመከራከሪያነት ያቀረቡት ላላው ነጥብ አመልካች የቤት ማህበሩ ሉቀመንበር ናቸው በማለት ጥፊተኛ መባላቸው ተገቢ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው። አመልካች የተከሰሱት ሕጋዊ ያልሆኑ ማህበራትን የሉቀመንበርነት ስልጣን አለኝ በማለት አደራጅተው ለማህበሩ አባለት ያላግባብ ቦታ እንዱሰጥ አድርገዋል፣በዚህም በመንግስትና በሕዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዲት አድርሰዋል በሚል ሲሆን የማህበራቱ ሕጋዊ አለመሆንና ማህበራቱ ሲደራጁ እንዱሁም ቦታውን ሲወስደ አመልካች የነበራቸው ሚና ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ነጥብ ነው።በመሆኑም የቤቱ ማህበራት ሕጋዊ ያለመሆናቸውና የተደራጁትም አመልካች በሉቀመንበርነት በነበራቸው ሚና ጭምር መሆኑ ከተረጋገጠ አመልካች በወንጀል የማይጠየቁበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።ላላው አመልካች በዚህ ድርጊታቸው ነጻ ተብለው በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 141 የተሰጠ ብይን የላለ መሆኑን የስር ፍርድ ቤትን መዝገብ አስቀርበን የተመለከትን በመሆኑ በዚህ ረገድ የተነሳው ቅሬታም እውነትነት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።በአጠቃላይ በአመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 04 እና 14 ቀን 2002 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 29 ቀን 2002 ዓ/ም የፀናው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195((2(ለ-2)) መሰረት ሙለ በሙለ ፀንቷል።
በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረት ቅጣቱን ተከታትል ያስፈፅም ዘንድ ውሳኔው መፅናቱ ለማ/ቤቱ ይገለፅለት ብለናል።ይፃፍ።
የማይነበብ አምስት የዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.